News today, Politics, social life, Technology

በ11 የአለም ዋንጫዎች ላይ የታደሙት ብራዚላዊ

የመጀመሪያ የአለም ዋንጫ ጨዋታን በአርጀንቲና በ1978 የተመለከቱት ዳኔል ስብሩዚ በኳታርም የአለም ዋንጫ ጨዋታዎችን ተከታትለዋል

“የአለም ዋንጫን መመልከት ከአዳዲስ ባህልና ልምድ ጋር መተዋውቅ ነው ፤ በ2026ቱ የአለም ዋንጫ ለመታደምም ዝግጁ ነኝ” ብለዋል

11 የአለም ዋንጫዎችን የተመለከቱት ብራዚላዊ በድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ስማቸውን ማስፈር ችለዋል።

ዳኔል ስብሩዚ የተባሉት የ76 አመት አዛውንት የሳኦሎ ከተማ ነዋሪ ናቸው።

ስብሩዚ በ1978 ወደ አርጀንቲና በማቅናት የመጀመሪያ የአለም ዋንጫ ጨዋታን ከተመለከቱ ወዲህ አለምን በኳስ ምክንያት ዞረዋል።

የዘንድሮውን የኳታር የአለም ዋንጫ ለመታደምም ዶሃ ገብተው ሰንብተዋል።

የ76 አመቱ አዛውንት በዶሃ 11ኛ የአለም ዋንጫ ጨዋታን ሲመለከቱም የአለም የድንቃድንቅ መዝገብ ክብረወሰን ይዘዋል በሚል የምስክር ወረቀት ሰጥቷቸዋል።

የአለም ዋንጫን መመልከት ከአዳዲስ ባህልና ልምድ ጋር መተዋውቅ ነው የሚሉት ስብሩዚ ፤ የአለም ዋንጫ ከመልከ ብዙ ተሰጥኦ ባለቤቶች ጋር የሚያገናኝ መድረክ መሆኑን አንስተዋል።

ከአርጀንቲና እስከ ኳታር አለም ዋንጫን ለመመልከት ሲጓዙም የብራዚልን ባህልና ወግ ሲያስተዋውቁ እንደነበር ተናግረዋል።

ባለፉት 44 አመታት በተለያዩ አልባሳት አጊጠው ብራዚልን እየደገፉ የሳኦ ፖሎን ባህል በስፋት ያስተዋወቁት ስፖርት አፍቃሪ፥ የአለም ዋንጫን በስታዲየም ከመመልከት የሚያስቆመኝ ሞት ብቻ ነው እያሉ ነው።

አሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ በጋራ በሚያዘጋጁት የ2026 የአለም ዋንጫ ለምታደምም ፍላጎታቸውን ገልጸዋል።

በዚህም በራሳቸው የተያዘውን ክብረወሰን ለማሻሻል ተስፋ አድርገዋል።

News today, Politics, social life, Technology

አርጀንቲና የኳታሩን የአለም ዋንጫ ያነሳችበት ጨዋታ በምስል

አርጀንቲና ለ3ኛ ጊዜ የዓለም ዋንጫን አንስታለች

የአርጀንቲና ብሄራዊ ቡድን

አርጀንቲና በመለያ ምት 4 ለ 2 ፈረንሳይን አሸንፋለች

በሉሳይል ስታዲየም የተደረገው ልብ አንጠልጣይ ፍልሚያ በአርጀንቲና አሸናፊነት ተደምድሟል።

አርጀንቲና ሶስት ጊዜ መርታ አቻ በሆነችበት ምሽት ሌዮኔል ሜሲ ሁለት ጎሎችን አስቆጥሯል።

ውሃ ሰማያዊ እና ነጭ ለባሾቹ በመጀመሪያው አጋማሽ 2 ለ 0 እየመሩ ቢወጡም ፈረንሳይ በኪሊያን ምባፔ የ80 እና 81ኛ ደቂቃ ሁለት ጎሎች አቻ ሆናለች።

በተጨማሪ 30 ደቂቃውም ሜሲ ሶስተኛውን ጎል ለሀገሩ ቢያስቆጥርም የፈረንሳዩ የ23 አመት ኮከብ ኪሊያን ምባፔ ባስቆጠራት ሶስተኛ ጎል ጨዋታው በመለያ ምት ተጠናቋል። በዚህም አርጀንቲና 4 ለ 2 በሆነ የፍጹም ቅጣት ምት ጎል አሸናፊ ሆናለች።

ሊዮኔል ሜሲ ከ36 አመት በፊት ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና ያሳካውን ክብር በደገመበት ምሽት የብራዚላዊውን ፔሌ የጎል አስቆጣሪነት ክብር ማሻሻል ችሏል።

የ35 አመቱ ሜሲ በ26 የአለም ዋንጫ ጨዋታዎች ተሰልፎ 13 ጎሎችን በማስቆጠሩም በብራዚላዊው ፔሌ ተይዞ የቆየውን ክብረወሰን ማሻሻል ችሏል።

አርጀንቲና በዛሬው የሉሳይል ስታዲየም ፍልሚያ ድል ማድረጓን ተከትሎ በመጀመሪያው የምድብ ጨዋታ ተሸንፋ (በሳኡዲ አረቢያ) ዋንጫውን በመውሰድ ስፔን በ2010 የያዘችውን ሪከርድ ተጋርታለች።

የላቲን አሜሪካዋ ሀገር ፈረንሳይን በመርታት ሶስተኛ ዋንጫዋን አንስታለች።

አርጀንቲና በ1978 ፣ 1986 እና በኳታር የዓለም ዋንጫን ወስዳለች።

News today, social life

ቁጥሮች የዓለም ዋንጫ አዘጋጅ ስለሆነችው ትንሿ ሀገር ኳታር ምን ይላሉ?

የአለም ዋንጫን የምታዘጋጀው ኳታር ስፋት የለንደን ከተማን አታክልም

ኳታር ዶሃ

ከ3 ሚሊየን ገደማ የሚኖርባ ሲሆን፤ የኳታር ዜጎች ከ300 ሺህ አይበልጡም

ኳታር ከ200 ቢሊየን ዶላር ወጪ ያደረገችበት ግዙፉ የዓለም የእግር ኳስ መድረክ የ2022 የዓለም ዋንጫ አዘጋጅታለች።

ውድ የዓለም ዋንጫን ስላዘጋጀቸው ትንሿ ሀገር ኳታር ቁጥሮች ምን ይላሉ?

ኳታር በፈረንጆቹ 1971 ከእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ነፃ ወጥታለች። የአልታኒ ቤተሰብ ከ1825 ጀምሮ ኳታርን እየመራ ነው።

ኳታር 3 ሚሊየን የሚጠጋ ህዝብ ይኖርባታል። ከአጠቃላይ ነዋሪው ግን የሀገሪቱ ዜጋ ከ300 ሺህ አይበልጥም። ከ100 በላይ ሀገራት ዜጎች ይኖሩባታል።

ከ80 በላይ ሀገራት ያለቪዛ መግባት ይችላሉ፤ ይህም ከመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት አንደኛ ከአለም 8ኛ ደረጃን እንድትይዝ አድርጓታል።

97 በመቶው የተማረ ህዝብ ያለባት ሲሆን፥ የሴቶች እጥረት ግን በስፋት ይስተዋልባታል፤ ከጠቅላላው ህዝብ 24 ነጥብ 7 በመቶው ብቻ ነው ሴት።

ኳታር ወንጀል ከማይፈፀምባቸው ሀገራትም ከ153 ሀገራት 31ኛ ደረጃን በመያዝ ሰላማዊነቷ ተመስክሮላታል።

በየብስ ከሳኡዲ አረቢያ ጋር ብቻ የምትዋሰነው ሀገር ስፋቷ ለንደንን አያክልም፤ የአሜሪካዋን ኒውዮርክ ከተማም 10 በመቶ ብቻ ነው የምትሸፍነው፤ 160 ኪሎ ሜትር ከሰሜን እስከ ደቡብ 80 ኪሎሜትር ከምስራቅ ወደ ምዕራብ ትረዝማለች።

አራት ማዕዘኗ ሀገር ደሴት ሳይሆኑ ጠባብ ከሆኑ ሀገራት 11ኛ ደረጃ መያዟንም መረጃዎች ያመላክታሉ። በአሳ ሀብቷ የምትታወቀው ዶሃ የተፈጥሮ ጋዝና የነዳጅ ክምችቷ የእድገት ግስጋሴዋን አፋጥኖታል።

ከሩስያና ኢራን በመቀጠል 3ኛዋ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት ያለባት ኳታር ለተከታታይ አመታት ፈጣን እድገት አስመዝግባለች።

የሀገሪቱ ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ወይም (ጂ ዲ ፒ) 216 ቢሊየን ደርሷል። ከ62 ሺ ዶላር በላይ የደረሰው የነፍስ ወከፍ ገቢም ከአለማችን ባለጠጋ ሀገራት ከፊት አሰልፏታል።

229 ቢሊየን ዶላር ወጪ አድርጋ በ8 ስታዲየሞች ያዘጋጀችውን የአለም ዋንጫ ለማቅረብም ስአታት ቀርተዋል

News today, Politics, social life

የሩሲያን ጦር ምልክት በተሸከርካሪው ላይ የቀረጸው ጀርመናዊ በ4 ሺህ ዩሮ ተቀጣ

የሀምቡርግ ከተማ ነዋሪ የሆነው ይህ ግለሰብ የሩሲያን ጦር ደግፏል በሚል የገንዘብ ቅጣት ተጥሎበታል

የሩሲያ ጦር በዩክሬን ለልዩ ዘመቻ በሚል ወደ ዩክሬን ከገባ ስምንት ወር ሆኖታል

የሩሲያን ጦር ምልክት በተሸከርካሪው ላይ የቀረጸው ጀርመናዊ በ4 ሺህ ዩሮ ተቀጣ።

የጀርመኗ ሀምቡርግ ከተማ ነዋሪ የሆነ አንድ ግለሰብ የግሉ ተሸከርካሪ ላይ በነጭ ቀለም የሩሲያ ጦር ምልክት የሆነውን የዜድ (“Z”) አርማ ቀርጿል ተብሏል።

ግለሰቡ ከስምንት ወራት በፊት ለልዩ ዘመቻ በሚል ወደ ዩክሬን ግዛት የገባውን የሩሲያ ጦር ደግፏል በሚል በሀምቡርግ ከተማ ፍርድ ቤት ክስ ተመስርቶበታል።

ይህ ግለሰቡ ባሳለፍነው መጋቢት ወር ላይ በነጭ ወረቀት ላይ የዜድ ምልክትን በደማቁ በመጻፍ በአደባባዮች ሲያሽከረክር እንደነበርም ተገልጿል።

የግለሰቡ ተደጋጋሚ ድርጊት ሩሲያ በዩክሬን እየፈጸመች ያለውን ጦርነት ለመደገፍ ያደረገው ጥረት ነው ያለው የሀምቡርግ አቃቢ ህግ ለማስተማሪያነት በሚል ግለሰቡ 4 ሺህ ዮሮ እንዲከፍል ቅጣት እንደተጣለበት የጀርመን ድምጽ ዘግቧል።

ሩሲያ በዩክሬን እያደረገች ላለው ጦርነት የህዝብ ግንኙነት ስራ ለመስራት ወይም ድጋፍ ለማግኘት በሚል የጦር ተሸከርካሪዎቿ የዜድ ምስልን ተጠቅመው እንዲንቀሳቀሱ አድርጋለች።

በሞስኮ እና በተወሰኑ ሀገራት የዜድ ምስል የተጻፈባቸው ምልክቶች በአደባባዮች ላይ መታየት ጀምረውም የነበረ ሲሆን በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይም ለተወሰኑ ቀናት በስፋት ተሰራጭተዋል።

ጀርመን የትኛውም ዜጋዋ የሩሲያ ጦር ምልክት የሆነው ይህ የዜድ ምስልን በአደባባይ ይዞ መገኘት አልያም ማሰራጨት ዓለም አቀፍ ወረራን መደገፍ ስለሚሆን ድርጊቱን ከልክላለች።

የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ስምነተኛ ወሩ ላይ የሚገኝ ሲሆን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዩክሬናዊያን ወደ ጎረቤት ሀገራት ሲሰደዱ በቢሊዮን የሚቆጠር መሰረተ ልማት ደግሞ መውደሙን የተመድ ሪፖርት ያስረዳል።

News today, social life

የብሪታንያው ፓውንድ በ37 ዓመታት ታሪክ ውስጥ ዝቅተኛ የመግዛት አቅም አስመዘገበ

የአውሮፓ ህብረት መገበያያ ዩሮ በ20 ዓመት ታሪክ ውስጥ ከዶላር በታች ተመንዝሯል

የሩሲያው ሩብል ደግሞ ከሰባት ዓመት በኋላ መነቃቃት አሳይቷል ተብሏል

የብሪታንያው ፓውንድ በ37 ዓመታት ታሪክ ውስጥ ዝቅተኛ የመግዛት አቅም አስመዘገበ፡፡

የአሜሪካ ዶላር፣ የአውሮፓ ህብረት ዩሮ፣ የብሪታንያ ፓውንድ ስተርሊንግ ፣ የቻይናው ዩዋን እና የሩሲያው ሩብል በዓለማችን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ውስጥ ዋነኛ መገበያያ ገንዘቦች ናቸው፡፡

ከእነዚህ መገበያያ ገንዘቦች ጀርባ ሀገራቱ ያሉ ሲሆን የዓለምን ኢኮኖሚ ለመቆጣጠርም የንግድ ፉክክሩ በእነዚሁ ሀገራት መካከል እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ዩክሬን የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ወይም ኔቶን እቀላቀላለሁ ማለቷን ተከትሎ ከሩሲያ ጋር ወደ ጦርነት ካመራች በኋላ የዓለም ንግድ እና ዲፕሎማሲ መዛነፍ ገጥሞታል፡፡

በአሜሪካ አስተባባሪነት በሩሲያ ላይ የተጣለው ማዕቀብ እና ሩሲያ በማዕቀቡ ላለመጎዳት የወሰደቻቸው የአጸፋ እርምጃዎች በዓለም ምግብ እና ነዳጅ ላይ ተከታታይ የዋጋ ጭማሪ እንዲደረግ አስገድዷል፡፡

በዚህም ምክንያት የአውሮፓ ህብረት ሀገራት መካከል የጋራ መገበያያ የሆነው ዩሮ ከሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት በፊት ከዶላር በላይ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ቅናሽ አሳይቷል፡፡

ከጦርነቱ በፊት አንድ ዩሮ ከአሜሪካ ዶላር ጋር ሲነጻጸር የዜሮ ነጥብ 14 ብልጫ የነበረው ሲሆን በአሁኑ ወቅት አንድ ዩሮ ከዶላር ጋር ሲነጻጸር የዜሮ ነጥብ 33 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል፡፡

ይህም ዩሮ ከአሜሪካ ጋር ሲነጻጸር የመግዛት አቅሙ ከ20 ዓመት በኋላ ቅናሽ ማሳየቱ ሲገለጽ ለዩሮ አቅም መዳከም ደግሞ በሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ምክንያት በሞስኮ ላይ ማዕቀብ መጣሉን ተከትሎ በአውሮፓ ያጋጠመው የነዳጅ እጥረት እንደሆነ ተገልጿል፡፡

የብሪታንያ ፓውንድ ስተርሊን ደግሞ በ37 ዓመት ታሪክ ውስጥ የታየ ታሪካዊ የመግዛት አቅም መዳከም እንደሆነ ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡

የብሪታንያ ብሄራዊ ስታስቲክስ ቢሮ እንዳለው ከሆነ አንድ ፓውንድ በ1 ነጥብ 14 ዶላር እየተመነዘረ ሲሆን ይህም ከፈረንጆቹ 1985 ጀምሮ ዝቅተኛው ሆኖ ተመዝግቧል ተብሏል፡፡

