
በሽንዞ አቤ ላይ ጥይት ተኩሶ የገደለው ግለሰብ በፖሊስ ተይዞ ምርመራ እየተደረገበት ነው ተባለ
የቀድሞው የጃፓን ጠቅላይ ሚንስትር ሽንዞ አቤ በምዕራብ የሀገሪቱ ክፍል ናራ ተብላ በምትጠራ ከተማ በተሰናዳ አንድ የፖለቲካ መድረክ ላይ ከሰዓታት በፊት ንግግር በማድረግ ላይ እያሉ ከኋላ በተተኮሰባቸው ጥይት ተመትተው ህክምና እያሉ ነበር ህይወታቸው ያለፈው።
በሽንዞ አቤ ላይ ጥይት የተኮሰው ግለሰብም በፖሊስ ተይዞ ምርመራ እየተደረገበት መሆኑም ተነግሯል።
