News today, Politics

የታይዋን የሚሳዔል ማምረቻ ከፍተኛ ተመራማሪ ሆቴል ውስጥ ሞተው ተገኙ

የሀገሪቱ መርማሪ ፖሊስ የኦው ያንግ የሞቱበትን ምክንያት በማጣራት ላይ መሆኑ አስታውቋል

የታይዋን መከላከያ ሚኒሰቴር “ኦው ያንግ የታይዋን የሚሳዔል የማምረት አቅምን ለማሳደግ ሲሰሩ የነበሩ ከፍተኛ ባለሙያ ናቸው”ብሏል

የታይዋን የሚሳዔል ማምረቻ ከፍተኛ ተመራማሪና በወታደራዊ ባለቤትነት የተያዘው የናሽናል ቹንግ-ሻን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ተቋም ምክትል ኃላፊ ኦው ያንግ ሊ-ህሲንግ ፤ ሆቴል ውስጥ ሞተው መገኘታቸውን  የታይዋን መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

እንደ የታይዋኑ ሴንትራል ኒውስ ኤጀንሲ ዘገባ ከሆነ ኦው ያንግ ሊ-ህሲንግ ሞተው የተገኙው በደቡባዊ ታይዋን በሚገኝ ሆቴል ውስጥ ነው፡፡

ከቤተሰቦቹ በተገኘ መረጃ መሰረት የ57 አመቱ ኦው ያንግ የሞት ምክንያት የልብ ድካም ሊሆን እንደሚችል ቢገለጽም፤ የሀገሪቱ መርማሪ ፖሊስ ትክክለኛው የሞት ምክንያት ለማወቅ አስፈላጊውን የማጣራት ሂደት ላይ መሆኑ አስታውቋል፡፡

ኦው ያንግ በዚህ አመት መጀመሪያ ላይ የተለያዩ የሚሳዔል ማምረቻ ፕሮጀክቶችን ለመከታተል በሚል ወደ ሃላፊነት የመጡ እንዲሁም ወደ ሃላፊነት ከመጡ ወዲህ የታይዋን የሚሳዔል የማምረት አቅምን ከእጥፍ በላይ ለማሳደግ ከፍተኛ ሚና ሲጫወቱ የቆዩ ከፍተኛ ባለሙያ እንደነበሩ የታይዋን መከላከያ ሚኒሰቴር መረጃ ያስረዳል፡፡

ታይና ከቻይና ሊቃጣባት የሚችለውን አደጋ ለመከላከል በሚል ሚሳዔልን በከፍተኛ ሁኔታ በማምረት ላይ ተጠምዳለች፡፡ በዚህ አመት ብቻ የሚሳዔል ማምረት አቅሟን ወደ 500 ለማሳደግ እየሰራች መሆኗም ይገለጻል፡፡

የወቅቱ የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት ተከትሎ ቻይና እርምጃ እወስዳለሁ ማለቷ፤ የታይዋን መሪዎች ነገሮች በቅርበት እንዲከታተሉ ያስገደደና ሁኔታ መፈጠሩ የሚታወቅ ነው፡፡

በዚህም አሁን ላይ የናንሲ ፔሎሲ ጉብኝት ተከትሎ ቻይና በምታደርገው የአየር ላይ ወታደራዊ እንቅስቃሴ በሩቅ ምስራቅ ከፍተኛ ውጥረት የነገሰ ሲሆን ታይዋን ከፍተኛ የውጊያ ጥንቃቄ እንዳወጀች ነው፡፡

የታይዋን ፕሬዝደንት ጻይ ኢንግ ዌን ሀገራቸው ማንንም እንደማትተነኩስና ነገርግን ራሷን እንደምትከላከል መናገራቸው አይዘነጋም፡፡

የቻይና ወታደራዊ እንቅስቃሴ ለታይዋን ብቻ ሳይሆን ለመላው አለም ኃላፊነት የጎደለው ነው ሲም ነበር የተናገሩት ፕሬዝዳንቷ፡፡

News today, Politics, social life

በእስራኤል ጥቃት አንድ የታጣቂ ቡድን መሪን ጨምሮ አስር ሰዎች ተገደሉ


እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ በፈጸመችው የአየር ጥቃት አንድ የፍልስጤም ታጣቂዎች ቡድን መሪን እና አንዲት ህጻንን ጨምሮ 11 ሰዎች መገደላቸውን ሪፖርቶች አመለከቱ።

ይህን የእስራኤል ጥቃት ተከትሎ በደርዘኖች የሚቆጠሩ ሮኬቶች ከጋዛ ወደ እስራኤል የተተኮሱ ሲሆን፣ በዚህም ሳቢያ በአካባቢው ከባድ ውጥረት ነግሷል።

ይህንንም ተከትሎ እስራኤል በወረራ በያዘችው የዌስት ባንክ አካባቢ ባደረገችው አሰሳ 19 የኢስላሚክ ጂሃድ ቡድን አባላት ናቸው የተባሉ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሏ ተገልጿል።

በእስራኤል ጥቃት ከተገደሉት 11 ሰዎች መካከል ታይሰር ጃባሪ የተባለ የታጣቂዎች መሪ ይገኝበታል።

የአየር ጥቃቱ ግለሰቡ የሚመራው የፍልስጤም እስላማዊ ጂሃድ የተባለው ቡድን “ጥቃት ሊሰነዝር” መሆኑን ተከትሎ የተወሰደ እርምጃ ነው ስትል እስራኤል ምክንያቷን አሳውቃለች።

ከተገደሉት መካከል የአምስት ዓመት ታዳጊ የምትገኝበት ሲሆን፣ ሌሎች በርካቶች ደግሞ የመቁሰል ጉዳት እንደደረሰባቸው የአካባቢው የጤና ባለሥልጣናት ተናግረዋል።

የፍልስጤም እስላማዊ ጂሃድ የተባለው ቡድን ለእሰራኤል ጥቃት “የመጀመሪያ ምልሽ” ባለው አጸፋ ከ100 በላይ ሮኬቶችን ወደ እስራኤል ሌሊቱን ተኩሷል።

ከተተኮሱት ሮኬቶች አብዛኞቹ በእስራኤል የሚሳኤል መከላከያ አማካይነት መክሰማቸው የተነገረ ሲሆን፣ በበርካታ የእስራኤል ከተሞች ውስጥ ሌሊቱን በሙሉ የጥቃት ማስጠንቀቂያ ደውሎች ሲሰሙ አድረዋል።
የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር እስከ ቅዳሜ ንጋት ድረስ የዘለቁ የሮኬት ጥቃቶችን ጋዛ ውስጥ በሚገኙ በርካታ የታጣቂዎቹ ይዞታዎች ላይ ሲፈጽም ማደሩን ኣሰውቋል።

ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ተመሳሳይ ግጭት ተከስቶ ከ200 በላይ ፍልስጤማዊያን እና በርካታ እስራኤላውያን ከተገደሉ በኋላ በግብፅ አደራዳሪነት የተኩስ አቁም መደረሱ ይታወሳል።

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ያይር ላፒድ ሠራዊታቸው ለአገራቸው ስጋት በሆኑ ኢላማዎች ላይ ፈጣን ፀረ ሽብር ጥቃት መፈጸሙን የገለጹ ሲሆን፣ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ደግሞ ግጭቱ የተራዘመ ሊሆን እንደሚችል ስጋታቸውን አመልክተዋል።

ጋዛ ውስጥ በእስላማዊ ቡድን ኢላማዎች ላይ ነው የተፈጸመው በተባለው ጥቃት “15 የሚሆኑ ታጣቂዎች” መገደላቸውን የእስራኤል ሠራዊት ቃል አቀባይ መናገራቸው ተዘግቧል።

የጋዛ የጤና ባለሥልጣንት ግን ታይሲር ጃባሪን ጨምሮ አራት የእስላማዊ ቡድኑ ታጣቂዎች በእስራኤል ጥቃት መገደላቸውን አረጋግጠዋል።

የእስራኤል የመከላከያ ኃይል ታይሲር ጃባሪ የፍልስጥኤም እስላማዊ ጂሃድ ቡድን “ከፍተኛ መሪ” መሆኑን እና “በርካታ የሽብር ጥቃቶችን” በእስራኤላውያን ሰላማዊ ሰዎች ላይ ፈጽሟል ሲል ይከሰዋል።

የጋዛ ባለሥልጣናት እንዳሳወቁት በጥቃቱ ከተገደሉት ሰዎች በተጨማሪ 79 ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው መናገራቸውን የፈረንሳይ ዜና ወኪል ዘግቧል።

የፍልስጥኤም እስላማዊ ጂሃድ ቡድን ዋና ፀሐፊ ዚያድ አል-ናኻላ ወደ ኢራን በጉዞ ላይ ሳሉ “ለተፈጸመው ጥቃት በሙሉ ኃይላችን ምላሽ እንሰጣለን፣ በአሸናፊነት የምንወጣበት ጦርነት ይሆናል። የማይነካ ቦታ አይኖርም፣ ቴል አቪቭ በሮኬቶቻችን ጥቃት ስር ትሆናለች” ማለታቸው ተዘግቧል።

የጋዛ ሰርጥን የሚያስተዳድረው ሐማስ የፍልስጤም ታጣቂ ቡድኖች ዝም እንደማይሉና በሚካሄደው ዘመቻ ውስጥ በአንድነት እንደሚቆሙ ገልጿል።

News today, Politics

ደቡባዊ ሴኔጋልን ለመገንጠል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች ትጥቅ ለመፍታት ከመንግስት ጋር ተስማሙ


ታጣቂዎቹ ላለፉት 40 ገደማ ዓመታት ደቡባዊ ሴኔጋልን ለመገንጠል ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ ነበር
በሀገሪቱ መንግስት እና በታጣቂዎቹ መካከል የሰላም ስምምነት ተፈርሟል

የሴኔጋል መንግስት እና ደቡባዊ ሴኔጋልን ለመገንጠል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች እርቅ አወረዱ።

በሴዛር አቶቴ ባዲያቴ የሚመራው የካሳማንቼ ኃይሎች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (MDFC) ላለፉት 40 ገደማ ዓመታት ነፍጥ አንግቦ በደቡባዊ ሴኔጋል ሲንቀሳቀስ ነበር።

ሆኖም አሁን ትጥቅ አውርዶ ሰላማዊ ትግል ለማድረግ መስማማቱን አስታውቋል።

ስምምነቱን በፀጋ የተቀበሉት ፕሬዝዳንት ማኪ ሳልም ከሴዛር አቶቴ ጋር ከትናንት በተስቲያ ሐሙስ ተፈራርመዋል እንደ ሲጂቲኤን ዘገባ።

ማኪ ሳል የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ናቸው።

ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን እንደሚያስችል ተስፋ የተጣለበት የሰላም ስምምነት በጊኒ ቢሳው ነው የተፈረመው።

ስምምነቱ በሸምጋዮች ጥረት እውን የሆነ ሲሆን፤ ማኪ ሳል አማጺ ቡድኑን ከመንግስታቸው ጋር ለማሸማገል ላደረጉት ጥረት የጊኒ ቢሳውን ፕሬዝዳንት ዑማሮ ሲሶኮ ኢምባሎን አመስግነዋል።

የካሳማንቼ ኃይሎች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (MDFC) ነፍጥ አንግበው ለረጅም ዓመታት ከተንቀሳቀሱ የአፍሪካ አማፂ ቡድኖች መካከል አንዱ ነው።

News today, Politics

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፤ ቤጂንግ ለናንሲ ፔሎሲ ጉብኝት በዚህ ደረጃ ምላሽ የመትሰጥበት “ምንም ምክንያት የለም” አሉ

ብሊንከን፤ ቻይና ታይዋንን በመክበብ የምታካሂደው ወታደራዊ ልምምድ “ውጥረትን የሚያባብስ” ነው ሲሉ ኮንነዋል

2022/8/5 16:12 GMT

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን

በፔሎሲ ጉብኝት የተበሳጨችው ቻይና “ከአሜሪካ ጋር ስታደረግ የነበረው ወታደራዊ ማቋረጧን” ይፋ እስከማድረግ ደርሳለች

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ቻይና ታይዋንን በመክበብ የምታካሂደው ወታደራዊ ልምምድ ‘ያለው ውጥረት የሚያባብስ’ ነው ሲሉ ኮነኑ።

ብሊንከን የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ ወደ ታይዋን ላደረጉት ጉብኝት ምላሽ ለመስጠት በሚል ቤጂንግ ለጀመረችው ወታደራዊ ልምምድ የምታቀርበው “ምንም ምክንያት የለም” ማለታቸውም ኤፒ ዘግቧል።

ቻይና ባሊስቲክ ሚሳኤሎችን በመተኮስ ተዋጊ ጄቶች እና የጦር መርከቦች በታይዋን ዙሪያ ማሰማራቷን ተከትሎ በዓለም ላይ እጅጉን የመርከብ መስመሮች የሚበዙበት ቀጠና አደጋ እንዳንዣበበበት እየተገለፀ ነው።

ከደቡብ ምስራቅ እስያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ለመወያየት በበካምቦድያ መዲና ፕኖም ፔን የሚገኙት ብሊንከን ጉዳዩን በማስመልከት በሰጡት መግለጫ “የቻይና ድርጊቶች ያለውን ውጥረት ትርጉም ባለው ደረጃ የሚያባብሱ ናቸው” ሲሉ ተደምጠዋል።

በቅርቡ በኢንዶኔዥያ በተካሄደው ስብሰባ ላይ ዋንግ ዪን፤ በ25 ዓመታት ውስጥ ታይዋንን የጎበኙ ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት ፒሎሲ ወደ ደሴቲቱ ሊጓዙ እንደሚችሉ ነገሬው ነበር ያሉት ብሊንከን፤ የቻይና ድርጊት ከጠበቅነው ውጭ ባይሆንም የተጋነነ ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

“እውነታው ግን የአፈ ጉባኤዋ ጉብኝት ሰላማዊ ነበር፤ እንደዚህ አይነት የተጋነነ እና ተመጣጣኝ ያልሆነ ወታደራዊ ምላሽ የሚያሰጥበት ምንም ምክንያት የለም” ሲሉም አክለዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ብሊንከን ይህን ይበሉ እንጂ፤ ናን ፔሎሲ ቻይና እንደ አንድ ግዛቷ አድርጋ በምትቆጥራት ታይዋን ላይ ያደረጉት ጉብኝት የቤጂንግ ሰዎች ኩፉኛ ማስቆጣቱ እየተገለጸ ነው።

በአሜሪካ ድርጊት እጅጉን የተበሳጨችው ቻይና ከአሜሪካ ጋር ወታደራዊ ትብብሯን ማቋረጧን ከሰዓታት በፊት አስታውቃለች።

ቻይና በውጭ ጉዳይ ሚንስትሯ በኩል በሰጠቸው መግለጫ፤ ቤጂንግ እስካሁን ከከፍተኛ ወታደራዊ ትብብሮች ባለፈ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ ከዚህ በፊት የነበራትን የከፍተኛ መሪዎች የጋራ ውይይት መድረኮችን ከአሜሪካ ጋር በትብብር ላለመስራት ወስናለች።

እንዲሁም ቻይና ከአሜሪካ ጋር የነበራትን የድንበር አልባ ወንጀል መከላከል፣ ስደተኞችን ማጓጓዝ፣ አደገኛ እጽ ዝውውር መከላከል እና ሌሎች ስምንት የትብብር መስኮችን አቋርጣለች።

ቻይና ሰሞኑን ታይዋንን በጎበኙት የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ ላይ ማዕቀብ መጣሏ ይታወሳል።

News today, Politics

ኢትዮጵያ የ“አንድ ቻይና” ፖሊሲን እደግፋለሁ አለች

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይህ የኢትዮጵያ አቋም ዛሬ የተጀመረ አይደለም ብሏል

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም

የናንሲ ፔሎሲን ጉዞ ተከትሎ በቻይና-ታይዋን ጉዳይ ከፍተኛ ውጥረት መንገሱ ይታወቃል

ኢትዮጵያ ለረጅም ዓመታት ስታራምድ የቆየችውን የ”አንድ ቻይና” ፖሊሲ አቋሟን እንዳጸናች መሆኗን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ከወቅታዊ ዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ኢትዮጵያ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች የሚከሰቱ ዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮች ያሳስቧታል ብለዋል።