ፓውንድ ስተርሊን ከአሜሪካ ዶላር ጋር ሲነጻጸር የ15 በመቶ ብልጫ እንዲሁም ከዩሮ ጋር ደግሞ የ12 በመቶ ብልጫ እንደተወሰደበት በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡

የሩሲያው ሩብል ደግሞ ከፈረንጆቹ 2015 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከዶላር ጋር ያለውን ልዩነት ያጠበበ ሲሆን ሞስኮ ነዳጇን በሩብል ለመሸጥ መወሰኗ እና ለእስያ ሀገራት ከፍተኛ መጠን ያለው ነዳጅ መሸጧ ለመገበያያ ገንዘቧ ማገገም ዋነኛ ምክንያቶች እንደሆኑ ተጠቅሷል፡፡

አሁን ላይ አንድ የአሜሪካን ዶላር በ60 ነጥብ 8 የሩሲያ ሩብል በመመንዘር ላይ የሚገኝ ሲሆን በአውሮፓ አሁንም የነዳጅ እጥረቱ የቀጠለ በመሆኑ የዩሮ እና ፓውንድ ስተርሊንግ አቅም እየቀነሰ ሊሄድ እንደሚችል ተገምቷል፡፡ 

News today, social life

የአውሮፓ ሀገራት ለኑሮ ውድነት ድጎማ 300 ቢሊየን ዩሮ ወጪ ማድረጋቸው ተገለጸ

ሩሲያ የአውሮፓ ህብረት የጣለብንን ማዕቀብ ሳያነሳ ነዳጅ አልክም ብላለች

ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ጣልያ፣ ስፔን እና ግሪክ በነዳጅ ዋጋ መናር ክፉኛ የተጎዱ ሀገራት ናቸው ተብሏል

የአውሮፓ ስድስት ሀገራት ለኑሮ ውድነቱ ድጎማ 300 ቢሊየን ዩሮ ወጪ ማድረጋቸው ተገለጸ።

የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ሰባት ወራት ሊሆነው ጥቂት ቀናት የቀሩት ሲሆን ጦርነቱን ተከትሎ የዓለም ነዳጅ እና ምግብ ዋጋ በየዕለቱ እየጨመረ ይገኛል።

ሩሲያ ለአውሮፓ ሀገራት 40 በመቶ የነዳጅ ፍላጎትን የምትሸፍን ቢሆንም ጦርነቱን ተከትሎ ነዳጅ ወደ አውሮፓ እንዳትልክ ማዕቀብ ተጥሎባታል።

በሩሲያ ነዳጅ ላይ ጥገኛ የሆኑት አውሮፓውያን ደግሞ ታይቶ በማይታወቅ የኢኮኖሚ አለመረጋጋት እየተጎዱ ሲሆን የዜጎቻቸውን ጥያቄ ለመመለስ የተለያዩ አማራጮችን በመከተል ላይ ናቸው።

ስድስት የአውሮፓ ሀገራት ብቻ እስካሁን ለሀይል ድጎማ በሚል ያወጡት ገንዘብ 300 ቢሊዮን ዩሮ እንደደረሰ ሮይተርስ ዘግቧል።

እነዚህ ሀገራት ከዓመታዊ መጠባበቂያ በጀታቸው ላይ 23 በመቶውን ለነዳጅ ድጎማ ያዋሉት ሲሆን ጉዳቱ ከዚህም በላይ ሊሆን እንደሚችል ተገልጿል።

የጀርመን መንግስት ካሳለፍነው የካቲት ወር ጀምሮ ለነዳጅ ድጎማ ያወጣው ወጪ 95 ቢሊዮን ዩሮ ሲደርስ ከአውሮፓ ሀገራት በጦርነቱ ከተጎዱ ሀገራት መካከል ዋነኛዋ ሆናለች።

ሌላኛዋ በነዳጅ ዋጋ መናር ከተጎዱ ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው ፈረንሳይ ስትሆን 67 ቢሊዮን ዩሮ ለነዳጅ ድጎማ ወጪ አድርጋለች ተብሏል፡፡ ይህም በዓመታዊ ምርቷ ላይ የ5 በመቶ ጉድለት እንዲመዘገብ አድርጓል ተብሏል።

ነዳጅን ተጠቅመው ለህብረተሰቡ የተለያዩ አገልግሎቶችን ለሚሰጡ ተቋማት የነዳጅ ድጎማ በማድረጓ 52 ቢሊዮን ዩሮ ወጪ ያደረገችው ሌላኛዋ አውሮፓት ሀገር ደግሞ ጣልያን ናት።

ደቡብ አውሮፓዊቷ ስፔንም ለነዳጅ ድጎማ በሚል 30 ቢሊዮን ዩሮ ወጪ ያደረገች ሲሆን በባንኮች እና ግዙፍ የሀይል ልማት ተቃማት ላይ የግብር ቅነሳ ማድረጓንም አስታውቃለች።

ሆላንድ፣ ግሪክ እና ሆላንድም ዜጎቻቸው በነዳጅ ዋጋ ጭማሪ እንዳይጎዱ በሚል እያንዳንዳቸው ከ6 እስከ 10 ቢሊዮን ዩሮ ወጪ አድርገዋልም ተብሏል።

News today, social life

በታይዋን የተከሰተው ጠንካራ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ጉዳት አስከተለ

የመሬት መንቀጥቀጡ በዋና ከተማዋ ታያፒ ጨምሮ በመላው ታይዋን ተሰምቷል ተብሏል

የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቨይ የተከሰተውን መሬት መንቀጥቀጥ መጠኑ 7 ነጥብ2 እና ጥልቀቱ 10 ኪ.ሜ መሆኑን ገልጿል

በታይዋን የተከሰተው ጠንካራ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ጉዳት አስከተለ

በጃፖን በሬክተርስኬል መጠኑ 6 ነጥብ 8 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ተከስቶ በ146 ሰዎች ላይ ጉዳት አድርሷል።

የታይዋን አየር ንብረት ቢሮ እንደገለጸው ህዝብ ተራርቆ በሚኖሮበት በደቡብ ምስራቅ ታይዋን የተከሰተው መሬት መንቀጥቀጥ ባቡሮች እንዲገለበጡ፣ የስቶር መደርደሪያዎች እንዲደረመሱና መንገዶች እንዲዘጉ ምክንያት ሆኗል።

ቢሮው የመሬት መንቀጥቀጡ መነሻ ታይተን ግዛት ሲሆን በአካባቢው የደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ ግን ጉዳት አላደረሰም ብሏል።

የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቨይ በትናንትናው እለት የተከሰተውን መሬት መንቀጥቀጥ መጠኑ 7ነጥብ2 እና ጥልቀቱ 10 ኪ.ሜ መሆኑን ገልጿል።

የታይዋን የእሳት ዲፖርትመንት በአደጋው የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን እና 146 ሰዎች መጎዳታቸውን አስታውቋል።

የታይዋን የሬይል ዋይ አስተዳደር ደግሞ ስድስት ባቡሮች መስመራቸውን ስተው መግልበጣቸውን እና በሰው ላይ ጉዳት አለመድረሱን ገልጿል።

በአደጋው በተዘጋው መንገድ ምክንያት በተራራማ አካባቢዎች መንገድ የተዘጋባቸውን 600 ሰዎች ለማውጣት ጥረት ላይ ናቸው።

የአሜሪካው የፖስፊክ የሱናሚ ማስጠንቀቂያ ማእከል ከመንቀጥቀጡ አደጋው በኋላ ማስጠንቀቂያ አውጥቶ የነበረ ቢሆንም ቆይቶ አንስቶታል።

የመሬት መንቀጥቀጡ በዋና ከተማዋ ታያፒ ጨምሮ በመላው ታይዋን ተሰምቷል ተብሏል።

በፈረንጆቹ 2016 በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ 100 ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።

News today, social life

ግብጽ በስዊዝ ካናል ላይ የ15 በመቶ የክፍያ ጭማሪ ማድረጓን አስታወቀች

ግብጽ ከስዊዝ ካናል በዓመት ሰባት ቢሊዮን ዶላር ገቢ እያገኘች ነው

የዋጋ ጭማሪው ከመጭው ጥር ወር ጀምሮ የተገበራል ተብሏል

ግብጽ በስዊዝ ካናል ላይ የ15 በመቶ የክፍያ ጭማሪ ማድረጓን አስታወቀች።

ሰሜን አፍሪካዊቷ ግብጽ ከቀጣዩ ጥር ወር ጀምሮ በስዊዝ ካናል በሚያልፉ መርከቦች ላይ የዋጋ ጭማሪ ማድረጓን አስታውቃለች።

ሮይተርስ የስዊዝ ካናል ሊቀመንበርን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ከሆነ ግብጽ በእቃ ጫኝ መርከቦች ላይ የ15 በመቶ በትራንዚት እና በጎብኚዎች መርከቦች ላይ ደግሞ የ10 በመቶ የአገልግሎት ክፍያ ተጨምሯል።

የግብጽ ዋነኛ የገቢ ምንጭ የሆነው የስዊዝ ካናል በፈረንጆቹ 1869 ዓመት ጀምሮ ለአገልግሎት ክፍት የሆነ ሲሆን ይህ የመርከቦች መጓጓዣ መስመር በቀን 50 መርከቦችን በማጓጓዝ ላይ ይገኛል።

ስዊዝ ካናል አገልግሎት መስጠት ከጀመረ 153 ዓመት የሞላው ሲሆን ግብጽ ከስዊዝ ካናል ባለፉት 12 ወራት ውስጥ ሰባት ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷን ገልጻለች።

ስዊዝ ካናል ከ153 ዓመት በፊት ሜድትራኒያን ባህርን እና ህንድ ውቂያኖስን በማገኛኘት በአውሮፓ እና እስያ መካከል የሚደረገውን የባህር ላይ ጉዞ በማሳጠር ዘመናዊ የባህር ትራንስፖርት ያቀላጥፋል፡፡

በወቅቱ የግብጽ መሪ የነበሩት ካዲቭ እስማኤል ፓሻ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት የጀመረው ይህ የመርከቦች መተላለፊያ መስመር ግንባታው 10 ዓመታትን ፈጅቷል።

በዓመት 300 ሚሊዮን ቶን እቃዎች የሚተላለፉበት ስዊዝ ካናል የአገልግሎት መጠኑን ለማስፋት ግብጽ በየጊዜው የተለያዩ ማሻሻያዎችን አድርጋለች።

የአሁኑ የግብጽ ፕሬዝዳንት አልሲሲ በፈረንጆቹ 2014 ላይ በስዊዝ ካናል ላይ የተደረገውን የ8 ቢሊዮን ዶላር የማስፋፋያ ግንባታ መመረቃቸው አይዘነጋም።

ስዊዝ ካናል በተሰራለት የማስፋፊያ ግንባታ መሰረት አሁን ላይ ስፋቱ 61 ሜትር በ312 ሜትር ላይ የደረሰ ሲሆን ከአንድ ዓመት በፊት ከቻይና የመጣ ኮንቴይነሮችን የጫነች እቃ ጫኝ መርከብ መተላለፊያ መስመሩን ለአንድ ወር ዘግታ የ100 መርከቦችን እንቅስቃሴ በመግታት የዓለምን ንግድ ማስተጓጎሏ ይታወሳል።

News today, social life

የቆጠቡትን ገንዘብ ማግኘት ያልቻሉ ሊባኖሳዊያን ባንኮችን በጦር መሳሪያ እያስፈራሩ ነው

ሊባኖስ በገጠማት የኢኮኖሚ ቀውስ ምክንያት ባንኮች ለደንበኞቻቸው ገንዘባቸውን መመለስ አልቻሉም

የሊባኖስ ባንኮች የፊታችን ሰኞ ጀምሮ በደህንነት ምክንያት ስራ ለማቆም ወስነዋል

የቆጠቡትን ገንዘብ ማግኘት ያልቻሉ ሊባኖሳዊያን ባንኮችን በጦር መሳሪያ እያስፈራሩ ነው፡፡

የመካከለኛዋ ምስራቅ ሀገር ሊባኖስ በገጠማት የኢኮኖሚ ቀውስ ምክንያት ዜጎች በባንክ የቆጠቡትን ገንዘብ ማግኘት አልቻሉም፡፡

ሊባኖስ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ያጋጠማት ሲሆን የሀገሪቱ መገበያያ ገንዘብም የመግዛት አቅሙ መሽመድመዱን ተከትሎ ዜጎች ለከፍተኛ ችግር ተዳርገዋል፡፡

አብዛኛው የሀገሪቱ ዜጎች ፍጆታ ከውጭ ሀገራት የሚገቡ በመሆኑ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ኢኮኖሚውን ወደ ከፋ አለመረጋጋት አስገብቶታል፡፡

በዚህም ምክንያት ባንኮች ከደንበኞቻቸው የተቆጠበ ገንዘብን መስጠት አለመቻላቸውን ተከትሎ የሀገሪቱ ዜጎች የጦር መሳሪያ በድብቅ እያስገቡ የባንክ ሰራተኞችን እያስፈራሩ እንደሆነ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

በየጊዜው የጦር መሳሪያ እየያዙ ወደ ባንኮች የሚያመሩ ዜጎች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ ባንኮች ከፍተኛ የደህንነት ችግር እንደገጠማቸው ተጠቅሷል፡፡

ለአብነትም በትናንትናው ዕለት አንዲት እንስት የካንሰር ህክምናዋን በቱርክ እየተከታተለች ለምትገኝ እህቷ ገንዘብ መላክ በመፈለግ ወደ ባንክ ብትሄድም ባንኩ ሊያስተናግዳት ባለመቻሉ የጦር መሳሪያ ለመጠቀም መገደዷን ተናግራለች፡፡

በዛሬው ዕለትም በአምስት የሊባኖስ የተለያዩ ቦታዎች የባንክ ደንበኞች የጦር መሳሪያ ተጠቅመው ገንዘባቸውን ከባንኮች ለመውሰድ መሞከራቸው ተገልጿል፡፡

የደንበኞቻቸው የጦር መሳሪያ እየያዙ መምጣት ያሳሰባቸው የሀገሪቱ ባኮችም ከቀጣዩ ሰኞ ጀምሮ ለሶስት ቀናት አገልግሎት ላለመስጠት መወሰናቸውን አሳውቀዋል፡፡ 

Politics, social life

አሜሪካ ኡሁሩ ኬንያታ “የኢትዮጵያና የዲ.አር.ሲ የሰላም መልዕክተኛ” ሆነው መሾማቸውን እንደምትቀበል ገለጸች

ኡሁሩ ኬንያታ የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ፖለቲካዊ መፍትሔ እንዲያገኝ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል

አሜሪካ ተለዋዋጭ ሁነታዎች በሚስተዋሉበት ቀጠና “ኬንያታ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ተስፋ አለን” ብላለች

አሜሪካ ኡሁሩ ኬንያታ የኬንያ የአፍሪካ ቀንድ የሰላም መልዕክተኛ ሆነው መሾም በደስታ እንደምትቀበል ገለጸች፡፡

የአሜሪካ መንግስት በውጭ ጉዳይ መሰሪያ ቤቱ የአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ በኩል ባወጣው መግለጫ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የአፍሪካ ቀንድ እና የታላላቅ ሀይቆች አካባቢ የሰላም መልዕክተኛ ሆነው መሾማቸውን በደስታ እንደሚቀበል አስታውቋል።

ቢሮው ተለዋዋጭ ሁነታዎች በሚስተዋሉበት ቀጠና ኬንያታ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ተስፋ አለን ብሏል፡፡

