News today

ሩሲያ በእህል ምርቶች ጉዳይ ላይ ከዩክሬን እና ቱርክ ጋር ለመደራደር ዝግጁ ነኝ አለች

ሩሲያ በእህል ምርቶች ጉዳይ ላይ ከዩክሬን እና ቱርክ ጋር ለመደራደር ዝግጁ ነኝ አለች

ሩሲያ በስንዴ እና በሌሎችም የእህል ምርቶች ጉዳይ ላይ ከዩክሬን እና ቱርክ ጋር ለመደራደር ዝግጁ መሆኗን ገለጸች።
ሩሲያ ይህን የገለጸችው በኢንዶኔዥያ መካሄድ በጀመረው የቡድን 20 (G20) አባል ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ነው።
በስብሰባው የተገኙት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ሃገራቸው በእህል ምርቶች ጉዳይ ላይ ከዩክሬን እና ቱርክ ጋር ለመደራደር ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል።
ቱርክ ከሰሞኑ ከዩክሬን የተሰረቁ የእህል ምርቶችን የጫኑ ናቸው ያለቻቸውን የሩሲያ የጭነት መርከቦች መያዟ ይታወሳል።

Leave a comment