ሰሞኑን በቻይና-ታይዋን ጉዳይ የተከሰተውን ውጥረት በትኩረት እየተከታተለች መሆኑንም ነው የተናገሩት።

የኢትዮጵያ የ“አንድ ቻይና” ፖሊሲ አቋም ዛሬ የተጀመረ አይደለም ያሉት አምባሳደር መለስ፥ “ከቻይና ጋር በነበረን ግንኙነት ሁሉ የኢትዮጵያ መንግስታት አፅንተው የያዙት አቋም ነው” ብለዋል።

አሁንም ኢትዮጵያ ለ“አንድ ቻይና” ፖሊሲ ፅኑ አቋም አላት ያሉም ሲሆን፥ ፖሊሲውን ኢትዮጵያ አባል የሆነችባቸው የተባበሩት መንግስታት እና የአፍሪካ ህብረትም እንደሚያራምዱት ገልጸዋል።

የኢትዮጵያን የሁለትዮሽና የባለብዙ ወገን ግንኙነትን የሚያጠናክር ውጤታማ ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ መቀጠሉንም ነው አምባሳደር መለስ ያነሱት።

የቻይና የመከላከያ ሰራዊት የተመሰረተበትን 95ኛ ዓመት ክብረ በዓል በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የኢፌዴሪ የመከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ የቻይና የመከላከያ ሰራዊት የሀገሩን ሉዓላዊነት፣ ጸጥታና ጥቅም ከማስከበር አልፎ ለዓለማችን ሰላምና መረጋጋት እያደረገ ላለው በጎ ሚና ያላቸውን አድናቆት መግለጻቸው የሚታወስ ነው።

የአሜሪካ አፈ ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲን የቻይናን ዛቻ ወደ ጎን በመተው ወደ ታይዋን መጓዛቸውን ተከትሎ በቻይና-ታይዋን ጉዳይ ከፍተኛ ውጥረት መንገሱ ይታወቃል።

ቻይና አሜሪካ በዴሞክራሲ ሽፋን ሉአላዊነቴን ተዳፍራለች ያለች ሲሆን፤ ቻይናን የሚዳፈሩ ሁሉ ይቀጣሉ ማለቷ አይዘነጋም።

የቻይና ጦር የፔሎሲን ጉብኝት ተከትሎ የአጸፋ እርጃ ለመውሰድ በተጠንቀቅ ላይ መሆኑን የገለፀ ሲሆን፤ በትናንትናው እለትም 27 የቻይና የጦር ጄቶች የታይዋንን የአየር ክልል ጥሰው ገብተዋል።

ሩሲያ፣ ሰሜን ከሮያ እና ኤርትራ ቻይናን በመደገፍ አቋማቸውን ያንፀባረቁ ሲሆን፤ ኤርትራ የፔሎሲን ጉብኝት ህግን የጣሰ ነው ስትልም ተችታለች።

News today, Politics

ሙሴቪኒ ከአሜሪካዋ ዲፕሎማት ጉብኝት አስቀድመው ‘ማንም ትዕዛዝ አይሰጠንም’ አሉ

የኡጋንዳ ፕሬዝዳንት ሙሴቪኒ
የምስሉ መግለጫ,ዬዌሪ ሙሴቪኒ

ከ 6 ሰአት በፊት

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአሜሪካ አምባሳደር የኡጋንዳ ጉብኝትን ተከትሎ ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ማንም ትዕዛዝ አይሰጠንም ሲሉ ለቢቢሲ ተናገሩ።

አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ-ግሪንፊልድ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝታቸው ዛሬ ሐሙስ ሐምሌ 28/2014 ዓ.ም. ከኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ ጋር ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

አምባሳደሯ ከዋሽንግተን ዲሲ መመሪያዎችን ይዘው ይመጡ እንደሆነ የተጠየቁት ሙሴቬኒ፤ “ማንም ትዕዛዝ አይሰጠንም” ሲሉ መልሰዋል።

ሙሴቬኒ አገራቸው ኡጋንዳ ከምዕራባውያን የሚላከውን እርዳታ በመልካም ጎኑ እንደምትመለከተው ጠቅሰው፤ አገራቸው ያለ እርዳታ መኖር እንደምትችልም ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንቱ ኡጋንዳ በሩሲያ እና በዩክሬን ጦርነት ዙሪያ የያዘችውን አቋም ለማስቀየር የተደረገ ጥረት እንደሌለ ገልጸዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ሩሲያ በዩክሬን ላይ የከፈተችውን ወረራ እንድታቆም ያወጣውን ምክር ሃሳብ በድምጸ ታዕቅቦ ካለፉት 16 የአፍሪካ አገራት መካከል ኡጋንዳ አንዷ መሆኗ ይታወቃል።

አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ-ግሪን ፊልድ ወደ ካምፓል የሚያመሩት የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኡጋንዳ ጉብኝት ካደረጉ ከቀናት በኋላ ነው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ በቅርቡ ኡጋንዳ እና ኢትዮጵያን ጨምሮ በአራት የአፍሪካ አገራት ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል።

ሙሴቬኒ፤ “ጥሩ ጓደኛ” ሲሉ የገለጿቸው አምባሳደር ቶማስ-ግሪንፊልድን ሁሌም ወደ ኡጋንዳ እንዲመጡ በራችን ከፍት ነው ካሉ በኋላ፤ አስተዳደራቸው ለምዕራባውያን ጫና እንደማይበረከክ ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ በሩሲያ እና በዩክሬን ጦርነት ዙሪያ አቋማቸው ምን እንደሆነ ሲጠየቁ፤ ጦርነቱን ከ1962ቱ የኩባ ሚሳኤል ቀውስ ጋር አነጻጸረውታል።

ሙሴቪኒ ዛሬ ላይ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) በሩሲያ ዙሪያ መገኘትን ሶቪየት ሕብረት አሜሪካ አፍንጫ ስር ኩባ ውስጥ ሚሳኤል ከመትከሏ ጋር አነጻጽረውታል።

የኩባ ሚሳኤል ቀውስ ተብሎ የሚታወቀው ክስተት የወቅቱ የዓለማችን ኃያላንን ወደ ኒውክሌር ጦርነት እንዲገቡ ከጫፍ አድርሶ ነበር።

በወቅቱ ሶቪየት ሕብርት የኩባን ደኅንነት ከአሜሪካ ጥቃት ለመጠበቅ በሚል፣ ኩባ ውስጥ የአሜሪካ ከተሞችን መምታት በሚያሰችሉ ስፍራዎች ላይ የኒውክሌር አረሮችን ማስወንጨፍ የሚችሉ ሚሳኤሎችን ተክላ ነበር።

ሙሴቬኒ ይህ ክስተት የአሜሪካንን የደኅንነት ስጋት ውስጥ ከትቶ እንደነበረ ተናግረው፤ በወቅቱ አገራቸው ለአሜሪካ ድጋፏን መሽጠቷን አስታውሰዋል።

ሙሴቬኒ ዛሬም ተመሳሳይ መርኅ ማረመድ አለብን ብለዋል።

ሙሴቬኒ ኔቶ በሩሲያ ዙሪያ መክተሙ፤ የሩሲያን እርምጃ እንዲገነዘቡ ያደርግዎታል ወይ ተብለው ሲጠይቁ፤ “በትክክል” ሲሉ መልሰዋል።

“ታሪክ የምትሉትን፤ እኔ ወቅታዊ ጉዳይ እለዋለሁ” ብለዋል ሙሴቬኒ።

News today, Politics

እኛ አንተነኩስም፤ ነገርግን ራሳችንን እንከላከላለን”- የታይዋን ፕሬዝደንት

በፔሎሲ ጉብኝት የተቆጣችው ቻይና በታይዋን ዙሪያ ወታደራዊ ልምምድ እያደረገች ነው

ከዓለም ዙሪያ

 2022/8/4 15:12 GMT

የታይዋን ፕሬዝደንት ጻይ ኢንግ ዌን

በታይዋን ዙረያ ወታደራዊ ልምምድ እያደረገች ያለችው ቻይና ወደ ታይዋን ሚሳየል አስወንጭፋለች

የታይዋን ፕሬዝደንት ጻይ ኢንግ ዌን ሀገራቸው ማንንም እንደማትተነኩስና እና ነገርግን ራሷን እንደምትከላከል ተናግረዋል፡፡

የቻይና ወታደራዊ እንቅስቃሴ ለታይዋን ብቻ ሳይሆን ለመላው አለም ኃላፊነት የጎደለው ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

 “የሀገራችንን ሰላም እና መረጋጋት ለመጠበቅ እራሳችንን እንሰጣለን” ያሉት ፕሬዝዳንቷ አለም አቀፉ ማህበረሰብ ፍትሃዊ ያልሆኑ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን ለማስቆም እንዲተባበር ጠይቃለች።

እናም የታይዋን ፕሬዝዳንት በመቀጠል “የፀጥታው ሁኔታ እንዳይባባስ ከአጋሮቻችን ጋር እየተገናኘን ነው” ብለዋል።

ቻይና በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ በእኛ ላይ የምታደርገውን የመረጃ ጦርነት አጠናክራ ስለምትቀጥል የታይዋን ህዝብ በንቃት እንዲጠብቅ አሳስባለች።

 ፕሬዝደንት ጻይ ኢንግ ዌን “የፀጥታው ሁኔታ እንዳይባባስ ከአጋሮቻችን እየተነጋገርን ነው” ብለዋል፡፡

በአሜሪካዋ አፈጉባኤ ጉብኝት የታይዋን ጉብኝት የተበሳጨችው ቻይና በዛሬ እለት ጠዋት የባለስቲክ ሚሳየሎችን ወደ ታይዋን አስወንጭፋለች፡፡ የጃፓን መከላከያ ሚኒስትር አምስት የሚሆኑ የቻይና ሚሳየሎች በታይዋን ደሴት ላይ አልፈው በጃፓን በየኢኮኖሚ ዞን ማረፋቸውን ጠቅሷል፡፡

ሚኒስቴር በጃፓን ልዩ በሆነው የኢኮኖሚ ቀጠና ውስጥ የወደቁ ከሚመስሉት አምስት የቻይና ባሊስቲክ ሚሳኤሎች አራቱ “በዋናዋ የታይዋን ደሴት ላይ” መብረራቸው ጠቁሟል።

በፔሎሲ ጉብኝት የተቆጣችው ቻይና በታይዋን ዙሪያ ወታደራዊ ልምምድ እያደረገች ነው፡፡

አለምአቀፉ ማህበረሰብ የቻይናን ድርጊት እንዲያስቆም እየጠየቀች ያለችው ታይዋን፣ ቻይና ገፍታ ጦርነት የምትከፍት ከሆነ ግን ራሷን ለመከላከል እንደምትገደድ ገልጻለች፡፡

News today, Politics

ሩሲያ ባለፉት ቀናት ውስጥ 500 የዩክሬን ወታደሮችን ገደልኩ አለች

ከምዕራባዊያን ለዩክሬን የተለገሱ በርካታ ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎችን ማውደሟንም ሩሲያ አክላለች

ሩሲያ በሞስኮ የኖርቄይ ዲፕሎማትንም ማባረሯን አስታውቃለች

ሩሲያ ባለፉት ቀናት ውስጥ 500 የዩክሬን ወታደሮችን ገደልኩ አለች፡፡

የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ስድስት ወራት 162ኛ ቀኑ ላይ የሚገኝ ሲሆን እስካሁን ጦርነቱ ከሁለቱ ሀገራት ባለፈ ዓለም አቀፋዊ ሆኗል።

የሩሲያ መከላከያ ሚንስቴር ባወጣው መግለጫ ባለፉት ቀናት በተካሄደው ጦርነት 500 የዩክሬን ወታደሮች መግደሉን አስታውቋል።ሚኒስቴሩ አክሎም ከአሜሪካ እና ሌሎች ምዕራባውያን ሀገራት ለዩክሬን የተለገሱ የጦር መሳሪያዎችን አውድሜያለሁም ብሏል።

የሩሲያ ጦር በዶንቴስክ እና ካርኪቭ አካባቢዎች ባካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ በርካታ የዩክሬን እና ቅጥረኛ ወታደሮች ይዞታዎችን እና የጦር ማዘዣዎችን ማውደሙንም አስታውቋል።

እንዲሁም ከረጅም እና አጭር ርቀት ሚሳኤል መሳሪያዎች፣ የጦር ተሽከርካሪዎች፣ መጋዝኖችን እና ሌሎች ወታደራዊ ስፍራዎችን የሩሲያ አየር ሀይል መምታቱን አርቲ ዘግቧል።

የሩሲያ ጦር 390 የዩክሬን የጦር አውሮፕላኖች ፣ 1506 ድሮኖች፣ 354 ጸረ አውሮፕላን ሚሲኤሎች እና ከ 11 ሺህ በላይ የጦር ታንኮች፣ ልዩ የጦር ተሽከርካሪዎች፣ ጸረ ሮኬት መሳሪያዎች እና ሌሎች የጦር መሳሪያዎች ማውደሙን ዘገባው አክሏል።

የዩክሬን መንግስት በሩሲያ መከላከያ ሚንስቴር መግለጫ ዙሪያ እስካሁን ምላሽ አልሰጠም።

በተያያዘ ዜና ሩሲያ ከሰሞኑ አንድ የኖርዌይ ዲፕሎማት በአንድ መዝናኛ ስፍራ ገብታ በተናገረችው ጸረ ሩሲያ ንግግር ምክንያት ሞስኮን ለቃ እንድትወጣ መወሰኗን አስታውቃለች።

News today, Politics

ኤርትራ፤ የፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት ዓለም አቀፍ ሕግ “የጣሰ ነው” አለች

ኤርትራ፤ የፔሎሲን ጉብኝት ያወገዘች ብቸኛ የአፍሪካ ሀገር ናት

የኤርትራ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ (ፎቶ ከፋይል)

አስመራ፤ የአፈጉባኤዋ ጉዞ የአንድ ቻይና ፖሊሲን የሚቃነረን፤ የቻይናንም አንድነት የሚጻረረ ነው ብላች

ኤርትራ፤ የአሜሪካ ምክር ቤት አፈጉባዔ የታይዋን ጉብኝት ዓለም አቀፍ ህግን የጣሰ መሆኑን ገለጸች።

የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፔሎሲን የታይዋን ጉብኝት አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል። መስሪያ ቤቱ ባወጣው መግለጫ የአሜሪካ ፖሊሲ የማይረባና በግልጽ የወጣ መሆኑን ጠቅሷል።

ዋሸንግተን ቻይናን ለመቆጣጠርና ለመያዝ ጥረት እያደረገች መሆኑን የገለጸችው አስመራ ይህ ድርጊት አጸያፊ ነው ብላለች።

ኤርትራ የፔሎሲ ጉብኝት ወደ ግጭት የሚያመራና የሚያባብስ እንደሆነም ነው የገለጸችው።

የአሜሪካ ምክር ቤት አፈጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት ግደለሽነትን የሚያመለክት እንደሆነ ነው የገለጸችው።

አሜሪካ ባለፉት ዓመታት በእስያ የማሳመን ስራ ስትሰራ የቆየችው ይህንን ታይዋንን ጉዳይ ለማሳካት እንደሆነም ነው ኤርትራ ያስታወቀችው።

የአሜሪካ አፈጉባዔ ወደ ታይዋን ያደረጉት ጉዞ ከዓለም አቀፍ ህግና መርህ ያፈነገጠ ነውም ብሏል የኤርትራ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት።

የአፈጉባኤዋ ጉዞ ድርጊቱ ፤የቻይና መንግስት ሉዓላዊነት ደንቦችን እና ድንጋጌዎች እንዲሁም “የአንድ-ቻይና” ፖሊሲ የሚጻረር እና የቻይናውያን ውህደት ሂደትን የሚያደናቅፍ ነውም ብሏል የኤርትራ መንግስት።

ኤርትራ፤ የፔሎሲን የታይዋን ጉብኝት ያወገዘች ብቸኛ የአፍሪካ ሀገር ናት።

ሩሲያ እና ሰሜን ኮሪያ ጉብኝቱን ማውገዛቸው ይታወሳል።

News today, Politics

ሶማሊያ የአልሸባብ የቀድሞ ሁለተኛ ቁልፍ ሰውን በሚኒስትርነት ሾመች


የሶማሊያ መንግስት የአልሸባብ መስራች ሙክታር ሮቦ አሊን (አቡ መንሱር) ሚኒስትር አደርጎ ሾሟል
አቡ መንሱር የአልሸባብ የሽበር ቡድን መስራችና በምክትልነት የመራ ሰው ነበረ