“ኡሁሩ ኬንያታ በሰሜን ኢትዮጵያ እና በምስራቅ ዲሞክራቲክ ኮንጎ ለተፈጠረው ግጭት የሰላም መልዕክተኛ ሆነው መሾማቸውን በደስታ እንቀበላለን፤ ኬንያታ በዚህ ጊዜ ሁለቱም ግጭቶች ለመፍታት የሚጫወቱት ሚና ወሳኝ ይሆናል” ብሏል ቢሮው በትዊተር ገጹ ላይ ባጋራው ጽሁፍ፡፡

አዲሱ የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ከቀናት በፊት በነበረው በዓለ ሲመታቸው በኢትዮጵያ እና በታላላቅ ሐይቆች ቀጠና (ግሬት ሌክስ) ሰላም ለማምጣት በሚደረገው ጥረት የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የሚያከናውኑትን ተግባር እንደሚቀጥሉ መናጋራቸው ይታወሳል።

ሁለት ዓመት ሊሞላው የተቃረበውን የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት መቀስቀስን ተከትሎ ተዋጊ ኃይሎችን ከማደራደር ጋር ተያይዞ ከአፍሪካ ህብረት በተጨማሪ የኡሁሩ ኬንያታ ስም በተደጋጋሚ ሲነሳ ቆይቷል።

በተለይም አሁን ላይ በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር ለመሰደራደር ዝግጁ መሆናቸው የሚገልጹት የትግራይ ኃይሎች፤ ከመንግስት ጋር በሚደረገው ድርድር ከአፍሪካ ህብረት ይልቅ በቅርቡ ስልጣናቸውን ያስረከቡት ኡሁሩ ኬንያታ እንዲያሸማግሏቸው በተደጋጋሚ በይፋ ጠይቀው እንደነበርም የሚታወስ ነው።

የኢትዮጵያ መንግስት በሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ለሚካሄደው ጦርነት መፍትሔ በመፈለጉ በኩል የአፍሪካ ህብረት ቀዳሚው አሸማጋይ ሊሆን እንደሚገባ ቀደም ሲል በያዘው አቋም እንደጸና መሆኑ ይታወሳል።

News today, Politics, social life

ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ፤ “ለዩክሬን የጦር መሳሪያዎችን ማቅረብ በሞራል ደረጃ ተቀባይነት ያለው ነው” አሉ

አባ ፍራንሲስ፤ እራስን መከላከል ህጋዊ ብቻ ሳይሆን የሰው ልጅ “ለሀገሩ ያለውን ፍቅር መግለጫ ነው” መሆኑም ተናግረዋል

ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ፤ የዩክሬን ጦርነት ራስን ለመከላከል የሚደረግ “ፍትሃዊ ጦርነት” ነው ብለዋል

የዓለም ካቶሊክ ቤተ-ክርስትያን ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ ፤ ራሷን በመከላከል ላይ ላለችው ዩክሬን የጦር መሳሪያዎችን ማቅረብ “በሞራል ደረጃ ተቀባይነት ያለው ነው” አሉ።

ሊቀ ጳጳሱ ይህን ያሉት ከሶስት ቀን የካዛኪስታን ቆይታ ሲመለሱ በአውሮፕላን ውስጥ ሆነው በነበረቻው 45 ደቂቃ የፈጀ ቃለ ምልልስ ላይ ከአንድ ጋዜጠኞች “ሀገራት ለዩክሬን የጦር መሳሪያ መላካችው ትክክል ነው?” ብሎ ላቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ነው።

አባ ፍራንሲስም “ይህ ፖለቲካዊ ውሳኔ ነው ፤ ነገር ግን መርሆችን ባከበረ መልኩ የሚደረግ ከሆነ ከሞራል አኳያ ተቀባይነት ያለው ውሳኔ ነው” ብለዋል።

የዩክሬን ጦርነት ራስን ለመከላከል የሚደረግና በመርህ ደረጃም “ፍትሃዊ” የሚባል ጦርነት መሆኑ ለዚህም የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሃሳባቸው እንድትጋራ የሚያስችል ማብራሪያም መስጠታቸውም ሮይተርስ ዘግቧል።

“እራስን መከላከል ህጋዊ ብቻ ሳይሆን የሰው ልጅ ለሀገሩ ያለውን ፍቅር መግለጫ ነው” ሲሉም አክለዋል። ሊቀ ጳጳሱ የሩሲያ – ዩክሬን ጦርንት እንዲያበቃ ምኞታቸው መሆኑንም ገልጸዋል።

ጦርነቱ እንዲቆም “ዩክሬን ለውይይት ክፍት እንድትሆን” የጠየቁት ሊቀ ጳጳሱ፤ በቅርቡ ከዩክሬን ጋር ምንም ዓይነት የድርድር ተስፋ እንደማይኖር ስለገለጸችው ሩሲያ ግን ያሉት ነገር የለም።

ያም ሆኖ ሊቀ ጳጳስ ፍራሲስ፤ ከሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በሞስኮ ተገናኝቶ ለመምከር ፍላጎት እንዳላቸው ባሰለፍነው ግንቦት ወር አስታውቀው እንደነበር አይዘነጋም።

ሊቀ ጳጳሱ፤ ከጣሊያኑ ኮሬ ዴላ ሴራ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቆይታ ወደ ሞስኮው መምጣት እፈልጋለሁ ሲሉ ለፑቲን መልዕክት መላካቸውንም ተናግረው ነበር።

መልዕክቱ የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት በተጀመረ በ20ኛው ቀን የተላከ መሆኑንም ነበር ሊቃ ጳጳስ ፍራንሲስ የተናገሩት።

የዓለም ካቶሊክ ቤተ-ክርስትያን ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ ጥያቄ ብያቀርቡም፤ በክሬምሊን ባለስልጣነት በኩል እስካሁን የተሰጠ ምላሽ የለም።

News today, social life

ደቡብ ሱዳን ነዳጅ ወደ ውጭ ለመላክ ጅቡቲ ወደብ ላይ ቦታ መግዛቷ አስታወቀች

የደቡብ ሱዳን መንግስት የነዳጅ ሚኒስትር ከፖርት ሱዳንና ሞምባሳ በተጨማሪ ጅቡቲን እንጠቀማለን ብለዋል

ደቡብ ሱዳን አሁን ላይ ነዳጅ የምትልከው “ፖርት ሱዳንን በመጠቀም ብቻ” መሆኑ ይታወቃል

ደቡብ ሱዳን ድፍድፍ ዘይትን ወደ ውጭ ለመላክ የጅቡቲ ወደብ እንደ አማራጭ መጠቀም እንደምርፈልግ አስታወቀች፡፡

የደቡብ ሱዳን መንግስት የነዳጅ ሚኒስትር ፉት ካንግ ኩል በነዳጅ ጉዳይ እየመከረ ባለውና የጅቡቲው የኢነርጂ እና ተፈጥሮ ሃብት ሚኒስትር ዩኑስ አሊ ጌዲ በተገኙበት የጁባው ኮንፈረንስ እንደተናገሩት ደቡብ ሱዳን ነዳጅን ወደ ውጭ ለመላክ እና እቃዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት በጅቡቲ ወደብ ላይ 12 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ገዝታለች ብሏል፡፡

 “እኛ ፖርት ሱዳን እና ሞምባሳን ብቻ ስንጠቀም ቆይተናል ነገር ግን በቅርቡ ወደ ጅቡቲ ለመሄድ ወስነናል” ሲሉም አክለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን አምባሳደር ጀምስ ሞርጋ ለአል ዐይን አማርኛ እንደናገሩት “በሞምባሳ በኩል ነዳጅ መላክ አንችልም፤ ስለዚህም ጅቡቲን መጠቀም ግድ ይለናል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ነገር ግን ነዳጅ ለመላክ መሰረተ ልማት ወሳኝ በመሆኑ በቅድሚያ “ከደቡብ ሱዳን-አትዮጵያ እስከ ጅቡቲ የሚያገናኘው መስመር መዘርጋት አለበት”ም ብለዋል አምባሳደሩ፡፡

ደቡብ ሱዳን፤ በሱዳን የተፈጠረውን የፖለቲካ አለመረጋጋት ተከትሎ ፖርት ሱዳንን በመጠቀም ነዳጅ ወደ ውጭ ሀገራት መላኳ ለማቆም ተገዳ የነበረ ቢሆንም፤ አንጻራዊ ሁኔታ መፈጠሩን ተከትሎ አሁን ፖርት ሱዳን ብቸኛ ነዳጅ የምትልክበት ወደብ አድርጋ በመጠቀም ላይ ትገኛለች፡፡

ደቡብ ሱዳን ኢኮኖሚዋ በነዳጅ ንግድ ላይ የተመሰረተ መሆኑ ይታወቃል፡፡ 

News today, social life

ስደተኞችን በግል ጄት ጭነው አውሮፓ ያሻገሩ ተከሰሱ

የቤልጂየም ፖሊስ ሁለት ጄቶችን ይዟል።
የምስሉ መግለጫ,ስደተኞቹ ሐሰተኛ የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ታድለዋል

15 መስከረም 2022

የግል ጄት በመጠቀም ስደተኞችን ወደ ምዕራብ አውሮፓ ያሻገሩ አምስት ሰዎች ተከሰሱ።

አምስቱ ሰዎች የተከሰሱት በጣሊያን ፍርድ ቤት ነው።

ተጠርጣሪዎቹ ስደተኞቹን ወደ አውሮፓ በግል አውሮፕላን ጭነው ያስገቡት ለሰዎቹ ሐሰተኛ የዲፕሎማት ፓስፖርት ካደሏቸው በኋላ ነው ተብሏል።

ፓስፖርቱ የካሪቢያን ደሴት የሆነችው ሴንት ኪተስ ኤንድ ኔቪሰ እንደሆነ ተመላክቷል።

የግል አውሮፕላኑ እነዚህን ስደተኞች ከቱርክ ከጫናቸው በኋላ በአንድ የአውሮፓ አገር አየር ማረፊያ አራግፈዋቸዋል።

በዚያም ግለሰቦቹ እውነተኛ ማንነታቸውን በመግለጽ የጥገኝነት ጥያቄን አቅርበዋል።

ፖሊስ እንደሚለው እነዚህን ግለሰቦች በግል ጄት ጭኖ አውሮፓ ለማስገባት ተጠርጣሪው ቡድን ከእያንዳንዳቸው 10ሺህ ዩሮ ሳይቀበል አልቀረም።

ድርጊቱን ፈጽመዋል ተብለው ከተጠረጠሩት አምስት ግለሰቦች መሀል ሦስቱ በሮምና በብራስልስ ከተሞች ተይዘዋል።

ሁለቱ አሁንም በፍለጋ ላይ ናቸው።

 ከተጠርጣሪዎቹ አንዱ ጣሊያናዊ ሲሆን ሦስት የግብጽ ዜጎችና አንዲት ቱኒዚያዊት ሴት በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የፖሊስ ኃላፊ የሆኑት ኮስታንቲኖ ስኩዲየር ለሮይተርስ ተናግረዋል።

ተጠርጣሪዎቹ የሌላ ግዙፍ ሕገ ወጥ የስደተኛ አሸጋጋሪ ቡድን አባላት እንደሆኑ ግምት በመውሰድ ክስ ተመሥርቶባቸዋል።

ወንጀለኞቹን አድኖ በመያዙ ረገድ ቤልጅየም፣ ጀርመን፣ ኦስትሪያ፣ ፈረንሳይ እና የአሜሪካ የጸጥታና ደኅንነት አካላት እገዛ እንዳደረጉ ተነግሯል።

News today, Politics, social life

ግብፅና ኳታር በኢኮኖሚና በሌሎች ዘርፎች በትብብር ለመስራት ስምምነት ተፈራረሙ

የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አለሲሲ ከ4 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በኳታር ጉብኝት አድርገዋል

ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አለሲሲ እና የኳታ ኢሚር ታሚም

ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አለሲሲ እና የኳታ ኢሚር ታሚም በሁለትሽ ጉዳዮች ላይ መክረዋል

የግብጹ ፕሬዝዳት አብዱልፈታህ አል ሲሲ በኳታር ይፋዊ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸው ተገልቷል።

ፕሬዝዳት አብዱልፈታህ አልሲሲ ከአራት ዓመታት ወዲህ በሳለፍነው ማክሰኞ ለመጀመሪያ ጊዜ ዶሃ ሲደርሱም በኳታር ኢሚር ታሚም አቀባባበል ተደርጎላቸዋል።

በትናትናው እለትም የግብጹ ፕሬዝዳት አብዱልፈታህ አልሲሲ እና የኳታሩ ኢሚር ታሚም በሀገራ የሆለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተመካክረዋል።

በዚህም የኳታሩ ኢሚር ታሚም ፕሬዝዳንት አል ሲሲ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ግንኙነት እንዲያደግ እየሰሩት ላው ስራ ማማስገናቸውን የኳታር የዜና ኤጀንሲ ዘግቧል።

የፕሬዝዳንት አል ሲሲ ግብኝት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ የሚያጠናከር እንደሚሆን ተስፋ እንዳላቸውም አስታውቀዋል።

ፕሬዝዳንት አል ሲሲ በበኩላቸው፤ ግብጽ ከኳታ ጋር በኢኮኖሚ፣ ፖለቲካ እና በደህንነት ዘርፎች ከኳታር ጋር ለመስራት ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል።

ውይይቱን ተከትሎም ሁለቱ ሀገራት መካከል በተለያዩ ዘርፎች ስምምነት የተካሄደ ሲሆን፤ ከስምምነቶቹ ውስጥም ልማትና ኢንቨስምንት እንዲሁም የማህበራዊ ዘርፍ ይገኝበታል።

News today, social life

ግብጽ ተንቀሳቃሽ የዳንስ ምስል በፌስቡክ ገጿ ላይ የለቀቀችን የዩንቨርሲቲ መምህር ከስራ አገደች

ከስራ የታገዱት ፕሮፌሰር ሞና አል ፕሪንስ የስዊዝ ልንል ዩንቨርስቲ መምህር ነበሩ

መምህሯ ለተማሪዎቿ አርአያ አልሆኑም በሚል ነው ከስራ የተባረሩት

ግብጽ የዳንስ ቪዲዮ በፌስቡክ ገጿ ላይ የፖሰተችን የዩንቨርሲቲ መምህር ከስራ አገደች።

ፕሮፌሰር ሞና አል ፕሪንስ በመባል የሚታወቁት እኝህ እንስት ከሰሞኑ በግላቸው የፌስቡክ ገጽ ላይ በሆድ የሚጨፈር የሰውነት እንቅስቃሴ ወይም ቤሊ ዳንስ ለተከታዮቻቸው አጋርተው ነበር።

እኝህ የስዊዝ ልንል ዩንቨርስቲ የእንግሊዝኛ ቋንቋ መምህር ግብጻውያን ሴቶች እና ወጣቶች በነጻነትን የሚፈልጉትን እንዲያደርጉ በማበረታታትም ይታወቃሉ።

በቅርቡ በግል የፌስቡክ ገጻቸው ለተከታዮቻቸው ባጋሩት ተንቀሳቃሽ የዳንስ ምስል የግብጽን ባህል እና እምነት የሚጻረር ነው በሚል ክስ ቀርቦባቸው እንደነበር ሮይተርስ ዘግቧል።

የግብጽ አስተዳድራዊ ፍርድ ቤትም መምህሯ ለተማሪዎቻቸው አርዓያ ያልሆነ እንቅስቃሴ አድርገዋል በሚል ከስራ እንዲታገዱ መወሰኑ ተገልጿል።

መምህር ሞና ለወጣቶች አርአያ ያልሆነ ተማሪዎችን ወዳልተፈለገ ድርጊት የሚመራ ተግባር እንደፈጸሙ ፍርድ ቤቱ አስታውቋል ተብሏል።

መምህር ሞና ዳንስ ከፈለጉ መብታቸው ነው ያለው ፍርድ ቤቱ የግል ነጻነት ማለት ወጣቶች ልቅ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ መገፋፋት ግን ወንጀል ነው ብሏል ተብሏል ።

