News today, Politics, social life, Technology

በ11 የአለም ዋንጫዎች ላይ የታደሙት ብራዚላዊ

የመጀመሪያ የአለም ዋንጫ ጨዋታን በአርጀንቲና በ1978 የተመለከቱት ዳኔል ስብሩዚ በኳታርም የአለም ዋንጫ ጨዋታዎችን ተከታትለዋል

“የአለም ዋንጫን መመልከት ከአዳዲስ ባህልና ልምድ ጋር መተዋውቅ ነው ፤ በ2026ቱ የአለም ዋንጫ ለመታደምም ዝግጁ ነኝ” ብለዋል

11 የአለም ዋንጫዎችን የተመለከቱት ብራዚላዊ በድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ስማቸውን ማስፈር ችለዋል።

ዳኔል ስብሩዚ የተባሉት የ76 አመት አዛውንት የሳኦሎ ከተማ ነዋሪ ናቸው።

ስብሩዚ በ1978 ወደ አርጀንቲና በማቅናት የመጀመሪያ የአለም ዋንጫ ጨዋታን ከተመለከቱ ወዲህ አለምን በኳስ ምክንያት ዞረዋል።

የዘንድሮውን የኳታር የአለም ዋንጫ ለመታደምም ዶሃ ገብተው ሰንብተዋል።

የ76 አመቱ አዛውንት በዶሃ 11ኛ የአለም ዋንጫ ጨዋታን ሲመለከቱም የአለም የድንቃድንቅ መዝገብ ክብረወሰን ይዘዋል በሚል የምስክር ወረቀት ሰጥቷቸዋል።

የአለም ዋንጫን መመልከት ከአዳዲስ ባህልና ልምድ ጋር መተዋውቅ ነው የሚሉት ስብሩዚ ፤ የአለም ዋንጫ ከመልከ ብዙ ተሰጥኦ ባለቤቶች ጋር የሚያገናኝ መድረክ መሆኑን አንስተዋል።

ከአርጀንቲና እስከ ኳታር አለም ዋንጫን ለመመልከት ሲጓዙም የብራዚልን ባህልና ወግ ሲያስተዋውቁ እንደነበር ተናግረዋል።

ባለፉት 44 አመታት በተለያዩ አልባሳት አጊጠው ብራዚልን እየደገፉ የሳኦ ፖሎን ባህል በስፋት ያስተዋወቁት ስፖርት አፍቃሪ፥ የአለም ዋንጫን በስታዲየም ከመመልከት የሚያስቆመኝ ሞት ብቻ ነው እያሉ ነው።

አሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ በጋራ በሚያዘጋጁት የ2026 የአለም ዋንጫ ለምታደምም ፍላጎታቸውን ገልጸዋል።

በዚህም በራሳቸው የተያዘውን ክብረወሰን ለማሻሻል ተስፋ አድርገዋል።

News today, Politics, social life, Technology

አርጀንቲና የኳታሩን የአለም ዋንጫ ያነሳችበት ጨዋታ በምስል

አርጀንቲና ለ3ኛ ጊዜ የዓለም ዋንጫን አንስታለች

የአርጀንቲና ብሄራዊ ቡድን

አርጀንቲና በመለያ ምት 4 ለ 2 ፈረንሳይን አሸንፋለች

በሉሳይል ስታዲየም የተደረገው ልብ አንጠልጣይ ፍልሚያ በአርጀንቲና አሸናፊነት ተደምድሟል።

አርጀንቲና ሶስት ጊዜ መርታ አቻ በሆነችበት ምሽት ሌዮኔል ሜሲ ሁለት ጎሎችን አስቆጥሯል።

ውሃ ሰማያዊ እና ነጭ ለባሾቹ በመጀመሪያው አጋማሽ 2 ለ 0 እየመሩ ቢወጡም ፈረንሳይ በኪሊያን ምባፔ የ80 እና 81ኛ ደቂቃ ሁለት ጎሎች አቻ ሆናለች።

በተጨማሪ 30 ደቂቃውም ሜሲ ሶስተኛውን ጎል ለሀገሩ ቢያስቆጥርም የፈረንሳዩ የ23 አመት ኮከብ ኪሊያን ምባፔ ባስቆጠራት ሶስተኛ ጎል ጨዋታው በመለያ ምት ተጠናቋል። በዚህም አርጀንቲና 4 ለ 2 በሆነ የፍጹም ቅጣት ምት ጎል አሸናፊ ሆናለች።

ሊዮኔል ሜሲ ከ36 አመት በፊት ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና ያሳካውን ክብር በደገመበት ምሽት የብራዚላዊውን ፔሌ የጎል አስቆጣሪነት ክብር ማሻሻል ችሏል።

የ35 አመቱ ሜሲ በ26 የአለም ዋንጫ ጨዋታዎች ተሰልፎ 13 ጎሎችን በማስቆጠሩም በብራዚላዊው ፔሌ ተይዞ የቆየውን ክብረወሰን ማሻሻል ችሏል።

አርጀንቲና በዛሬው የሉሳይል ስታዲየም ፍልሚያ ድል ማድረጓን ተከትሎ በመጀመሪያው የምድብ ጨዋታ ተሸንፋ (በሳኡዲ አረቢያ) ዋንጫውን በመውሰድ ስፔን በ2010 የያዘችውን ሪከርድ ተጋርታለች።

የላቲን አሜሪካዋ ሀገር ፈረንሳይን በመርታት ሶስተኛ ዋንጫዋን አንስታለች።

አርጀንቲና በ1978 ፣ 1986 እና በኳታር የዓለም ዋንጫን ወስዳለች።

News today, Politics

ጠ/ሚ ዐቢይ “የወሰን ውዝግብ ያለባቸው አካባቢዎች በህግ አግባብና በምክክር ይፈታሉ” አሉ

መንግስት “ሌብነት” ለመዋጋት በሀገራዊ ኮሚቴ ጥናት እያደረገ መሆኑን አስታውቋል

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ስለ ሰላም ስምምነቱ “ምን እንደሚመጣ ከወዲሁ መናገር አይቻልም” ብለዋል

የኢትዮጵያ ርዕሰ ብሄር ፕሬዝዳንት ሳህለ-ወርቅ ዘውዴ መስከረም 30፤ 2015 ዓ.ም በሁለቱ ም/ቤቶች መክፈቻ የመንግስትን የትኩረት አቅጣጫ አሳውቀዋል።

በዚህ የመንግስት የትኩረት አቅጣጫና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ለመስጠት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኙት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ከሀገሪቱ ጠቅላላ ምጣኔ-ሀብት እስከ ፖለቲካ ባህል፤ ከሰላም ስምምነቱ እስከ ደህንነት ስጋቶች ድረስ ከም/ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች መልስና ማብራሪያ ሰጠተዋል።

የሁለት ዓመታትን ጦርነት ይገታል ተብሎ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ስለተደረሰው ሰላም ስምምነትና ስጋት ጥያቄ የተነሰላቸው ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ “ሰላምና ብልጽግናን ለማስቀጠል ሲባል ጦርነትን ማስቆም የግድ ብሏል” ብለዋል።

የኢትዮጵያን ህልውናና አንድነት የሚገዳደር ሲፈጠር ግን “መፋለም” የግድ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ፤ አሉ ያሏቸውን ሰላም የሚያስከፋቸው ኃይሎችን አሳስበዋል።

ስለ ስምምነቱ ውጤት ሲናገሩም “ምን እንደሚመጣ ከወዲሁ መናገር አይቻልም” ብለዋል። “ሌላውን ተወያይተን ፈር እናስይዘዋለን” በማለትም የስምምነቱ ቀጣይ ድርድሮችና ውይይቶች እንደሚኖሩ ጠቁመዋል።

የምክር ቤቱ አባላት የሚያወዛግቡ አካባቢዎች በፕሪቶሪያው ስምምነት “በህገ-መንግስቱ ምላሽ ይሰጣቸዋል” መባሉ ላይ ጥያቄ አንስተዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ከወልቃይትና ራያ ጀርባ “ሽረባ” አለ ያሉ ሲሆን፤ ለዚህም የመንግስታቸው እጅ እንደሌለበት ተናግረዋል።

በተለይም የወልቃይት ጉዳይ ላይ አተኩረው ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚንስትር አብይ፤ ወልቃይት “የሁለት ህዝቦች ድልድይ ነው” መሆኑን አስምረዋል።

ወዝግቡ በህግ አግባብና በምክክር የሚፈታ ነው ብለዋል። ለወልቃይት “ዲሞክራሲያዊ እድል” መሰጠት አለበት ሲሉም ውዝግቡ በስምምነት እልባት እንደሚያገኝ ጠቁመዋል።

በአጠቃላይ መንግስታቸው ከስምምነቱ ማግስት ሶስት ጉዳዮች ላይ አተኩሮ እየሰራ መሆኑን ያሳወቁት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ እርዳታ ማቅረብ፣ የወደሙ መሰረተ-ልማቶችን መገንባት እና ተፈናቃዮች መመለስ ላይ መጠመዱን ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ስለ ሀገሪቱ ሰላምና ደህንነት ሲያብራሩ በተለይም ሸኔ ስለተባለው ታጣቂ ቡድን “ፍላጎቱ አይታወቅም” ብለዋል።

መንግስት “ለሰላም ሁሌም በሩ ክፍት ነው” ብለዋል። ህገ-መንግስቱን ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ለመነጋገገር በመንግስት በኩል አቋም እንዳለም ጠቁመዋል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ በታጣቂው ላይ እየተወሰደ ስላለ እርምጃ ዝርዝር ማብራሪያ ባይሰጡም “ውጤቱ በተጠበቀው ልክ አመርቂ ባይሆንም ስራዎች እየተሰሩ ነው” ሲሉ እየተወሰደ ስላለ ወታደራዊ እርምጃ ፍንጭ ሰጥተዋል።

ህገ-መንግስታዊ መብት ስለሆነው ተንቀሳቅሶ የመስራት መብትም ከምክር ቤቱ አባላት ጥያቄ ተነስቷል።

ህገ-መንግስታዊ መብት ስለመሆኑ ያልሸሸጉት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ ሆኖም ለሀገር ሰላም ሲባል መጉላላት እንደ ትልቅ ነገር መታየት እንደሌለበት ገልጸዋል።

ይልቁንም መንገደኞች ለፍተሻ እንዲተባበሩ ጠቁመዋል። “ወጣቶች ብር ተከፍሏቸው አዲስ አበባን ለማሸብት ይሞክራሉ” ያሉም ሲሆን፤ በዚህም የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች እየተያዙ ነው ብለዋል።

ስለ ኢትዮጵያ የፖለቲካ ባህል አስተያየታቸውን የሰነዘሩም ሲሆን፤ “የኢትዮጵያ የፖለቲካ ባህል ችግር አለበት” ሲሉም ብቃት መመዘኛ እንዳልሆነ ተናግረዋል።። “ሰፈር ነው የሚታየው” በማለትም “ብሄር” በፖለቲካው መንገሱን ጠቁመዋል። ይህም ባህል እየሆነ ሲሄድ አደገኛ ነው በማለት “በስራ ሳይሆን በጩኸት ለውጥ ይመጣል ብለው የሚፈልጉ ሰዎች የሚያመጡት ነው” ሲሉ አሳስበዋል።

“የሽግግር መንግስት እያሉ የሚጮሁ አሉ፤ ስትጮሁ ትኖራላችውሁ፤ የኢትዮጵያን ክንፍ ነው የምትቆርጡት፤ ጥንቃቄ እናድርግ” ብለዋል።

ስለ ሙስና በሀገሪቱ መንግስት ያነሱት ጠቅላይ ሚንስትር አብይ “ችግርን እንደ እድል የወሰዱ ሰዎች ቀይ መስመርን ቀይ ምንጣፍ አድርገዋል” በማለት ሌብነት በመንግስት መዋቅር ስር መስደዱን ለምክር ቤቱ አባላት ተናግረዋል።

 ሌብነት ከልምምድ እንደ መብት እየተወሰደ በመሆኑ መንግስት ተወያይቶ ሀገራዊ ኮሚቴ በማቋቋም ጥናት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

“ክሱ ብዙ ነው፤ እጅ የማይጠቆምበት ሰው የለም” በማለትም ህዝቡ ማስረጃ እንዲያቀርብ ጠይቀዋል።

News today, Politics

ኢትዮጵያ ተመድ ሩስያ ለዩክሬን ካሳ እንድትከፍል ያቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ በመቃወም ድምጽ ሰጠች

የውሳኔ ሃሳቡን ኢትዮጵያን ጨምሮ 14 ሀገራት የተቃወሙት ሲሆን 73 ሀገራት ደግሞ ድምፅ ከመስጠት ታቅበዋል

ይህም ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ ሀገራት ያልደገፉት የውሳኔ ሀሳብ ሆኖ እንዲመዘገብ አድርጎታል

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ትናንት ማምሻውን በሩስያ ላይ ያቀረበው አዲስ የውሳኔ ሃሳብ ተቃውሞ ገጥሞታል።

ኢትዮጵያን ጨምሮ 14 ሀገራት ሩስያ በዩክሬኑ ጦርነት ላደረሰችው ጉዳት ካሳ እንድትከፍል የሚያስገድደውን የውሳኔ ሀሳብ ተቃውመውታል።

አረብ ኤሚሬትስን ጨምሮ 73 ሀገራት በድምፀ ተአቅቦ ማለፋቸውን ተከትሎም የዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ የመንግስታቱ ድርጅት ካወጣቸው አምስት የውሳኔ ሀሳቦች ሁሉ ይሁንታ የተነፈገው ሆኖ ተመዝግቧል።

የውሳኔ ሀሳቡ በጦርነቱ ለተገደሉና ለቆሰሉ ዩክሬናውያን ሞስኮ ካሳ እንድትከፍል የሚጠይቅ ነው።

በጦርነቱ የጠፋውን የሰው ህይወትና የደረሰውን የንብረት ውድመት የሚያጣራ አለም አቀፍ ቡድን እንዲዋቀርም ተመላክቷል በዚሁ የውሳኔ ሀሳብ።

ዩክሬን – “የውሳኔ ሃሳቡ ፍትህ ለማስፈን ትልቅ ተስፋ ነው”

በመንግስታቱ ድርጅት የዩክሬን አምባሳደር ሰርጌ ኪይልይስታይ፥ ሩስያ ዩክሬንን ለማፈራረስ የመጨረሻ አቅሟን ተጠቅማለች ብለዋል።

“ከመኖሪያ ህንፃዎች እስከ ትምህርት ቤቶችና ሆስፒታሎች ያላፈራረሰችው የህዝብ ተቋም የለም፤ ባለፈው ወር ብቻ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ ጥቃት አድርሳ ግማሽ ዩክሬን በጨለማ ተውጧል” ነው ያሉት አምባሳደሩ።

የሩስያ ወታደሮች ይዘዋተው በቆዩ የዩክሬን ከተሞች የፈፀሟቸውን ወንጀሎችም በማንሳት ሞስኮ ተጠያቂ እንድትሆን የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ አድንቀዋል።

ዩክሬንን መልሶ የመገንባቱ ስራ ሲካሄድ በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸውን የመካስ እና ፍትህን የማስፈኑ ጉዳይም እኩል ሊካሄድ እንደሚገባም አብራርተዋል።

ኬቭ በጦርነቱ የደረሰውን ጉዳት ሳትጨምር ሳትቀንስ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ይፋ ለማድረግ መዘጋጀቷንም በመጥቀስ የውሳኔ ሃሳቡን ፍትህን ለማስፈን የተስፋ ብርሃን ነው ብለውታል።

ሩስያ – “የውሳኔ ሀሳቡ ህጋዊ ያልሆነና ተፈፃሚነት የሌለው ነው”

በመንግስታቱ ድርጅት ሩስያን የወከሉት ቫስሊ ንቤንዚያ በበኩላቸው፥ የውሳኔ ሀሳቡ በአለም አቀፉ ህግ ተቀባይነት የሌለውን ነገር ህጋዊ ለማስመሰል የሞከረና ተፈፃሚነት የሌለው ነገር ነው በሚል ተቃውመውታል።

ምዕራባውያን እንዳይንቀሳቀስ ያገዱትን በቢሊየን ዶላር የሚቆጠር የሩስያ ሃብት ለመዝረፍ የተቀነባበረ ነው፤ የመንግስታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤም ይህን ዘረፋ እንዲሸፍንላቸው የውሳኔ ሃሳቡን አቀርበዋል ሲሉም ሀገራት እንዲቃወሙት ጠይቀዋል።

የውሳኔ ሀሳቡን ማፅደቅ የምዕራባውያን የጦር መሳሪያ አምራቾችን ከመጥቀምና አለምን የባሰ ውጥረት ውስጥ ከመክተት ውጭ ፋይዳ እንደሌለውም አስገንዝበዋል።

ቻይና፣ ኢራን፣ አንጎላ፣ ቬንዙዌላን ጨምሮ 16 ሀገራት ለሩስያ ድጋፋቸውን በፊርማ ገልፀው፥ ፍትህ በተገቢው የህግ ስርአት እንጂ ምንም አይነት የህግ መሰረት በሌለው የውሳኔ ሃሳብ አይደለም ብለዋል።

በፀጥታው ምክር ቤት ድምፅን በድምፅ የመሻር ስልጣን ያላት ሩስያ የሚቀርቡባትን የውሳኔ ሃሳብ ውድቅ አድርጋለች።

በጠቅላላ ጉባኤው ግን ይሄው ድምፅን በድምፅ የመሻር ስልጣን የላትም፤ ይሁን እንጂ የጠቅላላ ጉባኤው የውሳኔ ሃሳብ እንደ ፀጥታው ምክርቤት ህጋዊ አስገዳጅነት የለውም።

በካናዳ፣ ጓቲማሚላ፣ ኔዘርላንድና ዩክሬን አነሳሽነት የቀረበው የትናንቱ ሩስያ የጦር ካሳ ትክፈል የውሳኔ ሀሳብ በ94 ሀገራት ድጋፍ ቢፀድቅም በሞስኮ ላይ ህጋዊ ጫና አያመጣም።

የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮልድሚር ዜለንስኪ ባስተላለፉት የቪዲዬ መልዕክት ግን ሩስያ ላደረሰችው ኪሳራ ሁሉ ካሳ መክፈሏ ከይቀሬ ነው ብለዋል።

የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ በበኩላቸው፥ እንዳይንቀሳቀስ ያገዱትን የሩስያ ሃብት በካሳ ስም ለዩክሬን ለመስጠት ላሰቡት ምዕራባውያን የትኛውንም ምላሽ እንሰጣለን ሲሉ ዝተዋል።

News today, Politics

ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ቻይና ለጋራ ጥቅም ከአሜሪካ ጋር ለመስራት ፈቃደኛ ነች አሉ

የፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት ተከትሎ የሁለቱም ኃያላን ሀገራት ግንኙነት ጥሩ የሚባል እንዳልሆነ ይታወቃል

የጆ ባይደን አስተዳደር ዋሽንግተን ከቤጂንግ ጋር ያሏት የግንኙነት መስመሮችን ክፍት እንደሚያደረግ አስታውቋል

የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ቻይና ለጋራ ጥቅም ከአሜሪካ ጋር ለመስራት ፍቃደኛ ናት ማለታቸው የቻይና መንግስት ቴሌቪዥን ዘግቧል፡፡

ፕሬዝዳንቱ በትናንትናው እለት በተዘጋጀውና በአሜሪካ – ቻይና ግንኙነት ዙሪያ ትኩረት የሚያደረገው የጋራ ብሔራዊ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ እንደተናገሩት ከሆነ ሁለቱም ኃያላን ሀገራት ግንኙነታቸውንና ትብብር በማጠናከር ለዓለምና መረጋጋት ትልቅ ሚና መጫወት አለባቸው ብለዋል፡፡

ዢ ይህን መልዕክት ያስተላለፉት በቅርቡ በኢንዶኔዥያ በሚካሄደው ቡድን-20 ስብሰባ ከፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ሊያደርጉት ከሚችሉት ውይይት በፊት መሆኑ ነው፡፡

ጆ ባይደን በበኩላቸው “አሜሪካ ከቻይና ጋር ግጭ አትፈልግም” ሲሉ ተደምጠዋል።

ፕሬዝዳንት ዢ ለሶስተኛ ጊዜ የቻይና መሪ ሆነው መመረጣቸውን ተከትሎ ዋሽንግተን ከቤጂንግ ጋር ያሏት የግንኙነት መስመሮችን ክፍት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አጽንዖት ሰጥተውም ተናግራል ፕሬዝዳንቱ።

የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት ተከትሎ የሁለቱም ሀገራት ግንኙነት ጥሩ የሚባል እንዳልሆነና በበርካታ ዛቻዎች የታጀበ መሆኑ ይታወቃል፡፡

በተለይም በፔሎሲ ጉብኝት ምክንያት የተበሳጨችው ቻይና እና ከአሜሪካ ጋር ወታደራዊ ትብብርን ጨምሮ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያም ንግግርና ውይይት የነበራት ቢሆንም ሁሉንም ማቋረጧ የሚታወስ ነው፡፡ 

ከዚህ ባለፈም የፕሬዝዳንት ዢ ሺን ፒንግ አስተዳደር፤ ሀገሪቱ ከአሜሪካ ጋር የነበራትን የድንበር አልባ ወንጀል መከላከል፣ ስደተኞችን የማጓጓዝ፣ አደገኛ ዕጽ ዝውውር መከላከል እና ሌሎች ስምንት የትብብር መስኮችን ማቋረጡን ገልጾ ነበር፡፡

አሜሪካ በበኩሏ የቻይና ድርጊት ተገቢ እንዳለሆነ ስትሞግት ቆይታለች፡፡

ያም ሆኖ የሁለቱም ኃያላን ሀገራት መሪዎች አሁን ላይ አዲስ ተረክ ይዘው መምጣታቸው የሀገራቱ ግንኙነት ወደ ተሻለ ደረጃ ያደርሷል ተብሏል፡፡

በተለይም ሀገራቱም ሀገራት ከተባበሩ ለዓለም ሰላም የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደሆነ ይታመናል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) ዋና ኃላፊ ከአሜሪካ-ቻይና ትብብር ውጭ የዓለም አቀፍ ቁልፍ ጉዳዮችን ለመፍታት የሚደረግ ‘ምንም መንገድ የለም’ ብለው እንደሚያምኑ በቅርቡ መናገራቸው አይዘነጋም፡፡

News today, Politics, social life

የሩሲያን ጦር ምልክት በተሸከርካሪው ላይ የቀረጸው ጀርመናዊ በ4 ሺህ ዩሮ ተቀጣ

የሀምቡርግ ከተማ ነዋሪ የሆነው ይህ ግለሰብ የሩሲያን ጦር ደግፏል በሚል የገንዘብ ቅጣት ተጥሎበታል

የሩሲያ ጦር በዩክሬን ለልዩ ዘመቻ በሚል ወደ ዩክሬን ከገባ ስምንት ወር ሆኖታል

የሩሲያን ጦር ምልክት በተሸከርካሪው ላይ የቀረጸው ጀርመናዊ በ4 ሺህ ዩሮ ተቀጣ።

የጀርመኗ ሀምቡርግ ከተማ ነዋሪ የሆነ አንድ ግለሰብ የግሉ ተሸከርካሪ ላይ በነጭ ቀለም የሩሲያ ጦር ምልክት የሆነውን የዜድ (“Z”) አርማ ቀርጿል ተብሏል።

ግለሰቡ ከስምንት ወራት በፊት ለልዩ ዘመቻ በሚል ወደ ዩክሬን ግዛት የገባውን የሩሲያ ጦር ደግፏል በሚል በሀምቡርግ ከተማ ፍርድ ቤት ክስ ተመስርቶበታል።

ይህ ግለሰቡ ባሳለፍነው መጋቢት ወር ላይ በነጭ ወረቀት ላይ የዜድ ምልክትን በደማቁ በመጻፍ በአደባባዮች ሲያሽከረክር እንደነበርም ተገልጿል።

የግለሰቡ ተደጋጋሚ ድርጊት ሩሲያ በዩክሬን እየፈጸመች ያለውን ጦርነት ለመደገፍ ያደረገው ጥረት ነው ያለው የሀምቡርግ አቃቢ ህግ ለማስተማሪያነት በሚል ግለሰቡ 4 ሺህ ዮሮ እንዲከፍል ቅጣት እንደተጣለበት የጀርመን ድምጽ ዘግቧል።

ሩሲያ በዩክሬን እያደረገች ላለው ጦርነት የህዝብ ግንኙነት ስራ ለመስራት ወይም ድጋፍ ለማግኘት በሚል የጦር ተሸከርካሪዎቿ የዜድ ምስልን ተጠቅመው እንዲንቀሳቀሱ አድርጋለች።

በሞስኮ እና በተወሰኑ ሀገራት የዜድ ምስል የተጻፈባቸው ምልክቶች በአደባባዮች ላይ መታየት ጀምረውም የነበረ ሲሆን በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይም ለተወሰኑ ቀናት በስፋት ተሰራጭተዋል።

ጀርመን የትኛውም ዜጋዋ የሩሲያ ጦር ምልክት የሆነው ይህ የዜድ ምስልን በአደባባይ ይዞ መገኘት አልያም ማሰራጨት ዓለም አቀፍ ወረራን መደገፍ ስለሚሆን ድርጊቱን ከልክላለች።

የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ስምነተኛ ወሩ ላይ የሚገኝ ሲሆን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዩክሬናዊያን ወደ ጎረቤት ሀገራት ሲሰደዱ በቢሊዮን የሚቆጠር መሰረተ ልማት ደግሞ መውደሙን የተመድ ሪፖርት ያስረዳል።

News today, Politics

ፑቲን ለ3ኛ ጊዜ መሪ ሆነው ለተመረጡት ፕሬዝዳንት ዢ የእንኳን ደስ አልዎት መልእክት አስተላለፉ

ፑቲን፤ በቀጣይ የዢ የስልጣን ዘመን ሞስኮ-ቤጂንግ ግንኙነት ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተስፋ አለኝ ብለዋል

የሩሲያ ፕሬዝዳንት ፑቲን እና የቻይናው አቻቸው ዢ መልካም የሚባል ግንኙነት ያላቸው መሪዎች ናቸው

የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላደሚር ፑቲን ለሶስተኛ ዙር የስልጣን ዘመን መሪ ሆነው ለተመረጡት የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ የእንኳን ደስ አልዎት መልእክት አስተላለፉ፡፡

ፑቲን በቀጣይ የዢ ጂንፒንግ የስልጣን ዘመን ሞስኮ-ቤጂንግ ግንኙነት ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸው ተስፋም ገልጸዋል፡፡

 “በሀገራቱ መካከል ያለውን… ስትራቴጂያዊ ትብብር ለማጠናከር ያለመ ገንቢ ውይይታችንን እና የቅርብ የጋራ ስራችንን ለመቀጠል ደስተኛ ነኝ” ማለታቸውንም ነው በክሬምሊን በኩል የወጣው መግለጫ የሚያመለክተው፡፡

የሩሲያው ፕሬዝዳንት አክለው፤ ለ ዢ “ብልጽግና እና አዲስ ስኬቶች” እንደሚመኙ ተናግረዋል::

ሞስኮ እና ቤጂንግ በተለይም ከቅርብ አመታት ወዲህ ከምዕራቡ ዓለም ጋር ባለቸው ግንኙነት የቅርብ አጋሮች ሆነው ብቅ ያሉበት አጋጣሚ ተፈጥረዋል።

በሀገራቱ መሪዎች መካከል ያለው ግንኙነትም እንዲሁ መልካም የሚባል እንደሆነ ይነገራል፡፡

መሪዎቹ በቅርቡ በኡዝቤኪስታን መዲና ሳማርካንድ ተገናኝተው በሀገራቱ መካከል ያለውን ሁለንተናዊ ትብብር ለማጎልበት እንደሚሰሩ መናገራቸው አይዘነጋም፡፡

ቭላድሚር ፑቲን እና ዢ ጂንፒንግ “ዓለምን በበላይነት ለመቆጣጠር የሚደረገው ሙከራ” አንቀበልም የሚል የጋራ አቋም ያላቸው መሪዎች መሆናቸው ይታወቃል፡፡

በሌላ በኩል ቻይና ከዩክሬን ጦርነት ጋር በተያያዘ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የመነጠል አደጋ ለተጋረጠባት ሩሲያ ያላትን ድጋፍ በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች ስታንጸባርቅ ይስተዋልል፡፡

 ቻይና በዩክሬን ጦርነት ጉዳይ አብዛኛው ጊዜ የመሃል አቋም ስታራምድና በሞስኮ ላይ የሚደረገው ዘመቻ ስትቃወም ነው የምትታየው፡፡

ይህም አሜሪካን ጨምሮ በምዕራባውያን ዘንዳ ባይወደድም፤ ፑቲን የቻይናው መሪ ዢ በዩክሬን ጉዳይ የሚያንጸባርቁት “ሚዛናዊ አቋም” እንደሚያደንቁ በቅርቡ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

በተጨማሪም ሀገራቱ ለዓለም ተምሳሌት የሆነ ገደብ የለሽ ትብብር ለማድረግ ከስምምነት መድረሳቸው አይዘነጋም፡፡

እናም የአሁኑ የፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ለሶስተኛ የስልጣን ዘመን መሪ ሆኖ መመረጥ በሞስኮ-ቤጂንግ መካካል ያለውን ጥሩ የሚባል ግንኙነት ወደ ከፍተኛ ደረጃ ያደርሷል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

News today, Politics

ታይዋን፤ ቻይና “አሮጌ አስተሳሰብን ማስወገድ አለባ” አለች

ታይዋን ልዩነቶችን በሰላማዊ፣ ፍትሃዊ እና በተጨባጭ መንገድ እንዲፈቱ ጠይቃለች

ቻይና “የታይዋን ነጻነትን” ለመቃወም የሚያሽችል ህገ-መንግስታዊ ማሻሻያ አድርጋለች

ታይዋን፤ ቻይና “አሮጌ አስተሳሰብን ማስወገድ አለባ” አለች፡፡

ታይፔ ይህን ያለችው ጉበኤውን ሲያካሂድ የሰነበተው የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ የታይዋን ነጻነትን በተመለከተ ያለውን ተቃውሞ በህገ መንግስቱ ላይ ካረጋገጠ በኋላ ነው፡፡

የታይዋን የድንበር ተሸጋሪ ፖሊሲዎች አስፈጻሚ አካል የሆነው የመይንላንድ ጉዳዮች ምክር ቤት ባወጣው መግለጫ “የቻይና ኮሚኒስት መንግስት አዲሱ አመራር የወረራ እና የመጋጨት አስተሳሰቡን አስወግዶ ልዩነቶችን በሰላማዊ፣ ፍትሃዊ እና በተጨባጭ መንገድ እንዲፈቱ እንጠይቃለን” ብሏል፡፡

የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ በህገ-መንግስቱ ላይ “የታይዋን ነጻነትን” ለመቃወም የሚያሽችለው ህገ-መንግስታዊ ማሻሻያ አድርጓል፡፡

ማሻሻያው ቅዳሜ ዕለት በፓርቲው ብሔራዊ ኮንግረስ ላይ ከ 2ሺህ በላይ ተወካዮች ያሳለፉት ውሳኔ አካል ነው መባሉን ኤኤፍፒ ዘግቧል፡፡

ለአንድ ሳምንት የቆየው ይህ የኮሙኒስት ፓርቲ ጉባኤ ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግን ፓርቲውን በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት በሊቀመንበርነት እንዲመሩ በመምረጥ በትናንትናው እለት መጠናቀቁ ይታወቃል፡፡

የፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ ከዚህ በተጨማሪም ቻይናን ከፈረንጆቹ 2012 ዓመት ጀምሮ በሬዝዳንትነት እየመሩ ላሉት ዢ ጂንፒንግን ተጨማሪ ስልጣንም እንደሰጠም ሽንዋ ዘግቧል።

ፕሬዝዳንቱ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ውስጥ ቻይናን ሲመሩ ከኮሙንስት ፓርቲ ጽንሰ ሀሳብ ባለፈ ለቻይናዊያን ይበጃል የሚሉትን ሀሳብ ወደ ተግባር መቀየር እንዲችሉ ፈቃድም ሰጥቷል።

ፓርቲው 25 አባላት ያሉት የፖሊት ቢሮ እና አዲስ ሰባት የማዕከላዊ አባላት የተመረጡ ሰዎችን ያሳወቁ ሲሆን በፖሊት ቢሮ አንድም ሴት አለማካተታቸው አነጋገሪ ሆነዋል፡፡

ቻይና ሴት የፖሊት ቢሮ አባል የሌለው ካቢኔ ስታዋቅር በ25 ዓመታት መጀመሪያው ነው ተብሎለታል፡፡

ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግን በፓርቲው ጉባኤ መዝጊያ ፕሮግራም ላይ ባደረጉት ንግግር ለቻይና ድል እንደሚዋጉ እና እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

በኮሮና ቫይረስ ፣ በሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት እየተፈተነ ያለውን ኢኮኖሚ ማስታግስ እንዲሁም የታይዋን ጉዳይ ለፕሬዝዳንት ሺ ፒንግ ዋነኛ ትኩረት የሚሰጡባቸው ጉዳዮች ናቸው።

News today, Politics, Technology

ኢራን የጸጥታው ም/ቤት ውሳኔን በመጣስ ለኢትዮጵያ ድሮን መሸጣን አሜሪካ አስታወቀች

ኢራን ሰው አልባ የጦር አውሮፕላን (ድሮን) ለኢትዮጵያ የሸጠችው ከአንድ ዓመት በፊት ነው ተብሏል

ኢራን “ሞሃጀር” የተሰኘውን ድሮን ለኢትዮጵያ መስጠቷን አሜሪካ ገልጻለች

ኢራን የጸጥታው ምክር ቤት ውሳኔን በመጣስ ለኢትዮጵያ ድሮን መሸጧን አሜሪካ አስታወቀች።

የአሜሪካ መንግስት እንዳሳወቀው ኢራን ከአንድ ዓመት በፊት ክረምት ላይ ለኢትዮጵያ ሰው አልባ አውሮፕላን ወይም ድሮን ማስተላለፏን ገልጿል።

