News today

“ሄሮን ቲፒ” አደገኛው የእስራኤል የውጊያ ድሮን

“ሄሮን ቲፒ” አደገኛው የእስራኤል የውጊያ ድሮን ምን የተለየ ያደርገዋል…ʔ
“ሄሮን ቲፒ (Heron TP)” ድሮን የእስራኤል አየር ኃይል ከታጠቃቸው አደገኛ የአውደ ውጊያ መሳሪያዎች ውስጥ በቀዳሚነት የሚጠቀስ ነው።
ሄሮን ቲፒ ድሮን በየትኛውም አይነት የአየር ፀባይ ለ30 ሰዓታት ያክል መስራ ይችላ የተባለ ሲሆን፤ በሰዓት 370 ኪሎ ሜትር ፍጥነት መጓዝ እንደሚችልም ተነግሯል።
ድሮኑ ለተልዕኮ በሚሰማራበት ወቅት አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ከባህር ጠለል በላይእስከ 45 ሺህ ጫማ ድረስ ከፍ ብሎ በመብረር ከራዳር እይታ ውጪ ጥቃት መሰንዘር ይችላል።