News today, social life

በዓለም ላይ 50 ሚሊዮን ዜጎች አሁንም በባርነት ውስጥ እንደሚኖሩ ተመድ ገለጸ


በዓረብ ሀገራት ከፍተኛ የግዳጅ ስራዎች ውስጥ የሚኖሩ ዜጎች እንዳሉ ተመድ ገልጿል

በዓለም ላይ 50 ሚሊዮን ዜጎች አሁንም በባርነት ውስጥ እንደሚኖሩ ተመድ ገለጸ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) ባወጣው ሪፖርት 50 ሚሊዮን የዓለማችን ዜጎች አሁንም በባርነት ውስጥ እንደሚኖሩ ገልጿል።

በዓለማችን ከሚኖሩ 150 ሰዎች ውስጥ አንድ ሰው በግዳጅ ስራ ላይ ወይም ጋብቻ ውስጥ እንደሚኖሩ የድርጅቱ ሪፖርት ያስረዳል።

ከፍተኛ የእድሜ ጣራ ያስመዘገቡ 15 የአፍሪካ ሀገራት
ዓለም አቀፉ የሰራተኞች ድርጅት ወይም አይኤልኦ እና የፍልሰተኞች ድርጅት በጋራ ባወጡት ዓመታዊ ሪፖርት 27 ሚሊዮን ዜጎች በግድ ስራ እንዲሰሩ እየተደረገ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 15 ሚሊዮን ያህሉ ሴቶች እና ህጻናት ናቸው ተብሏል፡፡

ተመድ በፈረንጆቹ 2017 ላይ ተመሳሳይ ሪፖርት ይፋ አድርጎ የነበር ሲሆን አሁን ላይ በባርነት የሚኖሩ ዜጎች ቁጥር ከአምስት ዓመት በፊት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር የ2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ህዝብ ጭማሪ ማሳየቱ ተገልጿል፡፡

በባርነት ተገደው ከሚሰሩ ዜጎች ውስጥ 22 ሚሊዮኑ በእስያ፣ 4 ነጥብ 1 ሚሊዮን ያህሉ ደግሞ በአውሮፓ፣ 3 ነጥብ 8 ሚሊዮኑ በአፍሪካ፣ እንዲሁም 3 ነጥብ 6 ሚሊዮን በአሜሪካ እና 900 ሺህ ያህሉ ደግሞ በመካከለኛው ምስራቅ ይኖራሉ ተብሏል፡፡

በዓረብ ሀገራት ከአንድ ሺህ ሰዎች መካከል ስድስቱ ተገደው ስራ የሚሰሩ ሲሆን ይህ አሃዝ በሌሎች አህጉራት ካለው ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛው እንደሆነ ተገልጿል፡፡

6 ነጥብ 3 ሚሊዮን ያህል ዜጎች ደግሞ ተገደው በሴተኛ አዳሪነት እንዲሰማሩ ተደርገዋል ያለው ተመድ በተለይም ስደተኞች የዚህ ድርጊት ሰለባ እንደሆኑ ተጠቅሷል፡፡

ተገደው በጋብቻ ውስጥ እየኖሩ ያሉት ዜጎች ቁጥር አሁን ላይ 22 ሚሊዮን ያህል ናቸው የተባለ ሲሆን ይህ አሃዝ ከአምስት ዓመት በፊት በጥናት ከተረጋገጠው ጋር ሲነጻጸር የ6 ነጥብ 6 ብልጫ ዓለው ተብሏል፡፡

እስያ እና ፓሲፊክ አካባቢዎች ከ14 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ተገደው በትዳር ውስጥ ያኖራሉ ያለው ተመድ ቀሪው በአፍሪካ እና አውሮፓ እንደሚኖሩ ተገልጿል፡፡

ዝቅተኛ ኢኮኖሚ ባለባቸው ሀገራት ውስጥ ከአምስቱ ሰዎች መካከል ሶስቱ በግድ በትዳር ውስጥ እየኖሩ ሲሆን በበለጸጉ ሀገራት ደግሞ 26 በመቶዎቹ ሰዎች በተመሳሳይ የግዳጅ ጋብቻ ውስጥ ያሉ ናቸው ተብሏል