ኢራን በፈረንጆቹ 2015 ላይ የጦር መሳሪያ ግብይት እንዳትፈጽም የሚከለክል ማዕቀብ በመንግስታቱ ድርጅት የተወሰነባት ሲሆን፤ ይሄንን ማዕቀብ በመጣስ ለኢትዮጵያ አስተላልፋለች ተብሏል።

2231 የተሰኘው ይህ የተመድ ውሳኔ በኢራን መጣሱን የአሜሪካ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ቪዳንት ፓቴል መናገራቸውን ዋቢ አድርጎ ሮይተርስ ዘግቧል።

ይህ የተባበሩት መንግስታት ውሳኔ በ2020 ላይ የሚያበቃ ቢሆንም በወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶናልድ ትራምፕ ማዕቀቡ እንዲራዘም ጠይቀው ነበር።

ይሁንና ይህ ማዕቀብ እንዲነሳ ያልተወሰነ በመሆኑ ኢራን ውሳኔውን በመጣስ ለኢትዮጵያ አሳልፋ ሰጥታለች ተብሏል፡።

እንደዘገባው ከሆነ ኢትዮጵያ ከኢራን የተረከበችውን ሞሃጀር የተሰኘውን ይሄንን ድሮን ከህወሃት ጋር በሚደረገው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ላይ እንዳዋለችውም ተገልጿል።

ኢራን ከኢትዮጵያ በተጨማሪ የጦር መሳሪያ ማዕቀቡን በመተላለፍ ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ለጀመረችው ጦርነት ድሮን ለሞስኮ ማስተላለፏንም አሜሪካ አስታውቃለች።

ኢራን በምዕራባዊያን የሚቀርቡባትን ክሶች ውድቅ ያደረገች ቢሆንም ከሩሲያ ጋር የሰው አልባ አውሮፕላን እና ሚሳኤል ግዢ ስምምነት መፈጸሟን አምናለች።

ዩክሬን በበኩሏ ኢራን ሻሂድ፣ጄራን እና ሌሎች ስያሜ ያላቸውን ድሮኖች ለሩሲያ በመሸጥ የዩክሬን ዋና ዋና ከተሞች እንዲደበደቡ አድርገዋል በሚል ከቴህራን ጋር ያላትን ግንኙነት እንደምታቋርጥ ዝታለች።

News today, Politics

ቦሪስ ጆንሰን ዳግም ለብሪታኒያ ጠቅላይ ሚንስትርነት እንደሚወዳደሩ ተገለጸ

ቦሪስ ጆንሰንን ተክተው ጠቅላይ ሚንስትር ሊዝ ትሩስ ስልጣን ለመልቀቅ መወሰናቸው ይታወሳል

ሪሺ ሱናክ፣ ሞርዳንት እና ቤን ዋላስ የቦሪስ ጆንሰን ዋነኛ ተፎካካሪ እንደሚሆኑ ይጠበቃል

የብሪታንያ የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን ዳግም ለጠቅላይ ሚንስትርነት እንደሚወዳደሩ ተገለጸ።

የቀድሞው ጋዜጠኛ እና የለንደን ከንቲባ የነበሩት ቦሪስ ጆንሰን ቴሬዛ ሜይን በመተካት ብሪታንያን ከፈረንጆቹ 2019 እስከ አሳለፍነው ነሀሴ ወር ጠቅላይ ሚንስትር ነበሩ።

የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የወጣውን ህግ ተላልፈዋል፣ ይዋሻሉ እና ሌሎች ያልተገቡ ባህሪያት አሏቸው በሚል የሀገሪቱ ምክር ቤት አባላት ጫና አሳድረውባቸው ስልጣን ለመልቀቅ ተገደውም ነበር።

ይሄንን ተከትሎም የ50 ዓመቷ ሊዝ ትሩስ ከሌሎች እጩዎች ጋር በመወዳደር እና አብላጫ ድምፅ በማግኘት ከመስከረም ጀምሮ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው በማገልገል ላይ ነበሩ።

ይሁንና በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት በዋጋ ግሽበት እየተፈተነ ያለውን የብሪታንያ ኢኮኖሚ ለማረጋጋት እርምጃ እንደሚወስዱ ቃል ገብተው የነበረ ቢሆንም ስልጣን ከያዙ በኋላ በወሰዷቸው እርምጃዎች የብሪታንያ መገበያያ ገንዘብ ፓውንድ ስተርሊንግ ከዶላር እና ዩሮ አንጻር አቅሙ መዳከሙ ተጨማሪ የኢኮኖሚ ቀውስ አስከትሏል።

ይሄንን ተከትሎም ጠቅላይ ሚንስትሯ በደረሰባቸው ጫና ስልጣናቸውን ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ እንደምያስረክቡ አስታውቀዋል።

ሊዝ ትሩስ በብሪታንያ መሪ ታሪክ ለአጭር ቀናት ብሪታንያን በመምራት የመጀመሪያዋ የሆኑ ሲሆን እሳቸውን ለመተካት እጩዎች ከወዲሁ እንቅስቃሴ ጀምረዋል።

ከአራት ወር በፊት ስልጣን የለቀቁት ቦሪስ ጆንሰን እንዲመለሱ በርካታ ብሪታንያዊያን በትዊተር ቦሪስ ይመለስ የሚል ዘመቻ ጀምረዋል።

ይሁንና የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር በስልጣን ዘመናቸው አሳይተውታል የተባለው ምርመራ አለመጠናቀቁ በቀላሉ ወደ ቀድሞ ቦታቸው እንዳይመለሱ ሊያደርጋቸው ይችላል ተብሏል።

ከቦሪስ ጆንሰን በመቀጠል የቀድሞው የብሪታንያ ፋይናንስ ሚንስትር እና የሊዝ ትሩስ ተቀናቃኝ የነበሩት ሪሺ ሱናክ እንዲሁም የቀድሞው የብሪታንያ መከላከያ ሚንስትር ቤን ዋላስ እና ሙርዶንት የቦሪስ ዋነኛ ተፎካካሪ እንደሚሆኑ ተገልጿል

News today, Politics

ኢራን ዜጎቿ ዩክሬንን ለቀው እንዲወጡ አሳሰበች

የዩክሬን ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ሩሲያ በኢራን ድሮኖች እየደበደበችን ነው ማለታቸው አይዘነጋም

በዩክሬን ጦርነት የኢራን ሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቅም ላይ ውለዋል መባሉ ቴህራን ውድቅ አድርጋለች

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዩክሬን የሚኖሩ የኢራን ዜጎች ለደህንነታቸው ሲሉ ለቀው እንዲወጡ ጠይቋል።

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቆንስላ ዲፓርትመንት በዛሬው እለት ባወጣው መግለጫ ፤በዩክሬን ውስጥ እየጨመረ የመጣውን የጸጥታ ችግር ግምት ውስጥ በማስገባት ሁሉም የኢራን ዜጎች ወደዚያ ሀገር ከመጓዝ እንዲቆጠቡ አሳስበዋል፡፡

ዲፓርትመንቱ የኢራን ዜጎች እንዲረጋጉ እንዲሁም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በኪቭ የሚገኘውን የኢራን ኤምባሲ ማነጋገር እንደሚችሉም ጠቁሟል፡፡

ዬክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ባሳለፍነው ሳምንት በሰጡት መግለጫ ፤ሩሲያ የኢራንን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በመጠቀም ጥቃት እያደረሰችብን ነው ሲሉ መናገራቸው የሚታወስ ነው፡፡

በዚህም የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ለሩሲያ የጦር መሳሪያ አቅረባለች በሚል ኢራን ላይተጨማሪ ማዕቀብ ሊጥል እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል።

የዩክሬን ዋና ከተማ ኪቭና ሌሎች ዩክሬን ከተሞች ላይ በተሰነዘርው ጥቃትና በደረሰው ፍንዳታ የኢራን ሻሄድ 136 ድሮች ጥቅም ላይ እንደዋሉ ሮይተርስ ዘግቧል።

በዚህም ሩሲያ የኢራን ድሮኖችን እየተጠቀመች ነው የምትለው ዩክሬን የአውሮፓ ህብረት በቴህራን ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ እንዲጥል በመወትወት ላይ ናት።

የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲምትሪ ኩሌባ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት “የአውሮፓ ህብረት ለሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖች በማቅረብ በኢራን ላይ ማዕቀብ ሊጥል ይገባል” ብለዋል።

በዚህም መሰረት በርካታ የህብረቱ ሚኒስትሮች ኢራን በጦርነቱ ውስጥ ያላትን “ግልጽ” ተሳትፎ በመጥቀስ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ አቅርበዋል።

በዛሬው እለት የአውሮፓ ህብረት መሪዎች እያካሄዱት ባለው ስብሰባ በቴህራን ተጨማሪ እርምጃዎችን ለመውሰድ ከስምመነት ሊደርሱ እንደሚችሉ ሮይተርስ ከህብረቱ የውስጥ ሰዎች ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክት ዘግቧል።

በተጨማሪም አሜሪካ፣ ፈረንሳይ እና እንግሊዝ የኢራን አጥፍቶ ጠፊ አውሮፕላኖች በዩክሬን ጦርነት ጥቅም ላይ ውለዋል መባሉን ተከትሎ የጸጥታው ምክር ቤት ዝግ ስብሰባ ጠርተዋል።

ሩሲያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን በዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖች መጠቀሟን እንዳይመረምር አስጠንቅቃለች፡፡

 ኢራን በበኩሏ ለዩክሬን ጦርነት የምትጠቀመው ወታደራዊ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ለሩሲያ አስረክባለች የሚለውን ውንጀላ ውድቅ አድርጋለች፡፡ 

News today, Politics

ሩሲያ የዩክሬኑን ግዙፍ ግድብ እንዳትመታ ምእራባውያን እንዲያስጠነቅቋት ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ጠየቁ

ሩሲያ የዩክሬኑን ግዙፍ ግድብ እንዳትመታ ምእራባውያን እንዲያስጠነቅቋት ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ጠየቁ

ሩሲያ ከሁለት ሺህ በላይ መካናይዝድ ጦሯን ግድቡ ወደሚገኝበት አካባቢ አሰማርታለች

ሩሲያ የዩክሬኑን ኖቫ ካኮቭካ የተሰኘውን ግዙፍ ግድብ እንዳትመታ ምእራባውያን እንዲያስጠነቅቋት ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ጠይቀዋል፡፡

ኖቫ ካኮቭካ የተሰኘው ግድብ ከተመታ ከኤሌክትሪክ አገልግሎት በተጨማሪ ዜጎች በውሀ ሊጥለቀለቁ እንደሚችሉ ተሰግቷል።

ስምንት ወራት የሞላው የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት በየጊዜው አዳዲስ ክስተቶችን ማስተናገዱን ቀጥሏል።

ሩሲያ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ በዩክሬን ዋና ዋና ከተሞች የሚገኙ መሰረተ ልማቶችን ጥቃት በማድረስ ላይ እንደሆነች ተገልጿል።

በዚህ የሩሲያ ጥቃትም ከ30 በመቶ በላይ የሚሆነው የዩክሬን የሀይል መሰረተ ልማቶች መውደማቸውን ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ተናግረዋል።

የሩሲያ ጥቃት መቀጠሉ ያሳሰባቸው የዩክሬን ፕሬዝዳንት ኖቫ ካኮቭካ የተሰኘው ግዙፉ የዩክሬን ግድብ እንዳይመታባቸው ሞስኮን ተማጽነዋል።

ፕሬዝዳንቱ አክለውም ይህ ለደቡብ ዩክሬን ግዛቶች ዋነኛ የሀይል ምንጭ የሆነው ይህ ግዙፍ ግድብ ከተመታ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ከመቋረጡ ባለፈ በርካታ ዜጎች ሊጥለቀለቁ እንደሚችሉ ፕሬዝዳንቱ ጠቁመዋል።

ሩሲያ በዚህ የዩክሬን ግድብ አካባቢ ከሁለት ሺህ በላይ መካናይዝድ ጦሯን ማስጠጋቷ ግድቡን ልታወድም እንደምትችል ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ስጋታቸውን ገልጸዋል።

በመሆኑም ምዕራባውያን እና ተመድ ሩሲያ የዩክሬንን ግድብ እንዳትመታ ጫና እንዲያደርጉ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ጠይቀዋል።ሩሲያ ከአንድ ወር በፊት የዩክሬን ግዛት የሆኑ አራት ግዛቶችን በህዝበ ውሳኔ ወደ ሞስኮ መጠቅለሏ ይታወሳል።

የመንግስታቱ ድርጅት ባሳለፍነው ሳምንት የሩሲያን ህዝበ ውሳኔ የሚቃወም ውሳኔ በአብላጫ መወሰኑም አይዘነጋም።

News today, Politics

ቻይና ጥቃት ከፈጸመች አሜሪካ ታይዋንን እንደምትከላከል ባይደን ተናገሩ

ቻይና “ጥቃት ከፈጸመች” አሜሪካ ታይዋንን እንደምትከላከል ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በድጋሚ አስጠነቀቁ።

ፕሬዝዳንቱ ከሲቢኤስ ጋር በነበራቸው ቃለ መጠይቅ የአሜሪካ ኃይሎች ታይዋንን ይከላከላሉ ወይ ተብለው ሲጠየቁ “አዎ” ብለው መልሰዋል።

እሑድ በተሰራጨው ቃለ መጠይቅ የአሜሪካ ፖሊሲ እንዳልተለወጠ ዋይት ሐውስ በድጋሚ እንዲናገር አስገድዶታል።

የዋሽንግተን ፖሊሲ ሁሌም “ስትራቴጂካዊ አሻሚነት” ያለው ሲሆን ታይዋንን ለመከላከል ቃል ባይገባም አማራጩን ደግሞ ሙሉ ለሙሉ አያስቀርም።

ታይዋን በምሥራቅ ቻይና የባሕር ዳርቻ ላይ የምትገኝ ራስ ገዝ ደሴት ስትሆን ቤይጂንግ የግዛቴ አካል ናት ስትል ትገልጻለች።

በጉዳዩ ላይ ዋሽንግተን ቁርጥ ያለ አቋም ሳትይዝ ለረዥም ጊዜ በዲፕሎማሲያዊ ዥዋዥዌ ተጉዛለች። በአንድ በኩል ከቤይጂንግ ጋር ላላት ግንኙነት መሠረት የሆነውን የአንድ ቻይና ፖሊሲ ታከብራለች።

በዚህ ፖሊሲ ታይዋን የቻይና አካል ስትሆን አቋሙም መገዳደሪያ የለውም። ስለዚህ አሜሪካ ታይዋንን እንደ የተለየ አገር ዕውቅና የማትሰጥ ሲሆን ከደሴቱ ጋር ምንም አይነት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትም የላትም። ነገር ግን የጠበቀ ግንኙነት ፈጥራለች።

አሜሪካ ከግዛቲቱ ጋር ባላት ውል መሰረት ለታይዋን የጦር መሳሪያ ትሸጣለች። ውሉ ደሴቲቱ ራሷን የምትከላከልበትን መንገድ ማቅረብ ያስፈልጋል ይላል።

ባይደን ከሲቢኤስ ቴሌቪዥን 60 ደቂቃ ከተሰኘው ፕሮግራም ጋር በነበራቸው ቃለ ምልልስ ይህንን በድጋሚ አስረግጠዋል።

“የአንድ-ቻይና ፖሊሲ አለ። ታይዋንም ነጻነቷ ላይ ራሷ ትወስናለች። እኛ አንንቀሳቀስም፣ ነፃነታቸውን አናበረታታም። ይህ የራሳቸው ውሳኔ ነው” ብለዋል።

ባይደን ታይዋን ጥቃት ከደረሰባት ለመከላከል ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት እንደሚኖር በግንቦት ወር ተመሳሳይ አስተያየት ሰጥተዋል። ዋይት ሐውስም በፍጥነት አሜሪካ ከረዥም ጊዜ ፖሊሲዋ አትወጣም በማለት በፍጥነት ምላሽ ሰጥቶ ነበር።

አሁንም ዋይት ሐውስ ባይደንን የሚቃረን መግለጫ አውጥቷል። “ፕሬዝዳንቱ ከዚህ ቀደምም በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ በቶኪዮ ይህንኑ ተናግረዋል። የታይዋን ፖሊሲ እንዳልተለወጠም ግልፅ አድርገዋል። ይህ እውነት ነው” ብሏል።

ይህ ግን በአንድ ዓመት ውስጥ ፕሬዝደንቱ ከይፋዊ የአገሪቱ አቋም ርቀው ለወታደራዊ እርምጃ ቃል ሲገቡ ይህ ለሦስተኛ ጊዜ ነው። በጥቅምት እና በግንቦት ተመሳሳይ አስተያየት ሰጥተዋል።

በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ዩናይትድ ስቴትስ ለታይዋን 1.1 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ የጦር መሳሪያዎች እና ፀረ ሚሳኤሎች ለመሸጥ ተስማምታለች። ይህም የቻይናን ክፉኛ አስቆጥቷል።

የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ በነሐሴ ወር በደሴቲቱ ያደረጉት አወዛጋቢ ጉብኝት በአሜሪካ እና በቻይና መካከል ያለውን ውጥረት አባብሶታል። ባይደን ጉብኝቱን ቀደም ብለው “ጥሩ ሃሳብ አይደለም” ብለው ነበር።

በምላሹ ቤይጂንግ በታይዋን ዙሪያ ለአምስት ቀናት የቆየ ወታደራዊ ከበባ በማድረግ ልምምድ አካሂዳለች።

ዩናይትድ ስቴትስ ወደ ደሴቲቱ ሚሳኤል መተኮሱን ብትናገርም ቤይጂንግ ግን ይህንን አላረጋገጠችም። ቻይና የተኮሰችው ሚሳኤሎች ምንም አይነት ስጋት እንዳልፈጠሩ ታይዋን ተናግራለች።

ቀደም ብሎ ተቀርጾ እሑድ በተላለፈው ቃለ መጠይቅ ሩሲያ በዩክሬን ጦርነት የኬሚካል ወይም የታክቲካል የጦር መሳሪያ እንዳትጠቀም ባይደን አስጠንቅቀዋል።

News today, Politics

አሜሪካ እና ታሊባን የእስረኛ ልውውጥ አደረጉ

በልውውጡ ፤ ታሊባን ለ17 ዓመታት ያክል በአሜሪካ እጅ የቆየው የጦር አዛዥ ባሻር ኑርዛይን ተቀብሏል

የጦር አዛዡ ባሻር ኑርዛይን ታሊባን ወደ ትጥቅ ትግል ሲገባ ለቡድኑ “የጦር መሳሪያ ድጋፍ” ሲያደረግ የነበረ ነው ተብሏል

ታሊባን በአሜሪካ እጅ የነበረውን የጦር አዛዥ ለማስፈታት ከሁለት አመት በላይ ታስሮ የነበረውን አሜሪካዊ የባህር ኃይል አርበኛ ለዋሽንግተን አሳልፎ መስጠቱን አስታወቀ፡፡

የአፍጋኒስታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሚር ካን ሙታቂ በካቡል ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት “ዛሬ ማርክ ፍሬሪችስ ለአሜሪካ ተላልፎ ተሰጥቷል ፤ እኛም የጦር መሪው ሃጂ ባሻር ኑርዛይ በካቡል አየር ማረፊያ ተሰጥቶናል” ብለዋል።

ልውውጡ የተከናወነው “ከረጅም ድርድር በኋላ” መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፤ በካቡል ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አንድ የሀገራችን ልጅ ወደ ሀገሩ ሲመለስ የነበረውን አስደናቂ ስነ ስርዓት በማየታችን ደስተኛ ነን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ኑርዛይ በአውሮፕላን ማረፊያው ሲደርስ በአዲሱ የአፍጋኒስታን እስላማዊ ኢሚሬትስ (አይኢኤኤ) መንግስት የጀግና አቀባበል እንደተደረገለትም ኤኤፍፒ ዘግቧል፡፡

በማህበራዊ የትስስር ገጾች በመዘዋወር ላይ ያሉ ፎቶዎች የሚያሳትም፤ኑርዛይን የአበባ ጉንጉን በያዙና ጭንብል በለበሱ የታሊባን ባለስልጣናት አቀባበል ሲደረግለት ነው፡፡

ለበርካታ አመታት በአሜሪካ እጅ የቆየው የጦር አዛዡ ባሻር ኑርዛይ ወደ ሀገሩ ከተመለሰ በኋላ በሰጠው መግለጫ የታሊባን አመራሮች እሱን ለመስፈታት የተጓዙት የድርድር ርቀት አድንቋል፡፡

“ታሊባን ጠንካራ ቁርጠኝነቱን ባያሳይ ኖሮ ዛሬ እዚህ ባልነበርኩ ነበር” ብሏል ኑርዛይ።

ባሻር ኑርዛይ – ከሄሮይን ኮንትሮባንድ ጋር በተያያዘ ለ17 ዓመታት በአሜሪካ ታስሮ የቆየ የጦር አዛዥ ሲሆን ማርክ ፍሬሪችስ ደግሞ እንደፈረንጆቹ በ2020 ታፍኖ ተወስዶ በታሊባን ቁጥጥር ስር የቆየ የአሜሪካ የባህር ኃይል አርበኛ ነው፡፡

የአሜሪካ የባህር ኃይል አርበኛው ማርክ ፍሬሪችስ በአፍጋኒስታን ውስጥ በግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ በሲቪል መሃንዲስነት ሲሰራ የነበረ እንደሆነም ነው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የገለጸው፡፡

ኑርዛይ በታሊባን ውስጥ ምንም አይነት ኦፊሴላዊ ቦታ አልነበረውም ነገር ግን በ 1990 ዎቹ ውስጥ ጠንካራው እንቅስቃሴ ብቅ ባለበት ወቅት “ጦር መሳሪያዎችን ጨምሮ ለታሊባን ጠንካራ ድጋፍ ያደረግ ነበር” ያሉት ደግሞ የአፍጋኒስታን መንግስት ቃል አቀባይ ዛቢሁላህ ሙጃሂድ ናቸው፡፡

ከአንድ አመት በፊት የአሜሪካና አጋሮቿ ጦር ከ20 ዓመታት ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት በኋላ አፍጋኒስታንን ለቀው መውጣታቸውን ተከትሎ፤ ታሊባን አፍጋኒስታንን እያስተዳደረ እንደሚገኝ የሚታወቅ ነው፡፡ 

News today, Politics

ሞስኮ፤ የሩሲያ ኃይሎች በዩክሬን የጦር ወንጀል ፈጽመዋል የሚለውን ውንጀላ “ውሸት” ነው አለች

ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ፤ የሩሲያ ኃይሎች በኢዚዮም የጦር ወንጀል ፈጽመዋል ሲሉ ከሰዋል

ኢዚዮም በተባለ ስፍራ 450 የሚጠጉ በጅምላ ተቀብረው የነበሩ አስክሬኖች እንደተገኙ መረጃዎች እየወጡ ነው

ሞስኮ፤ የሩሲያ ኃይሎች በዩክሬን ካርኪቭ ግዛት የጦር ወንጀል ፈጽመዋል የሚለውን ውንጀላ “ውሸት” ነው አለች፡፡

የሩሲያ ኃይሎች በዩክሬን ኃይሎች የመልሶ ማጥቃት እርምጃ የዩክሬኗ ካርኪቭ ግዛት መልቀቃቸውን ተከትሎ ኢዚዮም በተባለ ስፍራ 450 የሚጠጉ በጅምላ ተቀብረው የነበሩ አስክሬኖች እንደተገኙ መረጃዎች እየወጡ ነው፡፡

በጉዳዩ ላይ ምላሽ የሰጡት የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ክሱ መሰረተ ቢስ ነው ሲሉ ውድቅ አድርገዋል፡፡

ዲሚትሪ ፔስኮቭ፤ ክሱ “በቡቻ ውስጥ እንደነበረው ተመሳሳይ ነው፤ ‘ውሸት ነው’ እናም በዚህ ተረት ውስጥ ያለውን እውነት እንዲታወቅ እናደርጋለን” ሲሉም ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡

የሩሲያው ቃል አቀባይ ይህን ይበሉ እንጅ የኪቭ ባለስልጣናት በቦታው የጦር ወንጀል እንደተፈጸመ እንደሚያምኑ ይህንንም ሰንደው ለማስቀመጥ እየሞከሩ እንደሆነ በመደመጥ ላይ ናቸው፡፡

ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪ በቦታው ላይ የሚገኙ መርማሪዎች በእጃቸው የታሰሩ አስክሬኖችን ጨምሮ በርካታ የማሰቃየት ድርጊት የተፈጸመባቸው ሰዎች ለመኖራቸው አመላካች የሆኑ ማስረጃ ማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡

በጅምላ መቃብሩ ውስጥ አብዛኞቹ ንጹሀን ዜጎች ፣ ሴቶችና ህጻናትም ይገኙበታል ተብሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሩሲያ ኃይሎች ፈጽመውታል የተባለው ድርጊት በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በኩልም ቢሆን በከፍተኛ ደረጃ የተወገዘ ሆኗል፡፡

የአሜሪካ ብሄራዊ ደህንነት ቃል አቀባይ ጆን ኪርቢ፣ በኢዚዮም ደን መቃብሮች መገኘታቸው “እጅግ አስደንጋጭ ነው” ብለዋል።

 ድርጊቱ አስደንጋጭና የሩሲያ ኃይሎች ዩክሬን ውስጥ ከፈጸሟቸው ጭካኔ የተሞሉ ወንጀሎች ጋር የሚመሳሰል ነው ያሉት ቃል አቀባዩ፤ አሜሪካ የጦር ወንጀል በመሰነድ ድጋፍ መስጠት እንደምትቀጥልም ተናግረዋል፡፡

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በበኩላቸው “የተፈጸመውን እጅግ እናወግዛለን” ብለዋል።

በኢዚዮም ተገኘ በተባለው የጅምላ መቃብር “እጅጉን መደንገጡ” የገለጸው ደግሞ የአውሮፓ ህብረት ነው፡፡

ህብረቱ የተፈጸመውን ድርጊት አጥብቆ እንደሚያወግዝ የገለጹት የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ተወካይ ጆሴፕ ቦሬል፤ ድርጊቱ ዓለም አቀፍ ህግጋቶችን የጣሰ መሆኑ ተናግረዋል፡፡

 “በሩሲያ ኃይሎች የሚፈጸመው ኢሰብዓዊ ድርጊት የዓለም አቀፍ የሰብአዊ ህግጋትን እና የጄኔቫን ስምምነቶችን የጣሰ ነው፤ በአስቸኳይ መቆም አለበት” ብለዋል ጆሴፕ ቦሬል፡፡

አክለውም ፤የአውሮፓ ህብረት በዩክሬን ውስጥ እየተፈጸመ ላለው ወንጀል ሩሲያን ተጠያቂ ለመድረግ የሚደረጉ ሁሉንም ጥረቶችን ይደግፋል ብለዋል፡፡ 

News today, Politics

በሶማሊያ መንግስት የሚደገፉ ሚሊሻዎች 45 የአልሸባብ ታጣቂዎችን ገደሉ ተባለ

አልሸባብ በቅርቡ አንድ ሆቴል በመክበብ 21 ሰዎችን መግደሉ ይታወሳል

የሶማሊያ ፕሬዝደንቱ አልሸባብን ለማጥፋት ጠንካራ እንቅስቃሴ እየታየ መሆኑን ተናግረዋል

በሶማሊያ መንግስት የሚደገፉ ሚሊሻዎች ቢያንስ 45 የአልሸባብ ታጣቂዎችን መግደላቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

ግድያው የአልቃይዳ አጋር በሆነው ቡድን እና በፌዴራል መንግስት በሚደገፉ ሚሊሻዎች መካከል ከፍተኛ ግጭት የታየበት የግዛት የቅርብ ጊዜ ክስተት ነው ተብሏል።

አልሸባብ በሶማሊያ የሸሪዓ ህግን በጥብቅ እንዲተገበር ለማስገደድ ከአስር አመታት በላይ ጦርነት ከፍቷል።

ቡድኑን ለማጥፋት በአካባቢውም ሆነ በግዛቱ ሃይሎች ጥረት ቢደረግም ቡድኑ በመላ ሀገሪቱ ብጥብጥ ማድረጉን እንደቀጠለ ነው። 

ባለፈው ወር ታጣቂ ቡድኑ በዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ የሚገኘውን ሆቴል ለ30 ሰአታት ከበባ በማድረግ በትንሹ 21 ሰዎች ሲገደሉ ከመቶ በላይ ማቁሰሉ ይታወሳል።

በሰኔ ወር የአልሸባብ ታጣቂዎች ከኢትዮጵያ ጋር በሚያዋስኗቸው አቅራቢያ እና አዋሳኝ መንደሮች ላይ በርካታ ጥቃቶችን ፈጽመው ከ12 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተዘግቧል።

 በጥቃቱ በደርዘን የሚቆጠሩ የቡድኑ ታጣቂዎችም ተገድለዋል።

ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ግን አርብ ዕለት ሀገራቸው ከአልሸባብ ጋር በምታደርገው ትግል ትልቅ ስኬት እያየች ነው ብለዋል።

ፕሬዝደንቱ አልሸባብን ለማጥፋት ጠንካራ እንቅስቃሴ እየታየ መሆኑን ተናግረዋል።

News today, Politics

ፕሬዝዳንት ባይደን “የአሜሪካ ጦር ታይዋንን ከቻይና ወረራ ይከላከላል” አሉ

ታይዋን በቻይና እንዳትወረር ከጦር መሳሪያ በተጨማሪ የአሜሪካ ሰራዊት አባላት እንደሚሳተፉም አስታውቀዋል

በታይዋን ጉዳይ ቻይና ከአሜሪካ ጋር ያላትን ወታደራዊ ትብብርም ማቋረጧን ማስታወቋ ይታወሳል

የአሜሪካው ፕሬዝዳት ጆ ባይደን ጦራቸው ታይዋንን ከቻይና ወረራ እንደሚከላከል አስታወቁ።

ፕሬዝዳንት ባይደን ከሲ.ቢ.ሲ ቴሌቪዥን ጋር በነበራቸው ቆይታ ታይዋንን ተበመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ፤ ቻይና ታይዋን ላይ ያልተጠበቀ ጥቃት ከከፈተች ጦራቸው ራስ ገዝ የሆነችውን ታይዋንንን ለመከላከል ወደ ስፍራው ሊያቀና ይችላል ብለዋል።

ጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ የተጠየቁት ባይደን ባይደን፤ ከዩክሬን በተለየ በጦር መሳሪያ መደፍ ብቻ ሳይሆን የአሜሪካ ወታደሮች ታይዋንን ለመከላከል ወደ ስፍራው እንደሚያቀኑ አረጋግጧል።

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በግንቦት ወር በጃፓን አድርገውት በነበረው ጉብኝት ላይ ቻይና በታይዋን ላይ ወረራ ከፈጸመች፤ አሜሪካ ወታደራዊ አጸፋ ለመስጠት ዝግጁ መሆኗን መናራቸውም የሚታወስ ነው።

የቻይና መከላከያ ሚኒሰቴር ከወራት በፊት በበታይዋን ጉዳይ እንደማይደራደር እና ውጊያ መግጠም ካለባትም ለመግጠም ዝግጁ መሆኑን ለአሜሪካ መግለጹ ይታወሳል።

የቻይናው መከላከያ ሚኒስትር ዌዪ ፈንጊሄ፤ ከአሜሪካው የመከላከያ ሚኒስትር ሎልዩድ አውስቲን ጋር ከኢስያ የደህንነት ጉባዔ ጎን ለጎን ተገናኝተው ባደረጉት ውይይት፤ ታይዋንን ከቻይና መገንጠል የቻይና ወታደር “ማንኛውንም አይነት ዋጋ በመክፈል ከመዋጋት ውጭ ምርጫ እንዳይኖረው ያደርጋል” ሲሉ ነበር የተናገሩት።

“ህዝባዊ ነፃ አውጪ ጦር” በመባል የሚጠራው የቻይና ጦር የሀገሩን ብሔራዊ ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነትን ከማስጠበቅ በቀር ሌላ ምርጫ እንደማይኖረውም ሚኒስትሩ በወቅቱ አሜሪካን አሳስበዋል።

የአሜሪከ አፈ-ጉባኤ ናንሴ ፔሎሲ ባሳለፍነው ሐምሌ ወር ቻይና የግዛቷ አድርጋ የምትቆጥራትን ታይዋንን መጎብኘታቸውን ተከትሎ ቻይና አሜሪካ እና ታይዋን ጋር ያላት ግንኙነተ በከፍተኛ ደረጃ መሻከሩ የሚታወስ ነው።

ይህንን ተከትሎም ከአሜሪካ ጋር ወታደራዊ ትብብሮችን ማቋረጧን ያሳወቀች ሲሆን ከአሜሪካ ጋር የነበራትን የድንበር አልባ ወንጀል መከላከል፣ ስደተኞችን ማጓጓዝ፣ አደገኛ እጽ ዝውውር መከላከል እና ሌሎች ስምንት የትብብር መስኮችን አቋርጣለች።

News today, Politics

በአፍሪካ የነበሩ የዩክሬን ወታደሮች በኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

የዩክሬን ሰላም አስከባሪ ኃይል ሀገራቸው ከሩሲያ ጋር ጦርነት መጀመሯን ተከትሎ ወደ ኪቭ ለመመለስ ተገደዋል ተብሏል

ወታደሮቹ በተመድ ሰላም ማስከበር ተልዕኮ ስር በዲሞክራቲክ ኮንጎ ነበሩ

በአፍሪካ የነበሩ የዩክሬን ወታደሮች በኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

የመንግስታቱ ድርጅት በዲሞክራቲክ ኮንጎ ያለውን አለመረጋጋት ለመቆጣጠር ከተለያዩ ፈቃደኛ ሀገራት የተውጣጣ ሰላም አስከባሪ ጦር ማሰማራቱ ይታወሳል።