አዲሱ የሶማሊያ መንግስት በርካቶችን ያስገረመ አዲስ ከቢኔ ከሰሞኑ ይፋ አድርጓል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ሀምዛ አብዲ ቤሪ የተመራው አዲሱ የሶማሊያ መንግሰት የአልሸባብ የሽብር ቡድን ሁለተኛ ቁልፍ ሰውን በሚኒስትርነት በመሾሙ ነው በርካቶችን ያስገረመው።

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ “ከአልሻባብ ጋር እንደራደራለን” አሉ
በትናትናው እለት በሚቃዲሾ በተካሄደው ስነ ስርዓት ላይ የሶማሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር ልምድ እና ብቃት አላቸው ያላቸውን ሚኒስትሮቻቸውን አስተዋውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት ፤ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ “ሶማሊያውያን ከአለም ጋር ስምምነት ላይ ናቸው” በሚለው መርህ ላይ ለመስራት ቃል ገብተዋል።

ከዚህ ሁሉ ግን በርከቶችን ያስገረመው ጉዳይ በቅጽል ስሙ “አቡ መንሱር” በመባል የሚጠራው የአልሸባብ የሽብር ቡድን መስራች እና የቡድኑ ሁለተኛ ቁልፍ ሰው ሙክታር ሮቦ አሊ ሹመት ነበር።

ሙክታር ሮቦ አሊ (አቡ መንሱር) በአዲሱ የሶማሊየ መንግስት ካቢኔ ውስጥ የኃይማኖት ጉዳዮች እና የኢንዶውምንት ሚኒስትር ተደርገው መሾማቸውም ተነግሯል።

ሙክታር ሮቦ አሊ አልሸባብን ለቆ እስከወጣበት የፈረንጆቹ 2011 ድረስ የሽበር ቡድኑ ምክትል መሪ የነበረ ሲሆን፤ የሽብር ቡድኑ ይፋዊ ቃል አቀባይም ነበር።

በፈነረንጆቹ 2017 ላይ እጁን ለሶማሊያ መንግስት የሰጠው አቡ መንሱር፤ በወቅቱ በሰጠው መግለጫ ከቡድኑ ጋር የተለያየው ከ5 ዓመት በፊት እንደነበረ ገልጾ ነበር።

ሶስት የአልሸባብ ቡድን አመራሮችን መግደሉን የኢትዮጵያ መከላከያ አስታወቀ
በፈረንጆቹ 2018 ላይ ደግሞ የደቡብ ምእራብ ሶማሊያን በፕሬዝዳንትነት ለመምራት ተወዳድሮ እንደነበረም ይታወሳል።

አዲሱ ሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀምዛ አብዲ ቤሪ በቴሌቭዥን በሰጡት አስተያየት፤ አልሸባብን ከመልቀቁ በፊት ለጠቆመው ሰው 5 ሚሊየን ዶላር ሽልማት ተዘጋጅቶበት የነበረው ሰው አሁን ላይ የሶማሊያ ኃይማኖታዊ ጉዳይ ሚኒስትር ሆኗል ብለዋል።

News today, Politics

ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ያለውን ችግር ለመፍታት ዝግጁ መሆኗን ገለጸች

ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ያለውን ችግር ለመፍታት ዝግጁ መሆኗን ገለጸች

ሩሲያ፤ ቻይናን ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ የምትወስዳቸውን “ሚዛናዊ” እርምጃዎች እንደምትደግፍም ገልጻለች

ሩሲያ፤ ቻይናን ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ የምትወስዳቸውን “ሚዛናዊ” እርምጃዎች እንደምትደግፍም ገልጻለች።

ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ያለውን ጦርነት በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት ዝግጁ መሆኗን አስታወቀች።

የሩሲያ ቤተ መንግስት (ክሬምሊን) ቃል አቀባይ፤ ዲሚትሪ ፒስኮቭ ሀገራቸው ከዩክሬን ጋር ያለውን ችግር በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት አሁንም ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል።

ፒስኮቭ ከሰሞኑ በእስያ ፓስፊክ ባለው ውጥረት ዙሪያም አስተያየት መስጠታቸውን ሩሲያ ቱዴይ ዘጎቧል። ቃል አቀባዩ የእስያ ፓስፊክ ውጥረት ቀላል ግምት ሊሰጠው አይገባም ሲሉም ነው አስተያየት የሰጡት።

የአሜሪካ ምክርቤት አፈጉባዔ በታይዋን ያደረጉት ጉብኝት እንደቀላል መታየት እንደሌለበት ያነሱት ፒስኮቭ ጉዳዩ ከባድ እንደሆነ ገልጸዋል።

የፔሎሲን የቻይና ጉብኝት ተከትሎ የሶስተኛው የዓለም ጦርነት ይነሳል የሚል ፍርሃትን እንዳለ የገለጹት ቃል አቀባዩ፤ ይህ ግን እንደማይከሰት ተናግረዋል።

ፒስኮቭ፤ ሀገራቸው ቻይናን ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ የምትወስዳቸውን “ሚዛናዊ” እርምጃዎች እንደምትደግፍ ተናግረዋል።

ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ያለባትን ችግር በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ዝግጁ እንደሆነችም ማረጋገጫ ሰጥተዋል።

ሩሲያ እና ዩክሬን የጀመሩት ጦርነት አራት ወራት አልፈውታል።

ምዕራባውያን ሩሲያ፤ ዩክሬይንን፤ ቻይና ደግሞ ታይዋንን ትወራለች የሚል ፍርሃት አላቸው።

News today, Politics

አይመን አል ዘዋሂሪን ማን ሊተካ ይችላል?

አሜሪካ የአልቃይዳ መሪ አይመን አል ዘዋሂሪ መግደሏን አስታውቃለች

 2022/8/2 7:43 GMT

አይመን አልዘዋሪን ሊተካ ይችላል የተባለው ግብጻዊ ሰይፍ አል ማስሪ

ትውልደ ግብፃዊው አይመን አል ዘዋሂሪ፤ ኦሳማ ቢላደንን በመተካት አል ቃይዳን ሲመራ ነበር

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የአልቃይዳ መሪ አይማን አል ዘዋሂሪን እንደተገደለ መናገራቸው ይታወሳል።

 የሽብር ቡድኑ መሪ፤ የአሜሪካ የስለላ ተቋም (ሲአይ ኤ) በፈጸመው የድሮን ተልዕኮ መገደሉን ጆ ባይደን አረጋግጠዋል።

የቀድሞውን መሪ ኦሳማ ቢላደንን በመተካት አል ቃይዳን ሲመራ የነበረው ትውልደ ግብፃዊው አይመን ዘዋሂሪን የተገደለው በአፍጋኒስታን ካቡል መሆኑንም ጆ ባይደን ተናግረዋል።

አይማን አል ዘዋሂሪን የተገደለው የሽብር ቡድኑን ቁልፍ መሪዎችን ኢላማ በማድረግ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት እንደሆነም ተገልጿል።

የአል ዘዋሂሪን መገደልን ተከትሎ በቀጣይ የሽብር ቡድኑን ማን ይችላል በሚል የተለያዩ መላምቶች በመነሳት ላይ ናቸው።

አሁን ላይ እየወጡ ባሉ መረጃዎች ሌላኛው ግብጻዊ ሰይፍ አል ማስሪ ሊተካ እንደሚችል ግምቶች በመውጣት ላይ ናቸው።

ይህ ግብጻዊ በኢራን በረሀማ ስፍራዎች ውስጥ ተሸሽጎ እንዳለ የሚገመት ሲሆን ሟቹ የአልቃይዳ መሪ አይመን አልዘዋሪን ሊተካ ይችላል ተብሏል።

ሰይፍ አል ማስሪ ላለፉት 30 ዓመታት በአልቃይዳ የሽብር ቡድን ውስጥ የተለያዩ ተልዕኮዎችን ሲመራ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን የሽብር ቡድኑን ከዚህ በፊት ኦሳማ ቦንላደን በነበሩበት ጊዜ ወደ ነበረበት ቁመና ሊመልሰው እንደሚችል ተሰግቷል።

አልማስሪ በፈረንጆቹ 1998 ናይሮቢ በሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ ላይ የተፈጸመውን እና ለ224 ሰዎች ህይወት ማለፍ ምክንያት የሆነውን የሽብር ድርጊት በመምራት ይፈለጋል።

አሜሪካ ይሄን የሽብር ቡድን መሪ ለያዘ ፣ለገደለ ወይም ለጠቆመ ግለሰብ 7 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር እንደምትከፍል ይፋ አድርጋለች።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት፤ አል ቃይዳ መሪ መገደሉ፤ የቱንም ያህል ጊዜ ቢወስድም በመስከረም 11 ጥቃት የተጎዱት ዜጎች ፍትህ ማግኘታቸውን ያመለክታል ብለዋል።

ባይደን፤ የቡድኑ መሪ አይማን አል ዘዋሪ እንዲደመሰስ ላደረጉ የሀገራቸው የጸጥታ ኃይሎች ምስጋና አቅርበዋል።

ባይደን በካቡል በተደረገው ጥቃት ንጹኃን ኢላማ እንዳልተደረጉ ቢገልጹም ታሊባን ግን አጣጥሎታል።

በአፍጋኒስታን የተደረገውንና የአል ቃይዳ መሪ የተገደለበትን ጥቃት ታሊባን አውግዞታል።

የወቅቱ የአፍጋኒስታን ገዥ ታሊባን፤ አሜሪካ ጥቃት ያደረሰችው በመኖሪያ ቤት አካባቢ ነው ብሏል።

News today, Politics

አሜሪካ የአል ቃኢዳን መሪ ካቡል ውስጥ ገደለች

የኦሳማ ቢን ላደንን ሞት ተከትሎ አይማን አል-ዛዋሂሪን አል-ቃይዳን ሲመራ ቆይቷል

2 ነሐሴ 2022, 08:12 EAT

አሜሪካ የአል ቃኢዳውን መሪ አይማን አል-ዛዋሂሪን በአፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል ውስጥ በፈጸመችው የድሮን ጥቃት መግደሏን ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስታወቁ።

የአሜሪካ የደኅንነት መሥሪያ ቤት ሲአይኤ ባለፈው ዕሁድ ካቡል ውስጥ ባካሄደው የፀረ-ሽብር ዘመቻ ላይ ነው ዛዋሂሪን መግደል የቻለው ተብሏል።

ፕሬዝዳንት ባይደን አይማን አል-ዛዋሂሪ “በአሜሪካ ዜጎች ላይ ግድያ እና ጥቃትን የቀረጸ ሰው ነው’’ ብለዋል።

አክለውም “አሁን ፍትህ ተሰጥቷል ፤ ይህ የአሸባሪ ቡድን መሪ ከዚህ በኋላ በሕይወት የለም” ሲሉም ግድያውን ተከትሎ በሰጡት መግለጫ ላይ ተናግረዋል።

ዛዋሃሪ ከቀድሞው የአል-ቃኢዳ መሪ ቢን ላደን ጋር በመሆን ከ20 ዓመታት በፊት የተፈጸመውን የ9/11 ጥቃትን የመራ ሲሆን፣ አሜሪካ ለረጅም ዓመታት ስታፈላልገው የቆየችው የሽብር ቡድኑ መሪ ነው።

አይማን አል-ዛዋሂሪ የኦሳማ ቢን-ላደን ሕልፈትን ተከትሎም አል-ቃኢዳን ሲመራ ቆይቷል።

የአሜሪካ ባለሥልጣናት እንዳሉት ዛዋሂሪ በአንድ በጥብቅ በሚጠበቅ ቤት በረንዳ ላይ ተቀምጦ ባለበት ወቅት ነው የአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላን ሁለት ሚሳኤሎችን ተኩሶ የገደለው።

እንዲሁም በቤቱ ውስጥ የነበሩ ሌሎች የቤተሰብ አባላት ምንም ጉዳት እንዳልደረሰባቸው እና በጥቃቱ ዛዋሂሪ ብቻ ተነጥሎ መገደሉንም አክለው ተናግረዋል።

ባይደን በ71 ዓመቱ የአል ቃኢዳ መሪ ላይ እርምጃውን ለመውሰድ ለወራት ዕቅድ ከወጣ በኋላ “የተመጠነ እና ትክክለኛውን ኢላማ የመታ ጥቃት” እንዲሰነዘር የመጨረሻውን የይለፍ ፍቃድ መስጠታቸውን ተናግረዋል።

የሽብር ቡድን መሪው ግድያም እ.ኤ.አ. በ2001 በተፈጸመው ጥቃት 3,000 የሚጠጉ ወዳጅ፣ ቤተሰቦቻቸውን ላጡ አሜሪካዊያን ለሐዘናቸው መልስ የሚሆን የመጨረሻውን መደምደሚያ የሚሰጥ እርምጃ ነውም ሲሉ አክለዋል።

“የቱንም ያህል ጊዜ ይፍጅ፣ የትም ይደበቁ፣ ለሕዝባችን ስጋት የሆነ አካል ካለ አሜሪካ ታገኛቸዋለች፣ ቀጥሎም ታስወግዳቸዋለች” ያሉት ባይደን አክለውም “አገራችንን እና ሕዝባችንን ከመከላከል ወደ ኋላ አንልም” ሲሉም አክለዋል።

ባይደን ዛዋሂሪ እ.ኤ.አ በጥቅምት 2000 በኤደን የአሜሪካ የባሕር ኃይል ግዙፍ የጦር መርከብ ላይ በተሰነዘረ የአጥፍቶ መጥፋት ጥቃት 17 የአሜሪካ መርከበኞችን የገደለውን ጥቃት መርቷል ሲሉ ተናግረዋል።

እንዲሁም ለ223 ሰዎች ሕልፈት ምክንያት የሆኑት በ1998 በኬንያ እና በታንዛኒያ በአሜሪካ ኤምባሲዎች ላይ የተፈፀሙትን ጥቃቶችንም በማስተባበር ዛዋሂሪ ኃላፊነት እንዳለበትም አክለዋል።

ፕሬዝዳንት ባይደን አፍጋኒስታን ከእንግዲህ የአሸባሪዎች መሸሸጊያ አትሆንም ሲሉም አጥብቀው ተናግረዋል።

የታሊባን ቃል አቀባይ የአሜሪካን ዘመቻ ዓለም አቀፍ መርሆችን የጣሰ ነው ሲሉ ገልፀውታል።

አክለውም “እንዲህ ያሉ ድርጊቶች ላለፉት 20 ዓመታት ያልተሳኩ ሙከራዎችን መደጋገም ናቸው። ድርጊቱም የአሜሪካን፣ የአፍጋኒስታንን ብሎም የቀጠናውን ጥቅም ጥቅም የሚፃረር ነው’’ ብለዋል።

የአሜሪካ ባለሥልጣናት በበኩላቸው በአል ዛዋሂሪ ላይ የተካሄደው ዘመቻ ሕጋዊ መሰረት ያለው ነው ብለዋል።

News today, Politics

የቻይና ጦር የአፀፋ እርምጃ ለመውሰድ በከፍተኛ ተጠንቀቅ ላይ መሆኑን ገለፀ

P.R.C


የአሜሪካ አፈ ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ ጉብኝት የቻይናን ዛቻ ወደጎን ትተው የታይዋን ጉብኝታቸውን ጀምረዋል

የቻይና መከላከያ ሚኒስቴር የአፀፋ ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ በከፍተኛ ተጠንቀቅ ላይ መሆኑን አስታወቀ።

የቻይና መከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ወ ዩ ኪያን፤ የቻይና ጦር የሀገሪቱን ሉአላዊነት እና የግዛት አንድነት ለማስጠበቅ በከፍተኛ ዝግጅት ላይ ነው ብለዋል።

“የአሜሪካ ፖለቲከኞች የ 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ሕዝብ ጠላት መሆን አምሯቸዋል”- ቻይና
ቃል አቀባዩ የአሜሪካ አፈ ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ የቻይና አካል በሆነችው ታይዋን ክልል ለጉብኝት መግባታቸውን ተከትሎ የቻይና ጦር በተመረጡ ኢላማዎች ላይ ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ በተጠንቀቅ ላይ መሆኑን አስታውቀዋል።

የአሜሪካ አፈ ጉባኤ ናንሲ ሌሎሲ ታይዋንን ጨምሮ አምስት የእስያ ሀገራትን ጉብኝት መጀመራቸውን ተከትሎ ዓለም አይኑ ታይዋን ላይ አርፏል።