News today, Politics

ለተመድ ጠቅላላ ጉባዔ የአሜሪካ ቪዛ ሲጠይቁ የቆዩት የሩሲያ ልዑካን ወደ ኒውዮርክ ለመሄድ የሚያስችል ቪዛ አገኙ

አንጋፋው ዲፕሎማት ሰርጌ ላቭሮቭ “በፑቲን ምትክ በጠቅላላ ጉባዔው ሩሲያን ወክለው በመሳተፍ ላይ ናቸው” ተብሏል
ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጉባዔ የአሜሪካ ቪዛ ሲጠይቁ የቆዩት የሩሲያ ልዑካን ወደ ኒውዮርክ ለመሳተፍ የሚያችላቸው ቪዛ አግኝተዋል፡፡


የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ እና የሩሲያ ልዑካን ቡድን አባላት በኒውዮርኩ ስብሰባ ለመሳተፍ የሚያስችላቸው ቪዛ ማግኘታቸው የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡


ሩሲያ፤ 77 ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ለሚወክላት ልዑክ የቪዛ ጥያቄ ማቅረቧን ካቀረበች ብትቆይም አሁን ላይ የዘገየ ምላሽ ማግኘቷ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ሞስኮ፤ አሜሪካ በጠቅላላ ጉባኤው ሙሉ በሙሉ የሩሲያ ተሳትፎን ለመከላከል እየሞከረች ነው የሚል ክስ ስታሰማ መቆየቷም አይዘነጋም፡፡


“አሜሪካ ግዴታዎቿ እየጣሰች ነው” ሲሉም ነበር የከሬምሊን ሰዎች ዋሽንግተንን የወቀሱት፡፡
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዘንድሮ በሚካሄደው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ እንደማይገኙ ቀድመው መግለጻቸው ይታወሳል።


በዚህ መሰረት በጉባዔው ሩሲያን የሚወክሉት ከፑቲን ቀጥሎ ወዳጆቻቸው “ጠንካራው ዲፕሎማት” የሚሏቸው፤ ምዕራባውያን ደግሞ “አደገኛው” የሚሏቸው የዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሩቁ ሰርጌ ላቭሮቭ ሆነዋል።


ሰርጌ ላቭሮቭ የሀገራቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት በአውሮፓውያኑ 2004 ነበር። የ77 ዓመቱ ሰርጌ ላቭሮቭ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከመሆናቸው በፊት ለ10 ዓመታት ማለትም ከአውሮፓውያኑ 1994 እስከ 2004 በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሩሲያ ቋሚ መልዕክተኛ ነበሩ።


ሩሲያን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት 77 ኛው ጠቅላላ ጉባዔ ላይ የወከሉት ሰርጌ ላቭሮቭ በሀገራቸው ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት መስራት የጀመሩት በ22 ዓመታቸው ሲሆን በድምሩ ለግማሽ ክፍለ ዘመን (ለ 50 ዓመታት) ያገለገሉም ናቸው።


77 ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ በፈረንጆቹ ከዛሬ መስከረም 13 እስከ 20 በኒውዮርክ እንደሚካሄድ የወጣው መርሃ ግብር ያመለክታል።

social life

ደቡብ ኮሪያ በኮሪያ ጦርነት ወቅት የተለያዩ ቤተሰቦች እንዲገናኙ ከሰሜን ኮሪያ ጋር መነጋገር እንደሚፈልግ ገለጸች


አዲሱ የደቡብ ኮሪያ መንግስት በ1950ዎቹ በተካሄደው የኮሪያ ጦርነት ወቅት የተለያዩ ቤተሰቦች እንዲገናኙ ለማድረግ ከሰሜን ኮሪያ ጋር ለመነጋገር ማቀዱን ገልጿል።


በደቡብ እና ሰሜን ኮሪያ መካከል በኑክሌር የጦር መሳሪያ ጉዳይ ለረጅም ጊዜ የቆየ አለመግባባት አለ።


የቤተሰቦች መቀላቀል ጉዳይ እጅግ ሰብአዊና ሰሜታዊ የሚያደርግ ጉዳይ ነው። 
ነገርግን ሰሜን ኮሪያ የቤተሰቦችን መገናኘት ጉዳይ ከደቡብ ኮሪያ ጋር እንደመደራደሪያ ስለምትቆጥረው፣ሰሜን ኮሪያ የደቡብ ኮሪያን መንግስት እቅድ ላትቀበለው ትችላለች ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።