በዚህ ተልዕኮ ስራ ጦር ካዋጡ ሀገራት መካከል አንዷ አሁን ላይ ከሩሲያ ጋር ጦርነት ውስጥ ያለችው ዩክሬን ትገኝበታለች።

ሀገራቸው ከሩሲያ ጋር የገጠመችውን ጦርነት ለመመከት በሚል በዲሞክራቲክ ኮንጎ የነበሩ 250 የዩክሬን ወታደሮችም ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

እነዚህ ወታደሮች ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ በተመድ ዓመቻችነት ሲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወታደሮቹን ካጓጓዙ አየር መንገዶች መካከል አንዱ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።

በተመድ ስር ያለው የሰላም ማስከበር ተልዕኮ በዲሞክራቲክ ኮንጎ ዜጎች ተቃውሞ እያስተናገደ ሲሆን፤ ሰላም አስከባሪ ጦሩ ዜጎችን ከአማጺያን ጥቃት አልታደገም በሚል አየተተቸ ይገኛል።

የሀገሬው ዜጎችም ሰላም አስከባሪ ጦሩ ሀገራቸውን ለቆ እንዲወጣ በሰላማዊ ሰልፍ በመጠየቅ ላይ ሲሆን ይህ ሰላም አስከባሪ ጦር ከሁለት ወራት በፊት 36 ተቃዋሚዎችን ተኩሶ ገድሏል ተብሏል።

ከዚሁ ተቃውሞ ጋር በተያያዘም በኬንሺያሳ ያለው የተመድ ሰላም ማስከበር ተልዕኮ ቃል አቀባይ የዲሞክራቲክ ኮንጎን ሉዓላዊነት የሚጋፋ አስተያየት ሰጥቷል በሚል ሀገሪቱቱን ለቆ እንዲወጣ ተደርጓል።

ተመድ በዓለም ላይ ፈቃደኛ ከሆኑ ሀገራት ጦር በማዋጣት በ12 ሀገራት ላይ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ያለው ሲሆን ለ22 ዓመት የቆየው እና ብዙ ገንዘብ ወጪ የተደረገበት ስምሪቱ በዲሞክራቲክ ኮንጎ ያለው ነው።

News today, Politics

አፍሪካ ምን ማድረግ እንዳለባት ማንም ሊያዛት እንደማይገባ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ተናገሩ

አሜሪካ ከሩሲያ ጋር የሚወዳጁ የአፍሪካ ሀገራትን እንዳትቀጣም ፕሬዝዳንቱ አሳስበዋል

ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጋር በዋሸንግተን ተወያይተዋል

አፍሪካ ምን ማድረግ እንዳለባት ማንም ሊያዛት እንደማይገባ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ተናገሩ።

የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ሰባተኛ ወሩ ላይ የሚገኝ ሲሆን ጦርነቱን ተከትሎ ምዕራባዊያን ሩሲያን ከተቀረው ዓለም ለመነጠል የተለያዩ ጫናዎችን እያደረጉ ያገኛሉ።

አሜሪካንን ጨምሮ ምዕራባዊያን ሀገራት ዩክሬን በሩሲያ ላይ ድልን እንድትቀዳጅ የጦር መሳሪያ ድጋፍ ከመስጡ ጎን ለጎን በሞስኮ ላይ ማዕቀብ በመጣል ላይ ናቸው።

ይህ በዚህ እንዳለም አፍሪካን ጨምሮ ከሩሲያ ጋር ወዳጅነትን በሚመሰርቱ ሀገራት ላይ ግንኙነታቸውን እንዲያቋርጡ የተለያዩ ጫናዎችን በማድረግ ላይ ናቸው።

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛ ወደ ዋሸንግተን ተጉዘው በነጩ ቤተ መንግስት ከአሜሪካ አቻቸው ጋር ተወያይተዋል።

ሩሲያ የየትኛውም የዓለማችን ባለጸጋ ሀገር ጋር የተለየ ግንኙነት የላትም ያሉት ፕሬዝዳንት ራማፎዛ አሜሪካም በአፍሪካ የተለየ ተጽዕኖ ማድረግ እንደሌለባት አክለዋል።

የአፍሪካ ሀገራት ከሩሲያ ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንዲያቋርጡ ተጽዕኖ ልታደርግ እንደማይገባ የተናገሩት ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛ አፍሪካ ምን ማድረግ እንደሚገባት ማንም መናገር አይችልም ሲሉም አክለዋል።

አሜሪካ አፍሪካ ከሩሲያ ጋር ያላትን ግንኙነት እንድታቋርጥ የተለያዩ ጫናዎችን እያደረገች ሲሆን በአንድ ወር ውስጥ በተመድ የዋሸንግተን ተወካይ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ እና የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ወደ አፍሪካ በመምጣት ስድስት ሀገራትን ጎብኝተው መመለሳቸው ይታወሳል።

የመሪዎቹ ወደ አፍሪካ መምጣት ዋና አላማው ከሩሲያ ጋር ጠያላቸውን ግንኙነት እንዲያቋርጡ ጫና መፍጠር ሲሆን አፍሪካ ከሩሲያ ከአፈር ማዳበሪያ እና ስንዴ ውጪ ሌሎች ምርቶችን መግዛት እንደማይችሉ ተናግረውም ነበር።

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በምዕራብ አፍሪካ ባደረጉት ጉብኝት አፍሪካ በሩሲያ ላይ የተለሳለሰ አቋም አሳይተዋል በሚልም ትችት ሰንዝረዋል።

News today, Politics

ጆ ባይደን፤ ቭላድሚር ፑቲን ታክቲካል ኒውክሌር ጦር መሳሪያ እንዳይጠቀሙ አስጠነቀቁ

ባይደን፤ ፑቲን ኒውክሌር ከተጠቀመ “ጦርነቱን ከ2ኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ባልታየ ሁኔታ ይቀይረዋል” ሲሉ ተናግረዋል

ጆ ባይደን፤ “ፑቲን ቀይ መስመሩን ማለፍ የለበትም” ሲሉ አስጠንቅቀዋል

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን፤ቭላድሚር ፑቲን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እንዳይጠቀሙ አስጠነቀቁ፡፡

ፕሬዝዳንቱ ከሲቢኤስ ቴሌቪዥን ጋር ባረደጉት ቆይታ የታክቲካል የኒውክሌር መሳሪያ መጠቀም አደገኛ ሁኔታ ሊያስከትል ይችላል ብለዋል፡፡

ታክቲካል ኒውክሌር በመባል የሚታወቁት የአጭር ርቀት መሳሪያዎች ሲሆኑ፣ ስትራቴጂክ ኒውክሌር ደግሞ የረዥም ርቀት ተስወንጫፊ መሳሪያዎችን ያካትታሉ።

ፑቲን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ከተጠቀሙ “ጦርነቱን ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ባልታየ ሁኔታ ይቀይረዋል” ያሉት ባይደን፤ “ፑቲን ቀይ መስመሩን ማለፍ የለባቸውም!” ሲሉም አስጠንቅቀዋል፡:

ፑቲን የኒውክሌር መሳሪያ በዩክሬን ለመጠቀም አስበው ከሆነ ምን መልዕክት ማስተላለፍ ይፈልጋሉ ተብለው በሲቢኤስ የተጠየቁት ባይደን ጋዜጠኛውን “ተው! ተው! ተው!” ሲሉ ታይተዋል።

ፕሬዝዳንት ጆ-ባይደን አሜሪካ የኒውክሌር ጥቃትን ተከትሎ ምን እርምጃ እንደምትወስድ በግልጽ ባይናገሩም “ዓለም ላይ ታይተው ከሚታወቁ ቀውሶች ሁሉ የባሰ ይሆናል፤ የሚከሰተውን ጉዳት ያህልም ምላሽ እንሰጣለን” ብለዋል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ይህን ይበሉ እንጅ፤ የክሬምሊን ባለስልጣናት የሶሞኑ መግለጫዎች የሚያመለለክቱት በተቃራኒው ነው፡፡

በዩክሬን ላለው ቀውስ አሜሪካን ጨመሮ ለኪቭ የጦር መሳሪያ ድጋፍ የሚያደርጉትን ምዕራባውያን ተጠያቂ የሚያደርጉት የሩሲያው መሪ ፑቲን፤ በዩክሬን ምድር ያሰብነውን ዓላማ ከማሳከት የሚገታን ኃይል የለም እያሉ ነው፡፡

በዚህም ዩክሬንን ሽፋን ደረገው የሩሲያ እና አሜሪካ ፍጥጫ አደገኛ ሁኔታ እንዳያስከትል ተሰግተዋል፡፡አሜሪካ በሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ለኪቭ የሚያስፈለግ የጦር መሳሪያ በከፍተኛ ደረጃ ድጋፍ ከሚልኩ ሀገራት አንዷ መሆኗ ይታወቃል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ፤አሜሪካ 3 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት የጦር መሳሪያ ድጋፍ ለዩክሬን እንደምትሰጥ በቅረቡ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

ድጋፉ ዩክሬን ፤በአየር መከላከያ እንዲሁም የመድፍ ስርዓቶችና ጥይቶችን እንድታጎለብት ብሎም ከረዠም ርቀት ጥቃቶች እራሷን መከላከል እንደምትችል ለማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑንም ፕሬዝዳንቱ ገልጸው ነበር፡፡

News today, Politics

አሜሪካ እና ሶማሊያ ሽብርተኝነት ለመዋጋት የሚያደርጉት ትብብር አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገለጹ

በሶማሊያ ፖለቲከኛች መካከል የነበረው ሽኩቻ “አልሻባብ እንዲያንሰራራ” እድል የፈጠረ መሆኑ ይነገራል

የሶማሊው ፕሬዝዳንት ፤ “አሜሪካ በሶማሊያ ዘላቂ ልማት እና እድገት ውስጥ ስትራቴጂካዊ አጋር ነች” ብለዋል

አሜሪካ እና ሶማሊያ ሽብርተኝነት ለመዋጋት የሚያደርጉት ትብብር አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገለጹ፡፡

ለይፋዊ ስራ ጉብኝት በአሜሪካ የሚገኙት የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጋር ተገናኝተው በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

ሽብርተኝነትን መዋጋት፣ የሶማሊያ ድረቅ እና መልካም አስተዳደር ፕሬዝዳንቱ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በነበራቸው ቆይታ የመከሩባቸው አንኳር ጉዳዮች ናቸው፡፡

በውይይታቸው በተለይም ከሶማሊያ አልፎ የቀጠናው ስጋት የሆነውን ሽብርተኝነት ለመዋጋት ሀገራቱ የሚያደርጉት ትብብር አጠናክረው ለመቀጠል መስማማታቸው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ በትዊተር ገጻቸው ያጋሩት መረጃ ያመለክታል፡፡

“አሜሪካ በሶማሊያ ዘላቂ ልማት እና እድገት ውስጥ ስትራቴጂካዊ አጋር ነች”ም ብለዋል ፕሬዝዳንቱ፡፡

አሁን አሁን ከነበረበት ሁኔታ እያንሰራራ እየመጣ እንደሆነ የሚነገርለት አልሻባብን አደጋ ለመግታት በሚል፤ አሜሪካ በታጣቂ ቡድኑ ላይ የተለያዩ እርምጃዎች በመውሰድ ላይ መሆኗ የሚታወቅ ነው፡፡

በተጨማሪም ፕሬዝዳንት ባይደን የቀጠናው ስጋት የሆነውን አልሻባብ ለመምታት 600 የሚሆኑ የሃገራቸውን ወታደሮች ወደ ሶማሊያ እንደሚልኩ ማስታወቃቸው የሚታወስ ነው።

የአሜሪካ ጦር በድጋሚ በሶማሊያ እንዲሰማራ የማድረግ ውሳኔ በየሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ተቀባይነት ማግኘቱም አይዘነጋም፡፡

ሶማሊያ አሁንም በአልሻባብ እየተፈተነች ነው። በተለይም ከምርጫ ጋር በተያያዘ በሃገሪቱ ፖሊተከኞች መካከል የነበረው ሽኩቻ ለሰላምና ጸጥታ ይሰጥ የነበረውን ትኩረት አላልቶት እንደነበር በርካቶች ያነሳሉ።

አሁኑ ላይ አሜሪካ በአልሻባብ ላይ የምትወስዳቸው እርምጃዎች አሜሪካ ቡድኑን ከማዳከም አንጻር ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ይታመናል፡፡

የአሜሪካን ሚና እንደ ትልቅ የአጋርነት መገለጫ አድረጎ የሚወስደው የፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ አስተዳደር በቅረቡ “ለመረጋጋትና ሽብርተኝነትን ለመዋጋት በምናደርገው ትግል አሜሪካ ወትሮም ቢሆን ታማኝ አጋራችን ናት” ሲል በትዊተር ገጹ ላይ ባወጣው ጽሁፍ ማጋራቱም የሚታወስ ነው፡፡

News today, Politics

ፕሬዝደንት ኢሳያስ ከቻይና የምስራቅ አፍሪካ ልዩ መልእክተኛ ጋር በአስመራ ተነጋገሩ

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ፤ ጉብኝቱ በኤርትራ እና ቻይና መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ ግንኙነት የሚያጎለብት መሆኑ ተናግረዋል

የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በቻይና ጉብኝት እንዲያደርጉ መጋበዛቸው ይታወሳል

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከቻይና የምስራቅ አፍሪካ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ሹ ቢንግን ጋር በአስመራ ተናገገሩ፡፡

ፕሬዝዳንቱ ከልዩ መልዕክተኛው ጋር በነበራቸው ቆይታ በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ዘለግ ያለ ውይይት ማድረጋቸው የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትሩ የማነ ገ/መስቀል አስታውቀዋል፡፡

ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው ባጋሩት ጽሁፍ “ሁለቱ ወገኖች በኤርትራ ቅድሚያ በሚሰጣቸው የልማት መስኮች የሁለትዮሽ ትብብራቸውን ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ተወያይተዋል” ብለዋል፡፡

ኤርትራ እና ቻይና በቀጣናዊ ትስስራቸው ማዕቀፍ ውስጥ የልማት ትብብር ለማካሄድ መስማማተቸውም ጭምር ተናግረዋል ፡፡

ጉብኝቱ በኤርትራ እና ቻይና መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ ግንኙነት የበለጠ ለማጎልበት የሚያችል እንደሆነ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በውይይቱ መናገራቸውም ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

ኤርትራ እና ቻይና በተለያዩ መስኮች በትብብር የሚሰሩ ሀገራት መሆናቸው ይታወቃል፡፡

የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ በየካቲት በኤርትራ ባደረጉት ይፋወዊ የስራ ጉብኝት፤ በማዕድን ልማት፣ በምጽዋና አሰብ ወደቦች ልማት፣ በሰው ኃይል አቅም ግንባታ እና በመሰረተ ልማት ዘርፍ በጋራ ለመስራትም ከስምምነት መድረሳቸው የሚታወስ ነው፡፡

በተጨማሪም በውይይቱ ወቅት ቻይና ለኤርትራ ተጨማሪ የ100 ሚሊየን ዩዋን ድጋፍ ማድረጓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዋንግ ዪ በወቅቱ መግለጻቸው አይዘነጋም።

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በበኩላቸው የቻይናን የ100 ዓመታት የጋራ ተጠቃሚነት መርህ ጉዞ እና በዓለም ዐቀፍ ሕጎች ማዕቀፍ ውስጥ ሆና ዓለምን ሚዛናዊ ለማድረግ የምታደርውን ጥረት አድንቀዋል።

የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ፐሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በቻይና ጉብኝት እንዲያደርጉ ግብዣ እንደላኩላቸውም የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል በትዊተር ገጻቸው አስፍረው ነበር፡፡

ኤርትራ፤ ቻይና በዓለም አቀፍ መድረክ የምታራምዳቸው አቋሞች በመደገፍ የምትታወቅ ሀገር መሆኗም ይታወቃል፡፡

News today, Politics

በአርመን እና አዘርቤጃን መካከል በተካሄደው ጦርነት ከ200 በላይ ወታደሮች ተገደሉ

አለምአቀፉ ማህበረሰብ ባለፈው ሀሙስ የተደረሰውን ተኩስ አቁም በአዎንታ ተቀብሎታል

አርመኒያ እና አዘርቤጃን ናጋርኖ ካራባክ በተባለው ተራራማ ግዛት ምክነያት ከፈረንጆቹ 1988 ጀምሮ ፍጥጫ ውስጥ ነበሩ

በቅርቡ በድጋሚ በተቀሰቀሰው የአርመን እና የአዘርቤጃን ጦርነት ከ200 በላይ ወታደሮች ተገደሉ፡፡

ሮይርስ እንደዘገበው የአርመንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ፓሲኒያን በአርመን እና አዘርቤጃን መካከል በተቀሰቀሰው ጦርነት 135 ወታደሮች መገደላቸውን አረጋግጠዋል፡፡

አሁን 135 ወታደሮች ህይወታቸው አልፏል፤ ብዙዎች ቆስለዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ፓሺኒያን “እንዳለመተል ሆኖ ይህ የመጨረሻ አይደለም” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ሀለቱ ሀገራት በፈረንጆቹ 2020 ካደሩጉት ደምአፋሳሽ የስድስት ሳምንት ጦርነት ወዲህ በተቀሰቀሰው ጦርነት 71 ወታደሮች እንደተገደሉባት አዘርቤጃን ሪፖርት አድርጋለች፡፡

እስካሁን በሁለቱም ሀገራት የተገደሉ ወታደሮች ቁጥር ከ200 በላይ ሆኗል፡፡

አርመኒያ እና አዘርቤጃን ናጋርኖ ካራባክ በተባለው ተራራማ ግዛት ምክነያት ከፈረንጆቹ 1988 ጀምሮ ፍጥጫ ውስጥ ነበሩ፡፡ በፈረንጆቹ 1994 በተካሄድ የሰላም ድርድር ተኩስ አቁም የተፈራረሙ ቢሆንም ከዚያ ወዲህ አልፎ አልፎ ግጭት ውስጥ ሲገቡ ቆይተዋል፡፡

በቅርቡ የተጀመረውን ግጭት በሚመለከት ግን ሁለቱም ሀገራት ግጭቱን በመጀመር እየተካሰሱ ይገኛሉ፡፡ አርመን፣ የአዘርቤጃን ሃይሎች ናጎርኖ ካራባክን አልፈውጥቃት በመክፈት አርመን ውስጥ ቦታ ይዘዋል የሚል ክስ ስታቀርብ፣አዘርቤጃን ደግሞ ለተፈጸመባት ትንኮሳ ምላሽ መስጠቷን ትገልጻለች፡፡

አለምአቀፉ ማህበረሰብ ባለፈው ሀሙስ የተደረሰውን ተኩስ አቁም በአዎንታ ተቀብሎታል፡፡

News today, Politics

ቱርክ፤ በሩሲያ እና ቻይና የሚመራው የጸጥታ ጥምረት አባል የመሆን አላማ እንዳላት ፕሬዝደንት ኤርዶጋን ተናገሩ

ኤስሲኦ በሩሲያ እና ቻይና የተመሰረተ የጸጥታ ጥምረት ነው

ፕሬዝደንቱ ይህን ያሉት በኡዝቤክስታን በተካሄደው የኤስሲኦ ስብሰባ ላይ ከተካፈሉ በኋላ ነው

የቱርኩ ፕሬዝደንት ኤርዶጋን የኔቶ አባል የሆነችውን ሀገራቸው የሻንጋይ ኮኦፐሬሽን ኦርጋናይዜሽን(ኤስሲኦ) አባልጰየማድረግ አላማ እንዳላቸው ተናግረዋል።

ኤስሲኦ በሩሲያ እና ቻይና የተመሰረተ የጸጥታ ጥምረት ነው።

ፕሬዝደንቱ ይህን ያሉት በኡዝቤክስታን በተካሄደው የኤስሲኦ ስብሰባ ላይ ከተካፈሉ በኋላ መሆኑን ሮይተር ዘግቧል።

“በዚህ እርምጃ ከእነዚህ ሀገራት ጋር ያለን ግንኙነት ወደ ልዩ ቦታ ይደርሳል” ብሐዋል ፕሬዝደንት ኤርዶጋን።

ቱርክ በአሁኑ ወቅት ቻይና ሩሲያ ህንድ ፓኪስታን ኢራን ኪሪጊስታን ፓጃኪስታን ካዛኩስታን እና ኡዝቤኪስታን ያሉበት የጸጥታ ጥምረት የውይይት አጋር ነች።

በስብሰባው ላይ ከፕሬዝደንት ፒቲን ጋር የተነጋገሩት ኤርዶጋን በደቢብ ቱርክ በሚገኘው የኑክሌር ጣቢያ ጉዳይ የነበረውን ግጭት ለመፍታት ከስምምነት መድረሳቸውን ገልጸዋል።

በፈረንቹ 2001 የተቋቋመው በሩሲያ እና ቻይና የነበረ ሲሆን ከተመሰረተ ከአራት አመት በኋላ ህንድ እና ፓኪስታንን አካቷል፤ ይህም በቀጣናው ያለውን የምእራባውያን ጫና ለመቋቋም አላማ ያደረገ ነበር፡፡

Politics, social life

አሜሪካ ኡሁሩ ኬንያታ “የኢትዮጵያና የዲ.አር.ሲ የሰላም መልዕክተኛ” ሆነው መሾማቸውን እንደምትቀበል ገለጸች

ኡሁሩ ኬንያታ የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ፖለቲካዊ መፍትሔ እንዲያገኝ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል

አሜሪካ ተለዋዋጭ ሁነታዎች በሚስተዋሉበት ቀጠና “ኬንያታ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ተስፋ አለን” ብላለች

አሜሪካ ኡሁሩ ኬንያታ የኬንያ የአፍሪካ ቀንድ የሰላም መልዕክተኛ ሆነው መሾም በደስታ እንደምትቀበል ገለጸች፡፡

የአሜሪካ መንግስት በውጭ ጉዳይ መሰሪያ ቤቱ የአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ በኩል ባወጣው መግለጫ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የአፍሪካ ቀንድ እና የታላላቅ ሀይቆች አካባቢ የሰላም መልዕክተኛ ሆነው መሾማቸውን በደስታ እንደሚቀበል አስታውቋል።

ቢሮው ተለዋዋጭ ሁነታዎች በሚስተዋሉበት ቀጠና ኬንያታ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ተስፋ አለን ብሏል፡፡

“ኡሁሩ ኬንያታ በሰሜን ኢትዮጵያ እና በምስራቅ ዲሞክራቲክ ኮንጎ ለተፈጠረው ግጭት የሰላም መልዕክተኛ ሆነው መሾማቸውን በደስታ እንቀበላለን፤ ኬንያታ በዚህ ጊዜ ሁለቱም ግጭቶች ለመፍታት የሚጫወቱት ሚና ወሳኝ ይሆናል” ብሏል ቢሮው በትዊተር ገጹ ላይ ባጋራው ጽሁፍ፡፡

አዲሱ የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ከቀናት በፊት በነበረው በዓለ ሲመታቸው በኢትዮጵያ እና በታላላቅ ሐይቆች ቀጠና (ግሬት ሌክስ) ሰላም ለማምጣት በሚደረገው ጥረት የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የሚያከናውኑትን ተግባር እንደሚቀጥሉ መናጋራቸው ይታወሳል።

ሁለት ዓመት ሊሞላው የተቃረበውን የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት መቀስቀስን ተከትሎ ተዋጊ ኃይሎችን ከማደራደር ጋር ተያይዞ ከአፍሪካ ህብረት በተጨማሪ የኡሁሩ ኬንያታ ስም በተደጋጋሚ ሲነሳ ቆይቷል።

በተለይም አሁን ላይ በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር ለመሰደራደር ዝግጁ መሆናቸው የሚገልጹት የትግራይ ኃይሎች፤ ከመንግስት ጋር በሚደረገው ድርድር ከአፍሪካ ህብረት ይልቅ በቅርቡ ስልጣናቸውን ያስረከቡት ኡሁሩ ኬንያታ እንዲያሸማግሏቸው በተደጋጋሚ በይፋ ጠይቀው እንደነበርም የሚታወስ ነው።

የኢትዮጵያ መንግስት በሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ለሚካሄደው ጦርነት መፍትሔ በመፈለጉ በኩል የአፍሪካ ህብረት ቀዳሚው አሸማጋይ ሊሆን እንደሚገባ ቀደም ሲል በያዘው አቋም እንደጸና መሆኑ ይታወሳል።

News today, Politics

አረብ ኤምሬትስን ጨምሮ 5 ተጨማሪ የዓለማችን ሀገራት የሻንጋይ ትብብር ድርጅትን ተቀላቀሉ

ግብጽ፣ አረብ ኢምሬትስ፣ ኳታር ፣ ባህሬን እና ኩዌት ድርጅቱን በአጋርነት ተቀላቅለዋል

የምስራቅ ሀገራት ስብስብ የሆነው የሻንጋያ ትብብር ድርጅት ዓመታዊ ጉባኤ በኡዝበኪስታን ተካሂዷል

በአሜሪካ እና አውሮፓ ህብረት የሚመራውን የዓለም ተጽዕኖ ለመመከት የተቋቋመው የሻንጋይ ትብብር ድርጅት ዓመታዊ ጉባኤውን በኡዝበኪስታን አካሂዷል።

በሳመርካንድ ከተማ በተካሄደው በዚህ ጉባኤ ላይ የቻይና፣ ሩሲያ፣ ህንድ፣ ኢራን፣ ቱርክ እና ሌሎችም ሀገራት ፕሬዝዳንቶች እና ጠቅላይ ሚኒስትሮች ተሳትፈውበታል።

የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ድርጅቱን በአጋርነት ተቀላቀሉት የተባበሩት አረብ ኢምሬት፣ ግብጽ፣ ኳታር ፣ ባህሬን እና ኩዌት እንኳን ደህና መጡ ብለዋል።

ቤላሩስን ጨምሮ በርካታ የዓለማችን ሀገራት ወደዚህ ድርጅት ለመቀላቀል ፍላጎት እያሳዩ ሲሆን ኢራን በይፋ ድርጅቱን መቀላቀሏም ተገልጿል።

ፕሬዝዳንት ፑቲን በጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግር የሻንጋይ ትብብር ድርጅት የዓለምን ችግር ለመፍታት የተቋቋመ እንጂ ቡድን የመመስረቻ መድረክ አይደለም ብለዋል።

ለዓብነትም ድርጅቱ የዓለም ምግብ ችግሮችን፣ ሽብርተኝነትን እና የህይል እጥረቶችን ለመፍታት ይሰራል ሲሉም ፕሬዝዳንት ፑቲን አክለዋል።

በአፍሪካ፣እስያ እና ደቡብ አሜሪካ ሀገራት መካከል በራሳቸው በብሄራዊ የመገበያያ ገንዘባቸው ሰፊ የንግድ ልውውጥ መፍጠር የድርጅቱ ዋነኛ አላማ እንደሆነም ተገልጿል።

ሞስኮ በዩክሬን በጀመረችው ጦርነት ምክንያት ማዕቀቦች እንደተጣሉባት የገለቱት ፕሬዝዳንት ፑቲን ከ300 ሺህ ቶን በላይ የአፈር ማዳበሪያ ያለምንም ክፍያ ለታዳጊ ሀገራት እንደምታሰራጭም ተናግረዋል።

የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ፒንግ በበኩላቸው ቤጂንግ 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዩዋን እርዳታ ለታዳጊ ሀገራት የሰብዓዊ ድጋፎችን እንደምታደርግ በጉባኤው ላይ ገልቷል።

ሻንጋይ የትብብር ድርጅት በፈረንጆቹ 2001 ላይ በቻይናዋ ሻንጋይ የተቋቋመ ሲሆን ኡዝቤኪስታን፣ ቻይና፣ ሩሲያ፣ ህንድ፣ ፓኪስታን፣ ታጂኪስታን፣ ኪርጊስታን፣ እና ካዛኪስታን ደግሞ መስራች ሀገራት ናቸው።

አፍጋኒስታን፣ ኢራን፣ ቤላሩስ እና ሞንጎሊያ በታዛቢነት ድርጅቱን የተቀላቀሉ ሲሆን አርመኒያ፣ አዛርባጂያ፣ ቱርክ፣ ስሪላንካ፣ ቻምቦዲያ እና ኔፓል ደግሞ ድርጅቱን ለመቀላቀል በሂደት ላይ እንደሆኑ ተገልጿል።

ከዓለማችን ህዝብ ቁጥር ውስጥ ግማሽ ገደማ የሖነው በዚህ ድርጅት ውስጥ በመደራጀት ላይ ሲሆኑ የድርጅቱ ሊቀመንበርነትን አባል ሀገራቱ በዙር እየመሩት ይገኛሉ።

የኡዝቤኪስታን ፕሬዝዳንት ሻቭካት ሚርዚቭ የወቅቱ የሻንጋይ የትብብር ድርጅትን በሊቀመንበርነት በመምራት ላይ ይገኛሉ።

News today, Politics, social life

ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ፤ “ለዩክሬን የጦር መሳሪያዎችን ማቅረብ በሞራል ደረጃ ተቀባይነት ያለው ነው” አሉ

አባ ፍራንሲስ፤ እራስን መከላከል ህጋዊ ብቻ ሳይሆን የሰው ልጅ “ለሀገሩ ያለውን ፍቅር መግለጫ ነው” መሆኑም ተናግረዋል

ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ፤ የዩክሬን ጦርነት ራስን ለመከላከል የሚደረግ “ፍትሃዊ ጦርነት” ነው ብለዋል

የዓለም ካቶሊክ ቤተ-ክርስትያን ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ ፤ ራሷን በመከላከል ላይ ላለችው ዩክሬን የጦር መሳሪያዎችን ማቅረብ “በሞራል ደረጃ ተቀባይነት ያለው ነው” አሉ።

ሊቀ ጳጳሱ ይህን ያሉት ከሶስት ቀን የካዛኪስታን ቆይታ ሲመለሱ በአውሮፕላን ውስጥ ሆነው በነበረቻው 45 ደቂቃ የፈጀ ቃለ ምልልስ ላይ ከአንድ ጋዜጠኞች “ሀገራት ለዩክሬን የጦር መሳሪያ መላካችው ትክክል ነው?” ብሎ ላቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ነው።

አባ ፍራንሲስም “ይህ ፖለቲካዊ ውሳኔ ነው ፤ ነገር ግን መርሆችን ባከበረ መልኩ የሚደረግ ከሆነ ከሞራል አኳያ ተቀባይነት ያለው ውሳኔ ነው” ብለዋል።

የዩክሬን ጦርነት ራስን ለመከላከል የሚደረግና በመርህ ደረጃም “ፍትሃዊ” የሚባል ጦርነት መሆኑ ለዚህም የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሃሳባቸው እንድትጋራ የሚያስችል ማብራሪያም መስጠታቸውም ሮይተርስ ዘግቧል።

“እራስን መከላከል ህጋዊ ብቻ ሳይሆን የሰው ልጅ ለሀገሩ ያለውን ፍቅር መግለጫ ነው” ሲሉም አክለዋል። ሊቀ ጳጳሱ የሩሲያ – ዩክሬን ጦርንት እንዲያበቃ ምኞታቸው መሆኑንም ገልጸዋል።

ጦርነቱ እንዲቆም “ዩክሬን ለውይይት ክፍት እንድትሆን” የጠየቁት ሊቀ ጳጳሱ፤ በቅርቡ ከዩክሬን ጋር ምንም ዓይነት የድርድር ተስፋ እንደማይኖር ስለገለጸችው ሩሲያ ግን ያሉት ነገር የለም።

ያም ሆኖ ሊቀ ጳጳስ ፍራሲስ፤ ከሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በሞስኮ ተገናኝቶ ለመምከር ፍላጎት እንዳላቸው ባሰለፍነው ግንቦት ወር አስታውቀው እንደነበር አይዘነጋም።

ሊቀ ጳጳሱ፤ ከጣሊያኑ ኮሬ ዴላ ሴራ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቆይታ ወደ ሞስኮው መምጣት እፈልጋለሁ ሲሉ ለፑቲን መልዕክት መላካቸውንም ተናግረው ነበር።

መልዕክቱ የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት በተጀመረ በ20ኛው ቀን የተላከ መሆኑንም ነበር ሊቃ ጳጳስ ፍራንሲስ የተናገሩት።

የዓለም ካቶሊክ ቤተ-ክርስትያን ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ ጥያቄ ብያቀርቡም፤ በክሬምሊን ባለስልጣነት በኩል እስካሁን የተሰጠ ምላሽ የለም።

News today, Politics

ጀርመን በአውሮፓ ግዙፍ ሆነ የታጠቀ ጦር ለመገንባት ዝግጁ መሆኗን ገለጸች

የጀርመኑ መሪ ኦላፍ ሾልዝ የአውሮፓ ሀገራት በኔቶ ጥላ ስር ሆነው ኃላፊነታቸው እንዲወጡ አሳስበዋል

የሩስያ-ዩክሬን ጦርነት ጀርመን የመከላከያ ፖሊሲዋን እንድትለውጥ አስገድዷል

የጀርመኑ መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ ሀገራቸው የአውሮፓን ጸጥታ ለመምራት የሚያችላት ግዙፍ ሆነ የታጠቀ ጦር ለመገንባት ዝግጁ ነች አሉ፡፡

ኦላፍ ሾልዝ፤ በሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣኖች ፊት ባደረጉት ንግግር “ጀርመን ከፍተኛ የኢኮኖሚ አቅም ያላትና በአህጉሪቱ መሃል ያለች ሀገር እንደመሆኗ፤ ሰራዊታችን በአውሮፓ ውስጥ የመደበኛ መከላከያ የማዕዘን ድንጋይ መሆን አለበት” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

የሩስያ-ዩክሬን ጦርነት ፤ ጀርመን በመከላከያ ፖሊሲዋ ላይ ለውጥ በማድረግ ጦሯን ይበልጥ ለማጠናከር የ100 ቢሊዮን ዩሮ ልዩ ተጨማሪ ፈንድ ለማድረግ ያስገደደ መሆኑ ይታወቃል፡፡

