News today, Politics, Technology

ኢራን የጸጥታው ም/ቤት ውሳኔን በመጣስ ለኢትዮጵያ ድሮን መሸጣን አሜሪካ አስታወቀች

ኢራን ሰው አልባ የጦር አውሮፕላን (ድሮን) ለኢትዮጵያ የሸጠችው ከአንድ ዓመት በፊት ነው ተብሏል

ኢራን “ሞሃጀር” የተሰኘውን ድሮን ለኢትዮጵያ መስጠቷን አሜሪካ ገልጻለች

ኢራን የጸጥታው ምክር ቤት ውሳኔን በመጣስ ለኢትዮጵያ ድሮን መሸጧን አሜሪካ አስታወቀች።

የአሜሪካ መንግስት እንዳሳወቀው ኢራን ከአንድ ዓመት በፊት ክረምት ላይ ለኢትዮጵያ ሰው አልባ አውሮፕላን ወይም ድሮን ማስተላለፏን ገልጿል።

ኢራን በፈረንጆቹ 2015 ላይ የጦር መሳሪያ ግብይት እንዳትፈጽም የሚከለክል ማዕቀብ በመንግስታቱ ድርጅት የተወሰነባት ሲሆን፤ ይሄንን ማዕቀብ በመጣስ ለኢትዮጵያ አስተላልፋለች ተብሏል።

2231 የተሰኘው ይህ የተመድ ውሳኔ በኢራን መጣሱን የአሜሪካ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ቪዳንት ፓቴል መናገራቸውን ዋቢ አድርጎ ሮይተርስ ዘግቧል።

ይህ የተባበሩት መንግስታት ውሳኔ በ2020 ላይ የሚያበቃ ቢሆንም በወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶናልድ ትራምፕ ማዕቀቡ እንዲራዘም ጠይቀው ነበር።

ይሁንና ይህ ማዕቀብ እንዲነሳ ያልተወሰነ በመሆኑ ኢራን ውሳኔውን በመጣስ ለኢትዮጵያ አሳልፋ ሰጥታለች ተብሏል፡።

እንደዘገባው ከሆነ ኢትዮጵያ ከኢራን የተረከበችውን ሞሃጀር የተሰኘውን ይሄንን ድሮን ከህወሃት ጋር በሚደረገው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ላይ እንዳዋለችውም ተገልጿል።

ኢራን ከኢትዮጵያ በተጨማሪ የጦር መሳሪያ ማዕቀቡን በመተላለፍ ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ለጀመረችው ጦርነት ድሮን ለሞስኮ ማስተላለፏንም አሜሪካ አስታውቃለች።

ኢራን በምዕራባዊያን የሚቀርቡባትን ክሶች ውድቅ ያደረገች ቢሆንም ከሩሲያ ጋር የሰው አልባ አውሮፕላን እና ሚሳኤል ግዢ ስምምነት መፈጸሟን አምናለች።

ዩክሬን በበኩሏ ኢራን ሻሂድ፣ጄራን እና ሌሎች ስያሜ ያላቸውን ድሮኖች ለሩሲያ በመሸጥ የዩክሬን ዋና ዋና ከተሞች እንዲደበደቡ አድርገዋል በሚል ከቴህራን ጋር ያላትን ግንኙነት እንደምታቋርጥ ዝታለች።

News today, Technology

ዩክሬን ከ230 በላይ የኢራን ሰራሽ ድሮኖችን መትታ መጣሏን አስታወቀች

ሩሲያ ድሮኖቹን በመጠቀም የዩክሬን መሰረተ ልማቶች እያወደመች እንደሆነ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ተናግረዋል

ዩክሬን ከኢራን ጋር ያላትን ግንኙነት ለማቋረጥ እያሰበችበት እንደሆነም ተገልጿል

ዩክሬን ከ230 በላይ የኢራን ሰራሽ ድሮኖችን መትታ መጣሏን አስታወቀች።

የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ስምንት ወራት የሞላው ሲሆን የጦርነቱ ሁኔታ በየጊዜው እየተቀያየረ አዳዲስ ክስተቶችን እያስተናገደ ቀጥሏል፡፡

የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዶሚር ዘለንስኪ እንዳሉት ኢራን ሰራሽ የሆኑ ከ233 በላይ ለሩሲያ የተሰጡ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ወይም ድሮኖች ተመተው መውደቃቸውን ተናግረዋል፡፡

ሩሲያ እነዚህን ኢራን ሰራሽድሮኖቹን በመጠቀም የዩክሬን መሰረተ ልማቶች እያወደመችበት እንደሆነ የተናገሩት ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ በዛሬው ዕለት ብቻ 10 ድሮኖችን መትተው መጣላቸውን አክለዋል፡፡

ሩሲያ በተለይም የዩክሬን ዋና ዋና መሰረተ ልማቶችን እያወደመች እንደሆነ የገለጹት ፕሬዝዳንቱ በተለይም ከ30 በመቶ በላይ የሚሆነው የዩክሬን የሀይል ማመንጫ ጣቢያዎች ከጥቅም ውጪ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

በዚህም መሰረት የዩክሬን ዋና ዋና ከተሞች ከሀይል አቅርቦት ውጪ ሆነዋል የተባለ ሲሆን ከተሞቹን መልሶ የሀይል አቅርቦት እንዲያገኙ ከፍተኛ ወጪ እየጠየቁ እንደሆነም ፕሬዝዳንቱ አክለዋል፡፡

ክሪሚያን ከተቀረው የሩሲያ ክፍል ጋር ለማስተሳሰር የሚውለው ድልድይ በዩክሬን ተመቶብኛል ያለችው ሞስኮ በ10 ቀናት ውስጥ ከ190 በላይ የአየር ላይ ጥቃቶችን በዩክሬን ላይ አድርሳለች ተብሏል፡፡

ሩሲያ በአጠቃላይ በ16 የዩክሬን ግዛቶች ላይ የሚሳኤል፣ የድሮን እና ሌሎች ጥቃቶችን ሰንዝራለች የተባለ ሲሆን ኢራን ሰራሽ ድሮኖች ዋነኛ የጥቃቱ መፈጸሚያ እንደሆኑ ዩክሬን አስታውቃለች፡፡

ዩክሬን ከመሰረተ ልማት ውድመት በተጨማሪ 70 ንጹሃን ዜጎቿ እንደተገደሉባት ያስታወቀች ሲሆን ኢራን ለሩሲያ የጦር መሳሪያ ድጋፍ አድርጋለች ስትልም ክስ አቅርባለች፡፡

ኢራን በበኩሏ ለሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላን እንዳልሰጠች ብትገልጽም በትናንትናው ዕለት ሚሳኤል ለመስጠት ከሩሲያ ጋር ስምምነት መፈጸሟን ዓለም አቀፍ ዘገባዎች ጠቁመዋል፡፡ 

News today, Technology

የሩሲያው “ታይገር” ብረት ለበስ ተሸከርካሪ ከአሜሪካው “ሀምቪ” ብረት ለበስ ተሸከርካሪ ጋር ሲነጻፀሩ

የአሜሪካን ጨምሮ የ70 ሀገራት ወታደራዊ ተቋማት ለዩክሬን ድጋፍ እያደረጉ ነው

የሩሲያው “ታይገር” ብረት ለበስ ተሸከርካሪ ከአሜሪካው “ሀምቪ” ብረት ለበስ ተሸከርካሪ

የሩሲያው “ታይገር” ብረተ እና አሜሪካው “ሀምቪ” ብረተ ለበስ ተሸከርካሪዎች በዩክሬን ጦርነት ላይ እየተፋለሙ ነው

በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል ጦርነተ ከተጀም ሰባት ወራትን ያስቆጠረ ሲሆን፤ በርካታ ምእራባውያን ሀገራትም ለዩክሬን የመሳሪያ ድጋፍ በማድረግ ላይ ናቸው።

የሩሲያ መከላካያ ሚኒሰቴር በቅርቡ፤ የ70 ሀገራት ወታደራዊ ተቋማት ለዩክሬን ድጋፍ እያደረጉ እንደሆ እና ሩሲያ በዩክሬን ምድር ምዕራባውያን ጋር እየተዋጋች እንደሆነ መግለጹ ይታወሳል።