ፕሮፌሰር ሞና አል ፕሪንስ በፈረንጆቹ 2018 ላይ በተካሄደው የግብፅ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ ብቸኛዋ ሴት እጩ ተወዳዳሪ እንደነበሩ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል።

News today, social life

በዓለም ላይ 50 ሚሊዮን ዜጎች አሁንም በባርነት ውስጥ እንደሚኖሩ ተመድ ገለጸ


በዓረብ ሀገራት ከፍተኛ የግዳጅ ስራዎች ውስጥ የሚኖሩ ዜጎች እንዳሉ ተመድ ገልጿል

በዓለም ላይ 50 ሚሊዮን ዜጎች አሁንም በባርነት ውስጥ እንደሚኖሩ ተመድ ገለጸ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) ባወጣው ሪፖርት 50 ሚሊዮን የዓለማችን ዜጎች አሁንም በባርነት ውስጥ እንደሚኖሩ ገልጿል።

በዓለማችን ከሚኖሩ 150 ሰዎች ውስጥ አንድ ሰው በግዳጅ ስራ ላይ ወይም ጋብቻ ውስጥ እንደሚኖሩ የድርጅቱ ሪፖርት ያስረዳል።

ከፍተኛ የእድሜ ጣራ ያስመዘገቡ 15 የአፍሪካ ሀገራት
ዓለም አቀፉ የሰራተኞች ድርጅት ወይም አይኤልኦ እና የፍልሰተኞች ድርጅት በጋራ ባወጡት ዓመታዊ ሪፖርት 27 ሚሊዮን ዜጎች በግድ ስራ እንዲሰሩ እየተደረገ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 15 ሚሊዮን ያህሉ ሴቶች እና ህጻናት ናቸው ተብሏል፡፡

ተመድ በፈረንጆቹ 2017 ላይ ተመሳሳይ ሪፖርት ይፋ አድርጎ የነበር ሲሆን አሁን ላይ በባርነት የሚኖሩ ዜጎች ቁጥር ከአምስት ዓመት በፊት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር የ2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ህዝብ ጭማሪ ማሳየቱ ተገልጿል፡፡

በባርነት ተገደው ከሚሰሩ ዜጎች ውስጥ 22 ሚሊዮኑ በእስያ፣ 4 ነጥብ 1 ሚሊዮን ያህሉ ደግሞ በአውሮፓ፣ 3 ነጥብ 8 ሚሊዮኑ በአፍሪካ፣ እንዲሁም 3 ነጥብ 6 ሚሊዮን በአሜሪካ እና 900 ሺህ ያህሉ ደግሞ በመካከለኛው ምስራቅ ይኖራሉ ተብሏል፡፡

በዓረብ ሀገራት ከአንድ ሺህ ሰዎች መካከል ስድስቱ ተገደው ስራ የሚሰሩ ሲሆን ይህ አሃዝ በሌሎች አህጉራት ካለው ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛው እንደሆነ ተገልጿል፡፡

6 ነጥብ 3 ሚሊዮን ያህል ዜጎች ደግሞ ተገደው በሴተኛ አዳሪነት እንዲሰማሩ ተደርገዋል ያለው ተመድ በተለይም ስደተኞች የዚህ ድርጊት ሰለባ እንደሆኑ ተጠቅሷል፡፡

ተገደው በጋብቻ ውስጥ እየኖሩ ያሉት ዜጎች ቁጥር አሁን ላይ 22 ሚሊዮን ያህል ናቸው የተባለ ሲሆን ይህ አሃዝ ከአምስት ዓመት በፊት በጥናት ከተረጋገጠው ጋር ሲነጻጸር የ6 ነጥብ 6 ብልጫ ዓለው ተብሏል፡፡

እስያ እና ፓሲፊክ አካባቢዎች ከ14 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ተገደው በትዳር ውስጥ ያኖራሉ ያለው ተመድ ቀሪው በአፍሪካ እና አውሮፓ እንደሚኖሩ ተገልጿል፡፡

ዝቅተኛ ኢኮኖሚ ባለባቸው ሀገራት ውስጥ ከአምስቱ ሰዎች መካከል ሶስቱ በግድ በትዳር ውስጥ እየኖሩ ሲሆን በበለጸጉ ሀገራት ደግሞ 26 በመቶዎቹ ሰዎች በተመሳሳይ የግዳጅ ጋብቻ ውስጥ ያሉ ናቸው ተብሏል

News today, Politics, social life

የፌደራል መንግስት እና የህወሓት የድርድር ሂደት ይሳካ ይሆን…?


ምሁራኑ “ህወሓት አሁን ላይ ድርድሩን የጠየቀበት ምክንያት ተገዶ ይሆናል፤ ምክንያት ፈልጎ ሊያቋርጠው እንደሚችል ግምታቸውን አሰቀምጠዋል
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀው ህወሓት በሀገር መከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ ማጥቃቱን ተከትሎ ነበር በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የተጀመረው።


ይህ ጦርነት ላለፉት 23 ወራት የዘለቀ ሲሆን ጦርነቱን ለማስቆም አሊያም ለማሸማገል ራሱ የፌደራል መንግስትን ጨምሮ የአፍሪካ ህብረት የአዉሮፓ ህብረት የተባሩት መንግስታት ድርጅት እና የተለያዩ አካላት ጥረት እያደረጉ ቢሆንም ድርድሩ እስካሁን ሳይሳካ ቀርቷል።


የፌደራል መንግስት እና ህወሓት ድርድር ተስፋ እና ስጋቶች
መንግስት ከህወሃት ጋር ድርድር የሚካሄድበትን ቦታ ለመወሰን ከአፍሪካ ህብረት ጋር እየተነጋገረ መሆኑን አስታወቀ
አሁንም ጦርነት ለማስቆምና እልባት ለመፈለግ እየተደረገ ያለው ጥረት በህወሓት በኩል እንቅፋት እየገጠመው ነዉ ሲል መንግስት በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል።


መንግስት የሰላም ድርድሩን በአስቸኳይ ለመጀመር የሚያስችል የሰላም ምክረ- ሃሳብን የያዘ ሰነድ ማዘጋጀቱን ይፋ ቢያደርግም፣ ህውሓት በተቃራኒው ከፌደራል መንግስት ጥቃት እንደተከፈተበት በመግለጽ የተኩስ አቁም ስምምነቱ መፍረሱን ገልጾ ነበር።


የፌደራል መንግስትም ህወሓት ከነሀሴ 18 2014 አ.ም ጀምሮ በራያ፣ ወልቃይት ፣ ሰቆጣ እና አፋር ክልል አዋሳኝ ቦታዎች ጥቃት መፈጸሙን አስታውቋል።


ከተጠቀሰው ዕለት ጀምሮም በበትግራይ ክልል እና አማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች እንዲሁም በኢትዮ ሱዳን ድንበር አካባቢዎች ላይ ጦርነቱ መቀጠሉ የተገለጸ ሲሆን፤ ህወሓት የዘመን መለወጫ ዕለት ማለትም መስከረም 1 ቀን 2015 ዓ.ም ባወጣዉ መግለጫ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ለመወያየት እና ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት መዘጋጀቱን አስታውቋል።


ፃድቃን ገብረተንሳይና ጌታቸው ረዳን ያካተተ ከፌደራል መንግስት ጋር ለሚደረገው ድርድር የሚወክሉትን ቡድን ያፈ ያደረገው ህወሓት አለማቀፉ ማኅበረሰብ በታዛቢነትና ድጋፍ በማድረግ እንዲሳተፉ እንደሚፈልግም ገልጿል።


የህወሃትን የእደራደራለሁ መግለጫን ተከትሎ ብዙዎች ተስፋ እና ስጋትን እንደተሰማቸው በተለያዩ መንገዶች ሃሳባቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው።
አል ዐይን አማርኛ የህወሓት ለመደራደር ዝግጁ ነኝ ማለቱን ተከትሎ ስለጉዳዩ ምሁራንን አነጋግሯል።


አቶ አበበ ይርጋ በባህር ዳር ዩንቨርሲቲ ስር ባለው የብሉናይል ውሀ ኢንስቲትዩት የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ጥናት መምህር ናቸው፤ የህወሃትን በየትኛውም ቦታ እና ጊዜ በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ከፌደራል መንግስት ጋር እደራደራለሁ ማለቱን እንዴት ያዩታል? በሚል ላነሳንላቸው ጥያቄ፤
“ህወሀት ወደ ድርድር እንዲመጣ ለረጅም ጊዜ ሲለመን ነበር፣ ነገር ግን ቅድመ ሁኔታ ሲደርድር እና ሰላም እንዳይፈጠር የቻለውን ሁሉ ሲያደርግ ቆይቷል።

በድንገት ያለ ቅድመ ሁኔታ በየትኛውም ቦታ እደራደራለሁ ማለቱ ከልቡ አይመስለኝም፣ ይሄንን መግለጫም ያወጣው በሎጅስቲክስ እና ፕሮፓጋንዳ ሲያግዙት የቆዩት አካላት አዘውት ነው” ብዬ አስባለሁ ብለዋል።


“በኢትዮጵያ የተለየ ፍላጎት ያላቸው ሀገራት ቁጥራቸው እየጨመረ ነው” የሚሉት መምህር አበበ “ህወሓት እየተሸነፈ ሲመስላቸው እና ተጨማሪ ድጋፍ ለማሰባሰብ እንዲያመቻቸው” ለድርድር ዝግጁ መሆኑን እንዲያሳውቅ ሳያደርገው እንዳልቀረ ግምት እንዳላቸውም ጠቅሰዋል።


“ህወሓት እደራደራለሁ ማለቱ በፌደራል መንግስት ላይ በሚደረግ ጫና ምክንያት መከላከያ ሰራዊት ማጥቃቱን ትቶ አሁን ባለበት ቦታ እንዲቆም ቀስ በቀስም ለአራተኛ ዙር ጦርነት የመዘጋጃ ጊዜ እንደሚያገኝ በማሰቡ ሊሆን ይችላል” ሲሉም ተናግረዋል።


“ድርድሩ የውጭ ጣልቃ ገብነት የተጫነው ይመስላል” የሚሉት መምህር አበበ “ለኢትዮጵያ ዘላቂ መፍትሄ የሚያመጣላት ከድርድሩ ጎን ለጎን በህወሀት ጥቃት እየደረሰበት ያለውን የትግራይ፣ አማራ እና አፋር ክልሎች ህዝብን መታደግ ሲቻል እና መንግስታዊ አገልግሎቶችን መጀመር ብቻ” እንደሆነ ጠቁመዋል።


ሌላኛው በድርድሩ ዙሪያ አል ዐይን አማርኛ ያናገራቸው በጅግጅጋ ዩንቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ህግ መምህሩ ሰለሞን ጓዴ ናቸው።


እሳቸው እንዳሉት “በእኔ አመለካከት “ህወሓት አሁን ላይ ድርድሩን የጠየቀበት ምክንያት ተገዶ ይሆናል የሚል እሳቤ አለኝ ምክንያቱም ይፈልጉት የነበረዉ ስትራቴጂካዊ ቦታ ተይዞባቸዋል በዚህም ጫናዉ ሲበዛባቸዉና የጦርነት የበላይነትን ሲያጡ መጀመሪያ አጎንብሶ ከዛም አፈር ልሶ ለመነሳት የሚደረግ ሙከራ ነዉ ብዬ ነዉ የማምነዉ በአንድ ሳምንት ዉስጥ ሽንፈት ካልሆነ በስተቀር ሊፈጠር የሚችል አሳማኝ ምክንያት የለም” ሲሉ ገልጸዋል፡፡


“ህወሓት እንዳለው ወደ ድርድር ከመጣ የታጣቂዎቹ ትጥቅ መፍታት ጉዳይ የድርድሩ ዋነኛ ጉዳይ ይሆናል” የሚሉት መምህር ሰለሞን “ሰላም እንዲመጣ ከተፈለገ መተማመንን የሚያጎለብት ስራ መሰራት አለበት” ብለዋል፡፡


ድርድሩ ፍሬያማ እንዲሆን ከተፈለገ መጀመሪያ ሰላማዊ የሆነ አየር ያስፈልጋል፤ ሉዓላዊነት መከበር አለበት፣ ይህ የሚሆነው ደግሞ የህወሓት ታጣቂዎች ትጥቅ ሲፈቱ እና የሀገር መከላከያ ሰራዊት የሀገሪቱን ዳር ድንበር መቆጣጠር በሚያስችለው መንገድ ሲሰማራ ብቻ እንደሆነም መምህር ሰለሞን አክለዋል።


መምህር ሰለሞን አክለውም የህወሓት የእስካሁኑ የፖለቲካ ባህል ምን ጊዜም እራሱን ብቻ የሚያስቀድም በመሆኑ እደራደራለሁ ማለቱ ከልቡ ሊሆን እንደማይችል ተናግረዋል።


በመንግስትና ህወሓት መካከል የሚደረገው ድርድር ሁሉንም ያሳተፈ ኢንዲሆን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ም/ቤት ጠየቀ
“ህወሓት እኔ ያልመራሁት ነገር አይደረግም የሚል ድርቅ ያለ መንገድን የሚከተል ድርጅት ነው” የሚሉት መምህር ሰለሞን ድርድር በባህሪው ሰጥቶ መቀበልን እና ሰላማዊ ሁኔታዎችን የሚፈልግ በመሆኑ ድርድሩ የመሳካት እድሉ ጠባብ መሆኑን ጠቁመዋል።


ህወሓት ድርድሩን ቢጀምረው እንኳን ምክንያት ፈልጎ ሊያቋርጠው እንደሚችል ግምታቸውን ያስቀመጡት መምህር ሰለሞን የፌደራል መንግስት በህወሀት ወጥመድ ሊገባ እንደማይገባም አሳስበዋል።


የፌደራል መንግስት ከዚህ በፊት ባወጣው መግለጫ በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ከህወሃት ጋር በየትኛውም ቦታ እና ጊዜ እንደሚደራደር ማሳወቁ ይታወሳል።


ለዚህ ድርድርም በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የሚመራ አብይ ኮሚቴ መቋቋሙን እና ሌሎች ንዑስ ኮሚቴዎችም ተቋቁመው ስራ መጀመራቸው መገለጹ አይዘነጋም።

News today, social life

የሴኔጋል ፓርላማ አባላት እርስበርሳቸው ተደባደቡ

ሴኔጋል ከአንድ ወር በፊት ነበር የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ ያካሄደችው።

ገዥው ፓርቲ አብዛኛውን መቀመጫ በተቃዋሚ ፓርቲዎች በተነጠቀበት በዚህ ምርጫ ተመራጭ የሆኑ የምክር ቤት አባላት ዛሬ ስራቸው ጀምረዋል።

አባላቱ በዛሬው ስብሰባቸው የምክር ቤቱን ተጠሪ ፕሬዝዳንት መምረጥ የነበረባቸው ቢሆንም ወደ ስምምነት መምጣት አልቻሉም።

የምክር ቤቱ አባላት አለመስማማታቸው ተከትሎ በተፈጠረ አለመግባባት በወንበር እና ውሀ መያዣ ፕላስቲኮችን እርስ በርስ በመወራወር እንደተደባደቡ ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል።

በምክር ቤቱ አባላት የተፈጠረውን ሁከት ተከትሎም የሀገሪቱ ፖሊስ ገብቶ ተደባዳቢዎቹን በቁጥጥር ስር በማዋል ክስተቱን ተቆጣጥሯል ተብሏል።