የቀድሞ የመከላከያ ሚኒስትር ጀርመን በወዳጆቿ የተከበበች ሀገር ናት የሚል የተሳሳተ እምነት እንደነበራቸው ያነሱት ኦላፍ ሾልዝ፤ ጀርመን ከራሷ አልፎ የአውሮፓን ደህንነት የሚያረጋጋ ጦር የመገንባቷ ጉዳይ ግድ መሆኑም አንስተዋል፡፡

“ጀርመን ለአህጉራችን ደህንነት የመሪነት ሀላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆኗን በግልጽ እና በታማኝነት እያሳየን ነው” ብለዋል ኦላፍ ሾልዝ።

ኦላፍ ሾልዝ፤ የአውሮፓ ሀገራት በሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ጥላ ስር ሆነው የበለጠ ኃላፊነት ሊወጡ እንደሚገባም አሳስበዋል።

“እኛ አውሮፓውያን በኔቶ ውስጥ የበለጠ ሀላፊነት መውሰድ አለብን፤ ዘመናዊ እና ብቃት ያለው ጦር ያሏቸው ሁለቱ የአውሮፓ ሀገራት ፊንላንድ እና ስዊድን በቅርቡ ወደ ኔቶ መቀላቀላቸው በጣም ጥሩ ነው” ማታቸውም ዩሮ ኒውስ ዘግቧል፡፡

 ኦላፍ ሾልዝ ባለፈው አመት በአፍጋኒስታን እንደነበረው እንደ ኢራቅ ፣ ማሊ እና ኒጀር በመሳሰሉና የአውሮፓ ምክር ወይም የስልጠና ተልእኮዎችን የሚያስፈልጋቸው ሀገራት ላይ ተልእኮዎችን ለመወጣት የሚያስችሉ “የአውሮፓ ዋና መስሪያ ቤቶች” ማቋቋም እንደሚደግፉም ተናግረዋል፡፡

ለዩክሬን ወታደራዊ ድጋፍ ለመላክ ዘግይተዋል ተብለው ሲተቹ የነበሩት የጀርመኑ መራሄ መንግስት፤ አሁን ላይ ለኪቭ የሚያደርጉት ድጋፍ አጠናክረው መቀጠላቸው የሚታወቅ ነው፡፡

የጀርመን መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ ሀገራቸው ለዩክሬን አዲስ የጦር መሳሪያ ልታበረክት መሆኑን እና በቅርቡ እንደሚላክላት መናገራቸውም ይታወሳል።

ኦላፍ ሾልዝ ሃምሌ ላይ በዩክሬን ጉብኝት ማድረጋቸው የሚታወስ ሲሆን ሀገራቸው ዩክሬንን ለማገዝ ዝግጁ መሆኗን ለፕሬዝዳንት ዘለንስኪ መግለጻቸውም አይዘነጋም

News today, Politics

አራን፤ በሩሲያ እና ቻይና የሚመራውን የጸጥታ ጥምረት ልትቀላቀል ነው

ኤስሲኦ ተሰኘው የጸጥታ ቡድን የተመሰረተው በፈረንጆቹ 2011 ነበር

በአሜሪካ የሚደገፈው የአረብ-እስራኤል ጥምረት ኢራን ከሩሲያ ስትራቴጂካዊ ግንኙነት እንድትመሰርት ገፋፍቷታል ተብሏል

የአሜሪካን የኢኮኖሚ ማእቀብ ለመቋቋም ጥረት እያደረገች ያለችው ኢራን በሩሲያ እና በቻይና የሚመራው የሴንትራል እሲያ የጸጥታ አካል ቋሚ አባል ለመሆን ቀርባለች፡፡

ባለፈው ሃሙስ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሁሴን አሚርአብዶላሂያን ስብሰባውን በዚህ ሳምንት ያካሄደውን የሻንጋይ ኮኦፐሬሽን ድርጅት(ኤስሲኦ) ለመቀለቀል የሚያስችል መግባባቢያ ሰነድ መፈረማቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

በፈረንቹ 2001 የተቋቋመው በሩሲያ እና ቻይና የነበረ ሲሆን ከተመሰረተ ከአራት አመት በኋላ ህንድ እና ፓኪስታንን አካቷል፤ ይህም በቀጣናው ያለውን የምእራባውያን ጫና ለመቋቋም አላማ ያደረገ ነበር፡፡

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኢንስታግራም ገጻቸው እንደጻፉት ኢራን የኤስሲኦ ሙሉ አባል ለመሆን በመፈረም፣ ኢራን የኢኮኖሚ፤የንግድ እና የኢነርጅ ትብብር የምታደርግበት አዲስ ምእራፍ ውስጥ ገብታለች ሲሉ ጽፈዋል፡፡

የኢራን ፕሬዝደንት ኢብራሂም ሬኢሲ በኡዝቤክስታን የተካሄውን የተካፈሉ ሲሆን በወቅቱም ከሩሲያው ፕሬዝደንት ፑቲን ጋር ተገናኝተው የነበሩ መሆኑን የኢራን ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡

አውዛጋቢ በሆነው የኢራን የኑክለር ጉዳይ ምእራባውያን የጣሉባትን መእቀብ የምትቋቋምበትን መንገድ የኤስሲኦ አባልት እንዲረዷት መጠየቋን ተከትሎ ነበር ወደ ቡድኑ እንድትገባ የተፈቀደላት፡፡

 ያእደገ የመጣው ማእቀብ እና በአሜሪካ የሚደገፈው የአረብ-እስራኤል ጥምረት የኢራኑን መሪ ከሩሲያ ጋር ኢኮኖሚያዊ እና ስትራቴጂካዊ ግንኙነት እንድትመሰርት እንደገፋፋቸው ዘገባው ጠቅሷል፡፡

“ኢራን ከሩሲያ ጋር ያላትን ግንኙነት ከኢኮኖሚ እስከ ኤሮስፔስ እና የፖለቲካ ዘርፎች ለማሳደግ ቆርጣ ተነስታለች” ሲሉ ራይሲ ለፑቲን በስብሰባቸው ወቅት ተናግረዋል።

“በቴህራን እና በሞስኮ መካከል ያለው ትብብር በአገሮቻችን ላይ በዩኤስ ማዕቀቦች ላይ የተጣለውን ውስንነት በእጅጉ ያስወግዳል”ብለዋል።

News today, Politics

ኪም ጆንግ ኡን የሰሜን ኮሪያን “የኒውክሌር የታጠቀች ሀገር” ሲሉ አወጁ

የሀገሪቱ ፓርላማ በአደጋ ወቅት በጠላት ኢላማዎች ላይ የኒውክሌር ጥቃት እንድትፈጽም የሚፈቅ ህግ አጽድቋል

በኒውክሌር ጉዳይ ድርድር የለም ያሉት ኪም ጆንግ ኡን “ሰላም ሊገኝ የሚችለውም በኃይል ብቻ ነው” ብለዋል

የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ሀገራቸውን “የኒውክሌር የታጠቀች ሀገር” ሆናለች ሲሉ አወጁ፡፡

ኪም ጆንግ ኡን ሊቀለበስ የማይችል ነው ባሉት ውሳኔያቸው፤ ሀገራቸው የኒውክሌር የታጠቀች ሀገር የሆነችበትን አዲስ ህግ ይፋ አድርገዋል።

” ሀገራችን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ባለቤት ሆናለች” ብለዋል ኪም ጆንግ ኡን።

“በአዲሱ ህግ መሰረት የኒውክሌር ጦር መሳሪያዎቻችን ጉዳይ መደራደር የማይታሰብ ነው፤ ሰላም ሊገኝ የሚችለውም በኃይል ብቻ ነው” ሲሉም አክለዋል፡፡

“ሀገራችንን ከኒውክሌር ነፃ ለማድረግ ምንም አይነት ድርድር አይኖርም” ሲሉም ነው የተደመጡት ኪም ጆንግ ኡን፡፡

የሀገሪቱ ፓርላማም ዛሬ ረፋድ ላይ ሀገሪቱ አደጋዎች በሚጋረጡባት ወቅት በጠላት ኢላማዎች ላይ የኒውክሌር ጥቃትን እንድትጀምር የሚፈቅደውን ህግ አጽድቋል፡፡

በዚህም ሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ መያዝን እንደ ህጋዊ ጉዳይ ፣አስፈላጊና መሰረታዊ መብት አድርጋ በመመልከት ባጸደቀችው አዲስ ህግ ራሷን “የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ያላት ሀገር” መሆኗ አውጃለች ሲል የኮሪያ ሴንትራል ኒውስ ኤጀንሲ ዘግቧል፡፡

ነገር ግን በአዲሱ ህግ መሰረት የኒውክሌር ጦር መሳሪያን ከማንም ጋር እንደማትጋራ እንዲሁም የአቶሚክ ቴክኖሎጂ እና ቁሳቁስ እንደማታስተላልፍም አስታውቃለች።

ሰሜን ኮሪያ ከ2017 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የኒውክሌር ሙከራ ለማድረግ በዝግጅት ላይ እንደምትገኝ ታዛቢዎች እየገለጹ ነው።

እንደፈረንጆቹ በ2018 የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕና ሌሎች መሪዎች ሰሜን ኮሪያ ኒውክሌር ማበልጸጓን እንድትተው ኪም ጆንግ ኡንን ለማሳመን ያደረጉት ጥረት እንዳልተሳካ የሚታወስ ነው፡፡

News today, Politics

ከ80 በመቶ በላይ አሜሪካዊያን ሀገራቸው በተሳሳተ መንገድ ላይ እንዳለች ያምናሉ ተባለ

እድሜያቸው 55 እና ከዛ በላይ የሆኑ አሜሪካዊያን ሀገራቸው በትክክለኛው መንገድ ላይ ናት ብለው ያምናሉ ተብሏል

የአሜሪካው ሞንማውዝ የተሰኘው ዩንቨርስቲ በአሜሪካ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያጠናውን ጥናት ይፋ አድርጓል

ከ80 በመቶ በላይ አሜሪካዊያን ሀገራቸው በተሳሳተ መንገድ ላይ እንዳለች እንደሚያምኑ ጥናት አመለከተ።

የአሜሪካው ሞንማውዝ ዩንቨርስቲ ባሳለፍነው ሀምሌ ወር ላይ አሜሪካዊያን አሁን ባለው አስተዳድር  ላይ ያላቸውን አመለካከት ለማወቅ ጥናት አካሂዷል

በዚህ ጥናት ላይ 978 ሰዎች የተሳተፉ ሲሆን በጥናቱ ከተሳተፉ ሰዎች መካከል ከ80 በላይ ያህሉ አሜሪካ በተሳሳተ መንገድ እየተጓዘች እንደሆነ ያምናሉ።

በጥናቱ ከተሳተፉት ውስጥ እድሜያቸው 55 እና ከዛ በላይ ከሆናቸው ሰዎች ውስጥ 16 በመቶዎቹ ግን ሀገራቸው በትክክለኛው መንገድ ላይ መሆኗን ያምናሉ ሲል ዘ ሂል የተሰኘው የአሜሪካው ሚዲያ ዘግቧል።

በዚህ ጥናት መሰረት አሜሪካ በታሪኳ በህዝቧ ዝቅተኛ ግምት የተሰጠው የጥናት ውጤት አሳይታለች ተብሏል።

ዩንቨርሲቲው ግንቦት ወር ላይ ተመሳሳይ ጥናት ማካሄዱ የተገለጸ ሲሆን በሀምሌ ወር ላይ የተገኘው የጥናት ውጤት ግን ሀገራቸው በተሳሳተ ጎዳና ላይ እንደሆነች የሚያምኑ አሜሪካዊያን ቁጥር በ9 በመቶ ጨምረዋል።

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንእና ካቢኔያቸው

የጥናቱ ተሳታፊዎች ከመላው የአሜሪካ ግዛቶች የተካተቱ ሲሆን በዚህ ጥናት መሰረት አሜሪካ በታሪኳ ከፍተኛው ችግር ላይ ትገኛለች ተብሏል።

በትናቱ ከተሳተፉ ሰዎች ውስጥ 92 በመቶ የሚሆኑት የሪፐብሊካን ፓርቲ ደጋፊዎች አሜሪካ በተሳሳተ መንገድ ላይ ነች ብለው ያምናሉም ተብሏል።

በጥናቱ ከተሳተፉ የሪፐብሊካን ፓርቲ ደጋፊዎች ውስጥ 6 በመቶዎቹ ብቻ ሀገራቸው በትክክለኛውም መንገድ ላይ ናት የሚል አመለካከት እንዳላቸው ተገልጿል።

በአሜሪካ የጋዝ ምርቶች ዋጋ ማሻቀብ፣ እና የኑሮ ውድነቱ የአሜሪካዊያን ዋነኛ የወቅቱ ችግር እንደሆነም በጥናቱ የተሳተፉ ሰዎች ተናግረዋል።

ይሄንንም ተከትሎ በጥናቱ ከተሳተፉ አሜሪካዊያን ውስጥ 38 በመቶ የሚሆኑ አሜሪካዊያን በቅርቡ የሚካሄደውን የኮንግረስ ምርጫ ዲሞክራቶች እንዲቆጣጠሩት ሲፈልጉ 36 በመቶዎቹ መላሾች ደግሞ ኮንግረሱን ሪፐብሊካኖች እንዲይዙት እንደሚፈልጉም ጥናቱ ያሳያል።

Politics

ህንድ እና ቻይና ከአወዛጋቢው የድንበር አካባቢ ወታደሮቻቸውን ለማስወጣት ተስማሙ

ህንድ እና ቻይና 3800 ኪ.ሜ ያልተካለለ ድንበር ይጋራሉ

በፈረንጆቹ ሰኔ 2020 በሁለቱ ሀገራት ወታደሮች መካከል በተፈጠረ ግጭት ቢያንስ 20 የህንድ እና አራት የቻይና ወታደሮች መሞታቸው ይታወሳል

የሕንድ እና የቻይና ወታደሮች በነገው እለት አወዛጋቢ ከሆነው የሩቅ ምዕራባዊ ሂማሊያን ድንበር አካባቢ እንደሚለቁ የሕንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አርብ ዕለት አስታውቋል፡፡

ይህ ወሳኔ የተላለፈው በድንበሩ አካባቢ ተከስቶ የነበረውን ደም አፋሳሽ ግጫት ተከትሎ ከመጣው የሁለት አመታት ፍጥጫ በኋላ ነው፡፡

በከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናት መካከል ከበርካታ ዙር ንግግሮች በኋላ የመጣው ይህ ስምምነት በ1962 በድንበራቸው ላይ ጦርነት በፈጠሩት ኒውክሌር የታጠቁ የኤዥያ ግዙፍ ሃይሎች መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ለማስቀረት ኒው ዴሊ እና ቤጂንግ ያደረጉት ጥረት አካል ነው።

የወታደሮቹ መውጣት በቻይና በኩልም ተረጋግጧል ተብሏል፡፡ የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በሚቀጥለው ሳምንት ኡዝቤክስታን በሚደረገው ስብሰባ ላይ እንደሚገናኙ ይጠበቃል፡፡

የህንድ እና የቻይና ወታደሮች ሃሙስ እለት በምእራብ ሂማላያ በላዳክ ከሚገኘው የጎግራ-ሆት ስፕሪንግስ አካባቢ መውጣት ጀምረዋል ብሏል የህንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አሪንዳም ባግቺ በሰጡት መግለጫ “ሁለቱ ወገኖች በዚህ አካባቢ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በደረጃ፣ በተቀናጀ እና በተረጋገጠ መንገድ ለማቆም ተስማምተዋል፤ በዚህም ምክንያት የሁለቱም ወገኖች ወታደሮች ወደየአካባቢያቸው እንዲመለሱ ተደርጓል” ብለዋል።

በሁለቱም ወታደሮች በተገነባው አካባቢ ያሉ ሁሉም ጊዜያዊ መዋቅሮችም በስምምነቱ መሰረት ይፈርሳሉ ብለዋል።

በቅርቡ የተደረሰው ስምምነት ዝርዝር ይፋ ባይሆንም የሁለቱ ሀገራት ወታደሮች በወታደሮቻቸው መካከል መከላከያ ፈጥረው በአካባቢው የሚያደርጉትን ቅኝት ሊያቆሙ እንደሚችሉ የመከላከያ ኤክስፐርት ተናግረዋል።

በላዳክ ያገለገሉት የህንድ ሌተና ጄኔራል ራኬሽ ሻርማ “ይህ አዎንታዊ እርምጃ ነው” ብለዋል። “የፊት ለፊት ሁኔታ ተወግዷል።”

በፈረንጆቹ ሰኔ 2020 ቢያንስ 20 የህንድ እና አራት የቻይና ወታደሮች የሞቱበትን ግጭት ተከትሎ፣ ወታደሮች በቅርብ በተሰማሩባቸው በላዳክ ውስጥ ሌሎች አካባቢዎች ተመሳሳይ የመከላከያ ቦታዎችን ይአዋል፡፡

ነገር ግን ሻርማ እንዳሉት የሁለቱም ወገኖች ወታደሮች በላዳክ ውስጥ በዴምቾክ አካባቢ አቅራቢያ ቢያንስ አንድ ቦታ በቅርብ ርቀት ላይ እንደሚቆዩ እና ይህም በቀጣይ ንግግሮች ሊወሰድ ይችላል ብለዋል፡

ህንድ እና ቻይና 3800 ኪ.ሜ ያልተካለለ ድንበር ይጋራሉ፡፡

News today, Politics

ዶላርን ከገበያ የማስወጣት እንቅስቃሴ የማይቀር ነው-ፑቲን

ሩሲያ ከጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ ከበርካታ ሀገራት ጋር በሩብል ለመገበያየት ተስማምታለች

ከዓለም ዙሪያ

2022/9/12 13:28 GMT

ፕሬዝደንት ፑቱን

ሩሲያ ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ ከበርካታ ሀገራት ጋር በሩብል ለመገበያየት መስማማቷ ይታወሳል

ዶላን ከገበያ የማስወጣት እንቅስቃሴ የማይቀር ነው ሲሉ ፕሬዝደንት ፑቲን ተናግረዋል፡፡

ፕሬዝደንት ፑቱን በኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርገው ንግግር ባሰሙበት ወቅት ሩሲያ ከምእራባውያን የተሰነዘሩባትን መእቀቦች መቋቋም መቻሏን መግጻቸውን የሩሲያው አርቲ ዘግቧል፡፡

ሩሲያ ማእቀቦቹን የተቋቋመችው የተለያዩ የመከላከያ መንገዶችን በመጠቀም ነው ብለዋል ፑቲን፡፡

በቀጣይ የኢኮኖሚ አቅጣጫዎች ላይ የተናገሩት ፑቲን ዶላርን ከመገበያያነት የማስወጣት እንቅስቃሴ የማይቀር ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ሩሲያ በዩክሬን ላይ “ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ” ከጀመረች በኋላ አሜሪካን ጨምሮ ምእራባውያን በሺዎች የሚቆጠሩ ማእቀቦችን ጥለውባታል፡፡ ሩሲያ ከጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ ከበርካታ ሀገራት ጋር በሩብል ለመገበያየት ከስምምነት መድረሷ ይታወሳል፡፡

ሩሲያ ምእራባውያን ለሚገዙት ጋዝ በሩሲያ ገንዘብ ሩብል እንከፍሉ በማድረግ እና ከዚህም አለፍ ሲል የጋዝ ማስተላለፊያ መስመሮችን በመዝጋት በምእራባውያን ሀገራት የአጸፋ እርምጃ ወስዳለች፡፡ በቅርቡ ለጥገና በሚል የዘጋችው ጋዝን ከሩሲያ ወደ ጀርመን የሚደውስደው ኖርድ ስትሪም 1 የተሰኘውን የጋዝ ማስተላለፊያ መስመር እንደማትከፍት መግለጽ ይታወሳል፡፡

ጀርመን በሩሲያ ውሳኔ በእጅጉ አዝናለች፡፡

ሩሲያ እውቅና የሰጠቻቸው ሉሃንስክ ግዛት አሁን ሙሉበሙሉ ነጻ የወጣ ሲሆን የዶምባስ ግዛትን ሙሉ ለሙሉ ነጻ ለማውጣት ጦርነት እያካሄደች ትገኛለች፡፡

ዩክሬን በቅርቡ በሩሲያ ሃይሎች ላይ ድል በመቀዳጀት የተወሰኑ ቦታዎች ማስለቀቋን እየገለጸች፤ ነገርግን ሩሲያ ቦታ የለቀቀችው ጦሯን በደንብ ለማደራጀት ነው ብላለች፡፡

News today, Politics

ለንግሥት ኤልዛቤጥ ቀብር የቻይና መንግሥት መጋበዙ የምክር ቤት አባላትን አስቆጣ

በዳግማዊት ንግሥት ኤልዛቤጥ ሥርዓተ ቀብር ላይ የቻይና መንግሥት ተወካዮች እንዲገኙ የቀረበው ግብዣ እንዲሰረዝ የዩናይትድ ኪንግደም ፖለቲከኞች እና የምክር ቤት አባላት ጠየቁ።

የቻይና መንግሥት ተወካዮች በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ እንዲገኙ በዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) መንግሥት መጋበዛቸው አሳስቦናል በማለት ለአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ቢሮ ደብዳቤ ከጻፉት መካከል የወግ አጥባቂው ፓርቲ ጉምቱ አባላት ይገኙበታል።

የምክር ቤት አባላቱ በቻእና አነሳ በሆኑት ዊገር ሙስሊም ማኅብረሰብ አባላት ላይ “የዘር ማጥፋት” ወንጀል የሚያስጽሙት ባለሥልጣንት መጋበዛቸው አሳሳቢ ነው ብለዋል።

የፊታችን ሰኞ መስከረም 09/2015 ዓ.ም. በሚከናወነው የንግሥቲቱ ሥርዓተ ቀብር ላይ እንዲገኙ ለቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ይፋዊ ጥሪ የቀረበ ቢሆንም ፕሬዝዳንቱ ግን ይገኛሉ ተብሎ አይጠበቅም።

ፕሬዝዳንቱ በዚህ ሳምንት ከሁለት ዓመታት በኋላ በመጀመሪያቸው በሆነው የውጭ አገር የሥራ ጉብኝት ጉዟቸው ወደ ካዛኪስታን እና ኡዝቤኪስታን አቅንተዋል።

የቻይናው ‘ሳውዝ ቻይና ሞርኒን ፖስት’ ጋዜጣ ዲፕሎማቲክ ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው ከሆነ በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ ምክትል ፕሬዝዳንት ዋንግ ኪሻን ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በንግሥቷ ቀብር ላይ ማን ይገኛል?

በንግሥቲቱ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ወደ 500 የሚጠጉ ርዕሳነ ብሔራት እና የውጭ አገር ተወካዮች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

አብዛኞቹ መሪዎች በንግድ አውሮፕላን በረራዎች እንዲመጡ የተጠየቁ ሲሆን፤ ምዕራብ ለንደን ከሚገኝ ቦታ በአውቶብስ እንደሚጓጓዙም ተነግሯቸዋል ተብሏል።

በዕለቱ በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ ከሚገኙት መካከል ከመላው አውሮፓ የሚመጡ ንጉሣውያን ቤተሰብ አባላት ይገኙበታል።

የቤልጂየም፣ የኔዘርላንድስ፣ የስፔን ነገሥታት የሚገኙ ሲሆን፣ የኖርዌይ፣ የስዊድን፣ የዴንማርክ እና የሞናኮ ንጉሣውያን ቤተሰቦችም በቀብሩ ላይ እንዲገኙ ጥሪ ቀርቦላቸዋል።

ከአገራት መሪዎች መካከል የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከእነ ባለቤታቸው በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ እንደሚገኙ ዋይት ሐውስ አረጋግጧል።

ከኮመንዌልዝ አገራት መሪዎች መካከል የአውስትራሊ፣ የካናዳ እና የኒው ዚላንድ ጠቅላይ ሚንስትሮች ጥሪውን ተቀብለዋል።

የጀርመን፣ የጣሊያን፣ የፈረንሳይ፣ የደቡብ ኮሪያ፣ የብራዚል እና የቱርክ ፕሬዝዳንቶችም እንደሚገኙ ይጠበቃል።

ያልተገባዙትስ እነማን ናቸው?

ከሩሲያ፣ ከቤላሩስ እና ከሚያንማር በዩናይትድ ኪንግደም ንግሥት የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ እንዲገኙ የተጋበዙ ባለሥልጣንት የሉም።

ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በንግሥቲቱ ቀብር ላይ የመገኘት ዕቅድ እንደሌላቸው ቃል አቀባያቸው ቀደም ሲል ተናግረው ነበር።

ዩናይትድ ኪንግደም ከሶሪያ፣ ከቬንዙዌላ እና ከአፍጋኒስታን ጋር ሙሉ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ስለሌላት ከእነዚህ አገራት በሥነ ሥርዓቱ ላይ የሚገኝ አይኖርም።

ሰሜን ኮሪያ፣ ኢራን እና ኒካራጉዋ ደግሞ አምባሳደሮቻቸውን ብቻ እንዲልኩ ተጋብዘዋል።

News today, Politics

የቻይናና የሩሲያ የባህር ኃሎች በፓስፊክ ውቂያኖስ ላይ የውጊያ ልምምድ አካሄዱ

በሩሲያና በቻይና መርከቦች መካከል የመረጃ ልውውጥ እና የኢላማ ተኩስ የልምምዱ አካል ናቸው

የቻይናና የሩሲያ የባህር ኃሎች

የጦር ልምምዱ በሩሲያና በቻይና ባህር ኃሎች መካከል ያለውን ትብብር ለማጠናከር ያለመ ነው

የቻይና እና የሩሲያ ባህር ኃይሎች በፓስፊክ ውቂያኖስ ላይ ታክቲካዊ የውጊያ ልምምድ ማድረጋቸው ተገለፀ።

በጦር ልምምዱ ላይ የሩሲያ ባህር ኃይል አባላት ከቻይና አቻቸው ጋር የኮሙዩኒኬሽን እና ሌሎችም ወታደራዊ ልምምዶችን ማድረጋቸውን አር.ቲ ዘግቧል።

በልምመዱም በቻይና እና በሩሲያ የጦር መርከቦች መካከል ግንኙነት እንዴት መለዋወጥ እንደሚችል፣ የባህር ላይ የተኩስ ልምምድ እና የጦር መርከብ ሄሊኮፕተር ድጋፍ አሰጣጥ ላይ ልምምድ አድርገዋል።

የውጊያ ልምምዱ በቤጂንግ እና በሞስኮ የባህር ኃይሎች መካከል ያለውን ትብብር ለማጠናከር ታስቦ የተዘጋጀ ነው ተብሏ።

በተጨማሪም ልምምዱ የእሲያ-ፓስፊክ ቀጠናን ሰላም እና መረጋጋት ለማስጠበቅ እና በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ኢኮኖሚያዊ እንቅቃሴዎችን ለመጠበቅ ያለመ ነው።

የቻይና እና የሩሲያ ወታደሮች ከሳምንታት በፊት ሩሲያ አስተናጋጅነት በተካሄደው የቮሶቶክ 2022 ወታደራዊ ልምምድ ላይ የጋራ ልምምድ አድርገው እንደነበረ ይታወሳል።

በዚሁ ልምምድ ላይ የቻይና እና የሩሲያ ወታደሮች በጋራ ወታደራዊ የኢላማ ተኩስ ልምምድ ማድረጋቸው ተገልጿል።

በዚህም የሩሲያ የፓስፊክ የባህር ኃይል እና የቻይና ባህር ኃይል ከጦር መርከቦች ላይ በመሆን የምድር ላይ ኢላማዎችን የመምታት የተኩስ ልምምድ አካሂደዋል ነው የተባለው።

በወቅቱም ቻይን ቻይና የጦር ልምምዱ ከወቅቱ የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ጋር እንደማይገናኝ መግለጿ ይታወሳል።

News today, Politics

ለዩክሬን የረጅም ርቀት መሳሪያ ማስታጠቅ ቀይ መስመርን ማለፍ ነው ስትል ሩሲያ አስጠነቀቀች

ዩክሬን የረጅም ርቀት ተተኳሽ የጦር መሳሪያ እንዲሰጣት ለአሜሪካ ጥያቄ አቅርባለች

የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ 206ኛ ቀኑ ላይ ይገኛል

ለዩክሬን የረጅም ርቀት መሳሪያ ማስታጠቅ ቀይ መስመርን ነው ስትል ሩሲያ አስጠነቀቀች፡፡

ከስድስት ወር በፊት የተጀመረው የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት አሁንም እንደቀጠለ ሲሆን ሀያላን ሀገራት ጎራ ለይተው ድጋፍ በማሰባሰብ ላይ ይገኛሉ፡፡

በዚህ ጦርነት ሩሲያ እንድትሸነፍ አሜሪካ እና የአውሮፓ ሀገራት ለዩክሬን የተለያዩ ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎችን በማስታጠቅ ላይ ናቸው፡፡

ዩክሬንም ከነዚህ ሀገራት የሚደረግላትን የጦር መሳሪያ በመጠቀም በሩሲያ ተይዘው የነበሩ ቦታዎችን መልሳ በማስለቀቅ ላይ ስትሆን አሜሪካ የረጅም ርቀት ተምዘግዛጊ የጦር መሳሪያዎች እንዲሰጧት ጠይቃለች፡፡

ሩሲያ በበኩሏ ለዩክሬን የረጅም ርቀት ተምዘግዛጊ የጦር መሳሪያ ማስታጠቅ ማለት ቀይ መስመርን ማለፍ ነው ስትል አስጠንቅቃለች፡፡

የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እንዳሉት አሜሪካ ለዩክሬን የረጅም ርቀት የጦር መሳሪያ ካስታጠቀች ሞስኮ ራሷን ለመከላከል ስትል እርምጃ ትወስዳለች ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

የአሜሪካ መከላከያ ዋና አዛዥ ሊዮድ ኦስቲን ሀገራቸው ለዩክሬን ተጨማሪ የ675 ሚሊዮን ዶላር ግምት ያላቸው የጦር መሳሪያዎች ልትሰጥ እንደምትችል ተናግረዋል፡፡

የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዶሚር ዘለንስኪ በበኩላቸው ከአሜሪካ እና ምዕራባዊያን በሚደረግላቸው የጦር መሳሪያ ድጋፍ በሩሲያ ጦር ተይዘው የነበሩ አካባቢዎችን እያስለቀቁ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በሩሲያ የተያዙ ሌሎች የዩክሬን ግዛቶችን ለማስለቀቅም የረጅም ርቀት የጦር መሳሪያዎች እና ሌሎች አጋዥ መሳሪያዎች ድጋፍ እንዲደረግላቸው ለአሜሪካ እና አውሮፓ ህብረት ሀገራት ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

ለሰባት ወራት በዘለቀው የሩሲያ ጦርነት ከሁለቱም ወገኖች በርካታ ወታደሮች እና ንጹሃን የተገደሉ ሲሆን ከ10 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ደግሞ ወደ ጎረቤት ሀገራት እንደተሰደዱ ተመድ ገልጿል፡፡ 

News today, Politics, social life

ግብፅና ኳታር በኢኮኖሚና በሌሎች ዘርፎች በትብብር ለመስራት ስምምነት ተፈራረሙ

የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አለሲሲ ከ4 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በኳታር ጉብኝት አድርገዋል

ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አለሲሲ እና የኳታ ኢሚር ታሚም

ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አለሲሲ እና የኳታ ኢሚር ታሚም በሁለትሽ ጉዳዮች ላይ መክረዋል

የግብጹ ፕሬዝዳት አብዱልፈታህ አል ሲሲ በኳታር ይፋዊ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸው ተገልቷል።

ፕሬዝዳት አብዱልፈታህ አልሲሲ ከአራት ዓመታት ወዲህ በሳለፍነው ማክሰኞ ለመጀመሪያ ጊዜ ዶሃ ሲደርሱም በኳታር ኢሚር ታሚም አቀባባበል ተደርጎላቸዋል።

በትናትናው እለትም የግብጹ ፕሬዝዳት አብዱልፈታህ አልሲሲ እና የኳታሩ ኢሚር ታሚም በሀገራ የሆለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተመካክረዋል።

በዚህም የኳታሩ ኢሚር ታሚም ፕሬዝዳንት አል ሲሲ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ግንኙነት እንዲያደግ እየሰሩት ላው ስራ ማማስገናቸውን የኳታር የዜና ኤጀንሲ ዘግቧል።

የፕሬዝዳንት አል ሲሲ ግብኝት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ የሚያጠናከር እንደሚሆን ተስፋ እንዳላቸውም አስታውቀዋል።

ፕሬዝዳንት አል ሲሲ በበኩላቸው፤ ግብጽ ከኳታ ጋር በኢኮኖሚ፣ ፖለቲካ እና በደህንነት ዘርፎች ከኳታር ጋር ለመስራት ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል።

ውይይቱን ተከትሎም ሁለቱ ሀገራት መካከል በተለያዩ ዘርፎች ስምምነት የተካሄደ ሲሆን፤ ከስምምነቶቹ ውስጥም ልማትና ኢንቨስምንት እንዲሁም የማህበራዊ ዘርፍ ይገኝበታል።

News today, Politics

የስዊድኗ ጠቅላይ ሚኒስትር የስልጣን መልቀቂያ ደብዳቤ አስገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ማግዳሊና አንደርሰን የስልጣን መልቀቂያ ደብዳቤ ለፓርላማው አስገብተዋል

ጠቅላይ ሚኒስትሯ መልቀቂያ ያስገቡት ፓርቲያቸው በምርጫ መሸነፉን ተከትሎ ነው

የስዊድኗ ጠቅላይ ሚኒስትር የስልጣን መልቀቂያ ደብዳቤ አስገቡ ፡፡

ባለፈው እሁድ በስዊድን የህግ አውጪ ምክር ቤት ምርጫ ተካሂዶ የነበረ ሲሆን ሀገሪቱን በጠቅላይ ሚኒስትርነት የሚመሩት አንደርሰን ፓርቲ በምርጫው ተሸንፏል፡፡