አሜሪካ ለሩሲያ በተለያየ ጊዜ የተለያየ መጠን ያለው የጦር መሳሪ ለዩክሬን የሰጠች ሲሆን፤ ከእነዚህም ውወስጥ “ሀምቪ” የተባለው ብረት ለበስ የጦር ተሽከርካሪ አንዱ ነው።

ሩሲያም በዩክሬን ካሰለፈቻቸው የጦር ተሸከርካሪዎች ውስጥ “ታይገር” ብረተ ለበስ ተሸከርካሪ ይገኛል የተባለ ሲሆን፤ በጦርነቱ ላይም የሩሲያው “ታይገር” የአሜሪካውን ሀመቪ ሲያሳድድ እንደታየ ዩሩሲያ መገናኛ ብዙሃ ምንጮች ገልጸዋል።

የሩሲያው “ታይገር” ብረት ለበስ ተሸከርካሪ እና አሜሪካው “ሀምቪ” ብረት ለበስ ተሸከርካሪዎች አቅም እና ጥንካሬ ምን ይመስላል?

የሩሲያ የሩሲያው “ታይገር” ብረት ለበስ ተሸከርካሪ

“ታይገር ኤም “ አርዛማስክ በተባለ የጦር ተሸከርካሪ አምራች ኩብንያ ነው የተመረተው

በውጊያ ወቅት ወታደሮችን ለማጓጓዘ እንዲሁም መሳሪያዎችን ለማቀበል ይውላል

ፍጥነት፤ በሰዓት ከ125 እስከ 140 ኪሎ ሜትር ድረስ ይጓዛል

በጨለማ ውስጥ ያለምንም ችግር እንዲጓዝ የሚያችል የእይታ መሳሪያ ተገጥሞለታል

ሙሉ በሙሉ የጥይት መከላከያ አካል እና መስታወት ተገጥሞለታል

የሚታጠቃቸው መሳሪያዎችም

“2A72” አውቶማቲክ ጠመንጃ ከ30 ሚሊ ሜትር ካሊበር ጋር

“AGS-30” አውቶማቲክ የእጅ ቦምብ እና የጭስ ቦምብ ማስወንጨፊያ

ኮርኔት-ዲ ፀረ-ታንክ ሚሳይል ስርዓት እና ተንቀሳቃሽ የአየር ክልል መከላከያዎችን ይገኙበታል

አሜሪካው “ሀምቪ” ብረት ለበስ ተሸከርካሪ

“ሀምቪ” ብረት ለበስ ተሸከርካሪ በውጊያ ወቅት ወታደሮችን ለማጓጓዘ እንዲሁም መሳሪያዎችን ለማቀበል ይውላል

ፍጥነት፤ በሰዓት ከ105 እስከ 113 ኪሎ ሜትር ድረስ ይጓዛል

ሙሉ በሙሉ የጥይት መከላከያ አካል እና መስታወት ተገጥሞለታል

በተጨማሪም ከጎን እና ከኋላ ሙሉ በሙሉ የጥይት መከላከያ ተለጥፎለታል

የሚታጠቃቸው መሳሪያዎችም

• M2፣ M240፣ እና M249 ካሊበር መሳሪያ

• 25 ሚሊ ሜትር ፀረ አውሮፕላን መሳሪያ

• Mk-19 ቦምብ እና የጭስ ቦምብ ማስወንጨፊያ ከ40 ሚሊ ሜትር ካበር ጋር

• ፀረ ታንክ እና AIM-120 ሚሳዔል ማስወንጨፊያዎች እንዲሁም 105 ሚሜ መድፍ ይገኙበታል

News today, Technology

“አውዳሚው” የሚባለው ዘመናዊ የአሜሪካ የጦር መርከብ

የዘርፉ ባለሙያዎች “አጓጊ ግን የከሸፈ የመርከብ ጽንሰ-ሀሳብ” ይሉታል

አሜሪካ ካላት ግዙፍ የጦር መሳሪያዎች ውስጥ “ዩ.ኤስ.ኤስ ዙምዋልት” የጦር መርከብ አንዱ እንደሆነ ይነገራል።

4 ነጥብ 4 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር እንደወጣበት የሚነገረው የጦር መርከቡ በርካታ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎቸን የጣጠቀ እንደሆነ ይነገርለታል።