የከዓለም ዙሪያ ቤተሰብ ይሁኑ
ቴሌግራም፡ https://t.me/KeAlemiZuriya
ዩቲዩብ: https://youtube.com/c/Kealemizuriya
ድረገፅ: https://kealemizuriya.data.blog
ትዊተር: https://twitter.com/KeAlemiZuriya
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/KeAlemiZuriya
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/Kealemizuriya

social life

ደቡብ ኮሪያ በኮሪያ ጦርነት ወቅት የተለያዩ ቤተሰቦች እንዲገናኙ ከሰሜን ኮሪያ ጋር መነጋገር እንደሚፈልግ ገለጸች


አዲሱ የደቡብ ኮሪያ መንግስት በ1950ዎቹ በተካሄደው የኮሪያ ጦርነት ወቅት የተለያዩ ቤተሰቦች እንዲገናኙ ለማድረግ ከሰሜን ኮሪያ ጋር ለመነጋገር ማቀዱን ገልጿል።


በደቡብ እና ሰሜን ኮሪያ መካከል በኑክሌር የጦር መሳሪያ ጉዳይ ለረጅም ጊዜ የቆየ አለመግባባት አለ።


የቤተሰቦች መቀላቀል ጉዳይ እጅግ ሰብአዊና ሰሜታዊ የሚያደርግ ጉዳይ ነው። 
ነገርግን ሰሜን ኮሪያ የቤተሰቦችን መገናኘት ጉዳይ ከደቡብ ኮሪያ ጋር እንደመደራደሪያ ስለምትቆጥረው፣ሰሜን ኮሪያ የደቡብ ኮሪያን መንግስት እቅድ ላትቀበለው ትችላለች ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።


የኑክሌር አቅሟን በማሳደግ ላይ ያለችው ሰሜን ኮሪያ፣ ከደቡብ ኮሪያ እና ከአሜሪካ የቀረበላትን በኑክሌር ጉዳይ ውይይት በንቀት አልፋዋለች።
“ደቡብ እና ሰሜን የሚያመውን እውነታ መጋፈጥ አለባቸው፤የተለያዩ ቤተሰቦች የሚለው ቃል ከመጥፋቱ በፊት ችግሩን መፍታት አለብን” ሲሉ የውህደት ሚኒስትር ክዎን ዮንገዜ ተናግረዋል።


ሚኒስትሩ ኃላፊነት የሚሰማቸው የሁለቱ ኮሪያዎች በአካል ተገናኝተው ልባዊ እንደሚያደርጉ ተስፋ አለኝ ብለዋል።


የሁለቱ ኮሪያዎች የቤተሰብ መገናኘቱ የቆመው በፈረንጆቹ 2019 አሜሪካ ሰሜን ኮሪያ የኑክሌር ፕሮግራሟን እንድታቆምና በምትኩ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ጥቅም እንድታገኝ ያደረገችው ወይይት ያለውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ ነው።
አሜሪካ ሰሜን ኮሪያ ያለቅድመ ሁኔታ ወደ ኑክሌር ውይይት እንድትመጣ ብትጠይቅም፣ ሰሜን ኮሪያ አሜሪካ በሰሜን ኮሪያ ላይ ያላትን ጸብ አጫሪ ፖሊሲ መተው አለባት ስትል ቆይታለች።


ከበርካታ አስርት አመታት በኃላ የሚፈላለጉት ቤተሰቦች በህይወት ይኖሩ ይሆን እያሉ ይጨነቃሉ።


እንደ ዩኒፊኬሽን ሚኒስትሩ ከሆነ ከ133ሺ በላይ በሰሜን ኮሪያ ካሉ ቤተሰቦቻቸው ጋር ለመገናኘት ያመለከቱ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 70 በመቶ የሚሆኑት ህይወታቸው አልፏል።

News today, Politics, social life

የንግስት ኤልሳቤጥ ለ70 ዓመት የብሪታኒያ ንግስት ነበሩ

የብሪታንያ ንግስት ኤልሳቤጥ በ96 ዓመታቸው ማረፋቸው ተገለፀ።

ንግስቲቱ በስኮትላንድ ቤኪንግሀም ቤተ መንግሥት ማረፋቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

የንግስቲቱ የቀብር ስነ ስርዓት ከ10 ቀን በኋላ ክብራቸውን በጠበቀ መንገድ እንደሚከናወንም ተገልጿል።

የንግስት ኤልሳቤትን ህልፈተ ህይወት ተከትሎ ልዑል ቻርልስ የብሪታንያ በነገው ዕለት ንጉስ ሆነው እንደሚሾሙም ይጠበቃል።

ላለፉት 70 ዓመታት የብሪታንያ ንግስት የነበሩት ንግስት ኤልሳቤት በ96 ዓመታቸው ህይወታቸው አልፏል።

ንግስቲቱ በኮሮና ቫይረስ እንዳይጠቁ የእንግሊዝ መንግሥት ልዩ ጥበቃ ሲያደርግላቸው ቆይቶ ነበር።

ከትናንት በስቲያ የብሪታንያ አዲሷን ጠቅላይ ሚንስትር ሊዝ ትሩስን ሹመት ያጸደቁት ንግስቲቱ ዛሬ ከሰዓት መጠነኛ ህመም ከተሰማቸው በኋላ ምሽት ላይ ህይወታቸው ማለፉ ተሰምቷል።

በመላው ብሪታንያ ሀዘን ላይ የወደቁ ሲሆን የሀገሪቱ ሰንደቅ ዓላም ዝቅ ብሎ ከመውለብለቡ ባለፈ የብሪታንያ ብዙሀን መገናኛዎች ሌሎች ጉዳዮችን መዘገብ አቁመዋል።

News today, social life

በኮንጎ ሪባን በመቁረጥ ሰነ-ስርዓት ወቅት ድልድይ መደርመሱ አነጋገረ

በኮንጎ ሪባን በመቁረጥ ሰነ-ስርዓት ወቅት ድልድይ መደርመሱ አነጋገረ
September 7, 2022
በኮንጎ ሪባን በመቁረጥ ሰነ-ስርዓት ወቅት የተደረመሰው ድልድይ አነጋጋሪ ሆኗል


ድልድዩን ሊመርቁ የተገኙ የክብር እንዶች ድልድዩ ላይ ቆመው ሪባን በሚቆርጡበት ወቅት ድልድዩ ተደርምሷል፡፡ ሮይተርስ አረጋግጫለሁ ባለው ተንቀሳቃሽ ምስል ድልድዩ የሚመረቀው በኮንዶ ዋና ከተማ ሲሆን የምርቃት ሪባን የሚቆርጡ ሰዎች በድልድዩ ላይ በቆሙበት ወቅት ድልድዩ ሊደረመስ ችሏል፡፡


ተንቀሳቃሽ ምስሉ በቦታው የተገኙት ሰዎች በግርምት ሲመለከቱ ይታያሉ፡፡
ድልድዩ የእጅ መያዣዎቹን ጨምሮ ማእከላዊ አካሉ ተደርምሶ ከሁለት ሜትር ርቀት ላይ ማረፉን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡


 ለምርቃቱ የመጡት የክብር እንግዶች ከአደጋው ለማምለጥ ሲታገሉ በቦተው የነበሩ ተመልካቾች ሲስዉ ታይተዋል፡፡ በአደጋው የደረሰ ጉዳት የለም ተብሏል፡፡
ተንቀሳቃሽ ምስሉ በሰፊው የተሰራጨ ሲሆን ክስተቱ መነጋገሪያ ሆኗል፡፡

News today, social life

በቻይና በመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 65 ደረሰ

በቻይና ሲቹዋን ግዛት በሬክተር ስኬል 6 ነጥብ 8 መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል

በቻይና በመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 65 ደርሷል፡፡

ከፈረንጆቹ 2017ወዲህ በቻይና ደቡብ ምእራብ በምትገኘው ሲቹዋን ግዛት በተከሰተው ጠንካራ ነው በተባለው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 65 መድረሱን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

የነፍስ አድን ሰራተኞች በአስቸካሩ ሆኔታ ውሰት ሉ ሰዎችን ለማውጣት እና መሰረታዊ አገልግቶችን ለለመረስ እየሰሩ መሆናቸውንም ሀገባው ጠቅሷል፡፡

በአደጋው ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው 250 ሰዎች ህክም እየተደረገላቸው ይገኛል፤ ከተጎጅዎች መካል 10 የሚሆኑት ከባድ አደጋ የደረሰባቸው ናቸው ተብሏል፡፡

የነፍስ አድን ሰራተኞች ህይወታቸው ለአደጋ የተጋለጡ 200 ሰዎች ለማውጣት፣ ቴለኬኮሙኒኬሽንን፣ መብራት እና የውሃ አገልግሎቶችን ለመመለስ በመጣደፍ ላይ ናቸው፡፡

ሮይተርስ የቻይና ሚዲያዎችን ጠቅሶ እንደዘገበው የነፍስ አድን ሰራተኞቹ በሬክተር ስኬል 6 ነጥብ 8 በሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ለተጎዱ ሰዎች የምግብ አቅርቦት እያደረሱ ነው፡፡

በሲቹያን ግዛት የተከሰተው ጠንካራ የመሬት መንቀጥቀጥ እስከ ግዛቷ ተራራ ቦታዎች ድርስ ንዝረቱ መሰማቱን ዘገባው ገልጿል፡፡

News today, social life

ሱዳን በጎርፍ ተጥለቀለቀች

በመስከረም ወር ተጨማሪ ዜጎች ለጎርፍ አደጋ ሊጋለጡ እንደሚችሉ ተገልጿል

በሱዳን በጎርፍ የተወሰዱ ሰዎች 112 ደርሷል።

በሱዳን ካሳለፍነው ሰኔ ወር ጀምሮ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 112 ማሻቀቡን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

የዓባይ ወንዝ የውሃ መጠን በመጪዎቹ ቀናት የበለጠ ሊጨምር እንደሚችልም የገለፁት የሃገሪቱ የአደጋ መከላከል ባለስልጣናት አስጠንቅቀዋል።

በሱዳን በጎርፍ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 100 ደረሰ
ባለስልጣናቱ በዚህ ወር ብቻ ባጋጠመ አደጋ 112 ሱዳናውያን መሞታቸውንና 115 ሰዎች ደግሞ መጎዳታቸውን አስታውቀዋል።በድምሩ 84 ሺ 40 ቤቶች ሙሉ በሙሉ እና በከፊል መውደማቸው እና መጎዳታቸውንም ተናግረዋል ባለስልጣናቱ።

መሠል የጎርፍ አደጋዎች ለሱዳን አዲስ አይደሉም። ክረምት በመጣ ቁጥርም ያጋጥማል። ሆኖም ዘንድሮ በ1940ዎቹ ካጋጠመውና የከፋ ነበር ከተባለለት የበለጠ የጎርፍ አደጋ ማጋጠሙ ነው የተነገረው።

አደጋው ካለፉት ሁለት የክረምት ወራት ይልቅ በነሐሴ እና መስከረም ወራት ይከፋል መባሉም ብዙዎችን አስግቷል።

የጎርፍ አደጋው በስድስት ግዛቶች እየከፋ የመጣ ሲሆን የሀገሪቱ ወታደራዊ መንግስትም በነዚህ ግዛቶች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጇል።

ናይል፣ ዋይት ናይል፣ ኮርዶፋን፣ ዳርፉር እና ካሳላ ግዛቶች በጎርፍ አደጋው ክፉኛ ተጎድተዋል ተብሏል፡፡

እስካሁን ባለው የጎርፍ አደጋ ከ250 ሺህ በላይ ዜጎች ከመኖሪያ ቤታቸው የተፈናቀሉ ሲሆን በቀጣዮቹ ሳምንታት ተጨማሪ ጉዳት ሊከሰት እንደሚችል ተጠቅሷል።

News today, social life

ደቡብ ኮሪያ ለሳምሰንግ ኤሌክትሮኒክስ ኩባንያ ዋና አስተዳዳሪ ምህረት አደረገች


አስተዳዳሪው ፈጽመውታል በተባለው ሙስና ሁለት ዓመት ከመንፈቅ ተፈርዶባቸው እንደነበር ይታወሳል

ደቡብ ኮሪያ ለቢሊየነሩ የሳምሰንግ ኤሌክትሮኒክስ ኩባንያ ወራሽ እና ዋና አስተዳዳሪ ሊ ጄ ያንግን ምህረት አደረገች።

የግዙፉ የዓለማችን ኤሌክትሮኒክስ ኩባንያ ባለቤት ሊ ጄ ያንግ ከፕሬዝዳንት ዩን ሱክ ዮል ነው ምህረቱን ያገኙት።

በቀድሞዋ የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ፓርክ ጊዩን ሃይ የስልጣን ዘመን ፈጽመውታል በተባለው የሙስና ቅሌት ሁለት ዓመት ከመንፈቅ ተፈርዶባቸው እንደነበር ይታወሳል።

አንዱን ዓመት በእስር ያሳለፉም ሲሆን ባለፈው ዓመት ነሐሴ ላይ ለመታረም ቃል በመግባት ከእስር ቤት ወጥተው ነበር። የተፈረደባቸው የእስር ጊዜም ከሳምንት በፊት ተጠናቋል። ሆኖም የክስ መዝገባቸው ሙሉ በሙሉ አልተዘጋም። በክሱ ያጡትን ሙሉ መብት እና ነጻነት መልሶ ለማግኘት ምህረትን ማግኘት የግድ ይላቸው ነበር።

ይህን ተከትሎም ከፕሬዝዳንት ዩን ሱክ ዮል ምህረት ተሰጥቷቸዋል። ፕሬዝዳንታዊ ምህረቱ

ከሶስት ቀናት በኋላ የሚከበረውን የሃገሪቱን የነጻነት በዓል አስመልክቶ የተሰጠ ነው።ሌሎች 1 ሺ 691 ገደማ እስረኞችም የፕሬዝዳንት ዮል ምህረት አግኝተዋል።

ሊ ጄ ኩባንያቸው የቻይናን ጨምሮ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ የኤሌክትሮኒክስ ኩባንያዎች ከፍተኛ ፉክክር ውስጥ መግባቱን ተከትሎ ነው ምህረቱን ያገኙት።

በጥሩ ተወዳዳሪነቱ ለመቀጠል የሚያስችል አመራርን ሊሰጡ ይችላሉ በሚል ምህረቱን ስለማግኘታቸውም ተነግሯል።

ሃገሪቱ የገጠማትን ምጣኔ ሐብታዊ ጫና ለማቅለልና በተሻለ ሁኔታ ለመገንባት የሚያስችሉ ውጤታማ እርምጃዎችን እንዲወስዱም ስለመታዘዛቸውም የሃገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል።

ደቡብ ኮሪያ ለሃገሪቱ ምጣኔ ሃብታዊ ግንባታ የጎላጰአበርክቶ ላላቸው የቢዝነስ ሰዎች በእንዲህ ዐይነት መንገድ ምህረት የማድረግ ልምድ እንዳላትም ተነግሯል።

News today, social life

ቤይሩት ውስጥ በመሳሪያ አስገድዶ ገንዘቡን ከባንክ የወሰደው ጀግና ተባለ

መሳሪያ ታጥቆ ከቁጠባ ሂሳቡ ገንዘቡ እንዲሰጠው ያስገደደው ግለሰብ ጀግና ተብሏል።
የምስሉ መግለጫ,መሳሪያ ታጥቆ ከቁጠባ ሂሳቡ ገንዘቡ እንዲሰጠው ያስገደደው ግለሰብ ጀግና ተብሏል

ከ 3 ሰአት በፊት

መሳሪያ ታጥቆ ከቁጠባ ሂሳቡ ገንዘቡ እንዲሰጠው ያስገደደው የሊባኖስ ዜጋ በሕዝቡ ጀግና ተብሎ ተወደሰ።

ሊባኖስ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ውስጥ መግባቷን ተከትሎ ባንኮች ደንበኞቻቸው ወጪ በሚያደርጉት ገንዘብ ላይ ገደብ ጥላለች።

