News today, Politics

የሰሜን ኮሪያው መሪ ወታደሮቻቸው የኒውክሌር መከላከያ እንዲኖራቸውም መመሪያ ሰጥተዋል

የሰሜን ኮሪያው መሪ ወታደሮቻቸው የኒውክሌር መከላከያ እንዲኖራቸውም መመሪያ ሰጥተዋል

የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ሀገራቸው ከአሜሪካ ጋር ለሚደረግ ማንኛውም ወታደራዊ ግጭት ዝግጁ መሆኗን በልበሙሉነት ተናገሩ፡፡

ሮይተርስ ዮንሃፕ የዜና አገልግሎትን ጠቅሶ እንደዘገበው ፤ ኪም የደቡብ ኮሪያው ፕሬዝዳንት ዮን ሶክዬኦል እና ሰራዊታቸው “አደገኛ” ሙከራዎችን ካደረጉ የመጥፋት አደጋ ሊደርስባቸው እንደሚችልም አስጠንቅቋል።

የሰሜን ኮሪያው መሪ ወታደሮቻቸው የኒውክሌር መከላከያ እንዲኖራቸውም መመሪያ ሰጥተዋል።

ሰሜን ኮሪያ ሩሲያ ቀደም ሲል በተባበሩት መንግስታት ያቀረበቸውንና መጋቢት በነበረው የተመድ  ጸጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ውድቅ የተደረገውን የ“አሜሪካ በዩክሬን ውስጥ ባዮሎጂካል የጦር መሳሪያ ትሰራለች” ክስም አቅርባለች፡፡

የሞስኮ አጋር የሆነችው ፒዮንግያንግ፤ ዋሽንግተንን “የሰው ልጅን ለጥፋት የሚወረውር የባዮ ሽብርተኝነት መጥፎ ስፖንሰር” እና በ1950ዎቹ በኮሪያ ጦርነት ወቅት “የባክቴሪያ ጦርነት” ያደረገች ሀገር ናት ስትልም ወቅሳለች፡፡

ይህንን መሰል ወቀሳዎች ከሰሜን ኮሪያ በተጨማሪ ቻይና እና ሩሲያ ደጋግመው ሲሉት የሚደመጡ ቢሆንም በዋሽንግተን ግን ይህንን ስታስተባብል ትስተዋላለች።

የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን፤ ከሁለት ወራት በፊት የሰሜን ኮሪያ ጦር ሃይሎች ምስረታ ቀንን ምክንያት በማድረግ ባደረጉት ንግግር ከእኛ ጋር ግጭት ውስጥ ለመግባት የሚፈልግን ማንኛውንም ሀገር “እናጠፋለን” ሲሉ መዛታቸው የሚታወስ ነው፡፡

ማንኛውም ሀገር ሰሜን ኮሪያ ከነካ አጸፋው የከፋ እንደሚሆን ያስጠነቀቁት ኪም ጆንግ ኡን፤ ፒዮንግያንግ አሁንም ቢሆን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እድገትን ለማፋጠን ጠንክራ ትሰራለች ሲሉም ተደመጠዋል፡፡

ኪም “በማንኛውም ጊዜ ሪፐብሊኩ የጣለባችሁን ኃላፊነት የተሞላበት ተልእኮ እና ልዩ መከላከልን ለመፈጸም ዝግጁ መሆን አለባችሁ” የሚል መልእክት ለኒውክሌር ኃይል ማስተላለፈቻውም ነበር የሰሜን ኮሪያ የዜና አገልግሎት ኤጀንሲ በወቅቱ የዘገበው።

እናም አሁን አሜሪካ በዩክሬን ምድር ባዮሎጂካል መሳሪያዎችን እያመረተች ትገኛለች የሚሉት ኪም፤ ከአሜሪካ ጋር ግጭት እንዳይገቡ እጅጉን ተሰግቷል፡፡

ሩሲያ በየካቲት ወር መጨረሻ በዩክሬን ላይ ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ማካሄድ የጀመረችው፤ ዋሽንግተን በዩክሬን ውስጥ ባዮሎጂካል መሳሪያዎችን ለማምረት ለምርምር የገንዘብ ድጋፍ አድርጋለች የሚል ክስ ማቅረብ ከጀመረች በኋላና ወደፊት በሩሲያ ላይ ሊጋረጡ የሚችሉ አደጋዎችን ቀድሞ ለመከላከል በሚል እንደነበር አይዘነጋም፡፡