በፈረንጆቹ 2008 ግንባታው የተጀመረው የጦር መርከቡ በ2013 ላይ ይፋ የተደረገ ሲሆን፤ በፈረንጆቹ 2016 ላይ በአሜሪካ ባህር ኃይል ስራ ላይ እንደዋለም መረጃዎች ያመለክታሉ።

አሁን ላይ አሜሪካ ሁለት ዙምዋልት አውዳሚ የጦር መርከቦችን ያላት ሲሆን፤ እነዚህ “ዩ.ኤስ.ኤስ ሞንሶር” እና “ዩ.ኤስ.ኤስ ላይደን ቢ ጆንሰን” የሚል መጠሪያ ያላቸው ናቸው።

አውዳሚ ነው የተባለው የጦር መርከቡ አሜሪካ ካላት ጦር መርከቦች የወጣበት ዋጋ በእጥፍ የሚበልጥ ነው ብለዋል።

የቢላዋ ቅርጽ ያለው የመርከቡ የፊት ክፍል በከባድ የባህር ክፍል ላይ በቀላሉ እንዲጓዝ የሚያስችለው መሆኑንም ድፌንስ ኒውስ በመረጃው አስታውቋል።

መርከቡ 158 የባህር ኃይል አባላትን አሳፍሮ የሚጓዝ ሲሆን፤ 16 ሺ ቶን ገደማ ክብደት በመያዝ በሰዓት እስከ 56 ኪሎ ሜትር መብረር ይችላል ተብሏል።

መርከቡ ባለብዙ ተግባር ራዳሮች የተገጠሙለት ሲሆን፤ ከውኃ አካል ላይ ወደ ላይ ሚሳዔል ለማስወንጨፍ የሚያስችሉ 80 ሴሎች እንዳሉትም ተነግሯል።

ሆኖም ግን መርከቡ የፀረ መርከብ፣ የፀረ ባሀር ስርጓጅ ፣ የአየር መከላከያ ሚሳዔሎችን ማስወንጨፊያ የሌለው መሆኑ እንደክፍተት ይነሳበታል።

የወታደራዊ ጉዳዮች ባለሙያ የሆኑት ሴባስቲያን ሮብሊን፣ የመርከቡ ጽንሰ ሀሳብ እጅግ አጓጊ ነገር ግን የከሸፈ ነው ሲሉ ይገልጹታል።

News today, Technology

“አይበገሬው” የሚል መጠሪያ የተሰጠው “CV-22 ኦስፕሬይ” ሄሊኮፕተር

“CV-22 ኦስፕሬይ” ሄሊኮፕተር ለመንቀሳቀስ ሁለት አብራሪዎች ያስፈልጉታል

የተለያዩ የጦር መሳሪያ የሚተኩሰው ሄሊኮፕተሩ በሰዓት 445 ኪ.ሜ ይበራል

አሜሪካ ካሏት የጦር ሄሊኮፕተሮች ውስጥ “አይበገሬው” የሚል መጠሪያ የተሰጠው “CV-22 ኦስፕሬይ” ሄሊኮፕተር አንዱ ነው።

ቦይንግ እና ሄል ሄሊኮፕተር ቴክስትሮን ኩባንያዎች በጥምረት ያመረቱት ሄሊኮፕተሩ በፈረንጆቹ በ2006 ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰማራ ሲሆን፤ የተለያዩ ተልእኮዎችንም መፈጸም እንደቻለ ይነገርለታል።

ሄሊኮፕተሩ ከተሳተፈባቸው ዉጊያዎች ውስጥም ቀዳሚ እና ግዙፉ አሜሪካ በኢራቅ ያካሄደችው ዘመቻ እንደሆነም ነው መረጃዎች የሚጠቁሙት።

በውጊያ ወቅት የጦር መሳሪያዎችን ለመተኮስ እና ወታደሮችን ለማጓጓዝ የሚውለው ሄሊኮፕተሩ፤ በአንድ ጊዜ ተቀምጠው ከሆነ 24 ወታደሮችን ቆመው ከሆነ ደግሞ 32 ወታደሮችን ጭኖ መጓዝ ይችላል ተብሏል።

CV-22 ኦስፕሬይ ሄሊኮፕተር ምን የተለየ ያደርገዋል?