ይሄንን ተከትሎም ጠቅላይ ሚኒስትር አንደርሰን የግድ መንግስታቸውን አፍርሰው በምርጫው ላሸነፈው ቀኝ ዘመም ፓርቲዎች ስልጣን ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

በዛሬው ዕለትም ጠቅላይ ሚኒስትር አንደርሰን ለሀገሪቱ ህግ አውጪ ምክር ቤት የስልጣን መልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የስዊድን ግራ ዘመመም ፓርቲዎች ከዚህ በፊት የነበረውን ምርጫ አሸንፈፈው ጠቅላይ ሚኒስትር ማግደሊና አንደርሰንን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ሾመው የነበረ ሲሆን አሁን በተካሄደው ምርጫ ደግሞ ቀኝ ዘመም ፓርቲዎች በጠባብ ልዩነት አሸንፈዋል፡፡

ግራ ዘመም ፓርቲዎች ምርጫውን 173 ለ176 ድምጽ ልዩነት የተሸነፉ ሲሆን የሞደሬት ፓርቲ መሪ የሆኑት ኡልፍ ክሪሰትረሰን አዲስ መንግስት እንደሚመሰርቱ ይጠበቃልም ተብሏል፡፡

ላለፉት 11 ወራት ስዊድንን በጠቅላይ ሚኒስትርነት የመሩት አንደርሰን የኑሮ ውድነት፣ የስደተኞች አያያዝ እና የግድያ ወንጀሎች መበራከት በምርጫው እንዲሸነፉ ዋነኛ ምክንያቶች እንደሆኑ ተገልጿል፡፡

የስዊድን ቀኝ ዘመም ፓርቲዎች በሀገራቸው አጥፊዎች ረጅም ዓመት የሚቆይ እስር እንዲፈረድባቸው ማድረግ ፣ስደተኞች ለሀገራቸው ደህንነት አደጋ በማይሆኑበት መንገድ እንዲያዙ እና ሌሎችንም ጉዳዮች የምረጡኝ ቅስቀሳቸው ዋነኛ አጀንዳዎች ነበሩ፡፡

News today, Politics

ፑቲን፤ “ዓለምን በበላይነት ለመቆጣጠር የሚደረገውን ሙከራ” እንደማይቀበሉ ለቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ገለፁ

ፕሬዝዳንት ዢ፤ ቻይና ከሩሲያ ጋር ለመስራት እንደምትፈልግ ለፑቲን አረጋግጠውላቸዋል

2022/9/15 16:52 GMT

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና ቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ

ፑቲን፤ ለቻይናው ፕሬዝዳንት “በዩክሬን ጉዳይ ያንጸባረቁትን ሚዛናዊ አቋም አደንቃለሁ” ብለዋል

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን፤ “ዓለምን በበላይነት ለመቆጣጠር የሚደረገው ሙከራ” እንደማይቀበሉ ለቻይናው አቻቸው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ገለጹ።

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና ቻይናው ዢ ጂንፒንግ የዩክሬን-ሩሲያ ከተጀመረ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በኡዝቤኪስታን መዲና ሳማርካንድ ተገናኝተዋል

ሁለቱ መሪዎች የሻንጋይ የትብብር ድርጅት የመሪዎች ጉባኤ ላይ የጎንዮሽ ውይይት አድርገዋል።

በዚህም ፑቲን “አንድ የማይታወቅ ዓለም ለመፍጠር የተደረጉ ሙከራዎች በቅርብ ጊዜ በጣም አስቀያሚ ቅርጽ እየያዙ ነው፤ እናም ፈጽሞ ተቀባይነት የሌላቸው ናቸው” ሲሉ ነው ለቻይናው አቻቸው መናገራቸውን ነው ሮይተርስ የዘገበው፡፡

የፑቲንን ኃሳብ የሚጋሩትና “የቀድሞ ጓደኛዬን” በማግኘቴ ደስተኛ ነኝ ያሉት ፕሬዝዳንት ዢ በበኩላቸው ቻይና ከሩሲያ ጋር ለመስራት እንደምትፈልግ ለፑቲን አረጋግጠውላቸዋል።

አክለውም ቻይና “በተመሰቃቀለ ዓለም ውስጥ መረጋጋት እና አዎንታዊ ጉልበት ለማስፋፋት ትፈልጋለች ” ብለዋል።

በሌላ በኩል መሪዎቹ የዩክሬን አሁናዊ ሁኔታን አንስተው የተወያዩ ሲሆን ፤የቻይናው ፕሬዝዳንት የዩክሬን ጉዳይ እንደሚስስባቸው ለፑቲን መናገራቸውን ሮይተረስ ዘግቧል።

ዢ በዩክሬን ጉዳይ የተለያዩ ስጋቶችና ጥያቄዎች እንደነበራቸው እረዳለሁ ያሉት ፑቲን፤ የቻይናው መሪ በዩክሬን ጉዳይ ያንጸባረቁትን “ሚዛናዊ አቋም” እንደሚያደንቁ ገልጸውላቸዋል።

“ከዩክሬን ቀውስ ጋር በተያያዘ የቻይና ወዳጆቻችንን ላሳዩት ሚዛናዊ አቋም ትልቅ ክብር አለን” ሲሉም ነው ፑቲን ለዢ የገለጹላቸው።

መልካም የሚባል ግንኙነት እንዳለቸው የሚነገርላቸው መሪዎቹ በኡዝቤኪስታን ፊት ለፊት ሲገናኙ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ወታደራዊ ዘመቻ ከጀመረች ወዲህ የመጀመሪያ ነው ተብሏል፡፡

በተለይም በኮሮና ምክንያት ኩፉኛ የተፈተነችው ሀገር መሪ ለሆኑት ለቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ የመጀመሪያ የባህር ማዶ ጉዞ መሆኑ ነው።

የመሪዎቹ መገናኘት ፤ በዩክሬን ጦርነት ምክንያት ዓለም ፊቱን ላዞረባት ሞስኮ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው እየተገለጸ ነው።

ሞስኮ እና ቤጂንግ በተለይም ከቅርብ አመታት ወዲህ ከምዕራቡ ዓለም ጋር ባለቸው ግንኙነት የቅርብ አጋሮች ሆነው ብቅ ያሉበት አጋጣሚ ተፈጥረዋል።

News today, Politics

የዩክሬን ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ የመኪና አደጋ ደረሰባቸው

ፕሬዝደንት ዘሌሰንኪ ወታደሮቻቸው በመልሶ ማጥቃት 2 ሺህ ስኩዌር ኪሎ ሜትር ቦታ ከሩሲያ ነጻ መውጣቱን ተናግረዋል

ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪ ጦራቸው ከሩሲያ ያስለቀቃቸውን ስፍራዎች ጎብኝተው ሲመለሱ ነው አደጋው ያጋጠመው

የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪ

የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪ የመኪና ግጭት አደጋ እንደደረሰባቸው ቃል አቀባያቸው ይፋ አድርገዋል።

ፕሬዚዳንቱ በኪቭ ከተማ ውስጥ በእጀባ በመጓዝ ላይ እያሉ ያሉበት መኪና ከመንገደኛ መኪና ጋር መጋጨቱን የፕሬዝዳቱ ቃል አቀባይ ሰርጉ ነይክሪፎቭ ባጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

ከአደጋው በኋላ ፕሬዝዳንቱ በዶክተሮች እንደታዩ እና ከባድ ጉዳት እንዳልደረሰባቸው መረጋገጡንም ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል።

ከፕሬዝዳንቱ መኪናጋር የተጋጨው አሽከርካሪ በስፍራው የህክምና ክትትል ከተደረገለት በኋላ በአምቡላንስ ወዳልታወቀ ስፍራ እንደተወሰደም ቢቢቢ ዘግቧል።

የመኪና አደጋው ሁኔታ በህግ አስከባሪ አካላት ምርመራ እየተደረገበት መሆኑን ሰርጉ ነይክሪፎቭ አስታውቀዋል።

ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪ ጦራቸው ከሩሲያ ነጻ በማውጣት የተቆጣጠራትን ኢዚየም ከተማን ጎብኘተው ሲለመሱ እንደሆነም ታውቋል።

ፕሬዝደንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ ባሳለፍነው ሳምንት በሰጡት መገለጫ፤ ወታደሮቻቸው በወሰዱት የመልሶ ማጥቃት እርምጃ “2 ሺህ ስኩዌር ኪሎ ሜትር ቦታ ከሩሲያ ነጻ መውጣቱ” ተናግረዋል።

የዩክሬን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዲሚትሮ ኩሌባ ፤ እየተገኙ ያሉ ድሎች የዩክሬን ኃሎች የሩሲያ ጦርን ማሸነፍ እንደሚችሉ አማላካች ናቸው ብለዋል።

ጦርነቱ በፍጥነት እንዲጠናቀቅ ምዕራባውያንና የዩክሬን አጋሮች የሚያደርጉት የጦር መሳሪያ ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉበት ሲሉም ተማጽነዋል።

News today, Politics

የብሪታኒያ ንጉስ ርእሰ ብሄር የሆኑባቸው ሀገራት የትኞቹ ናቸው…ʔ

የብሪታኒያ ንግስ በዓለማችን ላይ ላሉ 15 ሀገራት ርእሰ ብሄር ናቸው

ሀገራቱ ሉዓላዊ ቢሆኑም የብሪታኒያ ጉስ ግን እስካሁን ድረስ ርእሰ ብሄራቸው ናቸው

የብሪታኒያ ንግስት ኤልሳቤጥ ከ70 ዓመታት የንግስና ዘመን በኋላ በ96 ዓመታቸው ማረፋቸው ይታወሳል።

ንጉስ ቻርልስ

ይህንን ተከትሎ የንግስት ኤልሳቤጥ የመጀመሪያ ልጅ ንጉስ ቻርልስ የንግስና ዙፋኑን ተረክበዋል።

በዚህም ንጉስ ቻርልስ ንግስት ኤላሳቤጥ በግንስና ዘመናቸው ከሀገራቸው በተጨማሪ ርእሰ ብሄር በነበሩባቸው ሀገራት ላይም ርእሰ ብሄር በመሆን ይመራሉ።

ሀገራቱ ከዚህ ቀደም የእንግሊዝ ቀኝ ግዛት የነበሩ ሲሆን፤ ከቀኝ ግዛት ከተላቀቁ በኋላም ግን ሀገራቱ የብሪታኒያ ንጉሳውያንን በሀገራቸው ርእሰ ብሄር አድረገው ሾመዋል።

የብሪታኒያ ንጉስ ርእሰ ብሄር የሆኑባቸው 15 ሀገራት የትኞቹ ናቸው..ʔ

1. ካናዳ

2. ጃማይካ

3. አውስትራሊያ

4. ኒውዚላንድ

5. በሃማስ

6. ፓፑዋ ኒው ጊኒ

7. ሰለሞን ደሴቶች

8. በሊዝ

9. ሴንት ኪትስ እና ኔቪስ

10. ሴንት ሉሲያ እና ገራኒድስ

11. ቱቫሉ

12. አንቲጉዋ እና ባበርቡዳ

13. ግሬናዳ

14. ሰለሞን ደሴቶች እንዲሁም

15. ብሪታኒያ ናቸው

የንግስት ኤልሳቤጥን ህልፈት ተከትሎ በተለያዩ ሀገራት ውስጥ የቢሪታኒያ ንጉሳውያንን ከሀገራቸው ርእሰ ብሄርነት የማንሳት እንቅስቃሴ መጀመሩ ይታወቃል።

የብሪታኒያ ቅኝ ግዛት የነበረችው አንቲጓና ባርቡዳ ደሴት የብሪታኒያ ንጉሳውያንን ከርዕሰ በሄርነት በማንሳት ሪፐብሊክ ለመሆን የሚያስችላትን ህዝበ ውሳኔ ልታካሂድ መሆኑን የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ጋስቶን ብራዎን አስታውቀዋል።

አንቲጓና ባርቡዳ በፈረንጆቹ 1981 ከቅኝ ግዛት ነጻ ብትወጣም፤ የበሪታኒያ ንግስት ግን የሀገሪቱ ርዕሰ ብሄር ነበሩ።

ደቡብ አሜሪካዊቷ ሀገር ባርባዶስ ባሳለፍነው ዓመት ህዳር ወር ላይ የብሪታኒያ ንጉሰውያንን ከርዕሰ ብሄርነት በማንሳት ሪፐብሊክነቷን ማወጇ ይታወሳል።

News today, Politics

የጀርመን መራሄ መንግስት “ሩሲያ ከዩክሬን ምድር ሙሉ በሙሉ ለቃ እንድትወጣ” ፑቲንን ጠየቁ


ኦላፍ ሾልዝ፤ ፑቲን በተቻለ ፍጥነት ወደ “ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ” እንዲመጡ አሳስበዋል
የጀርመኑ መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ “ሩሲያ ከዩክሬን ምድር ሙሉ በሙሉ ለቃ እንድትወጣ” ፑቲንን ጠየቁ፡፡


ኦላፍ ሾልዝ ከፑቲን ጋር በነበራቸው 90 ደቂቃ በፈጀ የስልክ ቆይታ ፤ “ፑቲን በተቻለ ፍጥነት ተኩስ አቁመው ወደ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ እንዲመጡና ወታደራቸው ሙሉ በሙሉ ከዩክሬን ምድር በማውጣት የዩክሬን ግዛት ሉዓላዊነት እንዲያከብሩ” ማሳሰባቸው ቃል አቀባያቸው ስቴፈን ሃበስተሬት አስታውቋል፡፡


ኦላፍ ሾልዝ በተጨማሪም ሩሲያ በተደጋጋሚ የምትወቅሰውን እህል ከዩክሬን ወደ ውጭ የመላክ ጉዳይ የተደረሰውን የእህል ስምምነት እንድታከብር ፑቲንን መናገራቸውም ኤኤፍፒ ዘግቧል።


ፑቲን የእህል ስምምነቱን እንዳያጣጥሉ እና ሙሉ በሙሉ መተግበሩን እንዲቀጥሉም የጀርመኑ መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ ተማጽነዋል፡፡


ኦላፍ ሾልዝ አሁን ላይ የጦርነቱ የስህበት ማዕከል ስለሆነው የዛፖሪዝሂያ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ደህንነት ጉዳይ በተመለከተም ለፑቲን ጥያቄ አንስተው ተወያይተዋል፡፡


በዚህም የጀርመኑ መሪ ፑቲን “ምንም አይነት መባባስ እንዲያስወግዱና በዓለም አቀፍ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ የተመከሩትን እርምጃዎች (ነጻ ቀጠና እንዲቋቋም) ሙሉ በሙሉ እንዲተገብሩ” ጠይቀዋል።


የጀርመኑ መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ ከፑቲን ጋር ዘለግ ያለ ቆይታ ያደረጉት፤ ሞስኮ በርሊን ለዩክሬን የጦር መሳሪያዎችን በመላክ ቀይ መስመር እየጣሰች ነው የሚል ማስጠንቀቅያ በሰጠቀችበት ማግስት መሆኑ ነው፡፡


በጀርመን የሩሲያ አምባሳደር ሰርጌይ ናቼቭ ፤ የዩክሬን መንግስት ጀርመን ስሪት አውዳሚ ጦር መሳሪያዎችን እየታጠቀ መሆኑ ሀቅ ነው ማለታቸው አይዘነጋም፡፡
የጦር መሳሪያዎች በሩሲያ ጦር ላይ ብቻ ሳይሆን በዶንባስ ክልል በሚገኙ ንጹሃን ዜጎችን ለማጥቃት እየዋሉ እንደሆነም ነበር የተናገሩት አምባሳደሩ፡፡


የጀርመን መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ ሀገራቸው ለዩክሬን አዲስ የጦር መሳሪያ ልታበረክት መሆኑን እና በቅርቡ እንደሚላክላት መናገራቸው ይታወሳል።


ኦላፍ ሾልዝ ሃምሌ ላይ በዩክሬን ጉብኝት ማድረጋቸው የሚታወስ ሲሆን ሀገራቸው ዩክሬንን ለማገዝ ዝግጁ መሆኗን ለፕሬዝዳንት ዘለንስኪ በገልጸውላቸዋል።


ጀርመን ቀይ መስመር አልፋለች ስትል ሩሲያ አስጠነቀቀች
ጀርመንም ለዩክሬን ጦር መሳሪያ ለማቅረብ በሚል ፖሊሲ እስከ ማሻሻል ደርሳ እንደነበረ ይታወሳል።


ሩሲያም በተለያዩ ጊዜያት ከምእራባውያን ለዩክሬን ያበረከቷቸው የረጅም ርቀት ሮኬትን ጨምሮ ይለያዩ የጦር መሳሪያዎችን አወደምኩ ማለቷ አይዘነጋም።

News today, Politics

ዢ ዢንፒንግ እና ፑቲን ስለ ዩክሬን ጦርነት እንደሚወያዩ ተገለጸ

የቻይናው መሪ ዢ ዢንፒንግ እና የሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን ስላለው ጦርነት እና በሌሎች “ዓለም አቀፋዊ እና ክልላዊ ጉዳዮች” ዙሪያ በሳምንቱ መጨረሻ እንደሚወያዩ ክሬምሊን ገለጸ።

መሪዎቹ በኡዝቤኪስታን የሚወያዩ ሲሆን ለምዕራቡ ዓለም “አማራጭ” በሚያሳየው ስብሰባ ላይ ነው የሚገናኙት ብሏል ክሬምሊን።

ዢ ዢንፒንግ እና ቭላድሚር ፑቲን

ዢ ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት በኋላ የመጀመሪያውን የባሕር ማዶ ጉብኝታቸውን እያደረጉ ነው።

ጉብኝቱ ዢ ሦስተኛ የሥልጣን ዘመን ለማግኘት በሚጥሩበት እና ፑቲን ከምዕራቡ ዓለም ጋር ያላቸው ግንኙነት በዩክሬን ጦርነት ምክንያት ዝቅተኛ ደረጃ በደረሰበት ወቅት የሚካሄድ ነው።

ዢ የሦስት ቀን ጉብኝታቸውን በካዛኪስታን ረቡዕ ጀምረዋል።

ከዚያም ለሁለት ቀናት በሚቆየውና በሳምርካንድ በሚካሄደው የሻንጋይ የትብብር ድርጅት (ኤስሲኦ) ስብሰባ ላይ ከፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር ይገናኛሉ።

ፑቲን ከሕንድ፣ ከፓኪስታን፣ ከቱርክ እና ከኢራን መሪዎች ጋርም ይገናኛሉ።

ከቻይናው መሪ ጋር የሚያደርጉት ውይይት “በተለየ መልኩ ጠቃሚ ነው” ሲሉ የክሬምሊን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ቃል አቀባይ ዩሪ ኡሻኮቭ ተናግረዋል።

ጉባኤው እየተካሄደ ካለው “ትልቅ የፖለቲካ ለውጥ ጀርባ የሚደረግ ነው” ብለዋል።

ኤስሲኦ እአአ በ2001 ከቀድሞ የሶቪየት ማዕከላዊ እስያ አራት አገራት ጋር የተመሠረተ ነው።

ቻይና እና ሩሲያ ድርጅቱን ለምዕራባውያን ቡድኖች እንደ አማራጭ ለማቀረብ ደፋ ቀና ሲሉ ቆይተዋል።

የዢ ጉብኝት ዜሮ ኮቪድ የተባለው ፖሊሲ በቀጠለበት እና በቻይና በአንዳንድ አካባቢዎች አሁንም የእንቅስቃሴ ገደብ በተጣለበት ወቅት ነው።

የተቀረው ዓለም ከቫይረሱ ጋር አብሮ መኖርን በመማር ወደ ቀድሞ  ሕይወት ሲመለስ ቤጂንግ ድንገተኛ ሁኔታ በተፈጠረ ቁጥር ሁሉንም ከተሞቿን እና ግዛቶችን መዝጋቷን ቀጥላለች።

ዢ ለመጨረሻ ጊዜ ከአገር ውጭ ጉብኝት ያደረጉት እአአ ጥር 2020 ምያንማርን ለመጎብኘት ሲያቀኑ ነው።

ይህም የመጀመርያው የእንቅስቃሴ ገደብ በውሃን ከመጣሉ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ ነበር።

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በቻይና ለመቆየት የተገደዱ ሲሆን ሐምሌ ላይ ከዋናው ቻይና ውጭ ወደ ሆንግ ኮንግ አቅንተዋል።

ፑቲንም በውጭ አገራት ያልተለመደ ጉዞ እያደረጉ ነው።

የሩሲያ ወታደሮች ዩክሬንን ከወረሩ በኋላ በሐምሌ ወር ቴህራን ላይ ከቱርክ እና ከኢራን መሪዎች ጋር ካደረጉት ስብሰባ ወዲህ ይህ ሁለተኛው የውጭ ጉብኝታቸው ነው።

ሁለቱ መሪዎች በዚህ ዓመት ለሁለተኛ ጊዜ ነው የሚገናኙት። ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኙት በየካቲት ወር ቤጂንግ ባዘጋጀችው የክረምት ኦሊምፒክ ነው።

በየካቲት የተካሄደውን ስብሰባ ተከትሎ ሁለቱ መሪዎች በጋራ ባወጡት መግለጫ በአገሮቻቸው መካከል ያለውን ወዳጅነት “ገደብ የለሽ” ብለውታል።

ሩሲያ ከቀናት በኋላ ዩክሬንን ወረረች። ቻይና ወረራውን ማውገዟንም ሆነ መደገፏን አልገለፀችም።

ቤጂንግ ለጦርነቱ ተጠያቂዎቹ ሁለቱም ወገኖች ናቸው ትላለች።

ቻይና በሩሲያ ላይ የተጣለው ዓለም አቀፍ ማዕቀብ አካል አይደለችም። በሁለቱ አገራት መካከል ያለው የንግድ ልውውጥም እያደገ መሄዱን ቀጥሏል።

ከዩክሬን ወረራ በኋላ ሕንድ እና ቻይና ከሩሲያ የሚያስገቡት ነዳጅ ጨምሯል።

ቻይና ከምዕራቡ ዓለም እና በተለይም ከአሜሪካ ጋር ያላትን ግንኙነት በቅርብ ወራት ወዲህ ውጥረት ነግሦበታል።

የታይዋን ጉዳይ ደግሞ ነገሩን አባብሶታል። ቻይና ደሴቱን የግዛቴ አካል ነው ትላለች።

የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ ደሴቲቱን መጎብኘታቸውን ተከትሎ “ምላሽ ለመስጠት” በሚል ቤጂንግ በታይዋን ዙሪያ ለአምስት ቀናት የሚቆይ ወታደራዊ ልምምድ አድርጋለች።

የቻይናን ጉዳይ የሚከታተሉ ባለሙያዎች እንደሚሉት በእንቅስቃሴ ገደብ እና ኢኮኖሚ መቀዛቀዝ ምክንያት ተግዳሮቶች ቢኖርባቸውም፣ ዢ ከሁለት ዓመት በኋላ ቻይናን ለቀው ለመውጣት መወሰናቸው በአመራሩ ላይ ያላቸውን እምነት ያሳያል።

ተንታኞች እንደሚሉት በመጪው ጥቅምት በሚካሄደው የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ኮንግረስ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ለሦስተኛ ጊዜ እንዲመረጡ ይጠብቃሉ።

የሻንጋይ የትብብር ድርጅት ማነው?

ኤስሲኦ በቻይና፣ ሩሲያ፣ ካዛኪስታን፣ ኪርጊስታን፣ ታጃኪስታን እና ኡዝቤኪስታን የተመሠረተ የአውሮፓ እና እስያ አገራት የፖለቲካ ፣ የምጣኔ ሀብት እና የደኅንነት ድርጅት ነው።

ኢራን በ2001 የተቋቋመውን ድርጅት ለመቀላቀል ፍላጎት አላት።

ቻይና በቤልት ኤንድ ሮድ ፕሮጀክቶቿ በቀጠናው ትልቅ መዋዕለ ንዋይ የምታፈስ ሲሆን አባላቱ በንግድ ዙሪያ ይወያያሉ።

ቤጂንግ ከአውሮፓ ጋር ለምታደርገው የንግድ ልውውጥ አዳዲስ የባቡር መስመሮችን ለመዘርጋት የምትፈልግ ሲሆን የመካከለኛው እስያ አገራት ደግሞ ከቻይና ጋር የበለጠ ግንኙነት ለመፍጠር ጉጉት አላቸው።

ኪርጊስታን በ2023 ከቻይና እና ኡዝቤኪስታን ጋር የሚያገናኛትን አዲስ የባቡር መስመር ዝርጋታ እንደምትጀምር አስታውቃለች።

News today, Politics

ሩሲያ በሌሎች ሀገራት ፍላጎቷን ለማስጠበቅ 300 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ማድረጓን አሜሪካ ገለጸች

ሩሲያ በአምስት አህጉራት ለሚገኙ ከ20 በላይ ሀገራት ገንዘብ ፈሰስ አድርጋለች ተብሏል

ሩሲያ እስካሁን በአሜሪካ ክስ ዙሪያ ምላሽ አልሰጠችም

ሩሲያ በሌሎች ሀገራት ፍላጎቷን ለማስጠበቅ 300 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ማድረጓን አሜሪካ ገለጸች።

የአሜሪካ የደህንነት ተቋም ባወጣው መረጃ ሩሲያ በተለያዩ የዓለማችን ሀገራት የፖለቲካ ፍላጎቷን ያስፈጽሙልኛል ያለቻቸውን እጩዎች እና ፓርቲዎች በገንዘብ እየረዳች ነው ብሏል።

እንደ ሮይተርስ ዘገባ ከሆነ ሩሲያ በአምስት አህጉራት ለሚገኙ ከ20 በላይ ሀገራት ከ300 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ፈሰስ አድርጋለች ።

በተለይም ከፈረንጆቹ 2014 ጀምሮ ለአውሮፓ፣ እስያ፣ አፍሪካ እና ሁለቱ የአሜሪካ አህጉራት ስር ላሉ ሀገራት በተለያየ መንገድ ገንዘብ ሰጥታለች ተብሏል።

ሩሲያ ገንዘቡን ፈሰስ የምታደርገው በፋውንዴሽን ስም በተቋቀቋሙ ድርጅቶች እና ለይስሙላ በተቋቋሙ የንግድ ድርጅቶች ስም እንደሆነም አሜሪካ ገልጻለች።

አሜሪካ በሩሲያ የገንዘብ ድጋፍ የተደረገላቸውን ሀገራት ለጊዜው ያልጠቀሰች ሲሆን ከአውሮፓ አልባኒያ፣ ቦስኒያ እና ሄርዜጎቪና፣ ሞንቴኔግሮ ሲሆኑ ከአፍሪካ ደግሞ ሜዳጋስካር አንዷ መሆኗን ኤኤፍፒ ከፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጽህፈት ቤት ያገኘውን መረጃ ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

ሩሲያ ገንዘቡን ወደ ምትፈልጋቸው ሀገራት እና የፓርቲ እጩዎች ቤልጂየም እና ኢኳዶር ከሚገኙት የሩሲያ ኢምባሲዎች በኩል እንደሆነም ተጠቅሷል።

አሜሪካም የፓለቲካ ፍላጎቶቿን ለማስፈጸም በተለያዩ የዓለማችን ሀገራት ላይ በሲአይኤ በኩል ጣልቃ በመግባት መፈንቅለ መንግስት እስከማስፈጸም የሚደርስ ሙከራ ታደርጋለች የሚል ክስ እንደሚነሳባት የጀርመን ድምጽ ዘግቧል።

በተለይም በኢራን እና በቺሊ ሲአይኤ መፈንቅለ መንግስት እንዲፈጸም አድርጓል በሚል የሚቀርብባትን ክስ አሜሪካ ውድቅ አድርጋለችም ተብሏል።

የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳድር በሩሲያ ላይ ያቀረበውን ክስ ራሷ አሜሪካ በዲሞክራሲ እና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ስም ትፈጽማለች በሚል የቀረበበትን ክስ ውድቅ ማድረጉም ተገልጿል።ሩሲያ በአሜሪካ በቀረበባት ክስ ዙሪያ እስካሁን ምላሽ እንዳልሰጠች ተገልጿል።

News today, Politics

ጀርመን ቀይ መስመር አልፋለች ስትል ሩሲያ አስጠነቀቀች

ጀርመን ለዩክሬን የጦር መሳሪያዎችን በመላኳ ነው ከሩሲያ ማስጠንቀቂያ የደረሳት

የጀርመን መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ

በበርሊን የሩሲያ አምባሳደር ጀርመን ለዩክሬን ያቀረበቻቸው የጦር መሳሪያዎች ነጹሃን እየተጎዱበት ነው ብለዋል

ጀርመን ለዩክሬን የጦር መሳሪያዎችን በመላክ ቀይ መስመር እየጣሰች ነው ሲሉ በበርሊን የሩሲያ አምባሳደር አስጠነቀቁ።

በጀርመን የሩሲያ አምባሳደር ሰርጌይ ናቼቭ፤ የዩክሬን መንግስት ጀርመን ስሪት አውዳሚ ጦር መሳሪያዎችን እየታጠቀ መሆኑ ሀቅ ነው ብለዋል።

ነገር ግን በእነዚህ የጦር መሳሪያዎች በሩሲያ ጦር ላይ ብቻ ሳይሆን በዶንባስ ክልል በሚገኙ ንጹሃን ዜጎችን ለማጥቃት እየዋሉ ነው፤ ይህ ደግሞ ቀይ መስመርን መጣስ ነው ማለታቸውን አር.ቲ ዘግቧል።

የጀርመን መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ ሀገራቸው ለዩክሬን አዲስ የጦር መሳሪያ ልታበረክት መሆኑን እና በቅርቡ እንደሚላክላት መናገራቸው ይታወሳል።

አዲሱ የጦር መሳሪያ “ሱፐር ሞዴል ዊፐን” በመባል እንደሚጠራም መራሄ መንግስቱ የተናገሩ ሲሆን፤ በተጨማሪም ትልቅ የአየር መከላከያ ስርዓት፤ ራዳር እና ድሮኖች ለዩክሬን እንደሚላኩ አረጋግጠዋል።

የጀርመን መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ ሃምሌ ላይ በዩክሬን ጉብኝት ማድረጋቸው የሚታወስ ሲሆን ሀገራቸው ዩክሬንን ለማገዝ ዝግጁ መሆኗን ለፕሬዝዳንት ዘለንስኪ በገልጸውላቸዋል።

ዩከሬን እና ሩሲያ ወደ ጦርነት መግባታቸውን ተከትሎ የተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ለዩክሬን የጦር መሳሪያ ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

ጀርመንም ለዩክሬን ጦር መሳሪያ ለማቅረብ በሚል ፖሊሲ እስከ ማሻሻል ደርሳ እንደነበረ ይታወሳል።

ሩሲያም በተለያዩ ጊዜያት ከምእራባውያን ለዩክሬን ያበረከቷቸው የረጅም ርቀት ሮኬትን ጨምሮ ይለያዩ የጦር መሳሪያዎችን አወደምኩ ማለቷ አይዘነጋም።

News today, Politics

ለተመድ ጠቅላላ ጉባዔ የአሜሪካ ቪዛ ሲጠይቁ የቆዩት የሩሲያ ልዑካን ወደ ኒውዮርክ ለመሄድ የሚያስችል ቪዛ አገኙ

አንጋፋው ዲፕሎማት ሰርጌ ላቭሮቭ “በፑቲን ምትክ በጠቅላላ ጉባዔው ሩሲያን ወክለው በመሳተፍ ላይ ናቸው” ተብሏል
ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጉባዔ የአሜሪካ ቪዛ ሲጠይቁ የቆዩት የሩሲያ ልዑካን ወደ ኒውዮርክ ለመሳተፍ የሚያችላቸው ቪዛ አግኝተዋል፡፡


የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ እና የሩሲያ ልዑካን ቡድን አባላት በኒውዮርኩ ስብሰባ ለመሳተፍ የሚያስችላቸው ቪዛ ማግኘታቸው የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡


ሩሲያ፤ 77 ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ለሚወክላት ልዑክ የቪዛ ጥያቄ ማቅረቧን ካቀረበች ብትቆይም አሁን ላይ የዘገየ ምላሽ ማግኘቷ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ሞስኮ፤ አሜሪካ በጠቅላላ ጉባኤው ሙሉ በሙሉ የሩሲያ ተሳትፎን ለመከላከል እየሞከረች ነው የሚል ክስ ስታሰማ መቆየቷም አይዘነጋም፡፡


“አሜሪካ ግዴታዎቿ እየጣሰች ነው” ሲሉም ነበር የከሬምሊን ሰዎች ዋሽንግተንን የወቀሱት፡፡
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዘንድሮ በሚካሄደው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ እንደማይገኙ ቀድመው መግለጻቸው ይታወሳል።


በዚህ መሰረት በጉባዔው ሩሲያን የሚወክሉት ከፑቲን ቀጥሎ ወዳጆቻቸው “ጠንካራው ዲፕሎማት” የሚሏቸው፤ ምዕራባውያን ደግሞ “አደገኛው” የሚሏቸው የዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሩቁ ሰርጌ ላቭሮቭ ሆነዋል።


ሰርጌ ላቭሮቭ የሀገራቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት በአውሮፓውያኑ 2004 ነበር። የ77 ዓመቱ ሰርጌ ላቭሮቭ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከመሆናቸው በፊት ለ10 ዓመታት ማለትም ከአውሮፓውያኑ 1994 እስከ 2004 በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሩሲያ ቋሚ መልዕክተኛ ነበሩ።


ሩሲያን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት 77 ኛው ጠቅላላ ጉባዔ ላይ የወከሉት ሰርጌ ላቭሮቭ በሀገራቸው ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት መስራት የጀመሩት በ22 ዓመታቸው ሲሆን በድምሩ ለግማሽ ክፍለ ዘመን (ለ 50 ዓመታት) ያገለገሉም ናቸው።


77 ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ በፈረንጆቹ ከዛሬ መስከረም 13 እስከ 20 በኒውዮርክ እንደሚካሄድ የወጣው መርሃ ግብር ያመለክታል።

News today, Politics

ሩሲያ በዩክሬን የውጊያ ግንባሮች ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃቶች እያደረስኩ ነው አለች

ሞስኮ የኪቭ ጦር በሰላማዊ ሰዎች ላይ “አስከፊ” የሚሉ በደሎች እየፈጸመ ነው ስትል ከሳለች

ፕሬዝደንት ዜለንስኪ በመልሶ ማጥቃት 6 ሺህ ስኩዌር ኪሎ ሜትር ቦታ ከሩሲያ ኃይሎች ነጻ ወጥቷል ብለዋል

ሩሲያ በዩክሬን የውጊያ ግንባሮች ላይ “መጠነ ሰፊ ጥቃቶች” እያደረስኩ ነው አለች፡፡

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር የሩሲያ ኃይሎች በዩክሬን ጦር ላይ “የአየር፣ የሮኬት እና መድፍ የተቀናጀ ከፍተኛ ጥቃት እያደረሱ ነው” ብሏል፡፡

የክሬምሊን ባለስልጣናት የኪቭ ጦር መልሶ በያዘው ግዛት ውስጥ በሲቪሎች ላይ በደል ፈጽሟል ሲሉ ከሰዋል።

የፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ቃል አቀባይ በካርኪቭ ክልል በሰላማዊ ሰዎች ላይ “አስከፊ” የሚሉ በደሎች መፈጸማቸው የሚያመላክቱ ዘገባዎች እየወጡ መሆኑን ተናግረዋል።

https://facebook.com/KeAlemiZuriya

“ብዙ የቅጣት እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው…ሰዎች እየተሰቃዩ ፣ እየተንገላቱ ነው “ሲሉም ነው ዲሚትሪ ፔስኮቭ ለጋዜጠኞች የተናገሩት።

ባለፈው ሳምንት የዩክሬን ኃይሎች የወሰዱት እርምጃን ተከትሎ የሩሲያ ጦር በዩክሬን ካርኪቭ ግዛት ውስጥ ከሚገኙት ሁለት አካባቢዎች (ባላክሊያ እና ኢዚየም ) ለማፈግፈግ መገደዳቸው ሮይተርስ መዘገቡ የሚታወስ ነው፡፡

በዚህም የዩክሬን ባለስልጣነት ወታደሮቻቸው ለሩሲያ ኃይሎች ወሳኝ አቅርቦት ማዕከል የሆነችውን ኩፒያንስክ መቆጣጠራቸው ሲገልጹ ቆይተዋል፡፡

ፕሬዝደንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ በሰጡት መገለጫ ወታደሮቻቸው በወሰዱት የመልሶ ማጥቃት እርምጃ “6 ሺህ ስኩዌር ኪሎ ሜትር ቦታ ከሩሲያ ነጻ መውጣቱ” ተናግረዋል።

የዩክሬን ባለስልጣነት ይህን ይበሉ እንጂ፤የተወሰደው የማፈግፈግ እርምጃ በምስራቅ ዩክሬን የመትገኘውን ዶንባስ ግዛት ነጻ ለማውጣት የሚያስችል በቂ ዝግጅት ለማድረግ ያለመ መሆኑን የምትገለጸው ሩሲያ በዩክሬን ምድር ፈለገቸውን ዓለማ ከመፈጸም የሚያግዳት ኃይል እንደሌለ በመግለጽ ላይ ናት፡፡

ሩሲያ፤ “ዓላማዬን እስከማሳካ የሚቆም ወታደራዊ ዘመቻ የለም” ስትል በትናንትናው እለት መግለጿም አይዘነጋም፡፡

የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት “ልዩ ወታደራዊ ዘመቻው መጀመሪያ ላይ የተቀመጡት አላማዎች እስኪሳኩ ድረስ ይቀጥላል” ብለዋል።

አሁን ላይ የሩሲያ አየር፣ ሮኬቶችና መድፍ ኃይሎች የኩፒያንስክ እና ኢዚዩም የከተማ ማዕከሎችን ጨምሮ በዩክሬን የጦር ኃይሎች ይዞታወች ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት በመሰንዘር ላይ እንደሆኑም ተናግረዋል።

ቃል አቀባዩ ከኪቭ ጋር ሊኖሩ ስለሚችሉ የሰላም ንግግሮች ተጠይቀውም፤ በሞስኮ እና በኪቭ መካከል የሚደረጉ “የድርድር ተስፋዎች የሉም” የሚል ምላሽ መስጠታቸው ኤኤፍፒ ዘግቧል።

News today, Politics, social life

የፌደራል መንግስት እና የህወሓት የድርድር ሂደት ይሳካ ይሆን…?


