News today, Politics

ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ያለውን ችግር ለመፍታት ዝግጁ መሆኗን ገለጸች

ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ያለውን ችግር ለመፍታት ዝግጁ መሆኗን ገለጸች

ሩሲያ፤ ቻይናን ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ የምትወስዳቸውን “ሚዛናዊ” እርምጃዎች እንደምትደግፍም ገልጻለች

ሩሲያ፤ ቻይናን ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ የምትወስዳቸውን “ሚዛናዊ” እርምጃዎች እንደምትደግፍም ገልጻለች።

ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ያለውን ጦርነት በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት ዝግጁ መሆኗን አስታወቀች።

የሩሲያ ቤተ መንግስት (ክሬምሊን) ቃል አቀባይ፤ ዲሚትሪ ፒስኮቭ ሀገራቸው ከዩክሬን ጋር ያለውን ችግር በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት አሁንም ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል።

ፒስኮቭ ከሰሞኑ በእስያ ፓስፊክ ባለው ውጥረት ዙሪያም አስተያየት መስጠታቸውን ሩሲያ ቱዴይ ዘጎቧል። ቃል አቀባዩ የእስያ ፓስፊክ ውጥረት ቀላል ግምት ሊሰጠው አይገባም ሲሉም ነው አስተያየት የሰጡት።

የአሜሪካ ምክርቤት አፈጉባዔ በታይዋን ያደረጉት ጉብኝት እንደቀላል መታየት እንደሌለበት ያነሱት ፒስኮቭ ጉዳዩ ከባድ እንደሆነ ገልጸዋል።

የፔሎሲን የቻይና ጉብኝት ተከትሎ የሶስተኛው የዓለም ጦርነት ይነሳል የሚል ፍርሃትን እንዳለ የገለጹት ቃል አቀባዩ፤ ይህ ግን እንደማይከሰት ተናግረዋል።

ፒስኮቭ፤ ሀገራቸው ቻይናን ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ የምትወስዳቸውን “ሚዛናዊ” እርምጃዎች እንደምትደግፍ ተናግረዋል።

ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ያለባትን ችግር በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ዝግጁ እንደሆነችም ማረጋገጫ ሰጥተዋል።

ሩሲያ እና ዩክሬን የጀመሩት ጦርነት አራት ወራት አልፈውታል።

ምዕራባውያን ሩሲያ፤ ዩክሬይንን፤ ቻይና ደግሞ ታይዋንን ትወራለች የሚል ፍርሃት አላቸው።