ሮልስ ሮይስ አሊሰን AE1107C ሞተር የተገጠመለት ሄሊኮፕተሩ ለመነሳትም ይሁን ለማረፍ መደርደሪያ አያስፈልገውም የተባለ ሲሆን፤ ቀጥ ብሎ ወደላይ የሚነሳ እና ባለበት ተወዳች እየተምዘገዘገ ማረፍ ይችላል።

የረቀቁ ቴክኖሎጂዎች የተገጠሙለት CV-22 ኦስፕሬይ ሄሊኮፕተር ዲጂታል ካርታ፣ ዲጂታል ሙሉ በሙሉ ዲጂታል የሆነ የአብራሪዎች ክፍል (ኮክፒት) እንዲሁም ራስን የመከላከል ስርዓቶች ተገጥመውለታል።

ሄሊኮፕተሩ ከባባድ ሮኬቶችን ጨምሮ ኒውክሌርን መቋቋም ይችላል የተባለ ሲሆን፤ “አይበገሬው” የተባለውም ከዚሁ በመነሳት ነው።

ሄሊኮፕተሩን ለማብረር ሁለት አብራሪዎች እና ሁለት የበረራ ኢንጂነሮች (መሃንዲሶች) የግድ ያስፈልጉታል ነው የተባለው።

CV-22 ኦስፕሬይ ሄሊኮፕተር በሰዓት 445 ኪሎ ሜትር የሚበር ሲሆን፤ በአንድ ጊዜ ነዳጅ ብቻ ከ925 ኪሎ ሜትሮች በላይ መብረር የሚችል ይችላል።

አየር ላይ ነዳጅ ከተሞላለት ደግሞ በየትኛውም የአየር ሁኔታ ውስጥ ከ3300 በላይ ኪሎ ሜትር ያለማቋረጥ መጓዝ እንደሚችል ተነግሯል።

ሄሊኮፕተሩ ላይ ወደላይ መተኮስን የሚያስችላቸው 7.62 ሚሊ ሜትር ሚኒገን ተገጠመለት ሲሆን፤ በመወጣጫው ላይ ደግሞ ካሊበር ማችን ገን ተገጥሞለተል።

News today, Technology

የአሜሪካው ናሳ ወደ ጨረቃ ሊያመጠቅ የነበረው ሮኬት ለሁለተኛ ጊዜ ከሸፈ

ሮኬቱ ላይ ነዳጅ መፍሰስ በማጋጠሙ ማስወንጨፉ ለሁለተኛ ጊዜ ተቋርጧል

የአሜሪካው ናሳ “አርቴሚስ 1” ሮኬት

አሜሪካ ከ50 ዓመታት በኋላ ተመራማሪዎችንና መሳሪያዎቻቸውን ወደ ጨረቃ ለመላክ እየሰራች ነው

የአሜሪካው ናሳ “አርቴሚስ 1” የተባለ ሮኬትን ወደ ጨረቃ ለማስወንጨፍ ያደረገው ሙከራ ለሁለተኛ ጊዜ መክሸፉ ተሰምቷል።

የናሳ ተመራማሪዎች በትናትናው እለት ሮኬቱን ለማስወንጨፍ የሚረዳውን የጠፈር ማስወንጨፊያ ስርዓት ለማስጀምር በተደጋጋሚ ቢሞክሩም ለሁለተኛ ጊዜ ሳይሳካቸው ቀርቷል።

የሮኬቱ ማስወንጨፍ ለሁለተኛ ጊዜ ሳይሳካ የቀረው በማስወንጨፊያው ላይ ባጋጠመው የነዳጅ መፍሰስ እንደሆነም ታውቋል።

ይህንን ተከትሎም የዘርፉ ባለሙያ ኢንጂነሮች በሮኬቱ ላይ ድጋሚ ፍተሻ ያደርጋሉ የተባለ ሲሆን፤ ይህም ጊዜ ሉወስድ ይችላል ተብሏል።