የኑክሌር አቅሟን በማሳደግ ላይ ያለችው ሰሜን ኮሪያ፣ ከደቡብ ኮሪያ እና ከአሜሪካ የቀረበላትን በኑክሌር ጉዳይ ውይይት በንቀት አልፋዋለች።
“ደቡብ እና ሰሜን የሚያመውን እውነታ መጋፈጥ አለባቸው፤የተለያዩ ቤተሰቦች የሚለው ቃል ከመጥፋቱ በፊት ችግሩን መፍታት አለብን” ሲሉ የውህደት ሚኒስትር ክዎን ዮንገዜ ተናግረዋል።


ሚኒስትሩ ኃላፊነት የሚሰማቸው የሁለቱ ኮሪያዎች በአካል ተገናኝተው ልባዊ እንደሚያደርጉ ተስፋ አለኝ ብለዋል።


የሁለቱ ኮሪያዎች የቤተሰብ መገናኘቱ የቆመው በፈረንጆቹ 2019 አሜሪካ ሰሜን ኮሪያ የኑክሌር ፕሮግራሟን እንድታቆምና በምትኩ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ጥቅም እንድታገኝ ያደረገችው ወይይት ያለውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ ነው።
አሜሪካ ሰሜን ኮሪያ ያለቅድመ ሁኔታ ወደ ኑክሌር ውይይት እንድትመጣ ብትጠይቅም፣ ሰሜን ኮሪያ አሜሪካ በሰሜን ኮሪያ ላይ ያላትን ጸብ አጫሪ ፖሊሲ መተው አለባት ስትል ቆይታለች።


ከበርካታ አስርት አመታት በኃላ የሚፈላለጉት ቤተሰቦች በህይወት ይኖሩ ይሆን እያሉ ይጨነቃሉ።


እንደ ዩኒፊኬሽን ሚኒስትሩ ከሆነ ከ133ሺ በላይ በሰሜን ኮሪያ ካሉ ቤተሰቦቻቸው ጋር ለመገናኘት ያመለከቱ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 70 በመቶ የሚሆኑት ህይወታቸው አልፏል።

Politics

ግሪክ የቱርክ ፕሬዝዳንት ዛቻ “ስጋት ፈጥሮብኛል ዓለም ይወቅልኝ” ስትል ጠየቀች

September 8, 2022
ኤርዶሃን፤ የኤጂያን የአየር ክልል ጥሳለች ባሏት ግሪክ ላይ “ከባድ ዋጋ ያስከፍልሻል” ሲሉ ዝተዋል


የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን ግሪክ በኤጂያን የአየር ክልል ላይ በሚንቀሳቀሱት የቱርክ አውሮፕላኖች ላይ የምትፈጥርው “የማስጨነቅ ድረጊት” የማታቆም ከሆነ አጻፋው ከባድ እንደሚሆን ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል፡፡


ፕሬዝዳንቱ በጥቁር ባህር አከባቢ በተደረገ ሰልፍ ባደረጉት ንግግር “ሄይ ግሪክ፣ ታሪክን ተመልከቺ፤ከዚህ በላይ የምትሄጂ ከሆነ ብዙ ዋጋ ትከፍያለሽ” ሲሉም ዝተዋል፡፡


ቱርክ በዩክሬኑ የዛፖሪዝሂያ ኒውክሌር ጣቢያ ግጭት ጉዳይ ማሸማገል ትችላለች- ፕሬዘዳንት ኤርዶሃን
የፕሬዝዳንቱ ዛቻ ስጋት ውስጥ የከተታት አቴንስም ታዲያ እየደረሰብኝ ያለውን ዛቻ ስጋት ፈጥሮብኛል ዓለም ይወቅልኝ እያለች ነው፡፡


ግሪክ ዓለም የአንካራን ባህሪ እንዲያወግዝ የሚጠይቅ ደብዳቤ ለኔቶ እና ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት መላኳንም ነው ሮይተርስ የዘገበው፡፡
ቱርክ በቅርብ ወራት ወዲህ አቴንስ ግጭት ቀስቃሽ ድርጊቶች እየፈጸመች እንደሆነና ይህም የተጀመረውን የሰላም ጥረት ሚያበላሽ መሆኑ ስትገልጽ መቆየቷ ይታወቃል፡፡