የአሜሪካዋ አፈጉባዔ የጉብኝታቸው አካል ወደሆነችው ታይዋን በዛሬው እለት ገብተዋል።

ቻይና በአሜሪካ ፖለቲካ ሶስተኛው የስልጣን ባለቤት እየሆኑት ናንሲ ፔሎሲ ታይዋንን ከጎበኙ እርምጃ እወስዳለሁ ማለቷን ተከትሎ በሩቅ ምስራቅ ውጥረት ነግሷል።

ታይዋን ለሶስት ቀናት ከፍተኛ የውጊያ ጥንቃቄ አወጀች
አፈ ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ ታይዋን መድረሳቸውን ተከትሎም የቻይና ሱ35 ጄቶች የታይዋንን የአየር ክልል ጥሰው መግባታቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል።

ቻይና፤የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ ታይዋንን የሚጎበኙ ከሆነ ጦሯ “ዝም ብሎ እንደማይቀመጥ”ቻይና ማስጠንቀቂያ አስተላልፋ እንደነበረ ይታወሳል።

News today, Politics

ፑቲን የኒዩክለር ጦርነት በየትኛውም መንገድ ቢሆን መቅረት እንዳለበት

ፑቲን የኒዩክለር ጦርነት በየትኛውም መንገድ ቢሆን መቅረት እንዳለበት አሳሰቡ
ፑቲን ሁሉም ሀገራት ኒውክለርን ለሰላማዊ ዓላማ እንዲጠቀሙ ሊፈቀድላቸው እንደሚገባም ጥያቄ አቅርበዋል

የኒውዩክለር ጦርነትን በማንኛውም ዋጋ ቢሆን ማስወገድ እንደሚገባ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አሳሰቡ።

ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የኒውክለር ጦር መሳሪያ ስርጭትን መከላከል ላይ ባተኮረው ጉባዔ ላይንግግር ማድረጋቸውን የሀገራቸው መገናኛ ብዙኃን አርቲ ዘግቧል።

ፕሬዝደንት ፑቲን አሜሪካ የሩሲያ “ዋነኛ ስጋት” ነች ሲሉ ፈረጁ
በቀጣይ ኒውክለርን በመጠቀም የሚረግን ጦርነት በየትኛውም መልኩ ማስቀረት እንደሚገባ ተናግረዋል።

የኒውክለር ጦርነት አሸናፊ የሌለውና ዓለም በፍጹም ሊሄድበት የማይገባ እንደሆነም ነው ቭላድሚር ፑቲን ያሳሰቡት።

ፑቲን ሀገራቸው ከአሜሪካ ለገባችውን ኒውክለርን ያለመታጠቅ ስምምነት እንደምትታመንም የገለጹት።

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን፤ የኒውክለር ጦር መሳሪያ ስርጭትን መከላከልን የሚተገብሩ ሁሉም ሀገራት ኒውክለርን ለሰላማዊ ዓላማ እንዲጠቀሙ ሊፈቀድላቸው እንደሚገባም ጥያቄ አቅርበዋል።

የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት እንዴት ሊጠናቀቅ ይችላል?
የኒውክለር ጦር መሳሪያ ስርጭትን መከላከል ውል ዓላማዎች ስርጭቱን መግታት፣ አለመታጠቅና ለሰላማዊ ኃይል መጠቀም የሚሉትን ያጠቃልላል።

ይህንን ስምምነት 192 ሀገራት የተቀላቀሉት ሲሆን ኒውክለር የታጠቁትም በዚህ ስምምነት ውስጥ ተሳታፊ ናቸው።

ፕሬዝደንት ቫላድሚር ፑቲን አሜሪካን ዋነኛ የሩሲያ ጠላት እንደሆነች ትናንት የሀገራቸው የባሕር ኃይል ቀን ሲከበር ይፋ አድርገዋል።

News today, Politics

ፕሬዝደንት ፑቲን አሜሪካ የሩሲያ “ዋነኛ ስጋት” ነች ሲሉ ፈረጁ!!

ፕሬዝደንት ፑቲን አሜሪካ የሩሲያ “ዋነኛ ስጋት” ነች ሲሉ ፈረጁ!!

ፕሬዝደንት ፑቲን ይህን ያሉት በሩሲያ በሴንት ፒተርስበርግ በተከበረው እና ታሪካዊ ነው በተባለው የባህር ቀን ላይ ነው፡፡ ባለፈው ቅዳሜ አዲስ የባህር ኃይል መተዳደሪያ ላይ ፊርማቸውን ያስቀመጡት ፕሬዝደንት ፑቲን አሜሪካ ዋነኛ የሩሲያ ተቀናቃኝ አድርገው አስቀምጠዋል፡፡

በአዲሱ የባህር ኃይል መተዳደሪያ በአርክቲክ እና በጥቁር ባህር ሊኖር የሚችለው የሩሲያ እቅድ መነደፉን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ በታላቁ ቄሳር ፒተር በተመሰረተችው የቀድሞዋ የንጉሠ ነገሥት ግዛት ሴንት ፒተርስበርግ በተከበረው የሩሲያ የባህር ኃይል ቀን ላይ ንግግር ያደረጉት ፑቲን ሩሲያን ታላቅ የባህር ሃይል እንዲኖራት የያደረጉትን ፒተርን አመስግነዋል፡፡

ፑቲን የባህር ሃይሉን ከጎበኙ በኋላ አጭር ንግግር ያደረጉት ሩሲያ ልዩ የሆነችው የዚርኮን ሃይፐርሶኒክ ክሩዝ ሚሳኤሎች በማሳየት ሩሲያ ወታደራዊ አቅም እንዳላት አስጠንቅቀዋል። ፕሬዝዳንቱ ንግግር ከማድረጋቸው ቀደም ብሎ የሩሲያን የባህር ኃይል ሰፊ ስትራቴጂካዊ አላማዎችን የያዘ ባለ55 ገጽ ሪፎርም ፈርመዋል፡፡

ከሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት በኋላ በሩሲያ እና በምእራባውያን መካከል ያለው ፍጥጫ አይሏል፡፡ሩሲያ የኔቶ ጦር ወደ ቀድሞ የሶቬት ሀገራት መስፋፋት ለደህንነቷ እንደማያሰጋት በመግለጽ ነበር በዩክሬን ላይ “ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ” ያወጀችው። ከዚህ በተጨማሪም ዩክሬንን ትጥቅ ማስፈታት እና የናዚን አስተሳሰብ ማጥፋት የዘመቻው አላማ መሆኑን ሩሲያ መግለጿ ይታወሳል።

በሩሲያ ርምጃ የተቆጡት ምእራባውያን ሩሲያን ያዳክማል ያሉትን ሁሉ ማእቀብ በሩሲያ ላይ ጥለዋል። የዶምባስ ግዛትን ነጻ የማውጣት የወሰነቸው ሩሲያ አሁንም በደቡብ እና ምሰራቃዊ ዩክሬን ጦርነት እያካሄደች ትገኛለች፡

News today, Politics

የቻይና ጦር ለጦርነት ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ


ፕሬዝዳንት ባይደንና የቻይና ሺ ጂንፒንግ በታይዋን እና በዩክሬን ሩሲያ ጦርነት ጉዳይ ይወያያሉ

በታይዋን ጉዳይ አለመግባባት ውስጥ ያሉት የአሜሪካ እና ቻይና ፕሬዝዳንቶች ውይይት ሊያደርጉ መሆኑ ተገለጸ።

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና አቻቸው ሺ ጂንፒንግ በታይዋን እና በዩክሬን ሩሲያ ጦርነት ላይ ትኩረት ያደረገ ንግግር እንደሚያደርጉም ነው የተገለጸው፡፡

የአሜሪካዋ አፈ ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ ታይዋንን የሚጎበኙ ከሆነ እርምጃ ልትወስድ እንደምትችል ቻይና አስጠነቀቀች
ሁለቱ መሪዎች ነገ ከአራት ወራት በኋላ በስልክ ንግግር እንደሚደርጉ አንድ ከፍተኛ የዋሸንግተን ባለስልጣን መናገራቸውን አሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

የአሜሪካዋ አፈ ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ ከሰሞኑ ታይዋንን እንደሚጎበኙ መግለጻቸውን ተከትሎ ቤጅንግ ቁጣዋን ገልጻለች፡፡

ከዚህ ባለፈም ቻይና አፈጉባዔዋ ወደ ታይዋን የሚሄዱ ካልሆነ እርምጃ ልትወስድ እንደምትችል አስጠንቅቃ ነበር፡፡

የሁለቱ ሀገራት መሪዎች የስልክ ውይይት ያደርጋሉ የተባለው በዚህ ውጥረት ውስጥም ሆነው እንደሆነ ተገልጿል፡፡

የመሪዎቹን የስልክ ንግግር አስመልክቶ ጥያቄ የቀረበለት የቻይና ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል፡፡

ምንም እንኳን ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና አቻቸው ሺ ጂንፒንግ በታይዋን ጉዳይ ላይ ቅድሚያ ሰጥተው እንደሚወያዩ ቢጠበቅም በአውሮፓ ያለው ወታደራዊ ሁኔታም የውይይታቸው አካል እንደሚሆን ተገምቷል፡፡

ቻይና በታይዋን ጉዳይ ለአሜሪካ ከባድ ማስጠንቀቂያ ሰጠች
መሪዎቹ በዩክሬን ሩሲያ ጦርነት ላይ ትኩረት ያደረገ ንግግር ይኖራቸዋል ተብሎ የተጠበቀ ሲሆን በእስካሁኑ ሂደት ዋሸንግተን ከዩክሬን፤ ቤጅንግ ደግሞ ከሩሲያ ጎን መሆናቸው ይታወሳል፡፡

የአሜሪካ ብሔራዊ የደህንነት ቃል አቀባይ ጆን ኪርቢ፤ ሁለቱ መሪዎች በኢኮኖሚ ውድድር ላይም ይነጋገራሉ ብለዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ባይደን ከቻይናው አቻቸው ጋር ነገ ውይይት የሚያደርጉት ከኮሮና ቫይረስ ካገገሙ በኋላ ነው፡፡

News today, Politics

ኢራን የእስራኤልን የስለላ ኔትወርክ መያዟን አስታወቀች


ኢራን የስለላ ቡድኑ አባላት መረጃ ሲሰበሰቡ እና ጸረ -ኢራን የሆነ ፕሮፖጋንዳ ሲጽፉ ነበር ብላለች

የኢራን የደህንነት ድርጅት እንዳስታወቀው ኢራን ወሳኝ በሆኑ ዘርፎች ላይ መረጃ ለመሰብሰብ ሲንቀሳቀስ የነበረ የእስራኤል የስለላ ኔትዎርክ ይዛለች።

በቴህራን ያለው የአል ዓይን ኒውስ ጋዜጠኛ ያየው የኢራን የደህንነት ድርጅት መግለጫ፣ የእስራኤሉ ሞሳድ አካል የሆነው መረብ ተበጥሷል፤ኪሳራም ደርሶበታል ብሏል።

መግለጫው የስለላ ቡድኑ አባላት ከእስራኤል ጋር የመስራት ታሪክ ካለው የተገንጣይ ቡድን አመራር ከሆኑት መካከል በአንዱ አማካኝነት ከሞሳድ ኃላፊ ጋር መገናኘታቸውን ጠቅሷል።

ከዚህ በተጨማሪም የስለላ ቡድኑ አባት መረጃ ሲሰበስቡ፣ የጦር መሳሪያ ስልጠና ሲወስዱ እንዲሁም ጸረ ኢራን የሆነ የፕሮፖጋንዳ መፈክር ሲጽፉ ነበር ብሏል መግለጫው።

የኢራን የደህንነት ሚኒስቴር የታሰሩት እነማን እንደሆኑ፣የየት ሀገር ዜጎች እንደሆኑ እና የት እንደታሰሩ ግልጽ አላደረገም።

ደህንነቱ ባለፈው ሳምንት ወሳኝ የሆነ ተቋም ላይ ጉዳት ሊያደርሱ የነበሩ የእስራኤል የስለላ መረብ መያዙን ባለፈዉ ቅዳሜ ገልጾ ነበር።

ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ “ይህ የስለላ ኔትወረክ በሰሜን ኢራን በሚገኘው የኩርዲስታን ግዛት በኩል ወደ ኢራን ገብቷል፤ ፍንዳታ ለማድረስ የሚያስችል ዘመናዊ መሳሪያ ታጥቀው የነበሩት የኔትውኩ አባላት በክትትል ተይዘዋል።”

ነገርግን የኩርዱ ኮምላ የተባለው ፖርቲ አባላቱ ከእስራኤሉ ሞሳድ ጋር ግንኙነት አላቸው የሚለውን ክስ አስተባብለዋል

News today, Politics

የሰሜን ኮሪያው መሪ ወታደሮቻቸው የኒውክሌር መከላከያ እንዲኖራቸውም መመሪያ ሰጥተዋል

የሰሜን ኮሪያው መሪ ወታደሮቻቸው የኒውክሌር መከላከያ እንዲኖራቸውም መመሪያ ሰጥተዋል

የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ሀገራቸው ከአሜሪካ ጋር ለሚደረግ ማንኛውም ወታደራዊ ግጭት ዝግጁ መሆኗን በልበሙሉነት ተናገሩ፡፡

ሮይተርስ ዮንሃፕ የዜና አገልግሎትን ጠቅሶ እንደዘገበው ፤ ኪም የደቡብ ኮሪያው ፕሬዝዳንት ዮን ሶክዬኦል እና ሰራዊታቸው “አደገኛ” ሙከራዎችን ካደረጉ የመጥፋት አደጋ ሊደርስባቸው እንደሚችልም አስጠንቅቋል።

የሰሜን ኮሪያው መሪ ወታደሮቻቸው የኒውክሌር መከላከያ እንዲኖራቸውም መመሪያ ሰጥተዋል።

ሰሜን ኮሪያ ሩሲያ ቀደም ሲል በተባበሩት መንግስታት ያቀረበቸውንና መጋቢት በነበረው የተመድ  ጸጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ውድቅ የተደረገውን የ“አሜሪካ በዩክሬን ውስጥ ባዮሎጂካል የጦር መሳሪያ ትሰራለች” ክስም አቅርባለች፡፡

የሞስኮ አጋር የሆነችው ፒዮንግያንግ፤ ዋሽንግተንን “የሰው ልጅን ለጥፋት የሚወረውር የባዮ ሽብርተኝነት መጥፎ ስፖንሰር” እና በ1950ዎቹ በኮሪያ ጦርነት ወቅት “የባክቴሪያ ጦርነት” ያደረገች ሀገር ናት ስትልም ወቅሳለች፡፡

ይህንን መሰል ወቀሳዎች ከሰሜን ኮሪያ በተጨማሪ ቻይና እና ሩሲያ ደጋግመው ሲሉት የሚደመጡ ቢሆንም በዋሽንግተን ግን ይህንን ስታስተባብል ትስተዋላለች።

የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን፤ ከሁለት ወራት በፊት የሰሜን ኮሪያ ጦር ሃይሎች ምስረታ ቀንን ምክንያት በማድረግ ባደረጉት ንግግር ከእኛ ጋር ግጭት ውስጥ ለመግባት የሚፈልግን ማንኛውንም ሀገር “እናጠፋለን” ሲሉ መዛታቸው የሚታወስ ነው፡፡

ማንኛውም ሀገር ሰሜን ኮሪያ ከነካ አጸፋው የከፋ እንደሚሆን ያስጠነቀቁት ኪም ጆንግ ኡን፤ ፒዮንግያንግ አሁንም ቢሆን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እድገትን ለማፋጠን ጠንክራ ትሰራለች ሲሉም ተደመጠዋል፡፡

ኪም “በማንኛውም ጊዜ ሪፐብሊኩ የጣለባችሁን ኃላፊነት የተሞላበት ተልእኮ እና ልዩ መከላከልን ለመፈጸም ዝግጁ መሆን አለባችሁ” የሚል መልእክት ለኒውክሌር ኃይል ማስተላለፈቻውም ነበር የሰሜን ኮሪያ የዜና አገልግሎት ኤጀንሲ በወቅቱ የዘገበው።

እናም አሁን አሜሪካ በዩክሬን ምድር ባዮሎጂካል መሳሪያዎችን እያመረተች ትገኛለች የሚሉት ኪም፤ ከአሜሪካ ጋር ግጭት እንዳይገቡ እጅጉን ተሰግቷል፡፡