ፍተሸው ከማስወንጨፊያ ስፍራ ይልቅ በመስሪያ ቦታው ላይ ተወስዶ ሊካሄድ እንደሚችል እና ይህም የሮኬቱን የማስወንጨፊያ ጊዜ እስከ ጥቅምት ወር ሊያዘገየው ይችላል ነው የተባለው።

ናሳ ሮኬቱን ባሳለፍነው ሰኞ ወደ ጨረቃ ለማስወንጨፍ ሞክሮ የነበረ ሲሆን፤ ሆኖም ግን አራቱ ትላልቅ ሞተሮች በትክክለኛ የሥራ ሙቀት ላይ መሆናቸውን ተቆጣጣሪዎች ማረጋገጥ ባለማቻላቸው ተቋርጦ ነበር።

ሮኬቱን የማስወንጨፍ ሙከራ ከትናትናው ጋር ለሁለተኛ ጊዜ የተካሄደ ሲሆን፤ መሳካት ግን አልቻለም።

አሜሪካ ከ50 ዓመታት በኋላ ተመራማሪዎችንና መሳሪያዎቻቸውን ወደ ጨረቃ ለመላክ እየሰራች ሲሆን፤ ይህም የአፖሎ ፕሮጀክት እአአ በ1972 ካበቃ በኋላ የተሰራ ነው።

6100 ሜትር የሚረዝመው ሮኬት አላማው ኦሪዮን የተባለውን ካፕሱል ወደ ጨረቃ ለማድረስ አላማ ኖሮት የተሰራ መሆኑንም ከናሳ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

News today, Technology

አፕል በአደጋ ወቅት ኔትዎርክ ከሌለበት ስፍራ በሳተላይት መልእት የሚልክ አይፎን 14 ይፋ አደረገ


አፕል ለስፖርተኞች የሚሆን “አልትራ” ስማርት ሰዓትም አስተዋውቋል

አፕል የመኪና አደጋ ቀደሞ መለየት የሚያችል ቴክኖሊጂ የተገጠመለት ስማርት ስልክም አስተዋውቋል

የአሜሪካው የቴክኖሎጂ ኩባያ አፕል በትናትናው ምሽት በበርካቶች ዘንድ ሲጠበቅ የነበረውን አይፎን 14 ስማርት ስልክን ጨምሮ ሌሎችም አዳዲስ የቴክኖለጂ ምርቶችን አስተዋውቋል።

አፕል ኩባያ በትናትናው እለት ባዘጋጀው መርሃ ግብር ላይ በቴክኖሎጂ የረቀቁ የአይፎን 14 ስማርት ስልኮች፣ ስማርት ሰዓት እንዲሁም የማዳመጫ ምርቶቹን ይፋ አድርጓል።

ክባያው ሁለት የአይፎን 14 ስማርክ ስልክ አይነቶችን ያስተዋወቀ ሲሆን፤ እነዚህም አይፎን 14 እና አይፎን 14 ፕላስ ናቸው።

ስማርት ስልኮቹ በቴክኖሎጂ የረቀቁ ናቸው የተባለ ሲሆን፤ ከዚህም ውስጥ በአደጋ ጊዜ ኔትዎርክ በሌለበት አካባቢ ላይ ስንሆን ከሳተላይት ጋር በመገናኘት መልእክት ለመላክ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ተገጥሞለታል።

ስማርት ስልኩ ያለ ሞባይል ኔዎርክ ከሳተላይት ጋር ተገናኝቶ መልእክት ለመላክ ዝቅተኛው 15 ሰከንድ ከፍ ካለ ደግሞ ጥቂት ደቂቃዎችን ሊፈጅበት ይችላል።

አዲሱ አይፎን 14 ከጀርባው ላይ ሶስት 12 ሜጋ ፒክስል ጥራት ያላቸው ካራዎች የተገጠሙ ሲሆን፤ የፊትለፊት (ሰልፊ) ካሜራውም 12 ሜጋ ፒከስል መሆኑ እና ለመጀመሪያ ጊዜ ራሱን የማስካከል ቴክኖሎጂም ተገጥሞለታል።