ምሁራኑ “ህወሓት አሁን ላይ ድርድሩን የጠየቀበት ምክንያት ተገዶ ይሆናል፤ ምክንያት ፈልጎ ሊያቋርጠው እንደሚችል ግምታቸውን አሰቀምጠዋል
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀው ህወሓት በሀገር መከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ ማጥቃቱን ተከትሎ ነበር በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የተጀመረው።


ይህ ጦርነት ላለፉት 23 ወራት የዘለቀ ሲሆን ጦርነቱን ለማስቆም አሊያም ለማሸማገል ራሱ የፌደራል መንግስትን ጨምሮ የአፍሪካ ህብረት የአዉሮፓ ህብረት የተባሩት መንግስታት ድርጅት እና የተለያዩ አካላት ጥረት እያደረጉ ቢሆንም ድርድሩ እስካሁን ሳይሳካ ቀርቷል።


የፌደራል መንግስት እና ህወሓት ድርድር ተስፋ እና ስጋቶች
መንግስት ከህወሃት ጋር ድርድር የሚካሄድበትን ቦታ ለመወሰን ከአፍሪካ ህብረት ጋር እየተነጋገረ መሆኑን አስታወቀ
አሁንም ጦርነት ለማስቆምና እልባት ለመፈለግ እየተደረገ ያለው ጥረት በህወሓት በኩል እንቅፋት እየገጠመው ነዉ ሲል መንግስት በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል።


መንግስት የሰላም ድርድሩን በአስቸኳይ ለመጀመር የሚያስችል የሰላም ምክረ- ሃሳብን የያዘ ሰነድ ማዘጋጀቱን ይፋ ቢያደርግም፣ ህውሓት በተቃራኒው ከፌደራል መንግስት ጥቃት እንደተከፈተበት በመግለጽ የተኩስ አቁም ስምምነቱ መፍረሱን ገልጾ ነበር።


የፌደራል መንግስትም ህወሓት ከነሀሴ 18 2014 አ.ም ጀምሮ በራያ፣ ወልቃይት ፣ ሰቆጣ እና አፋር ክልል አዋሳኝ ቦታዎች ጥቃት መፈጸሙን አስታውቋል።


ከተጠቀሰው ዕለት ጀምሮም በበትግራይ ክልል እና አማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች እንዲሁም በኢትዮ ሱዳን ድንበር አካባቢዎች ላይ ጦርነቱ መቀጠሉ የተገለጸ ሲሆን፤ ህወሓት የዘመን መለወጫ ዕለት ማለትም መስከረም 1 ቀን 2015 ዓ.ም ባወጣዉ መግለጫ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ለመወያየት እና ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት መዘጋጀቱን አስታውቋል።


ፃድቃን ገብረተንሳይና ጌታቸው ረዳን ያካተተ ከፌደራል መንግስት ጋር ለሚደረገው ድርድር የሚወክሉትን ቡድን ያፈ ያደረገው ህወሓት አለማቀፉ ማኅበረሰብ በታዛቢነትና ድጋፍ በማድረግ እንዲሳተፉ እንደሚፈልግም ገልጿል።


የህወሃትን የእደራደራለሁ መግለጫን ተከትሎ ብዙዎች ተስፋ እና ስጋትን እንደተሰማቸው በተለያዩ መንገዶች ሃሳባቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው።
አል ዐይን አማርኛ የህወሓት ለመደራደር ዝግጁ ነኝ ማለቱን ተከትሎ ስለጉዳዩ ምሁራንን አነጋግሯል።


አቶ አበበ ይርጋ በባህር ዳር ዩንቨርሲቲ ስር ባለው የብሉናይል ውሀ ኢንስቲትዩት የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ጥናት መምህር ናቸው፤ የህወሃትን በየትኛውም ቦታ እና ጊዜ በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ከፌደራል መንግስት ጋር እደራደራለሁ ማለቱን እንዴት ያዩታል? በሚል ላነሳንላቸው ጥያቄ፤
“ህወሀት ወደ ድርድር እንዲመጣ ለረጅም ጊዜ ሲለመን ነበር፣ ነገር ግን ቅድመ ሁኔታ ሲደርድር እና ሰላም እንዳይፈጠር የቻለውን ሁሉ ሲያደርግ ቆይቷል።

በድንገት ያለ ቅድመ ሁኔታ በየትኛውም ቦታ እደራደራለሁ ማለቱ ከልቡ አይመስለኝም፣ ይሄንን መግለጫም ያወጣው በሎጅስቲክስ እና ፕሮፓጋንዳ ሲያግዙት የቆዩት አካላት አዘውት ነው” ብዬ አስባለሁ ብለዋል።


“በኢትዮጵያ የተለየ ፍላጎት ያላቸው ሀገራት ቁጥራቸው እየጨመረ ነው” የሚሉት መምህር አበበ “ህወሓት እየተሸነፈ ሲመስላቸው እና ተጨማሪ ድጋፍ ለማሰባሰብ እንዲያመቻቸው” ለድርድር ዝግጁ መሆኑን እንዲያሳውቅ ሳያደርገው እንዳልቀረ ግምት እንዳላቸውም ጠቅሰዋል።


“ህወሓት እደራደራለሁ ማለቱ በፌደራል መንግስት ላይ በሚደረግ ጫና ምክንያት መከላከያ ሰራዊት ማጥቃቱን ትቶ አሁን ባለበት ቦታ እንዲቆም ቀስ በቀስም ለአራተኛ ዙር ጦርነት የመዘጋጃ ጊዜ እንደሚያገኝ በማሰቡ ሊሆን ይችላል” ሲሉም ተናግረዋል።


“ድርድሩ የውጭ ጣልቃ ገብነት የተጫነው ይመስላል” የሚሉት መምህር አበበ “ለኢትዮጵያ ዘላቂ መፍትሄ የሚያመጣላት ከድርድሩ ጎን ለጎን በህወሀት ጥቃት እየደረሰበት ያለውን የትግራይ፣ አማራ እና አፋር ክልሎች ህዝብን መታደግ ሲቻል እና መንግስታዊ አገልግሎቶችን መጀመር ብቻ” እንደሆነ ጠቁመዋል።


ሌላኛው በድርድሩ ዙሪያ አል ዐይን አማርኛ ያናገራቸው በጅግጅጋ ዩንቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ህግ መምህሩ ሰለሞን ጓዴ ናቸው።


እሳቸው እንዳሉት “በእኔ አመለካከት “ህወሓት አሁን ላይ ድርድሩን የጠየቀበት ምክንያት ተገዶ ይሆናል የሚል እሳቤ አለኝ ምክንያቱም ይፈልጉት የነበረዉ ስትራቴጂካዊ ቦታ ተይዞባቸዋል በዚህም ጫናዉ ሲበዛባቸዉና የጦርነት የበላይነትን ሲያጡ መጀመሪያ አጎንብሶ ከዛም አፈር ልሶ ለመነሳት የሚደረግ ሙከራ ነዉ ብዬ ነዉ የማምነዉ በአንድ ሳምንት ዉስጥ ሽንፈት ካልሆነ በስተቀር ሊፈጠር የሚችል አሳማኝ ምክንያት የለም” ሲሉ ገልጸዋል፡፡


“ህወሓት እንዳለው ወደ ድርድር ከመጣ የታጣቂዎቹ ትጥቅ መፍታት ጉዳይ የድርድሩ ዋነኛ ጉዳይ ይሆናል” የሚሉት መምህር ሰለሞን “ሰላም እንዲመጣ ከተፈለገ መተማመንን የሚያጎለብት ስራ መሰራት አለበት” ብለዋል፡፡


ድርድሩ ፍሬያማ እንዲሆን ከተፈለገ መጀመሪያ ሰላማዊ የሆነ አየር ያስፈልጋል፤ ሉዓላዊነት መከበር አለበት፣ ይህ የሚሆነው ደግሞ የህወሓት ታጣቂዎች ትጥቅ ሲፈቱ እና የሀገር መከላከያ ሰራዊት የሀገሪቱን ዳር ድንበር መቆጣጠር በሚያስችለው መንገድ ሲሰማራ ብቻ እንደሆነም መምህር ሰለሞን አክለዋል።


መምህር ሰለሞን አክለውም የህወሓት የእስካሁኑ የፖለቲካ ባህል ምን ጊዜም እራሱን ብቻ የሚያስቀድም በመሆኑ እደራደራለሁ ማለቱ ከልቡ ሊሆን እንደማይችል ተናግረዋል።


በመንግስትና ህወሓት መካከል የሚደረገው ድርድር ሁሉንም ያሳተፈ ኢንዲሆን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ም/ቤት ጠየቀ
“ህወሓት እኔ ያልመራሁት ነገር አይደረግም የሚል ድርቅ ያለ መንገድን የሚከተል ድርጅት ነው” የሚሉት መምህር ሰለሞን ድርድር በባህሪው ሰጥቶ መቀበልን እና ሰላማዊ ሁኔታዎችን የሚፈልግ በመሆኑ ድርድሩ የመሳካት እድሉ ጠባብ መሆኑን ጠቁመዋል።


ህወሓት ድርድሩን ቢጀምረው እንኳን ምክንያት ፈልጎ ሊያቋርጠው እንደሚችል ግምታቸውን ያስቀመጡት መምህር ሰለሞን የፌደራል መንግስት በህወሀት ወጥመድ ሊገባ እንደማይገባም አሳስበዋል።


የፌደራል መንግስት ከዚህ በፊት ባወጣው መግለጫ በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ከህወሃት ጋር በየትኛውም ቦታ እና ጊዜ እንደሚደራደር ማሳወቁ ይታወሳል።


ለዚህ ድርድርም በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የሚመራ አብይ ኮሚቴ መቋቋሙን እና ሌሎች ንዑስ ኮሚቴዎችም ተቋቁመው ስራ መጀመራቸው መገለጹ አይዘነጋም።

News today, Politics

የአሜሪካ መጠባበቂያ ነዳጅ ክምችት ከ40 ዓመት ገደማ በኋላ ቅናሽ ማሳየቱ ተገለጸ


የዋሸንግተን መጠባበቂያ ነዳጅ ክምችት ዝቅ ያለው በዩክሬን ሩሲያ ጦርነት ምክንያት የነዳጅ ዋጋ በመናሩ ነው


የአሜሪካ መጠባበቂያ ነዳጅ ከ40 ዓመት በኋላ ቅናሽ ማሳየቱ  ተገለጸ።
የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ስድስት ወራት ያለፈው ሲሆን ጦርነቱ በዓለም ምግብ እና ነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ እንዲመዘገብ ምክንያት ሆኗል።


 ጦርነቱ በዓለም ዲፕሎማሲ ላይ የተለያዩ መፋለሶችን ያስከተለ ሲሆን ሀገራት ከትብብር ይልቅ ጎራ ለይተው እንዲሰለፉ እያደረገም ይገኛል።
ባለፈው ሳምንት ብቻ 8 ነጥብ 4 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ ከመጠባበቂያዋ በማውጣት ለዜጎቿ እንዲሸጥ አድርጋለች።


አሜሪካ ከአንድ ዓመት በፊት በመጠባበቂያ ክፍሏ ያስቀመጠችው ነዳጅ 621 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ ነበር።


ይሁንና በሩሲያ ዩክሬን ጦርነት መከሰትን ተከትሎ ባጋጠመ የነዳጅ ዋጋ መናር ምክንያት ኢኮኖሚውን ለማረጋጋት በሚል ከመጠባበቂያ ክፍሏ እያወጣች በመሸጥ ላይ እንደምትገኝ ብሉምበርግ ዘግቧል።
አሁን ላይ የአሜሪካ መጠባበቂያ ነዳጅ ክምችት መጠን 434 ሚሊዮን በርሜል ላይ ደርሷልም ተብሏል።


ከፈረንጆቹ 1984 ዓመት ጀምሮ የአሜሪካ መጠባበቂያ ነዳጅ ክምችት መጠን አሁን ካለበት መጠን ዝቅ ብሎ እንደማያውቅ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል።


የአሜሪካ የነዳጅ አጠቃቀም መጠን በዚሁ ከቁጠለ ብሄራዊ የነዳጅ አጠቃቀም መጠን ወደ 358 ሚሊዮን በርሜል ዝቅ ይላል ተብሏል።


የዓለም ቀዳሚ ሰባት የበለጸጉ ሀገራት ስብስብ የሆነው የቡድን ሰባት ሀገራት በሩሲያ ነዳጅ ላይ የዋጋ ተመን ማውጣታቸው ይታወሳል
ሩሲያ በበኩሏ ነዳጇን በሚያዋጣት ዋጋ ብቻ እንደምትሸጥ ገልጻ ወደ አውሮፓ የምትልከውን ነዳጅ ሙሉ ለሙሉ ማቋረጧ አይዘነጋም። 

የከዓለም ዙሪያ ቤተሰብ ይሁኑ
ቴሌግራም፡ https://t.me/KeAlemiZuriya
ዩቲዩብ: https://youtube.com/c/Kealemizuriya
ድረገፅ: https://kealemizuriya.data.blog
ትዊተር: https://twitter.com/KeAlemiZuriya
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/KeAlemiZuriya
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/Kealemizuriya

News today, Politics

ሩሲያ በዩክሬን የውጊያ ግንባሮች ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃቶች እያደረስኩ ነው አለች


የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር የሩሲያ ኃይሎች በዩክሬን ጦር ላይ “የአየር፣ የሮኬት እና መድፍ የተቀናጀ ከፍተኛ ጥቃት እያደረሱ ነው” ብሏል፡፡


የክሬምሊን ባለስልጣናት የኪቭ ጦር መልሶ በያዘው ግዛት ውስጥ በሲቪሎች ላይ በደል ፈጽሟል ሲሉ ከሰዋል።


የፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ቃል አቀባይ በካርኪቭ ክልል በሰላማዊ ሰዎች ላይ “አስከፊ” የሚሉ በደሎች መፈጸማቸው የሚያመላክቱ ዘገባዎች እየወጡ መሆኑን ተናግረዋል።


“ብዙ የቅጣት እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው…ሰዎች እየተሰቃዩ ፣ እየተንገላቱ ነው “ሲሉም ነው ዲሚትሪ ፔስኮቭ ለጋዜጠኞች የተናገሩት።


ባለፈው ሳምንት የዩክሬን ኃይሎች የወሰዱት እርምጃን ተከትሎ የሩሲያ ጦር በዩክሬን ካርኪቭ ግዛት ውስጥ ከሚገኙት ሁለት አካባቢዎች (ባላክሊያ እና ኢዚየም ) ለማፈግፈግ መገደዳቸው ሮይተርስ መዘገቡ የሚታወስ ነው፡፡


በዚህም የዩክሬን ባለስልጣነት ወታደሮቻቸው ለሩሲያ ኃይሎች ወሳኝ አቅርቦት ማዕከል የሆነችውን ኩፒያንስክ መቆጣጠራቸው ሲገልጹ ቆይተዋል፡፡
ፕሬዝደንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ በሰጡት መገለጫ ወታደሮቻቸው በወሰዱት የመልሶ ማጥቃት እርምጃ “6 ሺህ ስኩዌር ኪሎ ሜትር ቦታ ከሩሲያ ነጻ መውጣቱ” ተናግረዋል።


የዩክሬን ባለስልጣነት ይህን ይበሉ እንጂ፤የተወሰደው የማፈግፈግ እርምጃ በምስራቅ ዩክሬን የመትገኘውን ዶንባስ ግዛት ነጻ ለማውጣት የሚያስችል በቂ ዝግጅት ለማድረግ ያለመ መሆኑን የምትገለጸው ሩሲያ በዩክሬን ምድር ፈለገቸውን ዓለማ ከመፈጸም የሚያግዳት ኃይል እንደሌለ በመግለጽ ላይ ናት፡፡


ሩሲያ፤ “ዓላማዬን እስከማሳካ የሚቆም ወታደራዊ ዘመቻ የለም” ስትል በትናንትናው እለት መግለጿም አይዘነጋም፡፡


የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት “ልዩ ወታደራዊ ዘመቻው መጀመሪያ ላይ የተቀመጡት አላማዎች እስኪሳኩ ድረስ ይቀጥላል” ብለዋል።


አሁን ላይ የሩሲያ አየር፣ ሮኬቶችና መድፍ ኃይሎች የኩፒያንስክ እና ኢዚዩም የከተማ ማዕከሎችን ጨምሮ በዩክሬን የጦር ኃይሎች ይዞታወች ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት በመሰንዘር ላይ እንደሆኑም ተናግረዋል።


ቃል አቀባዩ ከኪቭ ጋር ሊኖሩ ስለሚችሉ የሰላም ንግግሮች ተጠይቀውም፤ በሞስኮ እና በኪቭ መካከል የሚደረጉ “የድርድር ተስፋዎች የሉም” የሚል ምላሽ መስጠታቸው ኤኤፍፒ ዘግቧል።

News today, Politics

በአርመን እና በአዘርባጃን መካከል ጦርነት ተቀስቅሶ 49 ወታደሮች ተገደሉ

በአርመን እና በአዘርባጃን መካከል ጦርነት ተቀስቅሶ 49 ወታደሮች ተገደሉ
አርመን እና አዘርባጃን ጦርነት እንዲቀሰቀስ በማድረግ እርስበርሳቸው እየተካሰሱ ነው


የአርመኒያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ኒኮል ፓሺኒያን በትናንትናው እለት ከአዘርባጃን ጋር በነበረው ጦርነት 49 የአርመን ወታደሮች ተገድለዋል ሲሉ መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።


በአርመን ፖርላማ ቀርበው ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አዘርባጃን የአርመንን ይዞታዎች ማጥቃቷን እና ጦርነቱ አሁንም መቀጠሉን ተናግረዋል።
ሁለቱ ሀገራት ግጭቱ ወደ ጦርነት እንዲያመራ በማድረግ እርስበርሳቸው እየተካሰሱ ነው።


በአርመን እና አዘርባጃን መካከል ለአስርት አመታ ያሰቆጠረው አለመግባባት ኒጋርኖ ካራባክ በተባለ ቦታ መጀመሩ ይታወሳል።


በኒጋርኖ ካራባክ የተመረው የሁለቱ ሀገራት ጦርነት ቆሞ የነበረ ቢሆንም በድጋሚጨሊቀሰቀስ ችሏል።
ሪሲያ እና አሜሪካ ሁለቱም ሀገራት ግጭቱን ከማባባስ እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።

News today, Politics

አፍሪካ ህብረት፣ ተመድ ፣አውሮፓ፣አሜሪካ እና ኢጋድ ህወሓት ባወጣው መግለጫ ዙሪያ ምን አሉ?

አፍሪካ ህብረት “ተፋላሚ ወገኖች በአስቸኳይ ተኩስ ለማቆም እንዲሰሩና የፊት ለፊት ንግግር እንዲያካሄዱ” ጥሪ አቅርቧል

የኢትዮጵያ መንግስት ጦርነቱ በድጋሚ ከመቀስቀሱ በፊት ከህወሓት ጋር ያለቅደመ ሁኔታ በየትኛውም ቦታ እንደሚደራደር መግለጹ ይታወሳል

ህወሓት በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር በሚካሄደው የሰላም ድርድር ሂደት ውስጥ ለመሳተፍ ዝግጁ መሆኑን ትናንት ባውጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

 ህወሓት አቶ ጌታቸው ረዳን እና ጀነራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤን ያከተተ ተደራዳሪ ቡድን መሰየሙን ይፋ ማድረጉ ይታወቃል፡፡

    ህወሐት ትናንት ማምሻው በትግራይ የውጭ ግንኙነት ጸ/ቤቱ በኩል ባወጣው መግለጫ ፤ የተሰየመው ተዳራዳሪ ቡድን ወደፊት በሚደረገው ድርድር “የትግራይን መንግስት” የሚወከል ስልጣን ተሰጥቶታለል ብሏል፡፡

    ህወሓት የተሰየመው ተደራዳሪ ቡድን “ሳይዘገይ ወደ ድርድር እንደሚገባ”ም ጠቁሟል፡፡

    የአፍሪካ ህብረት በትግራይ ለተፈጠረው ችግር መፍትሔ “አያመጣም” ሲል የነበረው ህወሓት፤ በትናንትናው መግለጫው ግን በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር በሚደረግ ድርድር ላይ እንደሚሳተፍ ገልጿል፡፡

    ጦርነቱን በድርድር ለመፍታት ሲያደርግ የነበረው የአፍሪካ ህብረት የህወሓት መግለጫ በአወንታ እንደሚመለከው አስታውቋል፡፡

    የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ፤የትግራይ ክልል መንግስት ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታትና በአፍሪካ ህብረት በሚመራ የሰላም ሂደት ለመሳተፍ ፍቃደኝነት ማሳየቱን በበጎ እንደሚቀበሉት አስታውቀዋል፡፡

    እርመጃው በኢትዮጵያ ሰላም ለማስፈን ጥሩ እድል የሚፈጥር ነው ያሉት ሙሳ ፋኪ፤ “ተፋላሚ ወገኖች በአስቸኳይ ተኩስ ለማቆም እንዲሰሩና በአፍሪካ ህብረት መሪነት የፊት ለፊት ንግግር እንዲያካሄዱ” ጥሪ አቅርበዋል።

    ፊት ለፊት የሚደረገው ድርድር በሁለቱም ወገኖች ተቀባይነት ያላቸው “ዓለም አቀፍ አጋሮችን ያካተተ” እንደሚሆንም ፍንጭ ሰጥተዋል የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበሩ ሙሳ ፋኪ፡፡

    የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም ህወሓት በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር በሚደረገው የሰላም ሂደት ላይ ለመሳተፍ ባሳየው ፍላጎት ደሰተኛ መሆኑን ገልጿል፡፡

    የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ፤ ሁለቱም ወገኖች ይህንን የሰላም እድል በመጠቀም ግጭትን በማቆም ለውይይት እንዲመርጡ ጠይቀዋል።

    ሁለቱም ወገኖች፤ “በቅን ልቦና እና ሳይዘገዩ በአፍሪካ ህብረት የሚመራውን ሂደት በንቃት እንዲሳተፉና ውይይቱ እንዲካሄድ ምቹ ሁኔታዎችን እንዲፈጥሩ እናበረታታለን” ብለዋል ዋና ጸሃፊው፡፡

    ተመድ በአፍሪካ ህብረት የሚመራውን የሰላም ሂደት ለመደገፍ ያለውን ዝግጁነት በድጋሚ አረጋግጠዋል፡፡

    የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭትን በተመለከተ ተደጋጋሚ መግለጫዎች ስያወጣ የነበረው አውሮፓ ህብረት በበኩሉ የትግራይ ክልል መንግስት ጦርነቱ ባስቸኳይ እንዲቆምና በአፍሪካ ህብረት በሚመራው የሰላም ሂደት ለመሳተፍ ዝግጁ መሆኑን መግለጹ በበጎ እንደሚመለከተው ገልጿል፡፡

    የአውሮፓ ህብረት ምክትል ፕሬዝዳንት ጆሴፕ ቦሬል በትዊተር ገጻቸው ባጋሩት ጽሁፍ “እድሉ ሁሉም ሊጠቀሙበት ይገባል” ብለዋል፡፡

    ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ባወጣው መግለጫ ውጊያ ለማቆምና ያልተፈቱ ጉዳዮችን በውይይት ለመፍታት ዝግጁ መሆኑን ማስታወቁን “እናበረታታለን” ያሉት ደግሞ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አንቶኒ ብሊንከን ናቸው፡፡

     “ኤርትራና ሌሎችም ግጭቱን ከማቀጣጠል ሊቆጠቡ ይገባል” ሲሉም አክለዋል፡፡

    አሜሪካ የኢትዮጵያን አንድነት፣ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ትደግፋለች ያሉት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፤ አሜሪካ ከሀገሪቱ ጋር ወደነበራት “ጠንካራ አጋርነት” መመለስ እንደምትሻ ም አስታውቀዋል።

    ሌላው የትግራይ ክልል መንግስት ለውይይት ያወጣው መግለጫ ሚበረታታ መሆኑ የገለጸው ደግሞ፤ የኢትዮጵያ ሁኔታን በቅርበት ሲከታታል እንደነበር የገለጸው የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት /ኢጋድ/ ነው፡፡

    የኢጋድ ዋና ጸሃፊው ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ በግጭት ውስጥ ያሉት ኃይሎች በአፍሪካ ህብረት መሪነት ለሚደረግ የሰላም ንግግር ለመመለስ ባሳዩት ፈቃደኝነት መደሰታቸው ገልጸዋል፡፡

    “ኢጋድ ሁለቱም ወገኖች ለተኩስ ማቆምና ለሽምግልና ያሳዩት ቁርጠኝነት ይቀበላል”ም ነውም ያሉት ዋና ጸሃፊው፡፡

    በፌደራል መንግስቱ እና በህወሓት መካከል የነበረው ጦርነት ለወራት ጋብ ብሎ የነበረ ቢሆንም ጦርነቱ በድጋሚ ሊቀሰቀስ ችሏል፤ ጦርነቱን በመጀመር አንደኛቸው ሌላኛቸውን በመክሰስ ላይ ናቸው፡፡

    የኢትዮጵያ መንግስት በድጋሚ ጦርነት ከመቀስቀሱ በፊት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በየትኛው ቦታ ከህወሓት ጋር እንደሚደራደር መግለጹም ይታወሳል፡፡

    ህወሓትም በተመሳሳይ ለድርድር ዝግጁ መሆኑን ቢገልጽም ህወሓት በአፍሪካ ህብረት ላይ እምነት እንደሌላው ሲገልጽ ቆይቶ ነበር፡፡

    News today, Politics

    በስልጣን ላይ ያሉት ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አሜሪካን እያዋረዷት እንደሆነ ትራምፕ ተናግረዋል

    አሜሪካ በአፍጋኒስታን 87 ቢሊየን ዶላር ዋጋ ያላቸው ንብረቶችን ጥላ መውጣቷ ተገለጸ።

    የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቀጣዩ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ ለመወዳደር ድጋፍ በማሰባሰብ ላይ ይገኛሉ።

      የቀድሞው ፕሬዝዳንት በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች እያካሄዱት ባለው በዚህ ቅስቀሳ ላይ እንዳሉት አሜሪካ በአፍጋኒስታን ጥላው የወጣችው ባግራም የተሰኘው ወታደራዊ ማዘዣ ጣቢያ እጅግ ጠቃሚ እንደነበር ለጋፊዎቻቸው ተናግረዋል ሲል ራሺያን ቱዳይ ዘግቧል።

      ይህ ወታደራዊ ማዘዣ በተለይም አሜሪካ ከቻይና ጋር እያደረገች ላለው ወታደራዊ እና የንግድ የበላይነት ውድድር አስፈላጊ እንደነበር ጠቁመዋል።

      አሜሪካ ከፍተኛ በጀት ያፈሰሰችበት እና የቻይናን ኑክሌር መሰረተ ልማቶችን ለማጥቃት አመቺ ከሆነው ከባግራም ወታደራዊ ማዘዣ መውጣቷ ስህተት እንደሆነም የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጠቁመዋል።

      የወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አመራር አሜሪካንን በዓለም መድረክ እያሳነሰ መሆኑን የጠቀሱት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ እና የአሜሪካ ወዳጆች ማሳዘኑንም ተናግረዋል።

      ኣሜሪካ ከአፍጋኒስታን መውጣቷ የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ትልቁ ስህተት መሆኑንም ዶናልድ ትራምፕ ገልጸዋል።

      አሜሪካ በአፍጋኒስታን 85 ቢሊየን ዶላር ዋጋ ያላቸው ንብረቶችን ለታሊባን ጥላ መውጣቷን የቀድሞው ፕሬዝዳንት አክለዋል።

      አሜሪካ ከ20 ዓመት የአፍጋኒስታን ቆይታ በኋላ ለታሊባን ጥላ የወጣች ሲሆን አፍጋኒስታንን እያስተዳደረ የሚገኘው ታሊባን አንደኛ ዓመቱን ከሁለት ወራት በፊት ማክበሩ ይታወሳል።

      Politics

      ሩሲያ ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ ከበርካታ ሀገራት ጋር በሩብል ለመገበያየት መስማማቷ ይታወሳል

      ዶላን ከገበያ የማስወጣት እንቅስቃሴ የማይቀር ነው ሲሉ ፕሬዝደንት ፑቲን ተናግረዋል፡፡

      ፕሬዝደንት ፑቱን በኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርገው ንግግር ባሰሙበት ወቅት ሩሲያ ከምእራባውያን የተሰነዘሩባትን መእቀቦች መቋቋም መቻሏን መግጻቸውን የሩሲያው አርቲ ዘግቧል፡፡

      ሩሲያ ማእቀቦቹን የተቋቋመችው የተለያዩ የመከላከያ መንገዶችን በመጠቀም ነው ብለዋል ፑቲን፡፡

      በቀጣይ የኢኮኖሚ አቅጣጫዎች ላይ የተናገሩት ፑቲን ዶላርን ከመገበያያነት የማስወጣት እንቅስቃሴ የማይቀር ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

      ሩሲያ በዩክሬን ላይ “ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ” ከጀመረች በኋላ አሜሪካን ጨምሮ ምእራባውያን በሺዎች የሚቆጠሩ ማእቀቦችን ጥለውባታል፡፡ ሩሲያ ከጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ ከበርካታ ሀገራት ጋር በሩብል ለመገበያየት ከስምምነት መድረሷ ይታወሳል፡፡