ይህ ግለሰብ ግን መሳሪያ ታጥቆና ባንክ ውስጥ ነዳጅ አርከፍክፎ ለሆስፒታል ክፍያ ለመፈጸም የሚያስፈልገው ገንዘቡ እንዲሰጠው በኃይል መጠየቁን ኤኤፍፒ ዘግቧል።

በግለሰቡ እና በባንኩ መካከል ለስድስት ሰዓታት ከቆየ ፍጥጫ በኋላ ግለሰቡ የጠየቀውን ገንዘብ ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስ ማግኘት ችሏል።

ይህ በስም ያልተጠቀው ግለሰብ ተግባርም በሕዝቡ ዘንድ አድናቆትን አስገኝቶለታል። ከባንኩ ውጪ ተሰብስበው የነበሩ ሰዎች “ጀግና ነህ” እያሉ ጠርተውታል።

የግለሰቡ ወንድም ለጋዜጠኞች ሲናገር፤ “ወንድሜ በባንክ ሂሳቡ 210ሺህ ዶላር አለው። የሆስፒታል ወጪውን ለመሸፈን 5ሺህ 500 ዶላር ፈልጎ ነበር” ብሏል።

ከባንኩ ውጪ የነበሩት የግለሰቡ ወንድም እና ባለቤት፤ “ሁሉም ሰው ሊያደርገው የሚገባው ይሄን ነው። የራሳቸው የሆነውን ማግኘት አለባቸው” ብለዋል።

ኤልቢሲ የተሰኘ የቴሌቪዥን ጣቢያ የግለሰቡ ቤተሰብ አባላት በሆስፒታል እንደሚገኙ እና ገንዘብ እጅጉን ያስፈልጋቸው እንደነበር ዘግቧል።

የቴሌቪዥን ጣቢያው ጨምሮ እንደዘገበው ወደ ባንኩ በኃይል ከገባው ግለሰብ ጋር ድርድር ከተደረገ በኋላ ከቁጠባ ሂሳቡ 35ሺህ ዶላር ተሰጥቶታል።

ፖሊስ ግለሰቡን እና በእገታ ስር የቆዩ የባንክ ሠራተኞችን ከአካባቢው ይዞ የወጣ ሲሆን በግለሰቡ ላይ ክስ ይመሰረት እንደሆነ እስካሁን የተባለ ነገር የለም።

እአአ 2019 ላይ ሊባኖስ የገጠማትን ምጣኔ ሃብታዊ ቀውስ ለመቋቋም ያስችለኛል ብላ ተግባራዊ ካደረገቻቸው ውሳኔዎች መካከል ሰዎች ከቁጠባ ሂሳባቸው ወጪ በሚያደርጉት የገንዘብ መጠን ላይ ገደብ መጣል ነው።

ከዚህ በተጨማሪም ከአገር ውጪ በሚላክ የገንዘብ መጠን ላይም ገደብ ተጥሏል። ይሁን እንጂ እነዚህ ክልከላዎች ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል።

በሊባኖስ የተከሰተው ምጣሄ ሃብታዊ ቀውስ የአገሪቱ ገንዘብ ዋጋውን ከ90 በመቶ በላይ እንዲያጣ አድርጎታል።

የዋጋ ግሽበት ጣሪያ ነክቷል፤ እንደ መድሃኒት እና ስንዴ ባሉ ምርቶች ላይ እጥረት አጋጥሟል። የተባበሩት መንግሥታት ከአምስት ሊባኖሳዊያን አራቱ በድኅነት ውስጥ ይኖራሉ ይላል።

News today, social life

የሕዳሴ ግድበ 2ኛው ተርባይን ኃይል ማመንጨት ጀመረ

ዛሬ ሥራ የጀመረው ሁለተኛው ዩኒት 375 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም አለው
ሲጠናቀቅ ከአፍሪካ ትልቅ ግድብ እንደሚሆን የሚጠበቀው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ 2ኛው ተርባይን የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ጀመረ።


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በቤንሻንጉል ጉሙዝ ጉባ ወረዳ በታደሙበት ዝግጅት ነው በዛሬው ዕለት ሁለተኛው ተርባይን ኃይል ማመንጨት የጀመረው።


የሕዳሴ ግድብ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ጀመረ
የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ካሉት 13 ተርባይኖች መካከል ዩኒት 9 የሚባለው ሁለተኛው ተርባይን የተሳካ ተከላ እና ሙከራ ከተደረገ በኋላ ኃይል የማመንጨት ስራው ን ዛሬ በይፋ ጀምሯል።


ዛሬ በይፋ ሥራ የጀመረው ሁለተኛው ዩኒት 375 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳለው ተገልጿል።
ባሳለፍነው ጥር 25 2014 ዓ.ም በዚህም ግድቡ ካሉት ተርባይኖች ውስጥ አንዱ የሆነው እና ዩኒት 10 የሚል መጠሪያ ያለው ተርባይን 375 ሜጋ ዋት ኃይል ማመንጨት መጀመሩ ይታወሳል።


ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ ግድብ ለመገንባት የመረሰት ድንጋይ ካስቀመጠች አንድ አመት በኋላ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ግብጽና ሱደን በግድቡ ላይ ስጋት እንዳላቸው ጥያቄ አንስተዋል፡፡
ኢትዮጵያ፣ሱዳንና ግብጽ በግድቡ አስተዳደር ጉዳይ የሶስትዮች ንግግር እና ድርድር ከመጀሩ ቆይተዋል፤ ነገርግን እስካን ከስምምነት አልደረሱም፡፡


የኢትዮጵያ መንግስት ግድቡን እየገነባ ያለው ለልማት አላማ ብቻ መሆኑን እና በታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ላይ የጎላ ተጽእኖ እንደማያደርስ በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል፡፡ ግብጽና ሱዳን ግን በግድቡ ዙሪያ የየራሳቸው አቋም አላቸው፡፡


በተለይም ግብጽ በቅኝ ግዛት ዘመን የተፈረመ ስምምነትን ጭምር በመጥቀስ፤ ታሪካዊ የሆነ የውሃ ድርሻዋ ላይ ተጽእኖ እንሚያሳድር እና ግድቡ አሉታዊ ተጽእኖ እንደሚያሳድርባት ትገልጻለች፡፡


በ2013 ዓ.ም በአሜሪካ ዋሽንግተን ሲደረግ የነበረው የሶስትዮሽ ድርድር ከፈረስ በኋላ ድርድሩ በአፍሪካ ህብረት አመቻችነት እንዲካሄድ ተስማምተዋል፡፡


ድርድርሩ ወደ አፍሪካ ህብረት የመጣው ኢትዮጵያ፤ ድርድሩ ሳይጀመር የታዛቢነት ሚና የነበራቸው አሜሪካና የአለም ባንክ ሚናቸውን ወደ አደራዳሪነትና ወደ የስምምነት ሰነድ አርቃቂነት ከፍ በማድረጋቸው እና ኢትዮጵያም ይህን አልቀበልም በማለቷ ነው።


ኢትዮጵያ የግድቡ ጉዳይ የልማት ጉዳይ ነው ብትልም ፤ግብጽና ሱዳን የግድቡን ጉዳይ የጸጥታ ጉዳይ ነው በማለት ለተመድ የጸጥታው ም/ቤት በማቅረብ ም/ቤቱ ወይይት አድርጎበት ያውቃል።

News today, social life

ሲም ካርድ ያለው ሁሉ ገንዘብ መበደር የሚችልበትን ዕድል ለመፍጠር ያቀደው ቴሌብር

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ

ከአስራ አራት ወራት በፊት ወደ አገልግሎት የገባው ቴሌብር የተሰኘው የኢትዮ ቴሌኮም የሞባይል ገንዘብ ሥርዓት ባለፈው ሳምንት አርብ ከቁጠባ እና ብድር ጋር የተያያዙ አዳዲስ አገልግሎቶችን መስጠት ጀምሯል።

ከቢቢሲ ጋር ቆይታ ያደረጉት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ አዳዲሶቹ አገልግሎቶች በፋይናንስ ሥርዓት ያልተሸፈነውን 60 በመቶ የሚሆን የኅብተረሰብ ክፍል ተደራሽ ለማድረግ ያስችላል ብለዋል።

የነዳጅ ድጎማ እና የግብር ክፍያን ጨምሮ ባለፉት 14 ወራት ገንዘብ ለመላላክ፣ የግብይትና የአገልግሎት ክፍያን ለመፈጸም እንዲሁም ከውጭ አገራት ገንዘብ ለመቀበል ሲውል የነበረው ቴሌብር አሁን ደግሞ  ‘መላ’፣ ‘እንደኪሴ’ እና ‘ሰንዱቅ’ የተሰኙ አገልግሎቶችን ይፋ አድርጓል።

ኢትዮ ቴሌኮም የቴሌብር ደንበኞች ገንዘብ እንዲቆጥቡ፣ ሲያስፈልጋቸው እንዲበደሩ የሚረዱት አዳዲሶቹን አገልግሎቶች ለማስጀመር አስራ አራት ወራት በላይ ዘግይቷል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ኢትዮ ቴሌኮም እነዚህን አገልግሎቶች ለማስጀመር ከአንድ ዓመት በላይ የዘገየበትን ምክንያት ሲያስረዱ “የተሰጠን ፍቃድ እሱን አልፈቀደልንም ነበር። ስለዚህ በቴሌ ብር ሌሎቹን አገልግሎቶች እየሰጠን ከብሔራዊ ባንክ ፈቃድ ለማግኘት ሥራዎችን ስንሰራ ቆይተናል” ብለዋል። 

ለመሆኑ አገልግሎቶቹ ምንድን ናቸው?

የቴሌብር ቁጠባና ብድር

በቴሌብር አማካኝነት በቅርቡ የተጀመሩት ሦስት አገልግሎቶች ተጠቃሚዎች ያለዋስትና/ማስያዣ እንዲበደሩ ወይም እንዲቆጥቡ የሚያስችሉ መሆናቸውን ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ለቢቢሲ ገልጸዋል።

  • ሳንዱቅ

ይህ የቴሌብር አገልግሎት ደንበኞች ገንዘብ የሚቆጥቡበት ሲሆን፣ ለተቀማጭ ገንዘብ ወለድ የሚከፈልበትን እና ከወለድ ነጻ የሆነ አመራጮችን አካቷል።

እንደ ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ገለጻ፣ ወለድ የሚከፈልበት ቁጠባ በየቀኑ የሚሰላ እና ደንበኞች በቀን ያገኙትን መጠን የሚያመላክት ነው።

  • እንደ ኪሴ

የቴሌብር ደንበኞች ግብይት እየፈጸሙ ገንዘብ በሚያንሳቸው ጊዜ ቀሪውን ገንዘብ የሚያገኙት ሥርዓት ደግሞ እንደኪሴ ይሰኛል። 

እንደኪሴ ደንበኞች ለግብይት ከሚያጥራቸው ገንዘብ በተጨማሪ እንደ የኤሌክትሪክ እና ውሃ ያሉ የአገልግሎት ክፍያዎችን ለመፈጸምም ያስችላል።

ይህ አሰራር ደንበኞች ለክፍያ የጎደላቸውን እስከ 2 ሺህ ብር የሚሸፍንም ነው።  

  • መላ

ቴሌብር መላ፣ ደንበኞች የብድር አገልግሎት የሚያገኙበት መንገድ ሲሆን ግለሰቦችን እና የንግድ ተቋማትን የሚያካትት ነው።

በቴሌብር መላ ግለሰቦች በወር እስከ 10 ሺህ ብር፣ የንግድ ተቋማት ደግሞ እስከ 100 ሺህ መበደር እንደሚችሉ የሚያስረዱት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ፤ ግለሰቦች የተበደሩትን በቀን፣ በሳምንት እና በወር መመለስ የሚችሉበትን አሰራር ማቀፉን ጠቅሰዋል።

ለንግድ ተቋማት ደግሞ ለግለሰቦች ከተጠቀሰው የጊዜ ገደብ በተጨማሪ የ3፣ የ6 እና የ9 ወር የሚመልሱበትን አሰራር አካትቷል።

ቴሌብር መላ “ለሥራ ማስኬጃ እንዲሁም አዳዲስ ሃሳብ ኖሯቸው ወደ ንግድ መግባት ለሚፈልጉ ሰዎችን ታሳቢ አድርጎ የቀረበ ነው። ለዚያ ነው በፋይናንስ አገልግሎት ተደራሽ ያልሆነውን ማኅበረሰብ፣ ተደራሽ ለማድረግ ትልቅ አቅም ይሆናል ብለን ያሰብነው” ሲሉም አክለዋል።   

መላ፣ እንደ ኪሴ እና ሰንዱቅ በተሰኙት የቴሌብር አገልግሎቶች በመጀመሪያ ዓመት ውስጥ በየወሩ በአማካኝ ከ3 እስከ 4 ሚሊዮን ደንበኞችን ለማገልገል እና ከ19.5 እስከ 20 ቢሊዮን ብር ለማንቀሳቀስ ማቀዱን ኃላፊዋ ጠቅሰዋል።

ከዚህም ውስጥ ትልቁን ድርሻ የሚወስደው የብድር አገልግሎቱ ወይም ቴሌብር መላ ሲሆን 9.8 ቢሊዮን ብር ይሸፍናል።

6.4 ቢሊዮን ብር ክፍያን ለማጠናቀቅ ወይም እንደ ኪሴ ለተባለው አገልግሎት እንዲሁም 3.3 ቢሊዮን ብር ደግሞ በቁጠባ ወይም ሳንዱቅ በተሰኘው አገልግሎት የሚጠቃለል ነው።

ደጋግመው ብድር የሚወስዱ ደንበኞችን ጨምሮ በዓመት 108 ሚሊዮን ደንበኞችን ለማገልገል ማታቀዱንም አስረድተዋል።

አገልግሎቶቹ በተጀመሩ በቀናት ውስጥ የዕለት ብድር ወስደው የሚመልሱ እንዲሁም የሚቆጥቡ ደንበኞች መኖራቸውን ያነሱት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ተስፋ ሰጪ እና “አስገራሚ” ሁኔታዎች መኖራቸው ገልጸዋል።

በቴሌብር መላ የሚሰጠው ብድር በሙሉ ዋስትና ወይም ማስያዣ እንደማይጠየቅበትም ጨምረው አስረድተዋል።

News today, social life

የኦሮሚያ ክልል ባህልና እሴትን የሚያሳይ ቋሚ የኦንላይን ኤግዚቢሽን በጎግል ላይ ተከፈተ

የኦሮሚያ ክልል ባህልና እሴትን የሚያሳይ ቋሚ የኦንላይን ኤግዚቢሽን በጎግል ላይ ተከፈተ
የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ያዘጋጀው “የቱሪዝምና ቴክኖሎጂ” ሳምንት ዛሬ ተከፈተ
በፎቶግራፍና በተንቀሳቃሽ ምስል የተደገፈው ኤግዚቢሽኑ “በጎግል አርት ኤንድ ካልቸር” ላይ መታየት ጀምሯል

የኦሮሚያ ክልል ባህል እና እሴትን የሚያሳይ ቋሚ የኢንተርኔት (ኦንላይን) ኤግዚቢሽን በጎግል ላይ በይፋ ተከፍቷል።

በኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን አዘጋጅነት የተሰናዳው ይህ የኢንተርኔት (ኦንላይን) ኤግዚቢሽን “በጎግል አርት ኤንድ ካልቸር” መተግበሪያ ላይ የሚገኝ መሆኑ ተነግሯል።