ሩሲያ በየካቲት ወር መጨረሻ በዩክሬን ላይ ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ማካሄድ የጀመረችው፤ ዋሽንግተን በዩክሬን ውስጥ ባዮሎጂካል መሳሪያዎችን ለማምረት ለምርምር የገንዘብ ድጋፍ አድርጋለች የሚል ክስ ማቅረብ ከጀመረች በኋላና ወደፊት በሩሲያ ላይ ሊጋረጡ የሚችሉ አደጋዎችን ቀድሞ ለመከላከል በሚል እንደነበር አይዘነጋም፡፡

News today, Politics

አሜሪካ፤ ሩሲያ የዩክሬን ግዛቶች ለመጠቅለል መሰረት እየጣለች ነው አለች


አሜሪካ፤ ሩሲያ የዩክሬን ግዛቶች ለመጠቅለል መሰረት እየጣለች ነው አለች

በኔቶ የአሜሪካ ተልዕኮ “የሩስያን ቀጣይ እርምጃ እናውቃለን” ብሏል

አሜሪካ፤ ሩሲያ የዩክሬን ግዛቶችን በጉልበት የመጠቅለል እቅዷን ከቀጠለችበት ፈጣን ምላሽ እንወስዳለን ስትልም ዝታለች

ሩሲያ የዩክሬንን ሉዓላዊነት በቀጥታ በመጣስ ግዛቶችን የምትቆጣጠረው በስሯ ያሉ ግዛቶችን ለመጠቅለል የሚያስችላት መሰረት ለመጣል መሆኑን በሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) የአሜረካ ተልዕኮ ገለጸ፡፡

ተልዕኮው በትዊተር ገጹ ላይ ባጋራው ጽሁፉ “የሩስያን ቀጣይ እርምጃ እናውቃለን”ም ብሏል ፡፡

ሩሲያ የዩክሬን ግዛቶች በጉልበት የመጠቅለል እቅዷን ከቀጠለችበት ከአጋሮቻችን ጋር በመሆን በፍጥነት እና በከፍተኛ ሁኔታ ምላሽ እንሰጣለን ሲል ተልዕኮው ዝቷል፡፡

ሩሲያ በዩክሬን ምድር እየሄደችበት ያለው ግዛቶችን የመጠቅለል ወታደራዊ እርምጃ ያሰጋውና አሜሪካና አጋሮቿን በአባልነት ያቀፈው ኔቶ የጦሩን ቁጥር ለማሳደግ እየሰራ መሆኑ በድርጅቱ ዋና ጸሃፊ ጄንስ ስቶልተንበርግ አማካኝነት በቅርቡ መግለጹ አይዘነጋም፡፡

ዋና ጸሃፊው “የኔቶን ኃይል እናጠናክረዋለን እንዲሁም የከፍተኛ ዝግጁነት ሀይላችንን ቁጥር ከ 40 ሺህ ወደ 300 ሺህ እናሳድጋለን” ነበር ያሉት፡፡

ሩሲያ በበኩሏ አሜሪካም ሆነ ኔቶ አጋሮቿ በዚህ ጉዳይ ላይ እጃቸው ካስገቡና ወደ እንደ ክሪሚያ ወደ መሳሰሉ ግዛቶች ከተጠጉ ሶስተኛው የዓለም ጦርነት ይጀመራል ስትል ማስጠንቀቋ የሚታወስ ነው፡፡

የቀድሞው የሩሲያ ፕሬዝዳንት ድሚትሪ ሜድቬዴቭ በቅርቡ እንደተናገሩት ኔቶ ወደ ክሪሚያ የሚያደርገው ማንኛውም እንቅስቃሴ “ሶስተኛውን የዓለም ጦርነት የሚያስነሳ ነው”ም ብለው ነበር፡፡ 

News today, Politics

የብሪታንያ እጩ ጠቅላይ ሚንስትር ቻይናን በጠላትነት ፈረጁ


ቻይና የአውሮፓን ቴክኖሎጂ በመስረቅና ሩሲያን ትደግፋለች ሲሉ ሱናክ ከሰዋል

የብሪታንያ እጩ ጠቅላይ ሚንስትር ቻይናን በጠላትነት ፈረጁ።

የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን ከፓርቲያቸው እና ከስራ ባልደረቦቻቸው በደረሰባቸው ጫና ስልጣን እለቃለሁ ማለታቸው ይታወሳል።

ይሄንን ተከትሎም ቦሪስ ጆንሰንን ለመተካት 11 እጩዎች ቀርበው በመጨረሻም የህንድ ዝርያ ያላቸው ሪሺ ሱናክ እና ሊዝ ትሩስ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሰዋል።

ቻይና የእስያ ሀገራት የዓለማችን ኃያላን መጠቀሚያ ከመሆን እንዲቆጠቡ አስጠነቀቀች
የብሪታንያ ፋይናንስ ሚንስትር የሆኑት እና አሁን ላይ ቦሪስ ጆንሰንን ለመተካት በመጨረሻ ትንቅንቅ ላይ የሚገኙት ሪሺ ሱናክ ምርጫውን አሸንፈው የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር ከሆኑ በቻይና ላይ ማዕቀቦችን እንደሚጥሉ ተናግረዋል።

ቻይና የአውሮፓን እና የብሪታንያ ቴክኖሎጂዎችን እየሰረቀች ነው የሚሉት እጩ ጠቅላይ ሚንስትሩ በስልጣን ዘመናቸው ቻይና ለፋብሪካዎቿ ከብሪታንያ የምትገዛቸው የቴክኖሎጂ ውጤቶች እንዳይደርሷት አደርጋለሁ ሲሉም ተናግረዋል።

እጩ ጠቅላይ ሚንስትሩ አክለውም ቻይና ዩክሬንን ከወረረችው ሩሲያ ነዳጅ በገፍ በመግዛት ድጋፍ እያደረገች እንደሆነም ገልጸዋል።ቻይና ከዚህ በፊት እጩ ጠቅላይ ሚንስትር ሪሺ ሱናክ ከሌሎች እጩዎች ጋር ሲነጻጸሩ የተሻሉ መሪ እንደሆኑ ተናግራ ነበር።

እጩ ጠቅላይ ሚንስትር ሱናክ በምርጫው ካሸነፉ በብሪቴን ያሉ ከ30 በላይ የቻይና ባህል ማዕከላትን እንደሚዘጉም ዝተዋል።

ቻይና ከቴክኖሎጂ ወረራዎች ባለፈ በባህል እና ሌሎች ተያያዥ ዘርፎች ተጽዕኖ እየፈጠረች ነው የሚሉት ሱናክ ይህን በብሪታንያ ምድር እንዲከወን አልፈቅድም ሲሉም ተናግረዋል።

ቦሪስ ጆንሰንን የሚተኩት ጠቅላይ ሚንስትር በፈረንጆቹ መስከረም 5 ቀን 2022 የብሪታንያ ወግ አጥባቂ ፓርቲ ያሳውቃል ተብሏል።

News today, Politics

የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ወደ አውሮፓ የሚልኩት የነዳጅ መጠን በእጥፍ መጨመሩ ተገለጸ

የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ወደ አውሮፓ የሚልኩት የነዳጅ መጠን በእጥፍ መጨመሩ ተገለጸ

ከመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ወደ አውሮፓ የሚላከው የድፍድፍ ነዳጅ መጠን ካሳለፍነው ጥር ወር ወዲህ በ90 በመቶ መጨመሩ ተገለፀ።

የነዳጅ ፍላጎቱ የጨመረው የሩሲያ ዩክሬን ጦርነትን ተከትሎ የአውሮፓ ሀገራት በሩሲያ ነዳጅ ላይ ማዕቀብ መጣላቸውን ተከትሎ ነው።

ብሉምበርግ ባወጣው ሪፖርት መሰረት ባሳለፍነው 20 ቀናት ብቻ 1 ሚሊየን በርሜል ነዳጅ ከሳዑዲ አረቢያ በግብጽ በኩል በሚያልፍ መስመር ወደ አውሮፓ የገባ ሲሆን፤ 1.2 ሚሊየን በርሜል ደግሞ በስዊዝ ካናል በኩል ወደ አውሮፓ ገብቷል።

News today, Politics

የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ከህወሓት ጋር ስለሚደረገው ድርድርና ስለ ህዳሴ ግድብ ለመነገጋገር ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ


የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ከህወሓት ጋር ስለሚደረገው ድርድርና ስለ ህዳሴ ግድብ ለመነገጋገር ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ

ማይክ ሀመር በአዲስ አበባ ቆይታቸው የአፍሪካ ህብረት ጋርም የሚመክሩ ይሆናል

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሀመር

ልዩ መልእከተኛው ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ወደ ግብጽና እና አረብ ኢሚሬትስ ያቀናሉ

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሀመር በዛሬው እለት አዲስ አበባ ይገባሉ።

ማይክ ሀመር በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት መካከል ይደረጋል የተባለውን የሰላም ድርድር ለማፋጠን የሚደረገውን ጥረት የመገምገም ዕድል እንደሚኖራቸውም ነው የተገለጸው።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትናንት ማምሻውን ባወጣው መገልጫ፤ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ያለበትን ሁኔታ መገምገም እንዲሁም በጦርነቱ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የፈጸሙ አካላት ተጠያቂ ማድረግን የተመከቱ ጉዳዮች ማይክ ሀመር በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከሚመክሩባቸው አንኳር ጉዳዮች መሆናቸውን ጠቅሷል።

ልዩ መልዕክተኛው ከጦርነቱ በተጨማሪ ስለ ታላቁ ህዳሴ ግድብም ይነጋገራሉ ተብሏል።

ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን በሚወዛገቡበት ጉዳይ ላይ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ ለማምጣት የአሜሪካ ድጋፍ እንደሚያደርጉ መግለጫው የጠቀሰ ሲሆን ይህም የሁሉንም አካላት ፍላጎት በሚያረካ መልኩ ነው ተብሏል።

ማይክ ሀመር በአዲስ አበባ ቆይታቸው የሶስትዮሹን ድርድር ሲመራ ከነበረው የአፍሪካ ህብረት ጋርም የሚመክሩ ይሆናል።

ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ወደ ግብጽ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እንደሚያቀኑም ነው የተገለጸው።

ዴቪድ ሳተርፊልድን በመተካት በአፍሪካ ቀንድ አዲስ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው የተሾሙት ማይክ ሀመር ወደ ኢትዮጵያ ጉዞ ሲያደርጉ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ “አሜሪካ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሁሉም ህዝቦች ዘላቂ ሰላም፣ ደህንነት እና ብልጽግና ለማምጣት ያስችል ዘንድ ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ሂደትን መደገፍ እና ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶችን ለማራመድ ቁርጠኛ ነች” ነች ብሏል፡፡

በሰሜን ኢትዮጵያ የተከሰተው ግጭት የተለያዩ አሳዛኝ ክስተቶች እያስተናገደና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዋና አጀንዳ ሆኖ ቆይቷል።አሁን ላይ የጦርነቱ ተዋናዮች ማለትም የፌዴራል መንግስት እና ህወሐት ወደ የድርድር ሃሳብ መምጣታቸው የሚታወቅ ነው።

በፌዴራል መንግስት እና ህወሐት መካከል ያለውን ቀውስ በሰለማዊ መንገድ የሚፈታበት መንገድ ካለ፤ አሳዘኝ ውድመት ያስከተለውንና በርካቶችን ለሞትና እንግልት የዳራገውን ጦርነት በድርድር ለመፍታት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ከሰሞኑ የህወሐት ተደራዳሪ ቡዱን ማዋቀሩን በቃል አቀባዩ ጌታቸው ረዳ በኩል ያስታወቀው ህወሐት በኬንያ መንግስት አሸማጋይነት በናይሮቢ የሚደረግ የሰላም ንግግር ካለ በድርድሩ የሚሳተፍ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ለመላክ መዘጋጀቱን አስታውቋል።

የፌዴራል መንግስት በበኩሉ የሀገር ብሄራዊ ጥቅምን ባስጠበቀ መልኩ በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር በሚካሄድ ድርድር ለመነጋገር ዝግጁ መሆኑና ስራ መጀመንሩ፤ በጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ እንዲሁም በሌሎች ባለስልጣናት አማካኝነት ሲገልጽ ቆይቷል።

ሁለቱ አካላት ለሰላም ድርድሩ ያላቸውን ፍላጎት ቢገልጹም ውይይቱ መቼ ይጀመር፣ የትስ ቦታ ነው በሚለው ላይ በግልጽ የተባለ ነገር የለም።

News today, Politics

የሩሲያው ጋዝፕሮም ከኢራን ጋር የ40 ቢሊዮን ዶላር ንግድ ስምምነት ፈጸመ

የሩሲያው ጋዝፕሮም ከኢራን ጋር የ40 ቢሊዮን ዶላር ንግድ ስምምነት ፈጸመ
በስምምነቱት መሰረት ጋዝፕሮም ኢራን በቀን 100 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ጋዝ ማምረት የሚያስችላትን መሰረተ ልማት ይዘረጋል ተብሏል
የሩሲያ፣ ተርኪዬ እና ኢራን ፕሬዝዳንቶች በቴህራን እየተወያዩ ነው

የሩሲያው ጋዝፕሮም ከኢራን ጋር የ40 ቢሊዮን ዶላር ንግድ ስምምነት ተፈራረመ።

የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በኢራን ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸው።የፕሬዝዳንቱን ጉብኝት ተከትሎ ሁለቱ ሀገራት የንግድ እና ኢንቨስትመንት ስምምነቶችን ፈጽመዋል ተብሏል።

የሩሲያው ጋዝፕሮም የነዳጅ ኩባንያ ከኢራን አቻው ጋር የ40 ቢሊዮን ዶላር ስምምነት ተፈራርሟል ሲል አርቲ ዘግቧል።

ስምምነቱ ኢራን በሰሜናዊ የሀገሪቱ አካባቢ በቀን 100 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ተጨማሪ ነዳጅ እንድታመርት የሚያስችል መሰረተ ልማት ጋዝፕሮም ኩባንያ ይፈጽማል ተብሏል።

ቴህራን የሩሲያ፣ ተርኪዬ እና ኢራን የሶስትዮሽ ውይይት መድረክን በማስተናገድ ላይ ስትሆን የሶስቱም ሀገራት መሪዎች በመድረኩ ላይ ተገኝተዋል።

የሶስቱ ሀገራት መሪዎች ላለፉት በርካታ ዓመታት በእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ላለችው ሶሪያ የተሻለ መፍትሄ መፈለግ በሚቻልበት ዙሪያ ይወያያሉ ተብሏል።

ከዚህ በተጨማሪም የሶስቱ ሀገራት መሪዎች በተናጠል ዲፕሎማሲያዊ እና በአካባቢያዊ አጀንዳዎች ዙሪያ እንደሚወያዩ ተገልጿል።

ዩክሬን የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ጦር ወይም ኔቶን እቀላቀላለሁ ማለቷን ተከትሎ ሩሲያ ጦሯን ወደ ዩክሬን የላከች ሲሆን ጦርነቱ ከተጀመረ አምስት ወራት ሊሞላው ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርቶታል።

በዚህ ጦርነት ምክንያትም ከአሜሪካ እና ምዕራባውያን ሀገራት ከስድስት ሺህ በላይ ማዕቀቦች የተጣሉባት ሩሲያ የእስያ እና መካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ጋር አዳዲስ የንግድ ስምምነቶችን በማድረግ ላይ ትገኛለች።

ኢራን፣ ህንድ፣ ቻይና እና በተለያዩ አህጉራት የሚገኙ ሌሎች ሀገራት ደግሞ ከሩሲያ ጋር አዲስ የንግድ ስምምነቶችን በመፈጸም ላይ ናቸው።

News today, Politics

አምባሳደር ስለሺ በቀለ፤ ከአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ጋር በድርድርና በአጎአ ዙሪያ መወያየታቸው ተገለፀ

አምባሳደር ስለሺ በቀለ፤ ከአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ጋር በድርድርና በአጎአ ዙሪያ መወያየታቸው ተገለፀ
ልዩ መልዕክተኛ በዚህ ሳምንት ወደ አፍሪካ ቀንድ አካባቢ እንደሚመጡ ይጠበቃል

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ በአፍሪካ ቀንድ ከአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ሚካኤል ሃመር ጋር መነጋገራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

አምባሳደር ስለሺ እና በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት በተጀመረው ጥረትና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ነው ውይይት ማድረጋቸው የተገለጸው።

አሜሪካ ማይክ ሀመርን በአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አድርጋ ሾመች
ሁለቱ ዲፕሎማቶች ስለመንግስትና ህወሃት ድርድር፤ ስለሰብዓዊ ድጋፍ፣ ብሔራዊ ምክክር፣ የሕዳሴ ድርድር፣ አጉዋ እንዲሁም ኤአር 6600 እና S3199 መወያየታቸው ተገልጿል፡፡