      ሩሲያ ምእራባውያን ለሚገዙት ጋዝ በሩሲያ ገንዘብ ሩብል እንከፍሉ በማድረግ እና ከዚህም አለፍ ሲል የጋዝ ማስተላለፊያ መስመሮችን በመዝጋት በምእራባውያን ሀገራት የአጸፋ እርምጃ ወስዳለች፡፡ በቅርቡ ለጥገና በሚል የዘጋችው ጋዝን ከሩሲያ ወደ ጀርመን የሚደውስደው ኖርድ ስትሪም 1 የተሰኘውን የጋዝ ማስተላለፊያ መስመር እንደማትከፍት መግለጽ ይታወሳል፡፡

      ጀርመን በሩሲያ ውሳኔ በእጅጉ አዝናለች፡፡

      ሩሲያ እውቅና የሰጠቻቸው ሉሃንስክ ግዛት አሁን ሙሉበሙሉ ነጻ የወጣ ሲሆን የዶምባስ ግዛትን ሙሉ ለሙሉ ነጻ ለማውጣት ጦርነት እያካሄደች ትገኛለች፡፡

      ዩክሬን በቅርቡ በሩሲያ ሃይሎች ላይ ድል በመቀዳጀት የተወሰኑ ቦታዎች ማስለቀቋን እየገለጸች፤ ነገርግን ሩሲያ ቦታ የለቀቀችው ጦሯን በደንብ ለማደራጀት ነው ብላለች፡፡

      Politics

      ዩጋንዳ ለዲሞክራቲክ ኮንጎ 65 ሚሊዮን ዶላር ካሳ ከፈለች

      ዩጋንዳ ለዲሞክራቲክ ኮንጎ 65 ሚሊዮን ዶላር ካሳ ከፈለች

      የዩጋንዳ ወታደሮች ከ23 ዓመት በፊት በዲሞክራቲክ ኮንጎ ግዛት ገብተው ጥቃት ፈጽመው ነበር።

      ዲሞክራቲክ ኮንጎም ጉዳዩን ወደ ዓለም አቀፉ የግልግል ፍርድ ቤት በመውሰድ ክስ መስርታ ነበር።

      በዚህ ችሎት ላይ የዩጋንዳ ወታደሮቿ ባደረሱት ጉዳት መሰረት ለዲሞክራቲክ ኮንጎ 325 ሚሊዮን ዶላር በአምስት ዙር ክፍያ ካሳ እንድትከፍል የተወሰነባት ቢሆንም ላለፉት በርካታ ዓመታት ሳትከፍል ቆይታለች፡፡

      በችሎቱ የተረታችው ዩጋንዳም ከ325 ሚሊዮን ዶላር ክፍያ ውስጥ 65 ሚሊዮን ዶላር ገንዘቡን ከቀናት በፊት እንደከፈለች ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

      የዲሞክራቲክ ኮንጎ መንግስት ቃል አቀባይ ከዩጋንዳ መንግስት 65 ሚሊዮን ዶላር ካሳ ክፍያው እንደተከፈላቸው አረጋግጠዋል፡፡

      ዩጋንዳ የጎረቤቷን ዲሞክራቲክ ኮንጎ ሉዓላዊ ድንበሯን ጥሳ በመግባት ከ10 ዓመት በላይ በርካታ ቦታዎችን በመቆጣጠር እና አማጺያንን በመርዳት ወንጀል ተከሳ ጥፋተኛ ተብላለች፡፡

      በመጨረሻም ዩጋንዳ ጥፋቷን አምና ካሳዋን መክፈል መጀመሯን እና ከጎረቤቷ ጋር መልካም ግንኙነት እንደምትፈልግ አስታውቃለች፡፡

      የከዓለም ዙሪያ ቤተሰብ ይሁኑ
      ቴሌግራም፡ https://t.me/KeAlemiZuriya
      ዩቲዩብ: https://youtube.com/c/Kealemizuriya
      ድረገፅ: https://kealemizuriya.data.blog
      ትዊተር: https://twitter.com/KeAlemiZuriya
      ፌስቡክ: https://www.facebook.com/KeAlemiZuriya
      ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/Kealemizuriya

      Politics

      ሩሲያ፤ “ዓላማዬን እስከማሳካ የሚቆም ወታደራዊ ዘመቻ የለም” አለች


      የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ፤ በሞስኮ እና በኪቭ መካከል የሚደረጉ “የድርድር ተስፋዎች የሉም” ብለዋል
      ሞስኮ ይህን ያለችው ባለፈው ሳምንት የዩክሬን ኃይሎች በወሰዱት የመልሶ ማጥቃት እርመጃ የሩሲያ ኃይሎች ቁልፍ ወታደራዊ ይዞታዎች ለመልቀቅ መገደዳቸውን ተከትሎ “ሩሲያ በዩክሬን የጀመረችው ዘመቻ ታቆም ይሆን?” በሚል ለሚነሳው ጥያቄ በሰጠችው ምላሽ ነው።


       ፕሬዝደንት ዘሌሰንኪ ወታደሮቻቸው በወሰዱት የማጥቃት እርምጃ 2 ሺህ ስኩዌር ኪሎ ሜትር ቦታ ከሩሲያ ነጻ መውጣቱን ተናገሩ
      የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት “ልዩ ወታደራዊ ዘመቻው መጀመሪያ ላይ የተቀመጡት አላማዎች እስኪሳኩ ድረስ ይቀጥላል” ብለዋል።


      አሁን ላይ የሩሲያ አየር፣ ሮኬቶችና መድፍ ኃይሎች የኩፒያንስክ እና ኢዚዩም የከተማ ማዕከሎችን ጨምሮ በዩክሬን የጦር ኃይሎች ይዞታወች ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት በመሰንዘር ላይ እንደሆኑም ተናግረዋል።


      ቃል አቀባዩ ከኪቭ ጋር ሊኖሩ ስለሚችሉ የሰላም ንግግሮች ተጠይቀውም፤ በሞስኮ እና በኪቭ መካከል የሚደረጉ “የድርድር ተስፋዎች የሉም” የሚል ምላሽ መስጠታቸው ኤኤፍፒ ዘግቧል።


      ባለፈው ሳምንት የዩክሬን ኃይሎች የወሰዱት እርምጃን ተከትሎ የሩሲያ ጦር በዩክሬን ካርኪቭ ግዛት ውስጥ ከሚገኙት ሁለት አካባቢዎች (ባላክሊያ እና ኢዚየም ) ለማፈግፈግ መገደዳቸው ሮይተርስ ዘግቧል።


      በዚህም የዩክሬን ባለስልጣነት ወታደሮቻቸው ለሩሲያ ኃይሎች ወሳኝ አቅርቦት ማዕከል የሆነችውን ኩፒያንስክ መቆጣጠራቸው በመግለጽ ላይ ናቸው።
      ፕሬዝደንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ ቅዳሜ በሰጡት መገለጫ፤ወታደሮቻቸው በወሰዱት የመልሶ ማጥቃት እርምጃ “2 ሺህ ስኩዌር ኪሎ ሜትር ቦታ ከሩሲያ ነጻ መውጣቱ” ተናግረዋል።


      የጦር ግስጋሴው ሩሲያ በሚያዝያ ወር በኪቭ ዙሪያ ካሉ አካባቢዎች ከወጣች በኋላ የተገኘ በጣም ጠቃሚ ስኬት ነው ተብሎለታል።
      ሩሲያ፤ በቁጥጥሯ ስር ባሉ የዩክሬን ግዛቶች በመጪው ህዳር ወር “ህዝበ ውሳኔ” ልታካሂድ ነው
      የዩክሬን ባለስልጣነት ይህን ይበሉ እንጂ ፤ የሩሲያ ወታደሮች ያፈገፈጉት የዩክሬን መሪዎች እንደሚሉት ሳይሂን ለዓላማ እንደሆነ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኢጎር ኮናሼንኮቭ ተናግረዋል።


      ወታደሮቹ ከባላክሊያ እና ኢዚየም አካባቢዎች አፍግፍገው በዶኔትስክ ክልል ተሰባስበዋል ያሉት ኢጎር ኮናሼንኮቭ ፤ የተወሰደው የማፈግፈግ እርምጃ በምስራቅ ዩክሬን የመትገኘውን ዶንባስ ግዛት ነጻ ለማውጣት የሚያስችል በቂ ዝግጅት ለማድረግ ያለመ መሆኑ ገልጸዋል።

      News today, Politics, social life

      የንግስት ኤልሳቤጥ ለ70 ዓመት የብሪታኒያ ንግስት ነበሩ

      የብሪታንያ ንግስት ኤልሳቤጥ በ96 ዓመታቸው ማረፋቸው ተገለፀ።

      ንግስቲቱ በስኮትላንድ ቤኪንግሀም ቤተ መንግሥት ማረፋቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

      የንግስቲቱ የቀብር ስነ ስርዓት ከ10 ቀን በኋላ ክብራቸውን በጠበቀ መንገድ እንደሚከናወንም ተገልጿል።

      የንግስት ኤልሳቤትን ህልፈተ ህይወት ተከትሎ ልዑል ቻርልስ የብሪታንያ በነገው ዕለት ንጉስ ሆነው እንደሚሾሙም ይጠበቃል።

      ላለፉት 70 ዓመታት የብሪታንያ ንግስት የነበሩት ንግስት ኤልሳቤት በ96 ዓመታቸው ህይወታቸው አልፏል።

      ንግስቲቱ በኮሮና ቫይረስ እንዳይጠቁ የእንግሊዝ መንግሥት ልዩ ጥበቃ ሲያደርግላቸው ቆይቶ ነበር።

      ከትናንት በስቲያ የብሪታንያ አዲሷን ጠቅላይ ሚንስትር ሊዝ ትሩስን ሹመት ያጸደቁት ንግስቲቱ ዛሬ ከሰዓት መጠነኛ ህመም ከተሰማቸው በኋላ ምሽት ላይ ህይወታቸው ማለፉ ተሰምቷል።

      በመላው ብሪታንያ ሀዘን ላይ የወደቁ ሲሆን የሀገሪቱ ሰንደቅ ዓላም ዝቅ ብሎ ከመውለብለቡ ባለፈ የብሪታንያ ብዙሀን መገናኛዎች ሌሎች ጉዳዮችን መዘገብ አቁመዋል።

      Politics

      ግሪክ የቱርክ ፕሬዝዳንት ዛቻ “ስጋት ፈጥሮብኛል ዓለም ይወቅልኝ” ስትል ጠየቀች

      September 8, 2022
      ኤርዶሃን፤ የኤጂያን የአየር ክልል ጥሳለች ባሏት ግሪክ ላይ “ከባድ ዋጋ ያስከፍልሻል” ሲሉ ዝተዋል


      የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን ግሪክ በኤጂያን የአየር ክልል ላይ በሚንቀሳቀሱት የቱርክ አውሮፕላኖች ላይ የምትፈጥርው “የማስጨነቅ ድረጊት” የማታቆም ከሆነ አጻፋው ከባድ እንደሚሆን ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል፡፡


      ፕሬዝዳንቱ በጥቁር ባህር አከባቢ በተደረገ ሰልፍ ባደረጉት ንግግር “ሄይ ግሪክ፣ ታሪክን ተመልከቺ፤ከዚህ በላይ የምትሄጂ ከሆነ ብዙ ዋጋ ትከፍያለሽ” ሲሉም ዝተዋል፡፡


      ቱርክ በዩክሬኑ የዛፖሪዝሂያ ኒውክሌር ጣቢያ ግጭት ጉዳይ ማሸማገል ትችላለች- ፕሬዘዳንት ኤርዶሃን
      የፕሬዝዳንቱ ዛቻ ስጋት ውስጥ የከተታት አቴንስም ታዲያ እየደረሰብኝ ያለውን ዛቻ ስጋት ፈጥሮብኛል ዓለም ይወቅልኝ እያለች ነው፡፡


      ግሪክ ዓለም የአንካራን ባህሪ እንዲያወግዝ የሚጠይቅ ደብዳቤ ለኔቶ እና ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት መላኳንም ነው ሮይተርስ የዘገበው፡፡
      ቱርክ በቅርብ ወራት ወዲህ አቴንስ ግጭት ቀስቃሽ ድርጊቶች እየፈጸመች እንደሆነና ይህም የተጀመረውን የሰላም ጥረት ሚያበላሽ መሆኑ ስትገልጽ መቆየቷ ይታወቃል፡፡


      ሀገራት ከቱርክ የባህር ጠረፍ አቅራቢያ በሚገኙ የግሪክ ደሴቶች ዙሪያ በየቀኑ የአየር ሃይል ጥበቃዎችንና የመጥለፍ ተልእኮ እንቅስቀሰሴዎች የሚያደረጉ ሲሆን ለረዥም ጊዜ የቆዩ የባህርና የአየር ወሰን አለመግባባቶች እንዳሏቸው ይታወቃል።


      አቴንስ፤ አንካራ በግሪክ ደሴቶች የአየር ክልል ላይ የምታደርገው በረራ ተንኳሽ ነው ስትል ትከሳለች፡፡
      ቱርክ በበኩሏግሪክ ከአንደኛውና ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የተፈራረሙትን የሰላም ስምምነቶች በመጣስ ወታደሮቿን በኤጂያን ባህር ደሴቶች ላይ እያሰፈረች ነው የሚል ክስ ስታቀርብ ትደመጣለች፡፡


      በ 1922 የቱርክ ኃይሎች በኤጂያን የባህር ዳርቻ ወደ ከተማዋ ከገቡ በኋላ የግሪክን ወረራ ማብቃቱን ያስታወሱት ኤርዶሃን “ግሪክን የምንነግራት አንድ ቃል ብቻ ነው፡- ኢዝሚርን (ቀደም ባሉ ጊዜያት ቱርኮች አሸነፊ ሆነው የተቆጣጠሩት ስፋራ) አትርሺ ” ብለዋል ፕሬዝዳንቱ።


      በደሴቶቹ ላይ ያደረግሺው ወረራ እኛን አያስተሳስረንም ያሉት ፕሬዝዳንቱ “ጊዜው ሲደርስ አስፈላጊውን ነገር እናደርጋለን። እንደምንለው፣ አንድ ሌሊት በድንገት ልንመጣ እንችላለን”በማለትም ነው ፕሬዝዳንቱ በጎረቤት ሶሪያን ኦፕሬሽን ለማድረግ ባሰቡ ወቅት ደጋግመው ሲጠቀሙባቸው የነበሩትን ቃላቶች በኤቴንስ ላይ የሰነዘሩት፡፡


      የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜቭሉት ካቩሶግሉ አቴንስ ወታደሮቿን ወደዚያ (ደሴቶቹ) መላክ ከቀጠለች አንላራ የግሪክን ሉዓለዊነት ልትፈታተን እንደምትችል ባሳለፍነው ወርሃ ሰኔ ማስጠንቀቂያ አዘል መልዕክት ማስተላለፋቸው አይዘነጋም፡፡

      Politics

      ሀገራቱ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሱት አሜሪካና የአውሮፓ ህብረት በሩሲያ ላይ በጣሉት ማእቀብ ምክንያት ነው

      የሩሲያ ጉዝፉ የነዳጅ ኩባንያ ጋዝፕሮም ቻይና የጋዝ ግብይትን ከዶላር ይልቅ በሩብል እና በዩዋን እንድተክፍለው የሚያስችል ስምምነት መፈራረሙን አስታወቀ።

      የጋዝፕሮም ዋና ስራ አስፋጻ አሌክሲ ሚለር፤ ቻይና እና ሩሲያ የተፈራረሙት አዲሱ የክፍያ ስርዓት ሁለቱንም ሀገራት ተጠቃሚ የሚያደርግ እና አስተማማኝ ነው ሲሉ ተስምተዋል።

      ከቻይና ጋር የተደረሰው አዲሱ ስምምነት ሂሳብ ለመስራት ቀላል እንደሆነ እና ለሌሎችም ምሳሌ እንደሚሆን ሚለር አክለው አስታውቀዋል።

      ሁለቱም ሀገራት በዶላር መገበያየትን አቁመው መቼ በራሳቸው ገንዘብ መገበያየት ይጀምራሉ ለሚለው ግን ጋዝፕሮም ዝርዝር ከመስጠት ተቆጥቧል።

      ሁለቱ ሀገራት መገበያያቸውን ከዶላር ወደ ራሳቸው የመቀየር ሂደት ሩሲያ ዶላር እና ዮሮን ጨምሮ በምእራባውያን ከሚዘወሩ መገበያያዎች ላይ ካላት ጥገኝነት የማላቀቅ አካል እንደሆነ ተነግሯል።

      ሩሲያ ከዩክሬን ጋር በገባቸው ጦርነት ከምዕራባውያን 6 ሺህ ማእቀቦች የተጣሉባት ሲሆን፤ ሩሲያም ይህንን ተከትሎ ከቻይና እና ከምእራባውያን ውጪ ከሆኑ ሀገራት ጋር ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቷን ለማጠናከር እየሰራች ተገኛለች።

      የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በያዝነው የፈረንጆቹ 2022 ላይ የአውሮፓ ደንበኞቻቸው ከሩሲያ ጋዝን መግዛት መቀጠል ከፈለጉ በጋዝፕሮም ባንክ የሩብል የባንክ ሂሳብ እንዲከፍቱ ማሳሰባቸው ይታወሳል።

      ይህንን ስምምነት አልቀበል ላሉ የተወሰኑ ኩባንያዎች ሩሲያ ጋዝ ማቅረብ ያቆመች ሲሆን፤ ይህም የጋዝ እና የነዳጅን ጨምሮ የኃይል ዋጋ እንዲጨምር አድርጓል።

      News today, Politics

      ሩሲያ የተጣሉባት ማዕቀቦች ካልተነሱ ወደ አውሮፓ ነዳጅ እንደማትልክ ገለጸች

      የቡድን ሰባት አባል ሀገራት በሩሲያ ነዳጅ ላይ የዋጋ ተመን ማውጣታቸው ይታወሳል

      ሩሲያ የተጣሉባት ማዕቀቦች የማይነሱ ከሆነ ወደ አውሮፓ ነዳጅ እንደማትልክ ገልጻለች።

      የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ስድስት ወራት ያለፈው ሲሆን ጦርነቱ በዓለም ምግብ እና ነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ እንዲመዘገብ ምክንያት ሆኗል።

       ጦርነቱ በዓለም ዲፕሎማሲ ላይ የተለያዩ መፋለሶችን ያስከተለ ሲሆን ሀገራት ከትብብር ይልቅ ጎራ ለይተው እንዲሰለፉ እያደረገም ይገኛል።

      አሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት በሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ላይ በተለያየ መንገድ በመሳተፍ ላይ ሲሆኑ በሩሲያ ላይ ከስድስት ሺህ በላይ ማዕቀቦችን ጥለዋል።

      ሩሲያም የአጸፋ እርምጃ በመውሰድ ላይ ስትሆን ማዕቀቡ ለአውሮፓ ሀገራት የምታቀርበውን ጋዝ ሽያጭ እክል አስከትሏል።

      ይሄንን ተከትሎም 40 በመቶ ለሚሆኑ የአውሮፓ ሀገራት ነዳጅ ስታቀርብ የነበረችው ሩሲያ በማዕቀቡ ምክንያት ለአውሮፓውያን ነዳጅ መላክ አለመቻሏን በተደጋጋሚ ገልጻለች።

      በነዳጅ ዕጥረት እየተፈተነ ያለው የአውሮፓ ህብረትም በሩሲያ ላይ የጣለውን ማእቀብ እስከማላላት ቢደርስም በሩሲያ ላይ የተጣሉት ሁሉም ማዕቀቦች እስካልተነሱ ድረስ ሩሲያ ምንም አይነት ነዳጅ እንደማትልክ ራሺያ ቱዴይ ዘግቧል።

      የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቃል አቀባይ ድሚትሪ ፔስኮቭ ዛሬ በሰጡት መግለጫ የአውሮፓ ሀገራት እና ኩባንያዎች በሩሲያ ላይ የጣሉት ማዕቀብ ሳይነሳ አንዲት ጠብታ ነዳጅ አንልክም ሲሉ ተናግረዋል።

      የአውሮፓ ባለ ግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት የሆኑት ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ብሪታንያ፣ ቤልጂየም እና ሌሎች ሀገራት በነዳጅ ዕጥረት እየተፈተኑ ናቸው ተብሏል።

      እነዚህ ሀገራት ሩሲያ ነዳጇን እንደጦር መሳሪያ እየተጠቀመችበት ነው ሲሉም ሞስኮን ከሰዋል።

      የዓለማችን ሰባቱ ባለ ግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት የሆኑት የቡድን ሰባት አባል ሀገራት ከሰሞኑ  በሩሲያ ነዳጅ ላይ የዋጋ ተመን ማውጣታቸው ይታወሳል።

      እነዚህ ሀገራት ሩሲያ ነዳጇን በተተመነላት ዋጋ መሰረት ለአውሮፓ ሀገራት እንድትሸጥ የወሰኑ ቢሆንም ሩሲያ በበኩሏ ምንም አይነት ነዳጅ ወደ አውሮፓ አልሸጥም የሚል ውሳኔ አሳልፋለች።

      News today, Politics

      ሩሲያ የከባድ መሳሪያ ተተኳሾችን ከሰሜን ኮሪያ እየገዛች ነው ተባለ

      ሩሲያ በበኩሏ ኢኮኖሚዋ በመሻሻል ላይ መሆኑን አስታውቃለች

      ሩሲያ የከባድ መሳሪያ ተተኳሾችን ከሰሜን ኮሪያ እየገዛች ነው ተባለ፡፡

      ኒዮርክ ታይምስ የአሜሪካ የስለላ ተቋም መረጃን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ከሆነ ሩሲያ ከዩክሬን ጋር እያደረገች ባለው ጦርነት ምክንያት የጦር መሳሪያ እጥረት አጋጥሟታል፡፡

      ሩሲያ የየከባድ ጦር መሳሪያ ተተኳሽ እጥረት ያጋጠማት በአሜሪካ እና አውሮፓ ህብረት በተጣለባት ማዕቀብ እንደሆነ የጠቀሰው ዘገባው እጥረቱን ለማስታገስ ስትልም ከሰሜን ኮሪያ በመግዛት ላይ መሆኗንም ጠቅሷል፡፡

      አሁን ላይ ሩሲያ ሮኬቶች እና ሌሎች የረጅም ርቀት የጦር መሳሪያዎችን ለመግዛት ተገዳለች ያለው ዘገባው ጦርነቱ በቀጠለ ቁጥር የጦር መሳሪያውም የበለጠ እያጠራት እንደሚሄድ አመላክቷል፡፡

      ባሳለፍነው ሳምንት ሩሲያ ኢራን ሰራሽ ድሮኖችን ከቴህራን መግዛቷን የገለጸው ዘገባው ሩሲያ በአሜሪካ ማዕቀብ ከተጣለባቸው ሀገራት ጋር ግንኙነቷን እያጠበቀች መጥታለችም ብሏል፡፡

      የሰሜን ኮሪያ ፕሬዝዳንት ኪም ጆንግ ኡን በሩሲያ ዩክሬን ጦርነት መጀመር ዋነኛዋ ተጠያቂ አሜሪካ እንደሆነች ከዚህ በፊት ተናግረው ነበር፡፡

      ፕሬዝዳንቱ ከዩክሬን ወደ ሩሲያ ለተጠቃለሉ ዶምባስ እና ሉሃንስክ ግዛቶች ሉዓላዊነት ቀድመው እውቅና ከሰጡ ሀገራት መካከል ሰሜን ኮሪያ አንዷ ስትሆን ሶሪያ ደግሞ ሁለተኛዋ ሀገር ናት፡፡

      ሩሲያ በበኩሏ በአሜሪካ እና አውሮፓ ህብረት ከስድስት ሺህ በላይ ማዕቀቦች ቢጣሉብኝም ማዕቀቦቹ በሩሲያ ኢኮኖሚ ላይ ያደረሱት ተጽዕኖ ሁለት በመቶ ብቻ መሆኑን አስታውቃለች፡፡

      የሞስኮ መገበያያ የሆነው ሩብል ከአሜሪካው ዶላር ጋር ሲነጻጸር ከዚህ በፊት ከነበረው ልዩነት መቀነሱን እና የሩሲያ የወጪ ንግድም ጉድለት አለማሳየቱ ተገልጿል፡፡

      የፊንላንዱ የምሁራን ስብስብ ተቋም ባወጣው ጥናት ምዕራባዊያን በሩሲያ ላይ የጣሉት ማዕቀብ ጥቂት ጉዳት ብቻ ማድረሱን ጠቅሶ ሩሲያ በስድስት ወራት ውስጥ ብቻ 136 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷን አስታውቋል፡፡

      News today, Politics

      ፑቲን የቻይና ጦር የተሳተፈበትን “ቮስቶክ 2022” የጦር ልምምድ ላይ መገኘታቸው ተገለጸ

      በቮስቶክ 2022 የጦር ልምምድ ከ14 ሀገራት የተውጣጡ 50 ሺህ ወታደሮች ተሳታፊ ሆነዋል

      ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን፤ ቻይናን ጨምሮ በርካታ ሀገራት በሚሳተፉበት በግዙፉ የ“ቮስቶክ 2022” የጦር ልምምድ በሚካሄድበት ካቦራቭስክ ወታደራዊ ስፍራ መገኘተቻው የክሬምሊን ቃል አቀባይ ደሚትሪ ፔስኮቭ ገለጹ፡፡

      ፕሬዝዳንት ፑቲን በልምምድ ስፍራው የተገኙት ከመከላከያ ሚኒስትሩ ሰርጌይ ሾይጉ እና ከወታደራዊው አዛዥ ቫለሪ ገራሲሞቭ ጋር መሆኑን ቃል አቀባዩ፤ አስታውቀዋል።

      ፕሬዝዳንቱ ለሳምንት የዘለቀውን ልምምድ የመጨረሻ ምዕራፍ እንደሚከታተሉ መገለጻቸውም ዘ-ጋርዲያን ዘግቧል፡፡

      በሩሲያ አስተናጋጅነት ሲካሄድ የቆየው ግዙፉ ቮስቶክ 2022 የጦር ልምምድ ባሳለፍነው ሳምንት ሀሙስ እንደተጀመረ ሚታወስ ነው፡፡

      ቮስቶክ 2022 የሚል መጠሪያ የተሰጠውና በሩቅ ምስራቅ ሩሲያ እና በጃፓን ባህር ላይ ሲካሄድ የቆው ወታደራዊ ልምምድ በነገው እለት እንደሚጠናቀቅም ነው የተገለጸው፡፡

      በወታደራዊ ልምምዱ አዘጋጇ ሩሲያን ጨምሮ ቻይና፣ ቤላሩስ፣ ታጃኪስታን፣ ህንድ እና ሞንጎሊያን ጨምሮ በድምሩ 14 ሀገራት ተሳትፈዋል።

      በልምምዱ ከሀገራቱ የተውጣጡ 50 ሺህ ወታደሮች የተሳተፉ ሲሆን፤ የረጅም ርቀት ቦምብ ጣይ ጄቶ እንዲሁም የጦር ካርጎ አውሮፕላኖኖች የተካተቱባቸው ከ5 ሺህ በላይ የተለያዩ አይነት የጦር መሳሪያዎች ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡

      ከጦር መሳሪያዎቹ መካከልም 140 የጦር አውሮፕላኖች እና 60 የጦር መርከቦች እንደሚገኙበትም ነው የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር መረጃ የሚያመለክተው፡፡

      በዚህ የጦር ልምምድ ከሚሳተፉ ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው ቻይና ፤ የጦር ልምምዱ ከወቅቱ የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ጋር እንደማይገናኝ መግለጿ ይታወሳል።

      መሰል ወታደራዊ ልምምድ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን፤ የመጀመሪው የጦር ልምምድ እንደፈረንጆቹ 2018 መካሄዱ አይዘነጋም፡፡

      News today, Politics

      ሰሜን ኮሪያ ጥላትን ለማሳሳት በማለት 8 አንድ አይነት ቤተመንግሥት ሰራች


      2022/8/29 11:38 GMT

      ሰሜን ኮሪያ የፕሬዝዳንት ኪም ጆን ኡን

      ቤተ መንግስቶቹ ተመሳስለው የተገነቡት ፕሬዝዳንቱ ያሉበት እንዳይታወቅ እንደሆነ ተገልጿል

      ከምዕራባዊያን ጋር እሰጣ አገባ ውስጥ ያለችው ሰሜን ኮሪያ ጠላትን ለማሳሳት በሚል ስምንት ተመሳሳይ ቤተ መንግስቶችን መገንባቷ ተገልጿል።

      እንደ ዴይሊ ሜይል ዘገባ ከሆነ ሰሜን ኮሪያ የፕሬዝዳንት ኪም ጆን ኡን ደህንነትን ለመጠበቅ ሲባል በሀገሪቱ መዲና ፒዮንግያንግ ከተማ ተመሳሳይ ቅርጽ ያላቸው ቤተመግስቶችን ገንብታለች።

      ሰሜን ኮሪያ በጎረቤቷ ደቡብ ኮሪያ አማካኝነት እና በምዕራባዊያን የተቀናጀ ጥረት በፕሬዝዳንቱ ላይ ግድያ ሊፈጸም ይችላል የሚል ስጋት አላት።

      ይሄንን ስጋቷን ለማስወገድ እና ፕሬዝዳንቷን ለመጠበቅ ተመሳሳይ ቅርጽ፣ የቀለም ቅብ፣ መሰረተ ልማት እና ሌሎች ሚስጢራዊ ግንባታዎችን የያዘ ቤተ መንግስት መገንባቷን ዴይሊ ሜጠይል የሳተላይት ምስሎችን ዋቢ አድርጓል።

      እነዚህ ቅንጡ ስምንት ቤተ መንግስቶች በመሃል ፒዮንግያንግ ቻንግ ክዋንግሳን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሀገሪቱ ፓርቲ ጽህፈት ቤት ፊት ለፊት መገንባቱ ተገልጿል።

      ቤተ መንግስቶቹ የተገነቡባቸው አካባቢዎች ለሌሎች የሀገሪቱ ዜጎች ዝግ መሆኑን ተከትሎ አካባቢው “የተከለከለ ከተማ” ወይም ፎርቢድን ሲሰቲ የሚል ስምም ተሰጥቶታል ተብሏል።

      የሰሜን ኮሪያ ሀገራዊ ሚስጢራት እና ወታደራዊ እቅዶች በነዚህ ቤተመንግስቶች ውስጥ እንደሚረቀቁም ተገልጿል።

      ፕሬዝዳንት ኪም እና አስተዳድራቸው በሰሜን ኮሪያ ዋነኛ ስጋቷ ከሀገሬው ህዝብ ወይም ፖለቲከኞች ሳይሆን ከውጭ ሀገራት የሚሰነዘር እንደሚሆን እርግጠኛ ናቸው።

      ይሄንንም ስጋት ለመቀልበስ ጥቃቱ በሀገሪቱ ፕሬዝዳንት እና ወታደራዊ ተቋማቸው ላይ ስለሚሆን ጠላቶችን ለማሳሳት አጠቃላይ እንቅስቃሴያቸውን ገድበው በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው ተብሏል።

      ፕሬዝዳንት ኪም ራሳቸውን እና ሀገራቸውን ከአደጋ ለመጠበቅ በጠዋት እና በምድር ውስጥ የተዘጋጁ መጓጓዣዎችን እንደሚጠቀሙ ተገልጿል።

      ፕሬዝዳንት ኪም ከሀገሪቱ መዲና ፒዮንግያንግ ከተማ በተጨማሪ በመላው የሀገሪቱ ክፍል 13 ቤተ መንግስቶች አሏቸው የተባለ ሲሆን እነዚህ ቤተመንግስቶች በወዳጆቻቸው እና ዘመዶቻቸው ይጠበቃሉም ተብሏል።

      News today, Politics

      ጀርመን የቀድሞ ፕሬዝዳንቷን ወደ ሩሲያ ልትልክ ነው

      ጀርመን ወደ ሞስኮው ልኡክ የምትልከው ከነዳጅ ጋር በተያያዘ ከሩሲያ ጋር ለመምከር ነው
      ጀርመን የቀድሞ ፕሬዝዳንቷን ወደ ሩሲያ ልትልክ መሆኑ ተሰምቷል።

      ዩክሬን የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ጦርን እቀላቀላለሁ ማለቷን ተከትሎ ከሩሲጠያ ጋር በተቀሰቀሰው ጦርነት የዓለም ነዳጅ ዋጋ አሻቅቧል።
      40 በመቶ የነዳጅ ፍጆታቸውን ከሩሲያ የሚሸምቱት አውሮፓዊያን በዩክሬን ጉዳይ አጣብቂኝ ውስጥ ወድቀዋል።

      ከአውሮፓ ሀገራት መካከል ጀርመን ደግሞ የሩሲያ ነዳጅ ጥገኛ ከሆኑ ሀገራት መካከል ዋነኛዋ ስትሆን የአውሮፓ ህብረት እና አሜሪካ በሩሲያ ላይ ማዕቀብ መጣላቸውን ተከትሎ ነዳጅ እንደበፊቱ ማግኘት አልቻለችም።

      በዚህም ምክንያት የፕሬዝዳንት ፑቲን ወዳጅ እንደሆኑ የሚነገርላቸው የቀድሞቀው የጀርመን ፕሬዝዳንት በጌራልድ ሽሮደር የሚመራ ልኡክ ወደ ሞስኮ ልትልክ መሆኑን አስታውቃለች።

      የወቅቱ የጀርመን ፕሬዝዳንት ኦላፍ ሾልዝ ሩሲያ ወደ ጀርመን የምትልከውን ነዳጅ መጠን እንዳትቀንስ የሚያግባባ ልኡክ ወደ ሞስኮ እንደሚልኩ ሮይተርስ ዘግቧል።

      ይህን በነዳጅ ግብይት ዙሪያ ለመምከር ወደ ሞስኮ የሚያቀናውን ልኡክ የቀድሞው የጀርመን ፕሬዝዳንት ጌራልድ ሾልደር ሊመሩት እንደሚችሉ ፕሬዝዳንቱ አክለዋል።