የአይፎን 14 ካሜራዎች ፈጣን እንቅስቃሴ ያላቸውን ቁሶች ፎቶ ማንሳት ጨምሮ በዝቅተኛ ብርሃን ፎቶ በማንሳት ረገድ 49 በመቶ ማሻሻያ እንደተረገም ኩባያው አስታውቋል።

ለስማርት ስልቹ የመሸጫ ዋጋ የተቆረጠላቸው ሲሆን፤ በዚህ የአይፎን 14 ዋጋ 799 የአሜሪካ ዶላር፣ የአይፎን 14 ፕላስ ደግሞ 999 ዶላር መሆኑም ታውቋል።

አፕል ኩባንያ ትናንት ካስተዋወቃቸው የቴክኖሎጂ ምርቶች ውስጥ ሲሪየስ 8 የተሰኘው ስማርት ሰዓትም ይገኝበታል።

ሲሪየስ 8 የተሰኘው ስማርት ሰዓት የመኪና አደጋ ቀደሞ መለየት የሚያስችል ቴክኖሊጂ የተገጠመለት ሲሆን፤ አደጋ ከደረሰ በኋላም የአደጋው የደረሰበትን አካባቢ የሚጠቁም መልእክት መላክ ይችላል ተብሏል።

ስማርት ሰዓቱ በተጨማሪም ለሴቶች የወር አበባን መከታተል እንዲሁም የሰውነትን ሙቀት በመለካት ክትትል ማድረግን ጨምሮ በርካታ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በውስጡ ይዟል።

አልትራ የተባለው ስማርት ሰዓትም አፕል ትናንት ካስተዋወቃቸው ውስጥ ሲሆን፤ በተለይም ለስፖርተኞች የሚያለግል ነው ተብሏል።

አልትራ ስማርት ሰዓት ውሃ የማያስገባ በመሆኑ ለዋነተኞች እንዲሁም በቀላሉ የማይሰበር እና አቧሯ የማያስገባ መሆኑ ደግሞ ለአትሌቶች እና ለሌሎችም ስፖርተኞች ያገለግላል።

News today, Technology

የጃፓን ተመራማሪዎች የሰዎች ቀለድ የሚያስቀው ሮቦት ሰርተዋል

ሮቦቱን ሳቅ ያስተማሩት የጃፓን ክዮቶ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ናቸው

የሚስቀው ሮቦት ፕሮጀክት ሮቦቶችን ከሰው ልጅ ጋር የማመሳሰል እቅድ አንዱ ካል ነው

የጃፓን ተመራማሪዎች ከዚህ በፊት ያልተመለደ “በሰዎች ቀልድ የሚስቅ ሮቦት” መስራታቸውን ከሰሞኑ አስታውቀዋል።

ሮቦቱን ሳቅ ያስተማሩት የጃፓን ክዮቶ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ሲሆኑ፤ ዋና አላማዉም ሮቦቶች የበለጠ ከሰው ልጆች ጋር ለማመሳሰል እንደሆነም ተነግሯል።

ክዮቶ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ሮቦቱ ትክክለኛ የሰው ልጆችን ሳቅ እንዲስቅ ለማለማመድም ሰው ሰራሽ ክህሎት (አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ) መጠቀማቸውን አስታውቀዋል።

ተመራማሪዎቹ ኤሪካ የሚል ስያሜ ባለው ሮቦት ላይ ሳቅን የማስተማር ስራውን እየሰሩ ሲሆን፤ ይህ ስራም በሰዎች እና በሮቦቶች መካከል ያለው ንግግሮች የበለጠ ተፈጥሯዊ እንዲመስሉ እንደሚያደርግ ተስፋ ሰንቀዋል።

ርዝመታቸው ከሁለት እስከ ሶሰስተ ደቂቃ የሚቆዩ ንግግሮች በሰዎች እና በኤሪካ ሮቦት መካከል የተደረገ ሲሆን፤ ይህም አዲሱን ሲሰተም ለመመኮር እንደተካሄደ እና ስራውም በጎ ውጤት እንደተገኘበት አስታውቀዋል።