በኦሮሚያ ክልል የሚገኘው ወንጪ ሐይቅ ምርጥ የቱሪዝም መንደር ሆኖ በተመድ ተመረጠ
የኦንላይን ኤግዚቢሽኑ በዛሬው እለት በአዲስ አበባ መካሄድ በጀመረው “የቱሪዝምና ቴክኖሎጂ” ሳምንት ላይ በይፋ የተከፈተ ሲሆን፤ ኤግዚቢሽኑንም የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ አስጀምረውታል።

በኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ነጋ ዱፌራ ከአል ዐይን አማርኛ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ “በጎግል አርት ኤንድ ካልቸር” ላይ 21 የተለያዩ የክልሉን ባህል እና እሴት የሚያሳዩ ይዘቶች መጫናቸውን አስታውቀዋል።
“በጎግል አርት ኤንድ ካልቸር” ላይ የተጫኑት 21 ይዘቶች በክልሉ ባህላዊ መገልገያዎች፣ ምግቦች እና አለባበሶች ላይ ያተኮሩ መሆኑን አቶ ነጋ ዱፌራ አስታውቀዋል።

ሁሉም ይዘቶች “በጎግል አርት ኤንድ ካልቸር” መተግበሪያ ላይ መቀመጡን እና ማንኛውም ሰው መተግበሪያውን በማውረድ፤ ኢትዮጵያ ኦሮሚያ አሊያም ቪዚት ኦሮሚያ ሲል እነዚህ በምስል እና በጽሁፍ የተደገፉ ይዘቶች ማይት ይችላል ብለዋል።

“ጥምቀት በውኃ ላይ” በደምበል (ዝዋይ) ኃይቅ ላይ የተከበረው የከተራና ጥምቀት በዓል
እነዚህ ይዘቶች በቋሚነት እንደ ዲጂታል ሙዚየም በመተግበሪያው ላይ የሚቀመጡ መሆኑን እና በየትኛውም የዓለም ክፍል ያለ ሰው በማንኛውም ሰዓት ከፍቶ ሊመለከት የሚችለው እንደሆነ አቶ ነጋ ለአል ዐይን ገልጸዋል።

በተያያዘ የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ያዘጋጀው የቱሪዝም እና ቴክኖሎጂ ሳምንት በዛሬው እለት በስካይ ላይት ሆቴል በይፋ ተከፍቷል።

News today, social life

የዓለማችን ለኑሮ ምቹ የሆኑ 10 ከተሞች ይፋ ሆኑ


በዓለማችን ለኑሮ ምቹ የሆኑ 10 ከተሞች ይፋ ሆኑ። ከተሞቹ ምርጥ የተባሉት ለኑሮ ባላቸው ምቹነት መሠረት ነው።

አውሮፓዊቷ አገር የኦስትሪያ ዋና ከተማ ቪዬና ቀዳሚዋ የዓለማችን ምቹ ከተማ ተብላለች።

በተከታይነት ደግሞ የዴንማርክ ኮፐን ሃገን እና የስዊትዘርላንድ ዙሪክ ከተሞች ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃን ይዘዋል።

የካናዳ ከተማ የሆኑት ካልጋሪ እና ቫንኩቨር ደግሞ በአራተኝነት በቀጣይ ደረጃ ላይ የተቀመጡ ሲሆን፤ የስዊትዘላንዷ ጄኔቫ፣ የጀርመኗ ፍራንክፈርት፣ የካናዳዋ ቶሮንቶ፣ የኔዘርላንድስ አምስተርዳም፣ የጃፓን ኦሳካ እና የአውስትራሊያዋ ሜልበርን ቀዳሚዎቹን አስር ደረጃዎች ለመያዝ በቅተዋል።

ይህንን ደረጃ ይፋ ያደረገው ኢኮኖሚስት ኢንተለጀንስ ዩኒት እንደሚለው ከሆነ ከተሞች ለኑሮ ያላቸው ምቹነት ቢጨምርም ዓለም አቀፉ አማካይ ግን አሁንም ዝቅተኛ ነው ብሏል።

ለኑሮ ምቹነት ከታዩት ጉዳዮች አንዱ የኮሮናቫይረስ ስርጭት ተጽዕኖ መሆኑን ተጠቁሟል።

የዩክሬን ጦርነት ደግሞ ኪዬቭ ከጥናቱ ውጪ እንድትሆን ሲያስገድዳት፣ በሩሲያዎቹ ሞስኮ እና ሴንት ፒተርስበርግ ውጤት ላይም ተጽዕኖ አሳድሯል።

በዚሁ ጦርነት ምክንያት የምሥራቅ አውሮፓ ከተሞች ደረጃም ዝቅ ብሏል።

የምዕራብ አውሮፓ እና የካናዳ ከተሞች ደረጃውን በመምራት ቀዳሚ ሆነዋል።

ደማስቆ፣ ትሪፖሊ እና ሌጎስ ደግሞ ከማኅበራዊ አለመረጋጋት፣ ሽብር እና ግጭት ጋር ተተያይዞ በደረጃው መጨረሻ ላይ ለመገኘት ተገደዋል።

በዘንድሮው ጥናት 33 አዳዲስ ከተሞች ተካተዋል።

በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ያሉ ከተሞች ብዙ መሻሻል አላሳዩም ተብሏል።

የሶሪያዋ ደማስቆ በደረጃው የመጨረሻው ስፍራን ይዛለች።

ቴህራን፣ ዱዋላ፣ ሃራሬ፣ ዳካ፣ ፖርት ሞርስባይ፣ ካራቺ፣ አልጀርስ፣ ትሪፖሊ፣ ሌጎስ እና ደማስቆ ናቸው የመጨረሻዎቹን አስር ደረጃዎች የያዙት።

ለኑሮ ባላቸው ምቹነት መሻሻል ያሳዩ ከተሞችም ታይተተዋል።

እነዚህ ከተሞች በአብዛኛው በምዕራብ አውሮፓ የሚገኙ የጀርመን፣ የዩናይትድ ኪንግደም እና የፈረንሳይ ከተሞች ናቸው።

ፍራንክፈርት ካለፈው ዓመት 32 ደረጃዎችን በማሻሻል ሰባተኛ ደረጃ ላይ ለመቀመጥ በቅታለች።

ሃምቡርግ ደግሞ ከ31ኛ ወደ 16ኛ ተመንድጋለች።

የኒውዚላንድ እና የአውስታራሊያ ከተሞች ደግሞ ደረጃው ላይ ማሽቆልቆል አስመዝግበዋል።

በዚህም ዌሊንግተን እና ኦክላንድ 46 እና 33 ደረጃዎችን ለመውረድ ተገደዋል።

ድርጅቱ ይህን ደረጃ ለማውጣት የከተሞቹን መረጋጋት፣ የጤና ዘርፍ፣ ባህል እና አካባቢ፣ ትምህርት እና መሠረተ ልማት ከግምት ያስገባል።

ይህንን ደረጃ ይፋ ያደረገው ተቋም የዩክሬን ጦርነት እና ኮቪድ በሚቀጥለው ዓመት በሚኖረው የከተሞች ለኑሮ ምቹነት ደረጃ ላይ ተጽዕኖ ይኖራቸዋል ብለዋል።

ኢኮኖሚስት ኢንተለጀንስ ዩኒት ላለፉት 70 ዓመታት ኢኮኖሚያዊ ትንታኔዎች በመስጠት የሚታወቀው ሲሆን የዘ ኢኮኖሚስት ጋዜጣ እህት ኩባንያ ነው።

News today, social life

የአውስትራሊያው አየር መንገድ ባለሥልጣናት ሻንጣ በማውረድና በመጫን እንዲያግዙት ጠየቀ

ሻንጣ እያወረ ያለ ሰው

የአውስትራሊያው አየር መንገድ ካንታስ የጉልበት ሠራተኞች እጥረት ስላጋጠመው የአየር መንገዱ ከፍተኛ አመራሮች ሻንጣ በመጫን እና በማውረድ እንዲያግዙት ጠየቀ።

የአየር መንገዱን የዕለት ከዕለት የመንገደኞች ማስተናገድ ሥራውን የሚካታተለው ክፍል እንደገለጸው፣ ሲድኒ እና ሜልበርን ውስጥ በሚገኙ አየር ማረፊያዎች ቢያንስ 100 በጎ ፈቃደኛ የጉልበት ሠራተኞችን እንደሚፈልግ አስታውቋል።

ካንታስ የሚፈልጋቸው የጉልበት ሠራተኞች ሻንጣዎችን ከአውሮፕላኖች ላይ በማውረድና በመጫን እንዲሁም ሻንጣ የሚጫንባቸው ተሽከርካሪዎችን በአየር ማረፊያዎች ውስጥ የሚያንቀሳቅሱ ሾፌሮችን ነው።

በኮሮናቫይረስ ምክንያት አገራት ድንበሮቻቸውን ለአየር በረራዎች ዝግ አድርገው ከቆዩ በኋላ አሁን መክፈት በመጀመራቸው፣ ካንታስን ጨምሮ በዓለም ዙሪያ ያሉ አየር መንገዶች የተለያዩ ፈተናዎች እየገጠሟቸው ነው።

“ጉንፋን እና ኮቪድ በከፍተኛ ሁኔታ መሰራጨቱ እና በገበያው ላይ ሠራተኞችን ለማግኘት ያለው ፈተና አየር መንገዶች ሥራቸውን በተቀላጠፈ ሁኔታ እንዳያከናውኑ እንቅፋት ፈጥሯል” ሲሉ የካንታስ ባለሥልጣን የሆኑት ኮሊን ሁግስ ለቢቢሲ በኢሜይል ገልጸዋል።

“ያለው አማራጭ በከፍተኛ ኃላፊነት ላይ ሙሉ ጊዜያቸውን ወደሚሰሩ ሰዎች ፊትን ማዞር ነው” ሲሉም ሁግስ አክለዋል።

በዚህም ሳቢያ የካንታስ አየር መንገድ ሥራ አመራሮች ለቀጣይ ሦስት ወራት በፈረቃ፣ በቀን ለስድስት ወይም ለአራት ሰዓታት፣ በሳምንት ለሦስት ወይም ለአምስት ቀናት ሻንጣ የመጫን እና የማውረድ ሥራን እንዲያከናውኑ ተጠይቀዋል።

ካንታስ ባሰራጨው መልዕክት ላይ ለሻንጣ ጫኝነት እና አውራጅነት የሚያመለክቱ ኃላፊዎች ብቻቸውን አስከ 32 ኪሎ ግራም የሚመዝን ክብደት የማንሳት አቅም ሊኖራቸው ይገባል።

“አስካሁን ባለው ሥራችን የደንበኞቻችንን ፍላጎት እና የሚጠበቀውን ደረጃ ማሟላት እንዳላቻልን ግልጽ ነው፣ ስለዚህ ሥራችንን ለማሻሻል ሁሉንም ነገሮች ማድረግ ይጠበቅብናል” ሲሉ የካንታስ ቃል አቀባይ ለቢቢሲ ገልጸዋል።

አየር መንገዱ ከዚህም በፊት ከፍተኛ የመንገደኞች ቁጥር ለማስተናገድ በተገደደበት ጊዜ 200 የሚደርሱ የቢሮ ውስጥ ሠራተኞቹን በተመሳሳይ ሥራ ላይ እንዲያግዙት ማድረጉን አመልክቷል።

በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት አገራት የአየር ክልሎቻቸውን መዝጋታቸውን ተከትሎ ከባድ ቀውስ ከገጠማቸው አየር መንገዶች መካከል ካንታስ አንዱ ነው።

በዚህም ሳቢያ በመላው ዓለም ያሉ አየር መንገዶች በሺዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞቻቸውን መቀነሳቸው ይታወሳል።

አገራት የወረርሽኙን መስፋፋት ለመግታት ወስደዋቸው የነበሩትን ጥብቅ እርምጃዎችን በአሁኑ ወቅት ማላላት በመጀመራቸው ካንታስ እና ሌሎች አየር መንገዶች ሥራቸውን በቀደመው መልኩ ለማካሄድ ፈተና ገጥሟቸዋል።

News today, social life

ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የኮሮና ክትባቶችን አልተከተቡም መባሉ እያነጋገረ ነው

ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የኮሮና ክትባቶችን አልተከተቡም መባሉ እያነጋገረ ነው

ዶ/ር ቴድሮስ እንዳልተከተቡ የሚሳዩ ናቸው በሚል የተለቀቁ ተንቀሳቃሽ ምስሎች ሃሰተኛ መሆናቸውንም ድርጅቱ አስታውቋል
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም የኮሮና ክትባቶችን አልተከተቡም መባሉ እያነጋገረ ነው።

ዶ/ር ቴድሮስ አለመከተባቸውን የሚያሳዩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች (ቪዲዮ) ተለቀዋል።
የምስሎቹን እውነተኛነት ያጣጣለው የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተሩ አልተከተቡም መባሉን ያለ ሲሆን፤ የድርጅቱ ከፍተኛ ኃላፊዎች ሳይቀሩ ጉዳዩን በማስተባበል ላይ መሆናቸውም ነው የተነገረው።

ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር በመሆን በድጋሚ ተመረጡ 
በተለያዩ የማህበረሰብ ትስስር ገጾች በመዘዋወር ላይ ያለው ቪዲዮ ዶ/ር ቴድሮስ በአንድ ጆን ኮኸን በተባለ ሰው መቼ እንደተከተቡ ሲጠየቁ እና ክትባቶቹ በአፍሪካ በተለይም ኢትዮጵያ እስከሚደርሱ ድረስ ሳይከተቡ እንደሚቆዩ ሲናገሩ ያሳያል።

ሆኖም ቪዲዮው ሃሰተኛ ነው ሲል ድርጅታቸው አስተባብሏል። እንዲህ ዐይነቱ የፈጠራ ወሬ ወረርሽኙን ለመቆጣጠር አሁንም በመደረግ ላይ ያሉ ጥረቶችን ይጎዳል ሲልም ነው ጉዳዩን ባስተባበለበት ጽሁፉ የገለጸው።
እንደ ድርጅቱ ከሆነ ዶ/ር ቴድሮስ ባለፈው ዓመት ግንቦች ላይ የመጀመሪያውን ክትባት ወስደዋል። ከዚያም ወዲህ የማጠናከሪያ ክትባቶችን ተከትበዋል።

የድርጅት ቃል አቀባይ ጋቢ ስተርን ትናንት እሁድ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ “ውሸታሞች ሲዋሹ እና ህይወትን አደጋ ላይ ሲጥሉ እርምጃ መወሰድ አለበት” ብለዋል፤ መጻፋቸው በዶ/ር ቴድሮስ ላይ የተነዛውን ውሸት ለማስተባበል እንደሆነ በመጠቆም።
“ቁም ነገሩ ክትባቶች ህይወትን መታደጋቸው ነው”ም ብለዋል ቃል አቀባዩ።
ዶ/ር ቴድሮስን ጠያቂው ጆን ኮኸን ዋና ዳይሬክተሩ አልተከተብኩም በሚል የተናገሩት ነገር እንደሌለ ተናግሯል።

ባሳለፍነው ሰኔ በሳይንስ መጽሄት ላይ የወጣ መጣጥፍ ዶ/ር ቴድሮስ በባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት 2021 ግንቦት ላይ መከተባቸውን ያትታል።
ክትባቶች እያሉ ቀደም ብለው ለምን እንዳልተከተቡ የተጠየቁት ዋና ዳይሬክተሩ “ኢትዮጵያ ከምትባል ደሃ ሃገር እና አፍሪካ ከሚባል ደሃ አህጉር መምጣቴን አውቃለሁ፤ ስለሆነም አፍሪካ እና ሌሎች ደሃ እና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሃገራት ክትባቱን እስከሚያገኙ ለመጠበቅ እፈልግ ነበር” ሲሉ መመለሳቸውንም ያስቀምጣል።