አምባሳደር ስለሺ፤ የኢትዮጵያ መንግስት በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ ያልተቆጠበ ስራ እየሰራ መሆኑን ለዲፕሎማቱ መናገራቸው ተገልጿል፡፡

አሁን ላይ መንግስት በሀገሪቱ ሰላም ይመጣ ዘንድ የሥራ ሂደቶችን የጀመረ መሆኑን የገለጹት ዲፕሎማቱ፤ ይህንን ዕውን ለማድረግ ግን ሌኛው ወገንም ሊሰራ እንደሚገባ ነው ያነሱት።

በሌላኛው ወገን ያለው አካል ሰላም እንዲመጣ ቢሰራ መንግስት የጀመረው የሰላም ጥረት ዕውን እንደሚሆንም ነው የኢትዮጵያ ዲፕሎማት የገለጹት።

በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ሚካኤል ሃመር በበኩላቸው የተጀመረው የሰላም ጥረት እንዲሳካ ሀገራቸው ድጋፍ እንደምታደርግ ገልጸዋል።

የአሜሪካ ዲፕሎማት ኢትዮጵያውያን ሰላም እንዲያገኙ ሀገራቸው ድጋፍ ለማድረግ መዘጋጀቷንም ለአምባሳደር ስለሺ ገልጸዋል ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።

አምባሳደር ስለሺ መንግስት በግጭት እና በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የሰብዓዊ ድጋፍ የማድረሱ ስራ ያለእንቅፋት መቀጠሉን ማንሳታቸው ተገልጿል።

አሜሪካ የኢትዮጵያ መንግስት እየወሰዳቸው ላላቸው ጥረቶች አድናቆት እንዳለው መግለጹን የኢትዮጵያ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።

የሕዳሴ ግድብን በሚመለከት ኢትዮጵያ የምትከተለው አቋም ሚዛናዊ መሆኑን የገለጹ ሲሆን አምባሳደር ሚካኤል ሃመር ደግሞ ሶስቱ ሀገሮች ሁሉንም ጠቃሚ የሚያደርግ መንገድ ላይ ይደርሳሉ የሚል ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል።

አምባሳደር ስለሺ ኢትዮጵያ ከአግዋ ተጠቃሚነቷ የወጣችበት መንገድና ማዕቀብ ለመጣል የተዘጋጁት ኤአር 6600 እና S3199 ረቂቆችም ረጅም ጊዜ ላስቆጠረው የአዲስ አበባንና የዋሸንግተንን ግንኙነት የሚመጥን እንዳልሆነና መስተካከል እንዳለበት መጠየቃቸው ተገልጿል፡፡

“የሱዳን ሽግግር መንግስትን በኃይል መቀየር የአሜሪካን ድጋፍ ያሳጣል”- የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ
የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ወደ አጉዋ ተጠቃሚነት እንዲትመለስ ቅድመ ሁኔታዎች መሟላታቸው ጠቃሚ መሆኑን መግለጻቸውን ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የገለጸው።

በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ሚካኤል ሃመር በዚህ ሳምንት ወደ አፍሪካ ቀንድ አካባቢ እንደሚመጡ ይጠበቃል።

News today, Politics

አውሮፓ ህብረት ሩሲያ የምግብ አቅርቦትን እንደ ‘ድብቅ ሚሳኤል’ እየተጠቀመችበት ነው የሚል ክስ ያቀርባል

አውሮፓ ህብረት ሩሲያ የምግብ አቅርቦትን እንደ ‘ድብቅ ሚሳኤል’ እየተጠቀመችበት ነው የሚል ክስ ያቀርባል

የአውሮፓ ህብረት በዓለም አቀፍ የምግብ እና ማዳበሪያ ንግድ ላይ ያሉ ማነቆዎችን ለማቃለል በሞስኮ ባንኮች ላይ የጣለውን ማዕቀብ እንደሚያሻሽል አስታወቀ፡፡

ህብረቱ ማሻሻያወን ለማድረግ በሚያስችለው ረቂቅ ሰነድ ላይ በመምከረም ተሰምቷል፡፡

ህብረቱ በሩሲያ ባንኮች ላይ የወሰደውን እርምጃ ተከትሎ የዓለም የምግብ አቅርቦት ላይ ከፍተኛ ችግር መፈጠሩ አይዘነጋም፡፡

በተለይም ሩሲያ በጥቁር ባህር የሚገኙ ወደቦች ዝግ ማድረጓ፤ የምግብ እጥረቱ በተለይም እንደ አፍሪካ ባሉ ክፍለ አህጉራት ከፍተኛ ጫና መፍጠሩ የአፍሪካ ህብረትም ጭምር ሲገልጽ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡

እናም ችግሩን ከግምት ያስገባው የአውሮፓ ህብረት በሩሲያ የገንዘብ ተቋማት ላይ በጣለው ማዕቀብ ላይ ማሻሻያ አደርጋለሁ ብሏል፡፡

አንድ የአወሮፓ ህብረት ለሮይተርስ እንደተናገሩት ከሆነ፤ ረቂቅ ሰነዱ ረቡዕ የሚጸድቅ ይሆናል፡፡

አውሮፓ ህብረት ሩሲያ የምግብ አቅርቦትን እንደ ‘ድብቅ ሚሳኤል’ እየተጠቀመችበት ነው የሚል ክስ ሲያቀርብ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ቻርለስ ሚሸል ከአንድ ወር በፊት በኒውዮርክ በነበረው የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ስብሰባ እንደተናገሩት፤ ሩሲያ የምግብ አቅርቦትን እንድ ድብቅ ሚሳዔል በመጠቀም በማደግ ላይ የሚገኙ ሀገራትን ለከፋ ድህነት እየዳረገች ነው ሲሉ ከሰዋል፡፡

ሚሸል “የሚያሳዝነው ሩሲያ የጀመረችው ጦርነት በመላው ዓለም እየተዛመተ መሆኑ ነው፤ የምግብ ዋጋ እጅጉን እንዲንር በማድረግ የዓለም ህዝቦች ለድህነት እንዲዳረጉና የተለያዩ ቀጠናዎች እንዲታመሱ እያደረገ ነው ፤ለዚህ ሁሉ ቀውስ ተጠያቂ ሩሲያ መሆኗ ሊታወቅ ይገባል” ነበር ያሉት፡፡

ሩሲያ ግን በተወካይዋ አማካኝነት “መሰረተ ቢስ” ስትል በወቅቱ ክሱን ውድቅ ማድረጓ ይታወቃል፡፡

News today, Politics

እኛ የሙስሊም ሀገር ነን። ባህሎች እና ወጎች አሉን እናም እስልምና እነዚህን ድርጊቶች (የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን) ይከለክላል ” – አል ሃማሚ

እኛ የሙስሊም ሀገር ነን። ባህሎች እና ወጎች አሉን እናም እስልምና እነዚህን ድርጊቶች (የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን) ይከለክላል ” – አል ሃማሚ
ኢራቅ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ወንጀል እንዲሆን እና ከፍተኛ የሆነ ቅጣት እንዲጣል እየሰራች መሆኗን አሳውቃለች።
የኢራቅ መንግስት የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት የሚከለክል ህግ ለማፅደቅ ማቀዱን አስታውቋል።

ኢራቅ በመካከለኛው ምስራቅ ከሚገኙ ሶስት ብዙ አረቦች ከሚኖሩበት ሀገር መካከል አንዷና የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን #በግልፅ ወንጀል እንደሆነ ካላወጁ ሀገራት የምትጠቀስ ናት ፤ ሌሎቹ ጆርዳን እና ባህሬን ናቸው። ምንም እንኳን በግልፅ ወንጀል ነው ተብሎ ባይገለፅም ድርጊቱ በማህበረሰቡ ዘንድ እጅግ በጣም የተወገዘ ነው።
አሁን ያለው ሁኔታ ያላማራት ኢራቅ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን ወንጀል እንደሆነ በህግ ለመደንገግ እየሰራች ሲሆን ህጉ ከወጣ ኢራቅ ሌሎች ድርጊቱን በህግ ወንጀል እንደሆነ ካፀደቁ ሀገራት ተርታ ትሆናለች።
አብዛኛዎቹ የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን በቀጥታ በግልፅ የሚከለክሉ ሲሆን ከገንዘብ ቅጣት እስከ እስራት ፤ ሳውዲ አረቢያ ደግሞ #የሞት_ቅጣት ትቀጣለች።

በኢራቅ ፓርላማ የህግ ኮሚቴ ውስጥ ያሉት የፓርላማ አባል አሬፍ አል ሃማሚ ለDW በሰጡት ቃላቸው ፥ ” አዲሱ ህግ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ያላቸውን በወንጀል ተጠያቂ ያደርጋል ፤ በእነሱ ላይም ከባድ ቅጣት ይጥላል ” ብለዋል።

ህጉ እስካሁን ድምጽ ያልተሰጠበት ሲሆን ድምፅ እንዲሰጥበት እየተሰራ ነው። አል ሃማሚ ከሀገር ውስጥ እና ከዓለም አቀፍ #የሰብአዊ_መብት_ተሟጋች_ድርጅቶች ትችት ቢሰነዘርም ህጉ ይፀድቃል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል።

” እኛ የሙስሊም ሀገር ነን። ባህሎች እና ወጎች አሉን እናም እስልምና እነዚህን ድርጊቶች (የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን) ይከለክላል ” ሲሉም ገልፀዋል።

የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ያላቸውን ሰዎች እስከ ሞት ድረስ የምትቀጣድ ሳዑዲ አረቢያ ከወራት በፊት ድርጊቱን ያስተዋውቃል ያለችውን ምልክት ያለባቸውን ቁሳቁሶች ከየመደብሩ ስትሰበስብ እንደነበር ይታወሳል፤ በተጨማሪ ሁለት የምዕራባውያን የልጆች ፊልሞችን በሀገሯ እንዳይታዩ ማገዷም አይዘነጋም።

News today, Politics

አረብ ኤምሬትስና ፈረንሳይ በኢነርጂ ዘርፍ ሁሉን አቀፍ የስትራቴጂክ አጋርነት ስምምነት ተፈራረሙ

ስምምነቱ ነዳጅን ጨምሮ የኃይል አማራጮችን በዘላቂነትና በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ የሚያስችል ነው

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስና ፈረንሳይ በኢነርጂ ዘርፍ ሁሉን አቀፍ የስትራቴጂክ አጋርነት ስምምነት መፈራረማቸው ተገለፀ።

የፊርማ ስነ ስርዓቱ የአረብ ኤሚሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ ሞሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን እና የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በተገኙነት ነው የተካሄደው።

ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ በመጀመሪያ ይፋዊ የስራ ጉብኝታቸው ፈረንሳይን ለምን መረጡ?
በኃይል ዘርፍ የተደረሰው አጠቃላይ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ስምምነት በአረብ ኤምሬትስ እና በፈረንሳይ መካከል የመጀመሪያ ሲሆን፤ በአረብ ኢሚሬትሱ ኤዲኖክ እና በፈረንሳዩ ቶታል ኢነርጂ መካከል ሁለተኛው የስትራቴጂክ አጋርነት ስምምነት ነው።

የመጀመሪያው ስትራቴጂካዊ አጋርነት በአረብ ኤምሬትስ በ2023 ለሚካሄደው 28ኛው የአየር ንብረት ጉባዔ (COP28) ስብሰባ ለመዘጋጀት ውጤታማ የአየር ንብረት ርምጃዎችን ለማስፋት ልምድ ለመለዋወጥ ሲሆን፤ በተጨማሪም የነዳጅን ጨምሮ ኃይል አቅርቦት ደህንነት ለማረጋገጥ እና በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ የሚያስችል ነው።

በአረብ ኢሚሬትስ በኩል ስምምነቱን የፈረሙት ዶ/ር ሱልጣን አህመድ አል ጃበር ፤ “አረብ ኢምሬትስ እንደ አስተማማኝ የሃይል አቅራቢነቷ የኃይል አቅርቦት ደህንነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባትን እንደመትሰራ አስታውቀዋል

ስምምነቱ አረብ ኤሚሬትስ ለአጋሯ ፈረንሳይ በኃይል ዘርፍ ቀጣይነት ያለው እና ደህንነቱ የተጠበቀ ኃይል በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ የሚያስችል እንዲሁም የሁለቱን ወዳጅ ሀገራት ኢኮኖሚ እድገት እና ብልጽግናን የሚያግዝ ነው ብለዋል።

ፈረንሳይ እና አረብ ኢሚሬትስ በኢነርጂ ልማት ዘርፍ ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ ትብብር የነበራቸው ሲሆን የፈረንሳዩ ቶታል ኢነርጂ በአውሮፓውያኑ ከ1939 ጀምሮ በአቡዳቢ በነዳጅ እና ጋዝ ልማት ዘርፍ ተሰማርቶ እየሰራ ይገኛል።

አረብ ኢምሬትስ ካራካል የተሰኘ የኤርባስ ስሪት ሂልኮፕተሮችን ተረከበች
ከዚህ በተጨማሪም ሁለቱ ሀገራት የተለያዩ የንግድ ግንኙነቶችን ያላቸው ሲሆን፤ በፈረንጆቹ 2020 ብቻ የፈረንሳይ 3.1 ቢሊዮን ዩሮ ዋጋ ያለው ምርት ወደ አረብ ኤሚሬትስ ልካለች፤ በአንጻ ከአረብ ኢሚሬትስ 750 ሚሊዮን ዩሮ ግምት ያለው ምርት ወደ ሀገሯ አስገብታለች።

አረብ ኢሚሬትስ በመካከለኛው ምስራቅ ከሚገኙ ሀገራት ውስጥ በርካታ ቁጥር ያላቸው የፈረንሳይ ኩባንያዎችን ተቀብላ እያስተናገደች ሲሆን፤ በሀገሪቱ የሚገኝ 600 ኩባያዎች ከ30 ሺህ በላይ ሰራተኞችን መቅጠራቸው እና የሚቀጥሩት የሰው ሀይል መጠንም በየአመቱ በ10 በመቶ እድገት እንዳለው መረጃዎች ይጠቁማሉ

News today, Politics

ሩሲያ በጎግል ኩባንያ ላይ የ366 ሚሊዮን ዶላር ቅጣት አስተላለፈች

ሩሲያ በጎግል ኩባንያ ላይ የ366 ሚሊዮን ዶላር ቅጣት አስተላለፈች ሩሲያ ከዚህ በፊት 98 ቢሊዮን ዶላር እንዲከፍል መወሰኗ ይታወሳል

ሩሲያ ውሳኔውን በጎግል ላይ የወሰነችው ከዩክሬን ጋር በተያያዘ ከ 7 ሺህ በላይ ያልተገባ ምስል አሰራጭቷል በሚል ነው

ዩክሬን የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ጦር ወይም ኔቶን እቀላቀላለሁ ማለቷን ተከትሎ ነበር ከሩሲያ ጋር ወደ ይፋዊ ጦርነት ያመሩት።

ሩሲያ የአሜሪካዊያን ንብረት በሆነው ጎግል ኩባንያ ላይ 366 ሚሊዮን ዶላር እንዲከፍል ወስናለች።

በሞስኮ የሚገኘው ታጋንስኪ ግዛት ፍርድ ቤት ጎግል ኩባንያ ከዩክሬን ጦርነት ጋር በተያያዘ ሀሰተኛ ምስሎችን አሰራጭቷል በሚል የቅጣት ውሳኔ ማስተላለፉን አርቲ ዘግቧል።

ዘገባው አክሎም ጎግል ኩባንያ ስለ ዩክሬን ጦርነት ከሰባት ሺህ በላይ ሀሰተኛ ምስሎችን አስራጭቷል ብሏል።

ሩሲያ ሀሰተኛ ምስሎችን ማስተላለፍ በህግ የደነገገች ሲሆን ጎግል ኩባንያ ቅጣቱ የተላለፈበት ሀሰተኛ ምስል በማስተላለፍ እና ያስተላለፋቸውን ምስሎች ከድህረ ገጹ ላይ ለማጥፋት ፈቃደኛ ባለመሆኑ እንደሆነ ተጠቅሷል።

ሩሲያ ባሳለፍነው ታህሳስ ወር ላይ ይሄው ጎግል ኩባንያ ሆን ብሎ ሀሰተኛ ምስሎችን አሰራጭቷል በሚል 98 ቢሊዮን ዶላር እንዲከፍል ውሳኔ ማስተላለፏ ይታወሳል።

