News today, Politics

በሶማሊያ መንግስት የሚደገፉ ሚሊሻዎች 45 የአልሸባብ ታጣቂዎችን ገደሉ ተባለ

አልሸባብ በቅርቡ አንድ ሆቴል በመክበብ 21 ሰዎችን መግደሉ ይታወሳል

የሶማሊያ ፕሬዝደንቱ አልሸባብን ለማጥፋት ጠንካራ እንቅስቃሴ እየታየ መሆኑን ተናግረዋል

በሶማሊያ መንግስት የሚደገፉ ሚሊሻዎች ቢያንስ 45 የአልሸባብ ታጣቂዎችን መግደላቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

ግድያው የአልቃይዳ አጋር በሆነው ቡድን እና በፌዴራል መንግስት በሚደገፉ ሚሊሻዎች መካከል ከፍተኛ ግጭት የታየበት የግዛት የቅርብ ጊዜ ክስተት ነው ተብሏል።

አልሸባብ በሶማሊያ የሸሪዓ ህግን በጥብቅ እንዲተገበር ለማስገደድ ከአስር አመታት በላይ ጦርነት ከፍቷል።

ቡድኑን ለማጥፋት በአካባቢውም ሆነ በግዛቱ ሃይሎች ጥረት ቢደረግም ቡድኑ በመላ ሀገሪቱ ብጥብጥ ማድረጉን እንደቀጠለ ነው። 

ባለፈው ወር ታጣቂ ቡድኑ በዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ የሚገኘውን ሆቴል ለ30 ሰአታት ከበባ በማድረግ በትንሹ 21 ሰዎች ሲገደሉ ከመቶ በላይ ማቁሰሉ ይታወሳል።

በሰኔ ወር የአልሸባብ ታጣቂዎች ከኢትዮጵያ ጋር በሚያዋስኗቸው አቅራቢያ እና አዋሳኝ መንደሮች ላይ በርካታ ጥቃቶችን ፈጽመው ከ12 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተዘግቧል።

 በጥቃቱ በደርዘን የሚቆጠሩ የቡድኑ ታጣቂዎችም ተገድለዋል።

ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ግን አርብ ዕለት ሀገራቸው ከአልሸባብ ጋር በምታደርገው ትግል ትልቅ ስኬት እያየች ነው ብለዋል።

ፕሬዝደንቱ አልሸባብን ለማጥፋት ጠንካራ እንቅስቃሴ እየታየ መሆኑን ተናግረዋል።

News today, social life

የሴኔጋል ፓርላማ አባላት እርስበርሳቸው ተደባደቡ

ሴኔጋል ከአንድ ወር በፊት ነበር የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ ያካሄደችው።

ገዥው ፓርቲ አብዛኛውን መቀመጫ በተቃዋሚ ፓርቲዎች በተነጠቀበት በዚህ ምርጫ ተመራጭ የሆኑ የምክር ቤት አባላት ዛሬ ስራቸው ጀምረዋል።

አባላቱ በዛሬው ስብሰባቸው የምክር ቤቱን ተጠሪ ፕሬዝዳንት መምረጥ የነበረባቸው ቢሆንም ወደ ስምምነት መምጣት አልቻሉም።

የምክር ቤቱ አባላት አለመስማማታቸው ተከትሎ በተፈጠረ አለመግባባት በወንበር እና ውሀ መያዣ ፕላስቲኮችን እርስ በርስ በመወራወር እንደተደባደቡ ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል።

በምክር ቤቱ አባላት የተፈጠረውን ሁከት ተከትሎም የሀገሪቱ ፖሊስ ገብቶ ተደባዳቢዎቹን በቁጥጥር ስር በማዋል ክስተቱን ተቆጣጥሯል ተብሏል።

የከዓለም ዙሪያ ቤተሰብ ይሁኑ
ቴሌግራም፡ https://t.me/KeAlemiZuriya
ዩቲዩብ: https://youtube.com/c/Kealemizuriya
ድረገፅ: https://kealemizuriya.data.blog
ትዊተር: https://twitter.com/KeAlemiZuriya
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/KeAlemiZuriya
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/Kealemizuriya