ብራንድ አምባሳደር በመሆን ተፈራርማለች
ቡሩል ትሬዲንግ ኃ / የተ / የግ / ኩባንያ ( Burul Trading PL.C. ) እ.ኤ.አ መስከረም 2016 የተመሰረተ አስመጪና ላኪ ኩባንያ ሲሆን ፤ ኩባንያው “ ኢንጂ ፈርኒቸር ”የሚል የብራንድ ስያሜ በመያዝ ! “ ይታሽ ሞቢሊያ ” የተባለው እድሜ ጠገብና ግዙፍ የቱርክ ፈርኒቸር ኩባንያ ወኪል በመሆን የሚሰራ ነው ፡፡
በተጨማሪም ኩባኒያው ባለፉት ስድስት ዓመታት ባደረገው ጥረት ፤ ኢንጂ ፈርኒቸር በአሁነ ጊዜ ለሦስት የተለያዩ ታዋቂ የቱርክ ፈርኒቸር ኩባንያዎች “ የምስራቅ አፍሪካ ገበያ ብቸኛ ወኪል ” በመሆን እየሰራ ይገኛል ።
የኢንጂ ፈርኒቸር ዋና መሥሪያ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ፤ በሴንቸሪ ሞል አካባቢ የሚገኝ ሲሆን በአሁኑ ጊዜም አዲስ አበባ ውስጥ ሴንቸሪ ሞል ሦስተኛ ፎቅ እና ግራውንድ ፎቅ ላይ ሁለት ሾው ሩም በመክፈት ለደንበኞች አገልግሎት በመስጠት ላይ ነው።
ኢንጂ ፈርኒቸር የሚለውን የብራንድ ስም የመረጠው ፤ በሾው ሩማቸው ውስጥ የሚገኙትንና ከተለመደው ወጣ ያሉ ቅንጡ ውብና ማራኪ ፈርኒቸሮች የሚወክል ስያሜ በመሆኑ ነው።
ኢንጂ ፈርኒቸር እስካሁንም በልዩ ትእዛዝና በከፍተኛ ጥራት የሚመረቱ ፤ እጅግ ቅንጡ ፤ ከተለመደው ወጣ ያሉ ቅንጡ ፤ ውብና ማራኪ ፈርኒቸሮች የሚወክል ስያሜ በመሆኑ ነው ፡፡
ዘመናዊ የነገውን ፋሽን መሰረት ያደረጉ ፤ አዳዲስና ብራንድ የቤትና የቢሮ ፈርኒቸሮችን በከፍተኛ ወጪ በማስመጣት ፤ የውስጥ ዲዛይን ማማከርን ጨምሮ የተገዙ ፈርኒቸሮችን ደንበኞች ባሉበት ቦታ የማድረስና የማስረከብ አገልግሎቶችን በመስጠት ረገድም ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ግንባር ቀደምና ታዋቂ ኩባንያ ነው ፡፡
ኩባንያው አዲስ አበባ ከከፈተው የምስራቅ አፍሪካ ወኪል ቢሮ በተጨማሪ ፤ በናይኖቢ ፤ ኬንያ ሌላ አስመጪና ላኪ ኩባንያ አቋቁሞ እየሰራ ሲሆን ፤ በናይሮቢ የመጀመሪያውን ሾው ሩም እ.ኤ.አ. መስከረም 2022 ለመክፈት የሚያስችለውን የዝግጅት ሂደት አጠናቅቋል ፡፡
እንዲሁም ፤ በደንበኞቹ ጥያቄ መሰረት ፤ የሆቴልና የአፓርትመንት ፕሮጄክት ቅንጡ ፈርኒቸሮችን በማስመጣት በኬንያ ፤ በደቡብ ሱዳን ፤ በናይጄሪያና በታንዛኒያ ለሚገኙ ደንበኞቹ በማቅረብ ! ለአስመጪነት ስራው የሚያውለው ብቻ ሳይሆን ለአገራችንም ጭምር የውጭ ምንዛሪ ገቢ በማስገኘትና ለዜጎች የስራ እድል በመክፈት ረገድ የበኩሉን አስተዋፅኦ እያደረገ ይገኛል ፡፡
ኢንጂ ፈርኒቸር በአሁነ ጊዜም ምርትና አገልግሎቱን በውጤታማ ስልትና በላቀ ደረጃ በማስተዋወቅ ቢዝሱን በከፍተኛ ጥራትና ቅልጥፍና ለማሳደግ ፤ “ ተወዳጇን አርቲስት ሃናን ታሪክን ታዋቂ ኢትዮጵያዊ የኩባንያው የብራንድ አምባሳደር አድርጎ በዛሬው ዕለት በሃያት ሪጀንሲ ሆቴል አስፈርሟል።
ቴዲሾው መልቲ ሚዲያ
ህጋዊ ሰውነት አግኝቶ በማስታወቂያ የስራ ዘርፍ የተሰማራው ቴዲ ሾው መልቲ ሚዲያ፤ ባለፉት አምስት አመታት ባደረገው ጥረት፤ በርካታ የቪዲዮና የድምፅ ማስታወቂያ ክርኤቲቭ ፕሮዳክሽን ስራዎችን በጥራት በማከናወን ለአገር ውስጥና ለውጭ አገር ደንበኞች አስረክቧል፡፡
ከዚህ አንፃር ቴዲ ሾው የማስታወቂያ ኢንዱስትሪውን ከተቀላቀለ ወዲህ ማከናወን ከቻላቸው ስራዎች የሚከተሉት በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው፤
• ከ300 በላይ የቴሌቪዥን ማስታወቂያዎችን ለአገር ውስጥ ድርጅቶች ሰርቶ አስረክቧል
• ከ225 በላይ የሬዲዮ ማስታወቂያዎችን ለአገር ውስጥ ድርጅቶች ሰርቶ አስረክቧል
• 7-የቪዲዮና የኦዲዮ ፕሮዳክሽንኖችን በመስራት፤ በውጭ አገር ለሚገኙ ዓለም-አቀፍ ጅርጅቶች አስረክቧል
• እስካሁን 8-የብራንድ አምባሳደር ማስታወቂያ ስራዎችን የስምምነት ፊርማ ሥነ-ሥርዓት ያዘጋጀ ሲሆን፤ በዛሬው እለትም ባዘጋጀው ዘጠንኛው የብራንድ አምባሳደር ፊርማ ስነ-ስርአት፤ አናን ታሪክ የተባለቸውን ታዋቂ ኢትዮጵያዊ አርቲስት ከቡሩል ትሬዲንግ ጋር በከፍተኛ የኢትዮጵያ ብር በማፈራረም ስራ አስጀምሯል፡፡