የሩሲያ ዩክሬን ጦርነትን ተከትሎም በሁለቱ ሀገራት እና በተቀረው ዓለም ላይ በርካታ ለውጦች የተመዘገቡ ሲሆን ከ15 ሚሊዮን በላይ ዩክሬናዊያን ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል።

ይህ በዚህ እንዳለም የዓለም ምግብ እና ነዳጅ ዋጋ በእጅጉ አሻቅቧል።

በጦርነቱ ምክንያት በተከሰተው የዋጋ ግሽበት ምክንያትም በበርካታ ሀገራት ኑሮ ተወደደብን በሚል መንግስታት የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች እንዲደርጉ በሰላማዊ ሰልፍ በመጠየቅ ላይ ናቸው።

አምስት ወራት የሆነው ይህ የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት አሁንም የቀጠለ ሲሆን አሜሪካንን ጨምሮ ሌሎች የምዕራባዊያን ሀገራት ዩክሬንን በጦር መሳሪያ እና ሌሎች ወታደራዊ ድጋፎችን በመስጠት ላይ ናቸው።

News today, Politics

ፕሬዝዳንት ፑቲን ከዩክሬን ጦርነት በኋላ ከቀድሞ ሶቬት ሀገራት ውጭ ባደረጉት የመጀመሪያ ጉዞ ኢራንን ጎበኙ

ፕሬዝዳንት ፑቲን ከዩክሬን ጦርነት በኋላ ከቀድሞ ሶቬት ሀገራት ውጭ ባደረጉት የመጀመሪያ ጉዞ ኢራንን ጎበኙ

ፑቲን ከቱርኩ ፕሬዝደንት ኦርዶጋን ጋርም በኢራን ይመክሯሉ
ከኢራን ጋር “በአብዛኛዎቹ ጉዳዮች አቋማችን ተቀራራቢ ወይም ተመሳሳይ ነው” ብለዋል የፑቲን የውጭ ፖሊሲ አማካሪ

ፕሬዝዳንት ፑቲን ከዩክሬን ጦርነት በኋላ ከቀድሞ የሶቬት ሀገራት ውጭ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢራንን በመጎብኘት የኢራኑን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ካሚኒን አግኝተዋል፡፡

ፑቲን ፊታቸውን ወደ ህንድ፣ ኢራን እና ቻይና በማዞር የምእራባውያን ሀገራት ሩሲያን በኢኮኖሚ የማሽመድመድ እቅድ ላይ ጥላ ማጥላቱን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ሩሲያ በዩክሬን “ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ” መጀመሯን ተከትሎ ይህን የሚቃወሙት ምእራባውያን ሀገራት በታሪክ ከባድ ነው የተባለውን ማእቀብ በሩሲያ ላይ ጥለዋል፤ እየጣሉም ነው፡፡

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን የመካከለኛው ምስራቅ ጉብኝታቸው በሳኡዲ አረቢያ ካጠናቀቁ ሶስት ቀን በኋላ የሩሲያው ፕሬዝደንት ፑቲን ከኢራኑ ጠቅላይ መሪ እና በፈረንጆቹ በ1989 ወደ ስልጣን ከመጡት አሊ ካሚኒ ጋር ለመወያየት ኢራን ደርሰዋል፡፡

“ከካሜኔ ጋር ያለው ግንኙነት በጣም አስፈላጊ ነው” ሲሉ የፑቲን የውጭ ፖሊሲ አማካሪ ዩሪ ኡሻኮቭ በሞስኮ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡ “በሁለትዮሽ እና በአለምአቀፍ አጀንዳዎች ላይ በጣም አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ እምነት የሚጣልበት ውይይት በመካከላቸው ተፈጥሯል” ብለዋል አማካሪው፡፡

ከኢራን ጋር “በአብዛኛዎቹ ጉዳዮች አቋማችን ተቀራራቢ ወይም ተመሳሳይ ነው።” ብለዋል የፑቲን የውጭ ፖሊሲ አማካሪ

የፑቲን የኢራን ጉብኝት ከቱርክ ጣይብ ኤርዶጋን ጋር የሚገጣጠም ሲሆን ሁለቱ መሪዎች ቴህራን ላይ በመገናኘት የዩክሬን የጥቁር ባህር እህል ወደ ውጭ መላክን ለማስቀጠል ያለመ ስምምነት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ቱርክ በሰሜን ሶሪያ ወታደራዊ ዘመቻ የመክፈት እቅድ አላት፤ ነገርግን ሩሲያ ይህን ትቃወማለች፡፡ ሁለቱ መሪዎች በዚህ ጉዳይም ይመክራሉ ተብሏል፡፡

ሩሲያ እና ኢራን ምእራባውያን ሀገራት የሶሪያ የእርስበእርስ ጦርነት ከተጀመረ ከፈረንጆቹ 2011 ጀምሮ ከስልጣን እንዲወገድ የሚፈልጉት የሶሪያ መሪ በሽር አላሳድን ይደግፋሉ፡፡

News today, Politics

ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የምዕራባውያንን ማዕቀብና የሀገራቸውን ዕድገት እንደሚያደናቅፍ ተናገሩ

ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የምዕራባውያንን ማዕቀብና የሀገራቸውን ዕድገት እንደሚያደናቅፍ ተናገሩ

የሩሲያ የቴክኖሎጂ ልማት በምዕራባውያን ማዕቀብ እንደማይቆም የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት አስታወቁ።

ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዛሬ ባደረጉት ንግግር የምዕራባውያንን ማዕቀብና የሀገራቸውን ዕድገት የተመለከቱ ጉዳዮችን አንስተዋል።

ፑቲን በንግግራቸውም የሞስኮ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ዕድገት እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

ፑቲን በሩሲያ ያለው የድህነት ሁኔታ እየቀነሰ እንደሆነም ነው በንግግራቸው ያነሱት። የሀገሪቱ የቴክኖሎጂ ዕድገት ምዕራባውያን ማዕቀብ ስለጣሉ እንደማጠይቆምም ነው የገለጹት።

ምንም እንኳን ምዕራባውያን ማዕቀብ ቢጥሉም የሞስኮ እድገት ግን ቀጣይነቱ አይቀሬ እንደሆነ ነው ያነሱት፡፡ የሩሲያ ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት አሁን ባለው መልኩ እንደሚቀጥልም ፑቲን ተናግረዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ዛሬ በስትራቴጂክ ልማት ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር ስለኮሮና ቫይረስ ማንሳታቸውም ተጠቅሷል፡፡ ምንም እንኳን ዓለም አቀፍ ጫና ቢኖርም ኮሮና ካስከተለው ችግር ለመውጣት ሀገራቸው ጥሩ ሁኔታ ላይ መሆኗን ጠቅሰዋል፡፡

አሁን ላይ በሩሲያ ያለው የድህነት ደረጃ እንጅ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱንም ፕሬዝዳንቱ ጠቅሰዋል፡፡ ከዚህ ባለፈም በሀገሪቱ የሞት ምጣኔ መቀነስ ማሳየቱን ጠቅሰዋል፡፡

የሩሲያ መገናኛ ብዙሃን የሆነው ሩሲያ ቱዴይ እስካሁን ፕሬዝዳንቱ ተናገሯቸው ካላቸው ነጥቦች መካከል የዩክሬን ጉዳይ አልተገለጸም፡፡

ባለሙያዎች እንዳሉት በኢንዱስትሪዎች ላይ ያለው ማዕቀብ ከሶስት እስከ አምስት ዓመታት ባሉት ጊዜያት እንደሚቀለበስ ገልጸዋልም ተብሏል፡፡

News today, Politics

በሶማሊያ የመንገደኞች አውሮፕላን በማረፍ ላይ እያለ ባጋጠመው አደጋ ተገለበጠ፡፡

በሶማሊያ የመንገደኞች አውሮፕላን በማረፍ ላይ እያለ ባጋጠመው አደጋ ተገለበጠ፡፡

ሰበር አውሮፕላኑ በሞቃዲሾ አውሮፕላን ማረፊያ እያረፈ ባለበት ነው የመገልበጥ አደጋ ያጋጠመው

በጎረቤት ሀገር ሶማሊያ አንድ የመንገደኞች አውሮፕላን የመገልበጥ አደጋ ማስተናገዱን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

አደጋው ያጠመው የሀገር ውስጥ መንገደኞችን በማጓጓዝ ላይ የነበረ አውሮፕላን ሲሆን 33 መንገደኞችን ከባይደዋ ወደ ሀገሪቱ መዲና ሞቃዲሾ በማጓጓዝ ላይ ነበር፡፡

ይህ የመንገደኞች አውሮፕላን በሞቃዲሾ አውሮፕላን ማረፊያ በማረፍ ላይ ሳለ ባጋጠመው ግጭት ምክንያት የተገለበጠ ሲሆን በሁሉም ተሳፋሪዎች ላይ ያጋጠመ የጎላ ጉዳት እንደሌለ የሶማሊያ ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡

አውሮፕላኑ ጁባ አየር መንገድ እንደሚባል የተገለጸ ሲሆን ስለ አውሮፕላኑ አደጋ መንስኤ እስካሁን ምንም የወጣ መረጃ የለም፡፡

በሶማሊያ የአውሮፕላን አደጋ የተለመደ ሲሆን፤ ወደ ሞቃዲሾ የሚበሩ የተለያዩ ሀገራት አውሮፕላኖች ተደጋጋሚ የመከስከስ አደጋዎች ያጋጥማሉ፡፡

የአልሻባብ የሽብር ጥቃት ባዳከማት ሶማሊያ የአውሮፕላን በረራ ተመራጭ የትራንስፖርት መንገድ ቢሆንም ተደጋጋሚ የአውሮፕላን አደጋዎች መከሰት ሌላኛው የተጓዦች ስጋት ሆኗል።

ከዚህ በፊት የኬንያ የግል የመንገደኞች እና የጭነት አውሮፕላኖች በተደጋጋሚ አደጋዎችን በሶማሊያ ያስተናገዱ ሲሆን ከጥቂት አየር መንገዶች በስተቀር በርካታ አየር መንገዶች ወደ ሶማሊያ የሚያደርጉትን በረራዎች አቋርጠዋል።

News today, Politics

በሱዳን ብሉናይል ግዛት በተፈጠረ ግጭት ከ65 በላይ ሰዎች ተገደሉ፡፡

በሱዳን ብሉናይል ግዛት በተፈጠረ ግጭት ከ65 በላይ ሰዎች ተገደሉ፡፡

 በሱዳን ብሉናይል ተብሎ በሚጠራው ግዛት በበርቲ እና ሀውሳ ጎሳዎች መበካከል በተፈጠረ የጎሳ ግጭት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ65 በላይ የደረሰ ሲሆን ከ200 በላይ ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ከሰዎች መጎዳት ባለፈም ከ16 በላይ የንግድ ሱቆች በዚሁ የጎሳ ግጭት ምክንያት ሲወድሙ ሌሎች መሰረተ ልማቶችም እንደወደሙ ተገልጿል፡፡

ብሉናይል ግዛት ከደቡብ ሱዳን ጋር በሚዋሰኑ አካባቢዎች ያለ የሀገሪቱ ክፍል ሲሆን ከዚህ በፊት መሰል አደጋዎች ይከሰቱበታል፡፡

በደቡብ ሱዳንም ተመሳሳይ የጎሳ ግጭት ተከስቶ 65 ሰዎች የሞቱ ሲሆን ከ150 በላይ ሰዎች ደግሞ ቆስለው ነበር፡፡

የሱዳን ጤና ሚኒስትር ጀማል ናስር ኤል ሳያድ እንዳሉት ባሳለፍነው ቅዳሜ በተከሰተው በዚህ አደጋ የተጎዱ ሰዎች አብዛኞቹ ወጣቶች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ግጭቱ አሁንም የቀጠለ ሲሆን ዛሬ ጠዋት ላይ በብሉ ናይል ግዛት መቀመጫ ዳማዚን ከተማ ላይ በተከሰተው እና በቀጠለው በዚሁ አደጋ ከ16 በላይ የንግድ መገበያያዎች መውደማቸው ተገልጿል፡፡

ግጭቱ አሁንም የቀጠለ ሲሆን የሟቾች እና ተጎጂዎች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል የግዛቲቱ ባለስልጣናት የተናገሩ ሲሆን ተጨማሪ ወታደሮች እንዲገቡላቸው ጠይቀዋል፡፡

በአል ሩሳሪስ ሆስፒታል ያለው የህክምና ቁሳቁሶች እያለቁ መሆናቸውን የተናገሩት ባለስልጣናቱ በግጭቱ ቆስለው ወደ ህክምና ተቋማት የሚመጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ እየጨመረ መሆኑንም አክለዋል፡፡

የግዛቲት ባለስልጣናት በብሉ ናይል ዋና ዋና ከተሞች ለአንድ ወር የሚቆይ የሰዓት እላፊ ቢጥሉም በርካቶች አሁንም ግጭቱ ሊቀጥል እንደሚችል ስጋት እንዳላቸው ተገልጿል፡፡

News today, Politics

የአረብ ኢሚሬትስ ፕሬዝዳንት የፈረንሳይ ይፋዊ የስራ ጉብኝታቸውን ጀመሩ

የአረብ ኢሚሬትስ ፕሬዝዳንት የፈረንሳይ ይፋዊ የስራ ጉብኝታቸውን ጀመሩ
ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ በፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አቀባበል ተደርጎላቸዋል
አረብ ኢሚሬትስና ፈረንሳይ በኢነርጂና በትራንስፖርት መስኮች እንደሚፈራራሙ ይጠበቃል

የአረብ ኢሚሬትስ ፕሬዝዳንት መሀመድ ቢን ዛይድ የፈረንሳይ ይፋዊ የስራ ጉብኝታቸውን በይፋ ጀምረዋል።

በትናንትናው ለት ምሽት ፈረንሳይ ፓሪስ የደረሱት
ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ ዛሬ በፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑዔል ማክሮን በኤሊሴ ቤተ መንግስት ይፋዊ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።0
ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ በኤሊሴ ቤተመንግስት ከፈረንሳይ አቻቸው ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ተገናኝተው ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ሌሎች የፈረንሳይ ባለስልጣናትን ያነጋግራ።

ሼህ መሀመድ ቢን ዛይድ አልነሃያን በፈረንሳይ ቆይታቸው በኢነርጅ እና በትራንስፖርት መስኮች እንደሚፈራራሙ ኤኤፍፒ ዘግቧል፡፡

የፈረንሳዩ ጉብኝት ፕሬዝዳንቱ ስልጣን ከያዙ በኋላ ያደረጉት የመጀመሪያ አለምአቀፍ ጉብኝት ነው፡፡

News today, Politics

ባይደን በጉብኝታቸው ወቅት ኢራን ኒውከሌር እንዳይኖራት መስራት የሚለው ጉዳይ አንደኛው አጀንዳ ነበር

ባይደን በጉብኝታቸው ወቅት ኢራን ኒውከሌር እንዳይኖራት መስራት የሚለው ጉዳይ አንደኛው አጀንዳ ነበር

ኢራን አሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የመካከለኛው ምስራቅ ጉብኝት ወቅት ውጥረት ለመፍጠር የኢራን ፍራቻን ወይም ኢራኖፎቢያን ተጠቅማች ስትል ከሳለች፡፡

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እሁድ እለት ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በመካከለኛው ምስራቅ ጉብኝታቸው ወቅት ያቀረቡትን ተከታታይ ውንጀላዎች ውድቅ ማድረጉን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡ ኢራን አሜሪካ “ኢራኖፎቢያ”ን ቀጣናዊ ውጥረት ለመፍጠር ተጠቅማለች የሚል ክስ አቅርባለች፡፡

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ናስር ካናኒ የባይደን ጉብኝት አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ “አሜሪካ በድጋሚ በቀጠናው ውጥረት እና ቀውስ ለመፍጠር ፈልጋለች”፡፡

 ባይደን ወደ መካከለኛው ምስራቅ ባደረጉት ጉብኝት ኢራን በተግባሯ ቀጣናውን እንዳይረጋጋ እያደረገች ነው የሚል ክስ ሰንዝረዋል፤ አሜሪካ “ቴህራን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እንዳታገኝ” እንደሚያደርጉ፣ ተናግረዋል፡፡

በመግለጫው ላይ ካናኒ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት መግለጫ መሠረተ ቢስ እና በቀጠናው ውስጥ ውጥረቶችን ከማስነሳት እና ከመፍጠር ፖሊሲ ጋር የተጣጣመ ነው ብለዋል ።