ሀገራት ከቱርክ የባህር ጠረፍ አቅራቢያ በሚገኙ የግሪክ ደሴቶች ዙሪያ በየቀኑ የአየር ሃይል ጥበቃዎችንና የመጥለፍ ተልእኮ እንቅስቀሰሴዎች የሚያደረጉ ሲሆን ለረዥም ጊዜ የቆዩ የባህርና የአየር ወሰን አለመግባባቶች እንዳሏቸው ይታወቃል።


አቴንስ፤ አንካራ በግሪክ ደሴቶች የአየር ክልል ላይ የምታደርገው በረራ ተንኳሽ ነው ስትል ትከሳለች፡፡
ቱርክ በበኩሏግሪክ ከአንደኛውና ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የተፈራረሙትን የሰላም ስምምነቶች በመጣስ ወታደሮቿን በኤጂያን ባህር ደሴቶች ላይ እያሰፈረች ነው የሚል ክስ ስታቀርብ ትደመጣለች፡፡


በ 1922 የቱርክ ኃይሎች በኤጂያን የባህር ዳርቻ ወደ ከተማዋ ከገቡ በኋላ የግሪክን ወረራ ማብቃቱን ያስታወሱት ኤርዶሃን “ግሪክን የምንነግራት አንድ ቃል ብቻ ነው፡- ኢዝሚርን (ቀደም ባሉ ጊዜያት ቱርኮች አሸነፊ ሆነው የተቆጣጠሩት ስፋራ) አትርሺ ” ብለዋል ፕሬዝዳንቱ።


በደሴቶቹ ላይ ያደረግሺው ወረራ እኛን አያስተሳስረንም ያሉት ፕሬዝዳንቱ “ጊዜው ሲደርስ አስፈላጊውን ነገር እናደርጋለን። እንደምንለው፣ አንድ ሌሊት በድንገት ልንመጣ እንችላለን”በማለትም ነው ፕሬዝዳንቱ በጎረቤት ሶሪያን ኦፕሬሽን ለማድረግ ባሰቡ ወቅት ደጋግመው ሲጠቀሙባቸው የነበሩትን ቃላቶች በኤቴንስ ላይ የሰነዘሩት፡፡


የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜቭሉት ካቩሶግሉ አቴንስ ወታደሮቿን ወደዚያ (ደሴቶቹ) መላክ ከቀጠለች አንላራ የግሪክን ሉዓለዊነት ልትፈታተን እንደምትችል ባሳለፍነው ወርሃ ሰኔ ማስጠንቀቂያ አዘል መልዕክት ማስተላለፋቸው አይዘነጋም፡፡

News today, social life

በኮንጎ ሪባን በመቁረጥ ሰነ-ስርዓት ወቅት ድልድይ መደርመሱ አነጋገረ

በኮንጎ ሪባን በመቁረጥ ሰነ-ስርዓት ወቅት ድልድይ መደርመሱ አነጋገረ
September 7, 2022
በኮንጎ ሪባን በመቁረጥ ሰነ-ስርዓት ወቅት የተደረመሰው ድልድይ አነጋጋሪ ሆኗል


ድልድዩን ሊመርቁ የተገኙ የክብር እንዶች ድልድዩ ላይ ቆመው ሪባን በሚቆርጡበት ወቅት ድልድዩ ተደርምሷል፡፡ ሮይተርስ አረጋግጫለሁ ባለው ተንቀሳቃሽ ምስል ድልድዩ የሚመረቀው በኮንዶ ዋና ከተማ ሲሆን የምርቃት ሪባን የሚቆርጡ ሰዎች በድልድዩ ላይ በቆሙበት ወቅት ድልድዩ ሊደረመስ ችሏል፡፡


ተንቀሳቃሽ ምስሉ በቦታው የተገኙት ሰዎች በግርምት ሲመለከቱ ይታያሉ፡፡
ድልድዩ የእጅ መያዣዎቹን ጨምሮ ማእከላዊ አካሉ ተደርምሶ ከሁለት ሜትር ርቀት ላይ ማረፉን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡


 ለምርቃቱ የመጡት የክብር እንግዶች ከአደጋው ለማምለጥ ሲታገሉ በቦተው የነበሩ ተመልካቾች ሲስዉ ታይተዋል፡፡ በአደጋው የደረሰ ጉዳት የለም ተብሏል፡፡
ተንቀሳቃሽ ምስሉ በሰፊው የተሰራጨ ሲሆን ክስተቱ መነጋገሪያ ሆኗል፡፡

News today, Politics

ሩሲያ የተጣሉባት ማዕቀቦች ካልተነሱ ወደ አውሮፓ ነዳጅ እንደማትልክ ገለጸች

የቡድን ሰባት አባል ሀገራት በሩሲያ ነዳጅ ላይ የዋጋ ተመን ማውጣታቸው ይታወሳል

ሩሲያ የተጣሉባት ማዕቀቦች የማይነሱ ከሆነ ወደ አውሮፓ ነዳጅ እንደማትልክ ገልጻለች።

የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ስድስት ወራት ያለፈው ሲሆን ጦርነቱ በዓለም ምግብ እና ነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ እንዲመዘገብ ምክንያት ሆኗል።

 ጦርነቱ በዓለም ዲፕሎማሲ ላይ የተለያዩ መፋለሶችን ያስከተለ ሲሆን ሀገራት ከትብብር ይልቅ ጎራ ለይተው እንዲሰለፉ እያደረገም ይገኛል።

አሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት በሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ላይ በተለያየ መንገድ በመሳተፍ ላይ ሲሆኑ በሩሲያ ላይ ከስድስት ሺህ በላይ ማዕቀቦችን ጥለዋል።

ሩሲያም የአጸፋ እርምጃ በመውሰድ ላይ ስትሆን ማዕቀቡ ለአውሮፓ ሀገራት የምታቀርበውን ጋዝ ሽያጭ እክል አስከትሏል።

ይሄንን ተከትሎም 40 በመቶ ለሚሆኑ የአውሮፓ ሀገራት ነዳጅ ስታቀርብ የነበረችው ሩሲያ በማዕቀቡ ምክንያት ለአውሮፓውያን ነዳጅ መላክ አለመቻሏን በተደጋጋሚ ገልጻለች።

በነዳጅ ዕጥረት እየተፈተነ ያለው የአውሮፓ ህብረትም በሩሲያ ላይ የጣለውን ማእቀብ እስከማላላት ቢደርስም በሩሲያ ላይ የተጣሉት ሁሉም ማዕቀቦች እስካልተነሱ ድረስ ሩሲያ ምንም አይነት ነዳጅ እንደማትልክ ራሺያ ቱዴይ ዘግቧል።

የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቃል አቀባይ ድሚትሪ ፔስኮቭ ዛሬ በሰጡት መግለጫ የአውሮፓ ሀገራት እና ኩባንያዎች በሩሲያ ላይ የጣሉት ማዕቀብ ሳይነሳ አንዲት ጠብታ ነዳጅ አንልክም ሲሉ ተናግረዋል።

የአውሮፓ ባለ ግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት የሆኑት ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ብሪታንያ፣ ቤልጂየም እና ሌሎች ሀገራት በነዳጅ ዕጥረት እየተፈተኑ ናቸው ተብሏል።

እነዚህ ሀገራት ሩሲያ ነዳጇን እንደጦር መሳሪያ እየተጠቀመችበት ነው ሲሉም ሞስኮን ከሰዋል።

የዓለማችን ሰባቱ ባለ ግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት የሆኑት የቡድን ሰባት አባል ሀገራት ከሰሞኑ  በሩሲያ ነዳጅ ላይ የዋጋ ተመን ማውጣታቸው ይታወሳል።

እነዚህ ሀገራት ሩሲያ ነዳጇን በተተመነላት ዋጋ መሰረት ለአውሮፓ ሀገራት እንድትሸጥ የወሰኑ ቢሆንም ሩሲያ በበኩሏ ምንም አይነት ነዳጅ ወደ አውሮፓ አልሸጥም የሚል ውሳኔ አሳልፋለች።