News today, social life

የሕዳሴ ግድበ 2ኛው ተርባይን ኃይል ማመንጨት ጀመረ

ዛሬ ሥራ የጀመረው ሁለተኛው ዩኒት 375 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም አለው
ሲጠናቀቅ ከአፍሪካ ትልቅ ግድብ እንደሚሆን የሚጠበቀው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ 2ኛው ተርባይን የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ጀመረ።


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በቤንሻንጉል ጉሙዝ ጉባ ወረዳ በታደሙበት ዝግጅት ነው በዛሬው ዕለት ሁለተኛው ተርባይን ኃይል ማመንጨት የጀመረው።


የሕዳሴ ግድብ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ጀመረ
የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ካሉት 13 ተርባይኖች መካከል ዩኒት 9 የሚባለው ሁለተኛው ተርባይን የተሳካ ተከላ እና ሙከራ ከተደረገ በኋላ ኃይል የማመንጨት ስራው ን ዛሬ በይፋ ጀምሯል።


ዛሬ በይፋ ሥራ የጀመረው ሁለተኛው ዩኒት 375 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳለው ተገልጿል።
ባሳለፍነው ጥር 25 2014 ዓ.ም በዚህም ግድቡ ካሉት ተርባይኖች ውስጥ አንዱ የሆነው እና ዩኒት 10 የሚል መጠሪያ ያለው ተርባይን 375 ሜጋ ዋት ኃይል ማመንጨት መጀመሩ ይታወሳል።


ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ ግድብ ለመገንባት የመረሰት ድንጋይ ካስቀመጠች አንድ አመት በኋላ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ግብጽና ሱደን በግድቡ ላይ ስጋት እንዳላቸው ጥያቄ አንስተዋል፡፡
ኢትዮጵያ፣ሱዳንና ግብጽ በግድቡ አስተዳደር ጉዳይ የሶስትዮች ንግግር እና ድርድር ከመጀሩ ቆይተዋል፤ ነገርግን እስካን ከስምምነት አልደረሱም፡፡


የኢትዮጵያ መንግስት ግድቡን እየገነባ ያለው ለልማት አላማ ብቻ መሆኑን እና በታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ላይ የጎላ ተጽእኖ እንደማያደርስ በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል፡፡ ግብጽና ሱዳን ግን በግድቡ ዙሪያ የየራሳቸው አቋም አላቸው፡፡


በተለይም ግብጽ በቅኝ ግዛት ዘመን የተፈረመ ስምምነትን ጭምር በመጥቀስ፤ ታሪካዊ የሆነ የውሃ ድርሻዋ ላይ ተጽእኖ እንሚያሳድር እና ግድቡ አሉታዊ ተጽእኖ እንደሚያሳድርባት ትገልጻለች፡፡


በ2013 ዓ.ም በአሜሪካ ዋሽንግተን ሲደረግ የነበረው የሶስትዮሽ ድርድር ከፈረስ በኋላ ድርድሩ በአፍሪካ ህብረት አመቻችነት እንዲካሄድ ተስማምተዋል፡፡


ድርድርሩ ወደ አፍሪካ ህብረት የመጣው ኢትዮጵያ፤ ድርድሩ ሳይጀመር የታዛቢነት ሚና የነበራቸው አሜሪካና የአለም ባንክ ሚናቸውን ወደ አደራዳሪነትና ወደ የስምምነት ሰነድ አርቃቂነት ከፍ በማድረጋቸው እና ኢትዮጵያም ይህን አልቀበልም በማለቷ ነው።


ኢትዮጵያ የግድቡ ጉዳይ የልማት ጉዳይ ነው ብትልም ፤ግብጽና ሱዳን የግድቡን ጉዳይ የጸጥታ ጉዳይ ነው በማለት ለተመድ የጸጥታው ም/ቤት በማቅረብ ም/ቤቱ ወይይት አድርጎበት ያውቃል።