“ከኮሮና ክትባቶች ጋር በተያያዘ ዓለም ‘አስከፊ’ የሞራል ውድቀት እየደረሰበት ነው”- ቴድሮስ አድሃኖም (ዶ/ር)
በሌላ አገላለጽ ኢ-ፍትሐዊውን የክትባቶች ስርጭት በድርጊት እየተቃወሙ መሆኑንም ነው ዶ/ር ቴድሮስ የሚናገሩት።

ሆኖም አሁን በማህበራዊ ሚዲያዎች በመዘዋወር ላይ ያለው አጭር ቪዲዮ ይህን ምላሻቸውን በማካተት ከተዘጋጀ ዘጋቢ ፊልም (ዶክመንታሪ) ላይ ብዙዎችን ሊያሳስት በሚችል መልኩ ተቀንጭቦ መለቀቁን ነው ተቋማቸው ያስታወቀው።

News today, Politics, social life

ሩሲያ በ62 ካናዳዊያን ላይ ማዕቀብ ጣለች

የሞስኮ ማዕቀብ ካናዳ ከዚህ በፊት በሩሲያዊያን ላይ ለጣለችው ማዕቀብ የአጸፋ እርምጃ ነው ተብሏል

ሩሲ እና ካናዳ

ሩሲያ ካናዳዊያን ዲፕሎማቶች፣ የሀይማኖት መሪዎች፣ ፖለቲከኞችና ምሁራን ላይ ነው ማዕቀብ ጣለችው

ሩሲያ በ62 ካናዳዊያን ላይ ማዕቀብ መጣሏን አስታውቃለች።

ሩሲያ ዩክሬን የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ጦር ወይም ኔቶን እቀላቀላለሁ ማለቷን ተከትሎ ነበር ወደ ይፋዊ ጦርነት የገባችው።

 ይሄንን ጦርነት ተከትሎም በሩሲያ ላይ ከ6 ሺህ በላይ ማዕቀቦች ሲጣልባት ከ400 በላይ ዲፕሎማቶቿ ደግሞ ከተለያዩ ሀገራት ተሰናብተዋል።

ካናዳም የሩሲያ ዲፕሎማቶችን ከማባረሯ ባለፈ በሩሲያ ጋዜጠኞች ፣ ባለሀብቶች እና ሌሎች ዲፕሎማቶች ላይ ማዕቀብ ጥላለች።

የሩሲያ ውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ባወጣው መግለጫ ካናዳ ለወሰደችው ማዕቀብ ምላሽ በ62 ካናዳዊያን ላይ ማዕቀብ ጥላለች።

ይህ ማዕቀብ የተጣለባቸው ካናዳዊያን ወደ ሩሲያ እንዳይገቡ እና በሩሲያ ያላቸው ሀብት እንዳይንቀሳቀስ እንደሚደረግ ሮይተርስ ዘግቧል።

ሩሲያ ከዩክሬን ጦርነት ጋር በተያያዘ በሀገሪቱ እንዲሁም በተቋማቶቿ እና ባለሃብቶቿ ላይ ማዕቀብን ጨምሮ የተለያዩ እገዳዎችን የጣሉ እርምጃዎቹን የደገፉ ሀገራትን “ወዳጅ አይደሉም” ማለቷ ይታወሳል።

News today, Politics, social life

ሩሲያ ቱርክ በሩብል ለመገበያየት ተስማሙ


የሩሲያ እና የቱርክ ፕሬዝደንቶች በትናንትናው እለት በሩሲያ ሶቺ ከተማ ተገናኝተው መክረዋል

ሩሲያ እና ቱርክ፤ በሩሲያው ገንዘብ ሩብልስ ለመገበያየት ተስማምተዋል፡፡

የሩሲያ እና ቱርክ መሪዎች በትናንትናው እለት በሩሲያዋ ሶቺ ከተማ ባደረጉት ውይይት የኢኮኖሚ ትብብር ስምምነት መፈረማቸውን የሩሲያ አርቲ ሚዲያ ዘግቧል፡፡

ሩሲያ ያለባትን የውጭ ሀገራት እዳ በራሷ ገንዘብ “ሩብል” እንደምትከፍል አስታወቀች
ስምምነቱ መፈረሙን የገለጹት የቱርኩ ፕሬዝደንት ረሲፕ ተይፕ ኤርዶጋን ናቸው፡፡

ሩሲያ እና ዩክሬንን የማደራደር ሚያ ያላት ቱርክ ከሩሲያ ጋር በሩብልስ ለመገበያየት መስማማቷን ፕሬዘደንት ኤርዶጋን ተናግረዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ጣይብ ኤርዶጋን አርብ ዕለት በቱርክ እና በሩሲያ ልዑካን መካከል የተካሄዱት ስብሰባዎች ፍሬያማ እንደነበሩ እና በሩሲያ በሚያደርጉት ጉብኝት በሶሪያ ስላለው ሁኔታ ከሩሲያ አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር እንደሚመክሩ ተናግረዋል።

ሩሲያ በዩክሬን “ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ” ከጀመረች በኋላ ሩሲያ አሜሪካን ጨምሮ ከምእራባውያን ጋር ሁሉን አቀፍ ፍጥጫ ውስጥ ገብታለች፡፡

አሜሪካን ጨምሮ ምእራበውያን ሀገራት ሩሲያን ያዳክማል ያሉትን ማእቀብ ሁሉ በሩሲያ ላይ አዝንበዋል፤ ሩሲያ ማእቀቡን ለመመከት ምእራባውያን ሀገራት ጋዝ በሩብል እንዲገዙ አስገድዳለች፡፡

News today, Politics, social life

በእስራኤል ጥቃት አንድ የታጣቂ ቡድን መሪን ጨምሮ አስር ሰዎች ተገደሉ


እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ በፈጸመችው የአየር ጥቃት አንድ የፍልስጤም ታጣቂዎች ቡድን መሪን እና አንዲት ህጻንን ጨምሮ 11 ሰዎች መገደላቸውን ሪፖርቶች አመለከቱ።

ይህን የእስራኤል ጥቃት ተከትሎ በደርዘኖች የሚቆጠሩ ሮኬቶች ከጋዛ ወደ እስራኤል የተተኮሱ ሲሆን፣ በዚህም ሳቢያ በአካባቢው ከባድ ውጥረት ነግሷል።

ይህንንም ተከትሎ እስራኤል በወረራ በያዘችው የዌስት ባንክ አካባቢ ባደረገችው አሰሳ 19 የኢስላሚክ ጂሃድ ቡድን አባላት ናቸው የተባሉ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሏ ተገልጿል።

በእስራኤል ጥቃት ከተገደሉት 11 ሰዎች መካከል ታይሰር ጃባሪ የተባለ የታጣቂዎች መሪ ይገኝበታል።

የአየር ጥቃቱ ግለሰቡ የሚመራው የፍልስጤም እስላማዊ ጂሃድ የተባለው ቡድን “ጥቃት ሊሰነዝር” መሆኑን ተከትሎ የተወሰደ እርምጃ ነው ስትል እስራኤል ምክንያቷን አሳውቃለች።

ከተገደሉት መካከል የአምስት ዓመት ታዳጊ የምትገኝበት ሲሆን፣ ሌሎች በርካቶች ደግሞ የመቁሰል ጉዳት እንደደረሰባቸው የአካባቢው የጤና ባለሥልጣናት ተናግረዋል።

የፍልስጤም እስላማዊ ጂሃድ የተባለው ቡድን ለእሰራኤል ጥቃት “የመጀመሪያ ምልሽ” ባለው አጸፋ ከ100 በላይ ሮኬቶችን ወደ እስራኤል ሌሊቱን ተኩሷል።

ከተተኮሱት ሮኬቶች አብዛኞቹ በእስራኤል የሚሳኤል መከላከያ አማካይነት መክሰማቸው የተነገረ ሲሆን፣ በበርካታ የእስራኤል ከተሞች ውስጥ ሌሊቱን በሙሉ የጥቃት ማስጠንቀቂያ ደውሎች ሲሰሙ አድረዋል።
የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር እስከ ቅዳሜ ንጋት ድረስ የዘለቁ የሮኬት ጥቃቶችን ጋዛ ውስጥ በሚገኙ በርካታ የታጣቂዎቹ ይዞታዎች ላይ ሲፈጽም ማደሩን ኣሰውቋል።

ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ተመሳሳይ ግጭት ተከስቶ ከ200 በላይ ፍልስጤማዊያን እና በርካታ እስራኤላውያን ከተገደሉ በኋላ በግብፅ አደራዳሪነት የተኩስ አቁም መደረሱ ይታወሳል።

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ያይር ላፒድ ሠራዊታቸው ለአገራቸው ስጋት በሆኑ ኢላማዎች ላይ ፈጣን ፀረ ሽብር ጥቃት መፈጸሙን የገለጹ ሲሆን፣ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ደግሞ ግጭቱ የተራዘመ ሊሆን እንደሚችል ስጋታቸውን አመልክተዋል።

ጋዛ ውስጥ በእስላማዊ ቡድን ኢላማዎች ላይ ነው የተፈጸመው በተባለው ጥቃት “15 የሚሆኑ ታጣቂዎች” መገደላቸውን የእስራኤል ሠራዊት ቃል አቀባይ መናገራቸው ተዘግቧል።

የጋዛ የጤና ባለሥልጣንት ግን ታይሲር ጃባሪን ጨምሮ አራት የእስላማዊ ቡድኑ ታጣቂዎች በእስራኤል ጥቃት መገደላቸውን አረጋግጠዋል።

የእስራኤል የመከላከያ ኃይል ታይሲር ጃባሪ የፍልስጥኤም እስላማዊ ጂሃድ ቡድን “ከፍተኛ መሪ” መሆኑን እና “በርካታ የሽብር ጥቃቶችን” በእስራኤላውያን ሰላማዊ ሰዎች ላይ ፈጽሟል ሲል ይከሰዋል።

የጋዛ ባለሥልጣናት እንዳሳወቁት በጥቃቱ ከተገደሉት ሰዎች በተጨማሪ 79 ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው መናገራቸውን የፈረንሳይ ዜና ወኪል ዘግቧል።

የፍልስጥኤም እስላማዊ ጂሃድ ቡድን ዋና ፀሐፊ ዚያድ አል-ናኻላ ወደ ኢራን በጉዞ ላይ ሳሉ “ለተፈጸመው ጥቃት በሙሉ ኃይላችን ምላሽ እንሰጣለን፣ በአሸናፊነት የምንወጣበት ጦርነት ይሆናል። የማይነካ ቦታ አይኖርም፣ ቴል አቪቭ በሮኬቶቻችን ጥቃት ስር ትሆናለች” ማለታቸው ተዘግቧል።

የጋዛ ሰርጥን የሚያስተዳድረው ሐማስ የፍልስጤም ታጣቂ ቡድኖች ዝም እንደማይሉና በሚካሄደው ዘመቻ ውስጥ በአንድነት እንደሚቆሙ ገልጿል።

News today, social life

ሩሲያ ለኢትዮጵያ 162 ሚሊዮን ዶላር ብድር መሰረዝዋን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሩሲያ ለኢትዮጵያ 162 ሚሊዮን ዶላር ብድር መሰረዝዋን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።

ቃል አቀባዩ በዚህ ጊዜ እንዳሉት የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በኢትዮጵያ ያደረጉት ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የበለጠ ያጎለብተዋል ብለዋል።

ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት በተለያዩ ጊዜያት ከሶቭየት ህብረት የተበደረቻቸውን ብድሮች መሰረዟን በይፋ አሳውቃለች ብለዋል።

ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት ከሶቭየት ህብረት ወይም አሁን ላይ ሩሲያ ተብላ ከምትጠራው ሀገር 162 ሚሊዮን ዶላር የተበደረችውን ገንዘብ ሰርዛለች ያሉት አምባሳደር መለስ በብድር መልክ ሊከፈል የነበረው ገንዘብ ለምን አገልግሎት መዋል እንዳለበትም ሁለቱ ሀገራት ተስማምተዋልም ብለዋል።

ኢትዮጵያ ለሩሲያ በብድር መልክ ልትከፍለው የነበረው 162 ሚሊዮን ዶላር ባልቻ ሆስፒታልን እና መልካ ዋከና የሀይል ማመንጫ ጣቢያ ለማዘመን እንዲውል መስማማታቸውም ተገልጿል።

ቃል አቀባዩ አቶምባሳደር መለስ በመግለጫቸው አክለውም፣ በኢትዮጵያ በህገወጥ መንገድ ይኖሩ የነበሩ የውጭ ሀገራት ዜጎች ምዝገባ መጀመሩን እና እስካሁን 60 ሺህ ሰዎች መመዝገባቸውን ተናግረዋል።

በእስካሁኑ ምዝገባ የካናዳ፣ አሜሪካ፣ኮንጎ፣ ናይጀሪያ ፣ የመን፣ ሶሪያ፣ ኤርትራ ፣ሱዳን፣ቻይና፣ ቡሩንዲ ጋና፣ ህንድ፣ ባንግላዲሽ፣ ላይቤሪያ፣ ጣልያን እና የካሜሩን ዜግነት ያላቸው ህገወጥ ሰዎች መገኘታቸው ተገልጿል።

በዚህ ምዝገባ የተካተቱት በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ኢትዮጵያ የገቡ የቪዛ ጊዜያቸው የለፈበት፣ በህጋዊ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ፣ የስደተኝነት ፈቃድ የሌላቸው እና ፈቃድ ለማግኝት በሂደት ላይ ያሉ የውጭ ሀገራት ዜጎች ናቸው ተብሏል።

ዲፕሎማቶች፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እና ህጋዊ ቪዛ ያላቸው የውጭ ሀገራት ዜጎች በምዝገባው እንደማይካተቱም ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።

ህገወጥ የውጭ ሀገራትን የመመዝገብ ስራው በአዲስ አበባ 21 ቦታዎች፣ የኢምግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ቅርንጫፎች ሰበታ፣ ቡራዩ፣ ሆለታ፣ሱሉልታ፣ ለገጣፎ፣ ገላን እና ዱከም ከተሞች እየተመዘገቡ እንደሆነ ተገልጿል።

የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀመድ ግብጽን ከጎበኙ በኋላ በካይሮ ስለ ህዳሴው ግድብ ተናገሩት ተብሎ የወጣውን መረጃ የሶማሊያ መንግሥት አቋም እንዳልሆነ ኢትዮጵያ ትረዳለችም ሲሉ አምባሳደር መለስ በመግለጫቸው ተናግረዋል።

በግብፅ ብዙሃን መገናኛዎች የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ከግብጽ አቻቸው ጋር በጋራ ሆነው ተናገሩት ተብሎ የወጣው ዘገባ የአንድ ወገን አስተያየት ነው፣ በመሆኑም የሶማሊያ መንግስት በይፋ ስለ ህዳሴው ግድብ ያወጣው መግለጫ እንደሌለም ተገልጿል። 

News today, social life

ስለቀጠለው የወለጋ ጥቃት

አቶ ደመቀ መኮንን ”በወለጋ ተጨማሪ ጥቃትና ጭፍጨፋ እንዳይከሰት ነዋሪው ራሱን በተደራጀ መልኩ እንዲከላከል ይደረጋል” አሉ

ም/ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፤ በዜጎች ላይ ተጨማሪ ጥቃትና ጭፍጨፋ እንዳይከሰት በሁሉም አካባቢዎች ተጋላጭ ቀበሌዎችንና መንደሮችን በመለየት አስፈላጊው ጥበቃ እንደሚደረግ ገለጹ።

ከዚህ ባለፈም ነዋሪው ራሱን በተደራጀ መልኩ እንዲከላከል የሚሊሻ እና የኮሙኒቲ ፖሊሲንግ ስርዓት ተጠናክሮ እንዲቀጥል እንደሚደረግም ነው አቶ ደመቀ የገለጹት።