ሮቦቶቹ የበለጠ ከሰዎች ጋር እንዲግባቡ እና በቀልዶች የምር እንዲስቁ ለማስቻል አሁንም ቀሪ ስራች እንደሚቀሩ አስታውቀዋል።

በሰዎች እና በሮቦቶች መካከል ልክ ንደጓደኛ መደበኛ ንግግሮች እንዲኖሩ ለማስቻል እየሰሩ መሆኑን ያስታወቁት ተመራማሪዎቹ፤ ይህንን እውን ለማድረግ እን ከ10 እስከ 20 ዓመት ሊያስፈልገን ይችላል ብላዋል።

News today, Technology

ሚሳዔልና ተተኳሽ ቦምቦችን ጭኖ በሰዓት ከ2 ሺህ ኪ.ሜ በላይ የሚበረው “ሚኮያን ሚግ-35” ጄት

ሚኮያን MIG-35 ሩሲያ ካሏት አደገኛ የጦር ጄቶች ውስጥ አንዱ ነው

ሚኮያን MIG-35 ተዋጊ ጄት

እስከ ከ300 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ የሚገኙ የባሀር ላይና የአየር ላይ ጠላት ኢላማዎችን መለየት ይችላል

ሚኮያን MIG-35 ተዋጊ ጄት ሩሲያ ካሏት ጦር የውጊያ ጄቶች ውስጥ በአደገኛነቱ እና በፈጣንነቱ ብዙ ይነገርለታል።

ሚኮያን MIG-35 ተዋጊ ጄት በፈረንጆቹ 2007 የተመረተ ሲሆን፤ ሩሲያ አሁን ላይ ከዩክሬን ጋር ከገጠመችው ጦርነትን ጨምሮ በተለያዩ አውደ ውጊያዎች ላይ እንተጠቀመችበት ኤር ፎርስ ቴክኖሎጂ ድረ ገጽ አስነብቧል።

ተዋጊ ጄቱ ክሊሞቭ አር ዲ 33 MK የሚል መጠሪያ ያለው ሁለት ሞተሮች የተገጠሙለት ሲሆን፤ ከመሬት ለመነሳት 122 ሜትር የመንደርደሪያ፤ ለማረፍ ደግሞ 137 ሜትር ርዝመት ቦታ ያስፈልገዋል።

በሰዓት ከ2 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ አየር ላይ የሚከንፈው ሚኮያን MIG-35 ተዋጊ ጄት፤ በአንድ ጊዜ በተሞላለት ነዳጅ ከ3 ሸህ ኪሎ ሜትሮች ባለይ፤ እዛው አየር ላይ ነዳጅ ተከሞላለት ደግሞ ከ5 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ መጓዝ እንደሚችል ታውቋል።

ተዋጊ ጄቱ ፀረ መርከብ እና ፀረ አውሮፕላን ሚሳዔሎችን ጨምሮ የተለያዩ ተተኳሽ ቦምቦችን የመታጠቅ አቅም ያለው እንደሆነ ይነገራል።

ሚኮያን MIG-35 ተዋጊ ጄት ከሚታጠቃቸው እና ከሚያስወነጭፋቸው መሳሪያዎች መካከልም ሚግ-35 Kh-29TE ሚሳኤል እና KAB-500Kr TV ቦምቦች ተጠቃሽ ናቸው።

ሚኮያን MIG-35 ተዋጊ ጄት አየር ክልልን ጦሶ የገባን የጠላት አውሮፕላን ከ160 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ መለየት እንደሚችልም ኤር ፎርስ ቴክኖሎጂ ድረ ገጽ መረጃ ያመለክታል።

ታዲያ ይህ የጦር ጄት የአየር ክልል ጥሶ የገባን የጠላት አውሮፕላን ሚግ-35 Kh-31P ፀረ-ራዳር ሚሳኤል በመጠቀም የሚያወድም መሆኑ ተነግሯል።

ሚኮያን MIG-35 ተዋጊ ጄት በተጨማሪም የሀገርን የውሃ ክልል ጥሶ የገባን መርከብ ከ300 ኪሎ ሜትር ላይ የመለየት ብቃት ያለው ሲሆን፤ አስፈላጊ ሆኖ ከገተኘ Kh-31A ፀረ-መርከብ ሚሳኤል በማስወንጨፍ መምታት ይችላል ተብሏል።