News today, Technology

ሁዋዌይ በየትኛውም የዓለም ክፍል በሳተላይት የሚሰራ ሜት 50 ስማርት ስልክ ይፋ አደረገ

ሁዋዌይ ሜት 40 ስማርት ስልክን ከለቀቀ ከ2 ዓመት በኋላ ነው ሜት 50 ይፋ የተደረገው

የቻይናው የቴክኖሎጂ ቁሶች አምራች ሁዋዌይ ሜት 50 ስማርት ስልኩን በዛሬው እለት ይፋ ማድረጉ ተነግሯል።

አዲሱ የህዋዌይ ስማርት ስልክ ከዚህ በፊት በስማርት ስልኮች ላይ ያልተለመደ የሳተላይት ኮሙዩኒኬሽን የተገጠመለት መሆኑን ሲ.ጂ.ቲ.ኤን ዘግቧል።

በዚህም ስማርት ስልኩ ከጂ.ፒ.ኤስ ተመሳሳይነት ባለው በቻይናው ቤይ-ዶው ናቪጌሽን ሳተላይት ሲስትም (BDS) ኔትዎርክ አማኝነት በየትኛውም የዓለም ክፍል የሚባይል ኔትዎርክ ባይኖርም መስራት ይችላል።

 በተጨማሪም አዲሱ ሜት 50 ስማርት ስልክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአሜሪካው የጎግል አንድሮይድ ስማርት ስልክ በመላቀቅ ቻይና በራሷ ባመረተችው አዲስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ለገበያ የሚቀርብ ይሆናል ነው የተባለው።

ይህም ባትሪው ሊዘጋ 1 ፐርሰት እየቀረው 3 ሰዓት እንደቆይ ማድረግ እንደሚያስችልም ኩባያው አስታውቋል።

አዲሱ የሁዋዌይ ሜት 50 ስማርት ስልክ የባትሪ አቅም 4460 mAh መሆኑን ኩባያው አስታውቋል።

ስማርት ስልኩ ከጀርባው 4 የካሜራ ሌንሶች የተገጠሙለት ሲሆን፤ ሌንሶቹም 50 ሜጋ ፒክስል፣ 13 ሜጋ ፒክሰል እና 12 ሚክስል ናቸው።

ከፊትለፊት አሊያም ሰለፊ ካሜራው ደግሞ 1 ሲሆን፤ የሌንሱ ምስል የማንሳት ጥራትም 13 ሜጋ ፒከስል ነው ተብሏል።

ሁዋዌይ ሜት 40 የተባለ ስማርት ስልክን ከለቀቀ ከ2 ዓመት በኋላ ነው ሜት 50 ስማርት ስልክ ይፋ የተደረገው።

በርካቶቸ ሁዋዌይ ስማርት ስልኩን ይፋ ሳያደርግ ይህን ያክል የቆየው አሜሪካ በኩንያው ላይ በጣለችው ማእቀብ ሳቢያ ሳይሆን እንዳልቀረ ያምናሉ።