ቃል አቀባዩ አሜሪካ በክልሉ ሀገራት የውስጥ ጉዳይ ላይ በምታደርገው ተከታታይ ጣልቃ ገብነት፣ ተደጋጋሚ ወታደራዊ ወረራ እና ከፍተኛ የጦር መሳሪያ ሽያጭ በቀጣናው ውጥረት እና ቀውስ ለመፍጠር እየሞከረች ነው በማለት አውግዘዋል።

በመግለጫው ባለፉት አስርት አመታት የፍልስጤምን ህዝብ መብት ሲጣስ አሜሪካ ለእስራኤል የምታደርገውን “ጭፍን እና ያልተገደበ ድጋፍ” አውግዘዋል።

ካናኒ እንደተናገሩት ኢራን የኒውክሌር ቴክኖሎጅን አለምአቀፍ ህግን መሰረት ባደረገ መልኩ እንደምትጠቀም እና ማእቀቡ እንዲነሳ እንደምትጥር ገልጸዋል፡፡

ወደ ኒውክሌር መርሃ ግብሩ ስንመጣ ካናኒ የኢራንን የኒውክሌር ቴክኖሎጂን በሰላማዊ መንገድ የመጠቀም ስትራቴጂካዊ ፖሊሲ በአለምአቀፍ የህግ ማዕቀፍ ውስጥ ደግሟል እና ኢራን ማዕቀቡን ለማንሳት ድርድርዋን እንደምትቀጥል ተናግሯል።

ኢራን ለአካባቢው ፀጥታ፣ ሰላም፣ መረጋጋት እና ልማት ገንቢ ጥረቶችን ለማቅረብ ከአካባቢው ጎረቤቶች ጋር የሚደረገውን ውይይት እና ትብብር እንደምትቀበል በመግለጫው ተጠቅሷል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ከሰሞኑ እስራኤል እና ሳኡዲ አረቢያን ጨምሮ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ጉብኝት አድርገዋል፡፡ ባይደን በጉብኝታቸው ወቅት ኢራን ኒውከሌር እንዳይኖራት መስራት የሚለው ጉዳይ አንደኛው አጀንዳ ነበር፡፡

News today, Politics

ሳዑዲ አረቢያ የነዳጅ ምርቷን በቀን ወደ 13 ሚሊዮን በርሜል ለማሳደግ

ሳዑዲ አረቢያ የነዳጅ ምርቷን በቀን ወደ 13 ሚሊዮን በርሜል ለማሳደግ መወሰኗን አስታወቀች

ትናንት በተካሄደው የገልፍ ሀገራት-አሜሪካ የልማትና ደህንነት ጉባዔ ላይ ትኩረት ከነበሩት ውስጥ አንዱ የነዳጅ ጉዳይ ነበር።

የሳዑዲ ልዑል አልጋ ወራሽ መሃመድ ቢን ሰልማን፤ “ዘላቂ ልማትን ለማምጣት የአየር ንብረት ለውጥ ተግዳሮቶች ያገናዘበ ሚዛናዊ አካሄድ መከተልን ይጠይቃል” ብለዋል።

ከነዳጅ ጋር ተያይዞ ሊያጋጥም የሚችል እጥረትን ለመቅረፍም ሳዑዲ አረቢያ የነዳጅ ምርቷን በቀን ወደ 13 ሚሊዮን በርሜል ለማሳደግ መወሰኗንም አስታውቀዋል።

News today, Politics

የኢሚሬትስ ፕሬዝዳንት ለ1443 የሂጅራ ስኬት ለሳውዲ ንጉስ የደስታ መልእት አስተላልፈዋል

የኢሚሬትስ ፕሬዝዳንት ለ1443 የሂጅራ ስኬት ለሳውዲ ንጉስ የደስታ መልእት አስተላልፈዋል

የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ ሀገራቸው በመካከለኛው ምስራቅ ቀጠና መረጋጋት ላይ ዋነኛ አጋር ሆና እንደምተጥል አረጋገጡ።

የገልፍ ሀገራት-አሜሪካ የልማትና ደህንነት ጉባዔ በዛሬው እለት በሳዑዲ አረቢያ ጄዳህ ተካሂዷል።

በጉባዔው ላይ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን፣ የሳዑዲ ልዑል አልጋ ወራሽ መሃመድ ቢን ሰልማን እና የአረብ ኢሚሬትስ ፕሬዝዳንት መሃመድ ቢን ዛይድን ጨምሮ ሌሎችም የገልፍ ሀገራት መሪዎች ተሳትፈዋል።

በመካከለኛው ምስራቅ ቀጠና ለሩሲያ፣ ለቻይናና ለኢራን ክፍተት አንሰጥም- ፕሬዝዳንት ባይደን
የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን በጉባዔው ላይ ንግግር ያደረጉት፤ ሀገራቸው በቀጠናው ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር ለማሳደግ እንዲሁም አለም አቀፋዊ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን እና የጋራ ችግሮችን ለመጋፈጥ ፍላጎት እንዳላት አረጋግጠዋል።

አረብ ኢሚሬትስ በአለም አቀፍ ግንኙነት ላይ የምትከተለው ፖሊሲ በሚዛናዊነት ላይ የተመሰረተ እና ከአለም ሀገራት ጋር የጋራ የጥቅም መሰረትን በማስፋት ለሀገራዊ ልማትና ሰላምና መረጋጋት ግቦችን ማስፈን መሆኑን አስረድተዋል።

ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ እንዳሉት “በቀጠናችንም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ትልቅነት ለማንም የተሰወረ አይደለም” ያሉ ሲሆን፤ “እንዚህን ተግዳሮቶች ለመቋቋም እና የህዝቦቻችንን ምኞት ለማሳካት የጋራ ጥረቶችን ማጠናከር ይጠይቃል” ብለዋል።

የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ፕሬዝዳንት አክለውም ለ1443 የሂጅራ ስኬት ለሳዑዲ አረቢያው ንጉስ ሳልማን ቢን አብዱላዚዝ አል ሳኡድ የደስታ መልእክት አስተላልፈዋል።

ጉባዔውን በንግግር የከፈቱት የሳዑዲ ልዑል አልጋ ወራሽ መሃመድ ቢን ሰልማን፤ “ይህ የመሪዎች ጉባኤ ሀገሮቻችንን ከአሜሪካ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር አዲስ ምዕራፍ እንደሚከፍት ተስፋ እናደርጋለን” ብለዋል።

“ዘላቂ ልማትን ለማምጣት የአየር ንብረት ለውጥ ተግዳሮቶች ያገናዘበ ሚዛናዊ አካሄድ መከተልን ይጠይቃል” ያሉት መሃመድ ቢን ሰልማን፤ የአየር ንብረት ለውጥ ተግዳሮቶች ለመቋቋም የካርበን ልቀተን መቀነስ ልቀትን መሰረት ያደረገ አሰራር መከተላቸውን አስታውቀዋል።

News today, Politics

ጆ ባይደን በሳኡዲ

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የመካከለኛው ምስራቅ የባለ ግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤቷ አገር ሳኡዲ አረቢያ ገብተዋል። ጆ ምናልባት በዘመነ አሜሪካ የስልጣን ጊዜያቸው ነዳጅ ልመና የመጡ መሪ ያደርጋቸዋል። በዩክሬን ጦርነት ጉዳይ ሳኡዲ ከአፍሪካ አገሮች ጋር ተመሳሳይ ያለው አቋም የያዘች አገር ናት። የራሳችንን ጥቅም መሰረት አድርገን የምንራመድ እንጅ የማንንም ይሉይታ የምንቀበል አይደለንም ያለች አገር ናት ሳኡዲ። ሳኡዲ እንደበፈቱ አይነት
ለነ አሜሪካ የምትጨነቅ አገር አይደለችም።

News today, Politics

ኢትዮጵያዊነት የወለደው የታማኝነት እዳ

ኢትዮጵያዊነት የወለደው የታማኝነት እዳ
ለ40 አመት ትልቁን የመዲናን መስጊድ ሲጠብቁ የነበሩት ሸህ መሀመድ ሀቢብ አል አፋር መሞታቸውን የሳኡዲ መንግስት ዓሳውቋል።

በአረቡ አለም ውስጥ ኢትዮጵያዊነት
የታማኝነት እዳ ነው። በማንኛውም መንገድ ስማችን ሊጎድፍ ይችላል። በድህነታችን ላይ ሊሳለቁብን ይችላሉ። ሴት እህቶቻችን ለባርነት በመላካችን ሊንቁን ይችላሉ። በአንዳንድ አጥፊዎች ሊያሙን ይችላሉ። እነሱም የሚያምኑት አንድ የማይሸሸግ ነገር ግን አለን

ሙሉ ታሪካቸውን ሊንኩን ከፍታችሁ አንብቡ

ሱሌማን አብደላ

News today, Politics

ሰሜን ኮሪያ እውቅና ሰጠች

ሰሜን ኮሪያ በሩሲያ ለሚደገፉት ተገንጣይ ግዛቶች እውቅና ሰጠች

እርምጃው ለሁለቱ በሩሲያ ለሚደገፉ ተገንጣይ ግዛቶች ማለትም ለዶንቴስክን እና ለሉሃንስክ ግዛቶች የሀገርነት እውቅና በመስጠት ከሩሲያ እና ሶሪያ ቀጥሎ ሰሜን ኮሪያን 3ኛ ሀገር ያደርጋታል፡፡

News today, Politics

ጆ-ባይደን የእስራኤል እና የፍልስጤም ግጭትን የማርገብ ጉዳይ

ጆ-ባይደን የእስራኤል እና የፍልስጤም ግጭትን የማርገብ ጉዳይ ላይ ቅድሚያ ሰጥተው እንደሚሰሩ ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ-ባይደን የእስራኤል ጉብኝታቸውን ዛሬ ጀምረዋል።

ጆ ባይደን በአውሮፕላን ማረፊያ በተሰናዳው መድረክ ባደረጉት ንግግር “በእኔ እይታ አዲስ ባይሆንም የእስራኤላውያንም ሆነ የፍልጤማውያን የእኩልነት ነፃነት፣ ብልጽግና እና ዲሞክራሲ የወደፊት እጣ ፈንታ ለማረጋገጥ በሚጠቅመው ጉዳይ ላይ እንወያያለን” ብለዋል።

News today, Politics

ኢራን አዳዲስ ዴሮኖቿን ለሩሲያ የመስጠት ፍላጎት አላት ስትል አሜሪካ ከሰሰች

ምዕራባውያን ስጋት የሆኑት ሩሲያ እና ኢራን

ኢራን ለሩሲያ ድሮኖችን ለመስጠት እቅድ አላት ስትል አሜሪካ አስጠነቀቀች

ኢራን በጦርነት ላይ ላለችው ሩሲያ ሰው አልባ የጦር አውሮፕላኖችን (ድሮን) ልትሰጥ ነው ሲሉ አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ ባለስልጣን አስጠነቀቁ።

ኢራን ሩሲያ በዩክሬን ምድር ለምታደርገው ወታደራዊ ዘመቻ ድጋፏን ለሩሲያ ስትሰጥ ቆይታለች ያሉት ባለስልጣኑ አሁን ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮኖች) ለሩሲያ ልትሰጥ መሆኗን ደርሰንበታልም ብለዋል።
የKe alemi zuriya-ቤተሰብ ይሁኑ

👉የke alemi zuriya ሌሎች አድራሻዎች
instag:https://instagram.com/kealemizuriya
twitter:https://twitter.com/KeAlemiZuriya
YouTube:https://bit.ly/kealemizuriya
Telegram:https://t.me/KeAlemiZuriya
website:https://kealemizuriya.data.blog/
ቤተሰብ ስለሆኑ እናመሰግናለን

News today, Politics

ፑቲን ኢራን ሊጎበኙ ነው

ፑቲን ኢራንን ሊጎበኙ ነው

የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ኢራንን ሊጎበኙ ነው።
ፑቲን ቴህራንን የሚጎበኙት በቀጣይ ሳምንት እንደሆነ የኢራን ፓርላማ የኢኮኖሚ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ተናግረዋል።

የKe alemi zuriya-ቤተሰብ ይሁኑ
👉የke alemi zuriya ሌሎች አድራሻዎች
instag:https://instagram.com/kealemizuriya
twitter:https://twitter.com/KeAlemiZuriya
YouTube:https://bit.ly/kealemizuriya
Telegram:https://t.me/KeAlemiZuriya
website:https://kealemizuriya.data.blog/
  ቤተሰብ ስለሆኑ እናመሰግናለን

News today, Politics

የባይደን የሳኡዲ ጉበኝት

ፕሬዝዳንት ባይደን በሳኡዲ አረቢያ የጉብኝት እቅዳቸው ላይ የተነሳውን ትችት ተከላከሉ

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን በሳኡዲ አረቢያ የጉዞ እቅዳቸው ላይ የተነሳውን ትችት ተከላክለዋል፤ በሳኡዲ ቆይታቸው የመብት ጉዳይ አጀንዳ እንደሚሆንም ተናግረዋል።

ንጉስ ሳለማን በፈረንጆቹ 2018 ከተገደለው የዋሽንግቸን ፖስቱ ጋዜጠኛ ጀማል ካሾግጂ ግድያ አሉበት ተብሎ ይታመናል።

News today, Politics

የአለማችንን ልዕል ሀያል ወንዝ ይዞ በጓሮ አትክልት መብሸቅ እራስን ማሳነስ ነው።

የአለማችንን ልዕል ሀያል ወንዝ ይዞ በጓሮ አትክልት መብሸቅ እራስን ማሳነስ ነው።
.
ባለፈው ሳምንት በሳኡዲ የሪያድ አምባሳደር ሌንጮ ባቲና አብረዋቸው ያሉ ዲፕሎማቶች ከሳኡዲ የውጭ
ኢንቨስትመንት ክፍል አመራሮች ጋር ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትን የኢንቨስትመንት አማራጮች በተመለከተ ምክክር አድርገው ነበር። ታዲያ እኒህ የሳኡዲ ባለስልጣናት እናተኮ አላወቃችሁበትም እንጅ አላህ
ሁሉንም ነገር አሟልቶ ሰቷችሁ ነበር፣ በቀላሉ የከብት መኖ ብቻ በመሸጥ ሀብታ ትሆናለችሁ ሌላውን ተውትና ግን አላወቃችሁበትም አሉ።
.
ኢትዮጵያ ስትባል መናጢ ደሀ ችጋራም ምንም የለሌላት ምድረ በዳ የምትመስለው ብዙ ኢትዮጵያዊ አለ። አገራቸውን በመሳደብ የተጠመዱም ፖለቲከኞች አሉ። ውጩ አለም ግን ምነው የኛ ሆና በሆን እያለ እንዲህ ይጎመጃል። ታዲያ ይህ ስሜት ያላደረበት የአገሬ ፖለቲከኛ አሁንም ድረስ የኢትዮጵያን ገናናነት ከማሰብ ይልቅ ሰፈሬ ትቅደም እያለ ይዘምራል። ባህር አቋርጦ፣ አህጉር የነቀነቀው ቼ ጉቬራ በተወለደባት አለም አፍሪካ ውስጥ ግን
እንዲህ አይነት ፖለቲከኛ ተወልዷል

News today, Politics

ቱርክዬ በሽብር የተከሰሱ ኩርዶች ተላልፈው እንዲሰጧት

ቱርክዬ በሽብር የተከሰሱ ኩርዶች ተላልፈው እንዲሰጧት ለስዊድን ያቀረበችው ጥያቄ ውድቅ ሆነ

አንካራ 70 የኩርድ ታጣቂዎችን እንድትሰጣት ስዊድንን ብትጠይቅም ተቀባይነት አለማግኘቷ ተገልጿል፡፡
ሆኖም ስዊድን እና ፊንላንድ የአንካራን ጥያቄዎች የማያሟሉ ከሆነ የኔቶ አባልነታቸው ጥያቄ ውስጥ እንደሚገባ ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን አስጠንቅቀዋል፡፡
ስዊድን እና ፊንላንድ የኔቶ አባል ለመሆን ተፈራርመዋል፡፡ አባልነታቸውን ተቃውማ የነበረችው ቱርክዬም የኋላ ኋላ ጥያቄያቸውን ተቀብላለች፡፡
አሁን ግን ጥያቄዎቿ ካልተሟሉ ወደ ድጋፏን ልታነሳ እንደምትችል ነው አንካራ የዛተችው፡፡