      ወደ ሞስኮ የሚያቀናው የጀርመን ልኡክም በዋናነት ተልዕኮው ሩሲያ በኖርድ ስትሪም አንድ ተብሎ በሚጠራው የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ነዳጅ በበቂ መጠን እንድትልክ ማግባባት እንደሚሆን ተገልጿል።

      የቀድሞው የጀርመን ፕሬዝዳንት ጌራልድ ሽሮደር ወደ ሞስኮ አቅንተው ፕሬዝዳንት ፑቲንን ያገኙ ሲሆን የጀርመን መንግስት ከዚህ በፊት ነዳጅ ከሩሲያ የሚያገኝበት ኖርድ ስትሪም አንድን ትቶ ወደ ሁለት እንዲያተኩር አሳስበው ነበር።

      ጌራልድ ሽሩደር ጀርመንን ከፈረንጆቹ 1998 ጀምሮ እስከ 2005 ድረስ በፕሬዝዳንትነት ማገልገላቸው አይዘነጋም።

      የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ 170ኛ ቀኑ ላይ ሲሆን እስካሁን ከ10 ሚሊዮን በላይ ዩክሬናዊያን ሀገራቸውን ጥለው ወደ ጎረቡት ሀገራት መሰደዳቸውን ተመድ ከሰሞኑ ገልጿል።

      News today, Politics

      ጀርመን በማሊ ያሰማራችውን ሰላም አስከባሪ ጦር ልታስወጣ መሆኗን አስታወቀች

      ጀርመን በባማኮ የነበራትን ሰላም ማስከበር ስራ ያቋረጠችው ማሊ ከሩሲያ ጋር መስራቷን ተከትሎ ነው
      ጀርመን በማሊ ያሰማራችውን ሰላም አስከባሪ ጦር ልታስወጣ መሆኗን አስታወቀች።

      የአውሮፓ ሀገራት ከዘጠኝ ዓመት በፊት በምዕራብ አፍሪካ የሽብርተኞችን ጥቃት ለመከላከል በሚል በፈረንሳይ አስተባባሪነት ለሚመራው የተመድ ሰላም ማስከበር ተልዕኮ ጦራቸው አዋጥተው ነበር።

       ማሊ፣ቡርኪና ፋሶ፣ኒጀር እና ቻድ ደግሞ ከአምስት ሺህ በላይ የአውሮፓ ሀገራት ጦር የሰፈረባቸው ሀገራት ናቸው፡፡
      ይሁንና በማሊ በኮለኔል አስሚ ጎይታ የሚመራው ወታደራዊ መንግስት ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ ምዕራባውያን ሀገራት ደስተኛ ሊሆኑ አልቻሉም።

      ጀርመንም ከነዚህ ሀገራት መካከል ወነኛዋ ስትሆን የሩሲያ ቅጥረኛ ወታደሮች በማሊ መታየታቸውን ተከትሎ ወታደሮቿን ከማሊ ለማስወጣት መወሰኗን የጀርመን ድምጽ ዘግቧል።

      የጀርመን መከላከያ ሚኒስትር ክሪስቲን ላምምበርችት እንዳሉት ከምንም በላይ የወታደሮቻችን ደህንነት ቅድሚያ የሚሰጡት ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል ።

      ጀርመን ከአንድ ወር በፊት 60 ወታደሮቿን ከማሊ ያስወጣች ሲሆን የማሊ ወታደራዊ መንግሥት እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ ስጋት እንደደቀነባቸውም ተገልጿል።

      የማሊ ወታደራዊ መንግሥት ከዚህ በፊት የምዕራባውያን ሀገራት በሰላም ማስከበር ስም በርካታ ሰራዊት መስፈራቸውን እና የማሊን ሉዓላዊነት ሊጥሱ እንደማይገባ ገልጾ ነበር
      ለተመሳሳይ ተልዕኮ በሚል በማሊ በሶስት ካምፖች ሰፍሮ የነበረው የፈረንሳይ ጦር ከወራት በፊት ለቆ መውጣቱ ይታወሳል።

      የፈረንሳይ ፕሬዘዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እስካለፈው ሰኔ ወር ድረስ በምእራብ አፍሪካ አገራት ያለውን አብዛኛውን ጦር ወደ ፓሪስ የመመለስ እቅድ መያዙን ከዚህ በፊት መናገራቸውም አይዘነጋም፡፡
      የአውሮፓ አገራት ሰላም አስከባሪ ጦር ወደ ሳህል ቀጠና የሚሰማራው ከምዕራብ አፍሪካ አገራት ወደ አውሮፓ በመሻገር የሽብር ድርጊቶች እንዳይፈጸሙ ያለመ ነበር ተብሏል፡፡

      የማሊ እና ቡርኪናፋሶ ዜጎች ከዚህ በፊት በተለያዩ ከተሞች የፈርንሳይ ጦር አገራቸውን ለቀው እንዲወጡ የሚጠይቁ ሰላማዊ ሰልፎች ማካሄዳቸው ይታወሳል፡፡ 

      News today, Politics

      የኬንያ የምርጫ አፈጻጸም በሁሉም መመዘኛዎች ጥሩ የሚባል ነው – የኢጋድ የምርጫ ታዛቢ ቡድን


      ዶ/ር ሙላቱ ፤ አልፎ አልፎ የታዩት መስተጓጎል ለማስቀረት የምርጫ ቁሳቁስ አቅርቦትን በትክክል መፈጸሙን ማረጋገጥ እንደሚያሰፈልግ ተናግረዋል

      ኬንያ ያካሄደችው ምርጫ ከዝግጅቱ ጀምሮ ጠንካራ የሚባልና የምርጫ አስተዳደር አፈጻጸሙ በሁሉም መመዘኛዎች የሚበረታታ ነው ሲል የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) የምርጫ ታዛቢ ቡድን ገለጸ፡፡

      ባለፈው ማክሰኞ ናይሮቢ የደረሰውና በቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የሚመራው የኢጋድ የምርጫ ታዛቢ ቡድን የኬንያ ምርጫን ቅድመ ዝግጅትና የምርጫ ሂደቱን በተመለከተ መግለጫ አውጥቷል፡፡
      የታዛቢ ቡድኑ መሪ ዶ/ር ሙላት ተሾመ፤ የኬንያ የምርጫ እና የድንበር ጉዳዮች በሁሉም መመዘኛዎች ጥሩ ነው የሚባል የምርጫ ዝግጅት ማድረጉንና ምርጫ ማካሄዱን ተናግረዋል፡፡

      ዶ/ር ሙላቱ፤ ኬንያ ቀደም ሲል ባካሄደቻቸው ምርጫዎች፤ ከመራጮች ማንነት ማወቅና እና የውጤት ስርጭት ጋር በተያያዘ ይነሱ ነበሩ ችግሮች የሚቀርፍ ቴክኖሎጂ በዚህ ምርጫ ላይ ተግባራዊ መደረጉ እንዲሁም የሴቶችና ወጣቶች የምርጫ አስፈታሚዎች ውክልና መሻሻሉ በምርጫው ከታዘብናቸው በጎ እርምጃዎች ውስጥ ናቸውም ብለዋል፡፡

      “የምርጫ ጣቢያዎችን አደረጃጀት እና የዳስ አቀማመጥ ፣ የድምጽ መስጫ ሚስጥራዊነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉና በየምርጫ ጣቢያው የሚኖሩ ረጃጅም ሰልፎች የሚያስቀሩ በቂ የዳስ ቤቶች መኖራቸው ታዛቢ ቡድኑ ከተመለከታቸውና ከተሻሻሉ ወሳኝ የምርጫ ዝግጅቶች መካከል ናቸው” ሲሉም አክለዋል፡፡

      ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ፤ በአንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች የታየውን አይነት መስተጓጎል ለማስቀረት የምርጫ ቁሳቁስ አቅርቦትን በትክክል መፈጸሙን በማረጋገጥ ረገድ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚያስፈልግም አሳስበዋል፡፡

      ከምርጫ አስተዳደር ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን በማስተናገድ እና የህዝብን እምነት በማሳደግ እስከ ምርጫው ቀን ድረስ የፍትህ አካላት ሚና ከፍተኛ እንደነበርም ገልጸዋል የኢጋድ ታዛቢ ቡድን መሪው ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ።

      ከተመለከትናቸው ጉዳዮች አንዱ በእጅ መመዝገቢያ አጠቃቀምን በተመለከተ የፍተህ አካላት የነበራቸው ሚና ነው ያሉት ዶ/ር ሙላቱ፤ በኬንያ ዲሞክራሲን ከማጠናከር አንጻር የኬንያ የፍትህ አካላት በህዝብ ያላቸውን ተአማኒነት እንደ ተጨባጭ ስኬት እንቆጥረዋለንም ብለዋል።

      በመጨረሻም የኬንያ ህዝብ ምርጫው ሰላማዊ፣ ግልጽ እና ስርዓት ባለው መንገድ ለመሳተፍ ላሳየው ትዕግስት እና ቁርጠኝነት አመስግነዋል።

      የኢጋድ ታዛቢ ቡድኑ ከቀጣናዊው ተቋም ስድስት አባል ሃገራት ማለትም ከኢትዮጵያ፣ ከኬንያ፣ ከሱዳን፣ ከደቡብ ሱዳን፣ ከጅቡቲ፣ ከሶማሊያ እና ከኡጋንዳ የተውጣጡ ሰባት ዋና እና 24 ጊዜያዊ አባላት የተዋቀረ መሆኑ ይታወቃል፡፡

      News today, Politics

      ከህወሓት ጋር በሚደረገው ድርድር ላይ የአፍሪካ ህብረትን የሚደግፉ የአፍሪካ ታዋቂ ሰዎች ቢካተቱ እንደማይቃወም መንግስት አስታወቀ


      መንግሥት በትግራይ ክልል መሰረታዊ አገልግሎት ለማስጀመር በቅድመ ሁኔታነት እንደማያስቀምጥ ገለጸ

      የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል።

      ቃል አቀባዩ በዚህ ጊዜ እንዳሉት የፌደራል መንግሥት ከህወሓት ጋር በሚደረገው ድርድር ላይ የመሰረታዊ አገልግሎቶችን ለማስጀመር በቅድመ ሁኔታነት እንደማያስቀምጥ ተናግረዋል።

      የፌደራል መንግስት እና ህወሓት ድርድር ተስፋ እና ስጋቶች
      “አገልግሎቶችን ለማስጀመር ዋናው መሰረታዊ ነገር ቅድመ ሁኔታ ሳይሆን ምክክር እና ዝርዝር ውይይት ማድረግ ያስፈልጋል” ብለዋል።

      ከዚህ በፊት ትግራይ ክልልን ጨምሮ በሌሎች የሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች አገልግሎቱን ማስጀመር የሚያስችል አስተማማኝ ሰላም እና መተማመን መፈጠር እንደሚያስፈልግ አምባሳደር መለስ ገልጸዋል።

      ቃል አቀባዩ አክለውም የፌደራል መንግስት ከህወሓት ጋር በሚደረገው ድርድር ላይ በቦታ እና ጊዜ እንደማይወሰን ገልጸው በድርድሩ ላይ የአፍሪካ ህብረትን አቋም የሚደግፉ ታዋቂ አፍሪካዊያን ቢሳተፉ የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃውሞ እንደሌለው አክለዋል።

      መንግሥት ከህወሃት ጋር ያደርገዋል የተባለው ንግግር የሚመራው በአፍሪካ ሕብረት ብቻ እንደሆነ መግለጹ ይታወሳል።

      ህወሓት በበኩሉ በቃል አቀባዩ በኩል በሰጠው መግለጫ፤ የአፍሪካ ሕብረት ከኦባሳንጆ ይልቅ፤ ኡሁሩ ኬንያታን ወይም ታቦ ኢንቤኬን ወይም ሌላ ሰው ከሰየመ ችግር እንደሌለበት ገልጿል።

      ህወሓት በኬንያ ድርድር ለማድረግ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ለመላክ መዘጋጀቱን በሊቀ መንበሩ ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ማስታወቁ ይታወሳል።

      የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ በመግለጫቸው አክለውም፤ እስካሁን ባለው ጊዜ በህገወጥ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ የገቡ 70 ሺህ የውጭ ሀገራት ዜጎች መመዝገባቸውን ገልጸዋል።

      በህገወጥ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ የገቡ የውጭ ሀገራት ዜጎችን የመመዝገብ ስራው እስከ ነሀሴ 13 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ መራዘሙ ተገልጿል።

      ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ስለ “ድርድር” ምን አሉ?
      ምዝገባው የተራዘመበት ምክንያት በቀነ ገደብ በተለያዩ ምክንያቶች ያልተመዘገቡ የዉጭ ሀገራት ዜገች ዕድሉን ለመስጠት እንደሆነም ቃል አቀባዩ ገልጸዋል።

      የውጭ ሀገራት ዜጎችን መመዝገብ ያስፈለገው ምን ያህል የውጭ ሀገራት ዜጎች በኢትዮጵያ እንዳሉ ለማወቅ እና ከተመዘገቡ በኋላ ወደ ህጋዊ መስመር ለማምጣት በማስፈለጉ ነው ተብሏል።

      እስካሁን ባለው ምዝገባ ከካናዳ፣ አሜሪካ፣ ኮንጎ፣ ናይጄሪያ፣ የመን፣ ሶሪያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ቻይና፣ ኤርትራ፣ ቡሩንዲ ፣ ጋና፣ ባንግላዲሽ፣ ሕንድ፣ ላይቤሪያ፣ ካሜሮን እና ጣሊያን የመጡ ህገወጥ ዜጎች ተመዝግበዋል።

      News today, Politics

      ላቲቪያ ሩሲያን በሽብርተኝነት ፈረጀች

      ሌላኛዋ የሩሲያ ጎረቤት ኢስቶኒያ ድንበሯን ለሞስኮ ዝግ አድርጋለች

      የላቲቪያ ፓርላማ

      ላቲቪያ ሌሎች የአውቶፓ ሀገራት ሩሲያ ላይ ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወስዱ ጠይቃለች

      የቀድሞ የሶቪየት ህብረት አንድ አካል የነበረችው እና የምስራቅ አውሮፓዋ ላቲቪያ ሩሲያን በሽብርተኝነት ፈርጃለች።

      የሀገሪቱ ፓርላማ ዛሬ እንደወሰነው ከሆነ በፕሬዝዳንት ፑቲን የሚመራው የሩሲያ መንግስትን በሽብርተኝነት ፈርጇል።

      ከሁለት ሚሊዮን ያልበለጠ ህዝብ ብዛት ያላት ላቲቪያ የሩሲያ እና ቤላሩስ ዜግነት ያላቸው መንገደኞች በአውሮፓ ሀገራት እንዲዘዋወሩ የሚፈቅደው የሸንገን ቪዛን እንዳይጠቀሙም እገዳ መጣሏን ሮይተርስ ዘግቧል።

      ሩሲያ በዩክሬን ዜጎች ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እያደረሰች ነው በሚል የምትከሰው ላቲቪያ ሁሉም የአውሮፓ ሀገራት በሩሲያ ላይ ተመሳሳይ ማዕቀብ እንዲጥሉ ጥሪ አቅርባለች።

      ሌላኛዋ የቀድሞ የሶቪየት ህብረት አንድ አካል የነበረችው ኢስቶኒያ ድንበሯን ለሩሲያ ዜጎች የዘጋች ሲሆን ምክንያቷ ደግሞ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ወረራ እና በዜጎቿ ላይ ስቃይ እያደረሰች ነው በሚል ነው።

      ዩክሬን የሰሜን አትላንቲክ ቃልኪዳን ጦር ወይም ኔቶን እቀላቀላለሁ ማለቷን ተከትሎ ነበር ከስድስት ወራት በፊት ከሩሲያ ጋር ወደ ጦርነት የገቡት።

      በዚህ ጦርነት ምክንያት የዓለም የምግብ እና ነዳጅ ዋጋ ያሻቀበ ሲሆን ከ10 ሚሊዮን በላይ ዩክሬናዊያን ደግሞ ወደ ጎረቤት ሀገራት መሰደዳቸውን ተመድ ከሰሞኑ ሪፖርት ማድረጉ ይታወሳል።

      News today, Politics

      ቭላድሚር ፑቲን፤ ከማሊ የሽግግር መንግስት ፕሬዝዳንት ጋር መወያየታቸውን ገለጹ


      ምዕራባውያን፤ ሩሲያ በማሊ የምታደርገው ተሳትፎ እያደገ መምጣቱ እንዳሳሰባቸው ሲገልጹ ነበር
      የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከማሊ የሽግግር መንግስት ፕሬዝዳንት ጋር መወያየታቸውን የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታወቀ።


      ቭላድሚር ፑቲንና የማሊው መሪ አሲሚ ጎይታ፤ በሁለትዮሽ ትብብር ማለትም በንግድ፣ በኢኮኖሚና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ መወያየታቸው ተገልጿል።
      የማሊው መሪ አሲሚ ጎይታ፤ ሩሲያ ላደረገችላቸው ድጋፍ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን ማመስገናቸውም ተሰምቷል።


      መሪዎቹ፤ የሩስያ የምግብ፣ የማዳበሪያ እና የነዳጅ ምርቶች ወደ ማሊ መድረስ በሚችሉባቸው ነጥቦች ላይም መነጋገራቸው ተሰምቷል።
      የሚመለከታቸው የሩሲያ እና የማሊ ተቋማት የሥራ ክፍሎች የሁለቱን ሀገራት ትብብር እንዲያጠናክሩ ስምምነት ተደርጓል ተብሏል።


      መሪዎቹ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጭምር ያለው የሩሲያ እና የማሊ የውጭ ግንኙነት ትብብር እንዳስደሰታቸውም ገልጸጸዋል ተብሏል።
      የማሊው የሽግግር መንግስት መሪ አሲሚ ጎይታ በማሊ አካባቢ ያለውን ሁኔታ ለማረጋጋትና በአሸባሪ ቡድኖች እርምጃ ለመውሰድ የታቀደውን ዕቅድ ጨምሮ፤ በማሊ ውስጥ የተከናወኑ ስራዎችን ለፕሬዝዳንት ፑቲን ገልጸውላቸዋል ተብሏል።


      ቭላድሚር ፑቲን ፤ እ.ኤ.አ. በ 2023 በሴንት ፒተርስበርግ ከተማ ሊካሄድ የታቀደው የሩሲያ አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ከመላው አፍሪካ ሀገራት ጋር ያለውን ወዳጅነት ለማጠናከር እንደሚያግዝ ገልጸዋል።


      ምዕራባውያን ሀገራት፤ ሩሲያ የፈረንሳይ ቅኝ ግዛት በነበረችው ማሊ ውስጥ የምታደርገው ተሳትፎ እያደገ መምጣቱም እንዳሳሰባቸው ሲገለጽ ቆይቷል።
      በዩክሬን ሩሲያ ጦርነት ምክንያት 40 ሚሊየን አፍሪካዊያን ለምግብ እጥረት እንደሚጋለጡ አሜሪካ ገለጸች


      የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጂን ይቭስ ሊ ድሪያን የካቲት ወር ላይ፤ በማሊ መፈንቅለ መንግሥት ያካሄደው ወታደራዊ ኃይል “ሕገ ወጥ እና ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ነው” ማለታቸው ይታወሳል።
      ይህንን ተከትሎም የማሊ ወታደራዊ መሪዎች፤ በማሊ የነበሩት የፈረንሳይ አምባሳደር ጆል ሜየር በ 72 ሰዓት ውስጥ ከማሊ እንዲወጡ ማድረጋቸው ይታወሳል።

      News today, Politics

      ቻይና በዩክሬን ለተፈጠረው ቀውስ “ዋና ቀስቃሽ” አሜሪካ ናት አለች



      ቻይና እና ሩሲያ በመካከላቸው “ገደብ የለሽ አጋርነት” እንዲኖር በመስማማት በጋራ እየሰሩ ያሉ ሀገራት ናቸው
      በታይዋን ጉዳይ ከአሜሪካ ጋር መካረር ውስጥ የገባችው ቻይና፤ በዩክሬን ለተፈጠረው ዩክሬን ቀውስ “ዋና ቀስቃሽ” አሜሪካ ናት አለች፡፡


      በሞስኮ የቻይና አምባሳደር ዣንግ ሃንሁዊ ረቡዕ ታትሞ ከወጣው የሩስያ መንግስት የዜና ወኪል ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ፤ ዋሽንግተን በኔቶ የመከላከያ ህብረት ተደጋጋሚ መስፋፋት በማድረግና እና ዩክሬንን ከአውሮፓ ህብረት ጋር ለማስማማት ለሚፈልጉ ሃይሎች ድጋፍ በመስጠት ሩሲያን ወደ ጥግ እየገፋቸው ነው በማለት ከሰዋል። 


      አምባሳደር ዣንግ “ዋሽንግተን የዩክሬን ቀውስ ዋና አነሳሽ እና ቀስቃሽ ናት፤ አሁንም በሩሲያ ላይ ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ አጠቃላይ ማዕቀብ መጣልንና ለዩክሬን የጦር መሳሪያ እና ወታደራዊ ቁሳቁሶችን ማቅረብ ቀጥላበታለች” ሲሉ መናገራቸውም ኤኤፍፒ ዘግቧል፡፡
      “የእነሱ (አሜሪካውያን) የመጨረሻ ግባቸው ሩሲያን በተራዘመ ጦርነት እና በማዕቀብ ማዳከም ነው”ም ብለዋል፡፡


      የሩስያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በየካቲት ወር ወደ ቤጂንግ ተጉዘው ከቻይናው አቻቸው ዢ ጂንፒንግ ጋር ባደረጉት ምክክር በሀገራቱ መካካል “ገደብ የለሽ አጋርነት” እንዲኖር መስማማታቸው የሚታወስ ነው፡፡
      የሀገራቱን ወቅታዊ ግንኙነት በተመለከተ የተጠየቁት አምባሳደር ዣንግም የሲኖ-ሩሲያ ግንኙነት “በታሪክ ውስጥ እጅግ በጣም ጥሩ በሚባል ደረጃ ላይ ይገኛል” ብለዋል፡፡


      የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ሀገራቸው የሩሲያን ሉዓላዊነት እና ደህንነትን እንደምትደግፍ ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በነበራቸው የስልክ ውይይት በቅረቡ መግለጻቸው አይዘነጋም፡፡
      ቤጂንግ “በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለማጠናከር ፈቃደኛ ነች”ም ነበር ያሉት ዢ፡፡


      የሩሲያ እና የቻይና ወዳጅነት የ21ኛው ክፍለ ዘመን የትብብር ምሳሌ መሆኑን ፕሬዘዳንት ፑቲን ከወራት በፊት ከቻይናው አቻቻው ጋር በነበራቸው የበይነ መረብ ውይይት መናገራቸውም የሚታወስ ነው።
      ሀገራቱ በወታደራዊ፣ በቴክኖሎጂ፣ በጠፈር ሳይንስ፣ ንግድ እና ኢንቨስትመንትን ጨምሮ በሌሎች ሁለትዮሽ እና ዓለም አቀፋዊ አጀንዳዎች ዙሪያ በጋራ እንደሚሰሩ ይታወቃል፡፡ 

      News today, Politics

      አሜሪካዊቷ ከፍተኛ ዲፕሎማት፤ የአፍሪካ ሃገራት “ሊያልፉት የማይገባ ቀይ መስመር አለ” ማለታቸው እያነጋገረ ነው

      አሜሪካዊቷ ከፍተኛ ዲፕሎማት፤ የአፍሪካ ሃገራት “ሊያልፉት የማይገባ ቀይ መስመር አለ” ማለታቸው እያነጋገረ ነው
      ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ፤ የአፍሪካ ሃገራት ከስንዴ እና ማዳበሪያ ውጭ ከሩሲያ ምንም ነገር እንዳይገዙ አስጠንቅቀዋል
      አምባሳደር ሊንዳ ከሰሞኑ ሶስት የአፍሪካ ሃገራትን መጎብኘታቸው የሚታወስ ነው

      አፍሮ አሜሪካዊቷ የአሜሪካ ከፍተኛ ዲፕሎማት፤ የአፍሪካ ሃገራት ከስንዴ እና ማዳበሪያ ውጭ ከሩሲያ ምንም ነገር እንዳይገዙ ማስጠንቀቃቸው እያነጋገረ ነው፡፡

      በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑት ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ የአፍሪካ ሃገራት ሊያልፉት የማይገባ ቀይ መስመር እንዳለ ተናግረዋል፡፡

      ግሪንፊልድ ከሰሞኑ ኡጋንዳን፣ ጋናን እና ኬፕቨርዴን ጎብኝተዋል፡፡ ጉብኝታቸው የሩሲያውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሰርጌ ላቭሮቭን የአፍሪካ ጉብኝት ተከትሎ የተደረገ ነው፡፡ ዲፕሎማቷ ግን ከሩሲያ እና ቻይና ጋር ለመፎካከር በሚል ወደ አፍሪካ እንዳልመጡ ተናግረዋል፡፡

      በሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ምክንያት ለከፋ የምግብ ዋስትና ችግር ለተዳረገችው አፍሪካ መፍትሔ ለማፈላለግ በማሰብ እንደሚጎበኟትም ነበር ከጉዞው በፊት የተናገሩት፡፡

      ሆኖም ኡጋንዳ ከደረሱ በኋላ የአፍሪካ ሃገራት ሊያልፉት የማይገባ ቀይ መስመር እንዳለ መናገራቸው እያነጋገረ ነው፡፡

      “የአፍሪካ ሃገራት እህልን ጨምሮ የሩሲያን የግብርና ምርቶች እና የአፈር ማዳበሪያን ሊገዙ ይችላሉ” ሲሉ ለአሶሼትድ ፕሬስ የተናገሩት አምባሳደር ሊንዳ ነገር ግን ነዳጅንና የነዳጅ ምርቶችን ሊገበያዩ እንደማይችሉ ገልጸዋል፡፡

      የሚገበያዩ ከሆነ በሩሲያ ላይ የተጣሉ ማዕቀቦችን መጣስ እንደሚሆን ነው አምባሳደሯ የተናገሩት፡፡ በመሆኑም “ማዕቀቡን እንዳይጥሱ እናሳስባለን” ብለዋል ይህ ካልሆነ ተመሳሳይ እጣ ፋንታ ሊጠብቃቸው እንደሚችል በማስጠንቀቅ፡፡

      ብዙዎቹ የአፍሪካ ሃገራት በሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ገለልተኛ አቋምን መርጠዋል፡፡ ሩሲያን አውግዘው ከምዕራባውያን ጎን እንዲሰለፉ ቢፈለግም ከኬንያ በስተቀር አቋማቸውን በአደባባይ ለማንጸባረቅ የደፈሩ ጥቂቶች ናቸው፡፡ ሆኖም ይህ የጦርነቱን ዳፋ ከመቅመስ አላዳናቸውም፡፡ በተለይም ብዙዎቹ በሩሲያ እና ዩክሬን የስንዴና ሌሎች የግብርና ምርቶች እንዲሁም የአፈር ማዳበሪያ ላይ ጥገኛ መሆናቸው ለከፋ ጉዳት ዳርጓቸዋል፡፡ ለከፋ የምግብ ዋስትና ችግር እና ኑሮ ውድነት የተዳረጉም ጥቂት አይደሉም፡፡

      በዚህ መካከል ነው የአፍሮ አሜሪካዊቷ የአምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ ማስጠንቀቂያ የመጣው፡፡ ምን ያህል ውጤት ሊያመጣ እንደሚችል አልታወቀም፡፡ ነዳጅን ጨምሮ በከፋ የሸቀጦች ዋጋ ንረት እየተጠበሱ መሆኑን ተከትሎ የመጣውን እንቀበላለን በሚል የሩሲያን ነዳጅ ሊገዙ የሚችሉ አንዳንድ የአፍሪካ ሃገራት እንደሚኖሩ ይጠበቃል፡፡

      ከአምባሳደር ሊንዳ ጉብኝት በፊት “ምን ማድረግ እንዳለብን ማንም ሊነግረን አይችልም” በሚል የተናገሩት የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዮሪ ሙሴቪኒ ከጉብኝቱ በኋላ “አፍሪካን ከአንጀት መርዳት ከፈለጉ ባልተሳተፍንበት ጦርነት ከጣሉት ማዕቀብ ሊለዩን ይገባል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

      News today, Politics

      የቡድን ሰባት አባል ሀገራት፤ ሩሲያ ዛፖሪዥያ የኒውክለር ጣቢያን ለዩክሬን ልትሰጥ ይገባል አሉ

      የቡድን ሰባት አባል ሀገራት፤ ሩሲያ ዛፖሪዥያ የኒውክለር ጣቢያን ለዩክሬን ልትሰጥ ይገባል አሉ
      ሩሲያ፤ በዛፖሪዥያ የኒውክለር ጣቢያ ዙሪያ የጸጥታው ም/ቤት እንዲሰበሰብ ጠየቀች
      ሞስኮ፤ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጣትም ጠይቃለች

      ሩሲያ፤ የዛፖሪዥያ ኒውክለር ጣቢያን፤ ለዩክሬን አሳልፋ ልትሰጥ እንደሚገባ የቡድን ሰባት አባል ሀገራት ጠየቁ።

      የሀገራቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፤ በዛፖሪዥያ ያለውን የኒውክለር ጣቢያ መያዝና መቆጣጠር ያለባት ዩክሬን ናት ብለዋል።

      ሩሲያ፤ የዩክሬን ጦር በግዙፉ “ዛፖሪዥያ ኒውክሌር ጣቢያ” ላይ ተኩስ ከፍቷል ስትል ከሰሰች
      ሚኒስትሮቹ የዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ፤ የኒውክለር መሳሪያዎችን ደህንነት ለመጠበቅ ለሚያደርገው ጥረት ድጋፍ እንደሚያደርጉም ገልጸዋል።

      ምንም እንኳን የቡድን ሰባት አባል ሀገራት ሞስኮ በዛፖሮዝሂ ያለውን የኒውክለር ጣቢያ እንዳትቆጣጠርና ለዩክሬን አሳልፋ እንዲሰጥ ቢጠይቁም ሩሲያም ሌላ ቅሬታ አሰምታለች።

      ሞስኮ፤ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ጥበቃ ምክር ቤት፤ በኒውክለር ጣቢያው ዙሪያ ስብሰባ እንዲያደርግ ጠርታለች።

      በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሩሲያ ቋሚ መልዕከተኛ ጽ/ቤት፤ የጸጥታው ጥበቃ ምክር ቤት አባል ሀገራት በዛፖሪዥያ ኒውክለር ጣቢያ ዙሪያ ስብሰባ እንዲያደርጉ ጥሪ ማቅረቡ ተሰምቷል።

      በዚህ ስብሰባ ላይም ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ እና የተባበሩት መምግስታት የኒውክለር ተቆጣጣሪ ማብራሪያ እንዲሰጧት ሞስኮ ጠይቃለች።

      ዩክሬን በኒውክለር ጣቢያው ላይ የድሮን ጥቃት እያደረገች ነው ስትል ሞስኮ ብትከስም፤ ዩክሬን ግን ይህንን አስተባብላለች። ዩክሬን በበኩሏ ሩሲያ የኒውክለር ጣቢውን በመጠቀም ትቃት እየሰነዘረች ነው ስትል ትከሳለች።

      ሩሲያ በግዝፈቱ ሁለተኛ የሆነውን የዩክሬን የኃይል ጣቢያ ተቆጣጠረች
      የዩክሬን ብሔራዊ የደህንነት ምክር ቤት፤ሩሲያ የኒውክለር ጣቢያውን ለወታደራዊ ምሽግ እየተጠቀመች ነው ሲል ወቅሷል። የሩሲያ ከባድ መሳሪያዎች እና ወታደራዊ ሰዎች በዛፖሪዥያ የኒውክለር ጣቢያ መኖራቸውንም ዩክሬን ገልጻለች።

      የቡድን አባት አባል ሀገራት የዛፖሪዥያ የኒውክለር ጣቢያን በሚመለከት ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንዳሉ ገልጸዋል።

      News today, Politics

      ቻይና፤ አሜሪካ ጸብ አጫሪ ድርጊት ከፈጸመች ምላሽ ለመስጠት መዘጋጀቷን ገለጸች

      ቤጅንግ፤ ከዋሸንግተን ጋር ያላትን ወታደራዊ ትብብር ማቋረጧን መግለጿ ይታወሳል

      የፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት በአሜሪካ እና ቻይና መካከል ከፍተኛ ውጥረት እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል

      ቻይና፤ አሜሪካ ከዚህ በኋላ ጸብ አጫሪ ድርጊት ከፈጸመች ምላሽ ለመስጠት መዘጋጀቷን የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታወቀ፡፡

      የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው መግለጫ ዋሸንግተን በቻይና ብሔራዊ ጥቅም ላይ ያነጣጠረ ጸብ አጫሪ ድርጊት ከፈጸመች እንደማይታገስ ገልጿል፡፡ የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ዋንግ ዌንቢን ዛሬ በመግለጫቸው አሜሪካ፤ ቻይናን ለመያዝ ታይዋንን ከመጠቀም እንድትቆጠብ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል፡፡ 

      የቻይና ባለስልጣናት አሜሪካ ፤ ታይዋንን በመጠቀም፣ የቤጅንግ ብሔራዊ ጥቅም እየጎዳች መሆኑን በተደጋጋሚ እየገለጹ ናቸው፡፡ ቃል አቀባይ ዋንግ ዌንቢንም ይህንኑ ሃሳብ በዛሬ ድጋሚ አንስተውታል፡፡ የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ፤ የናንሲ ፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት ጸብ አጫሪ መሆኑን ገልጸው፤ ከዚህ በኋላ ግን ለጸብ የሚያነሳሳ ድርጊት ከዋሸንግተን ከመጣ ቻይና አጸፋውን ለመመለስ መዘጋጀቷን ተናግረዋል፡፡ 

      ቻይና ከአሜሪካ ጋር የነበራትን ወታደራዊ ትብብር ማቋረጧን ተከትሎ ዋሸንግተን ድርጊቱን አውግዛ ነበር፡፡ ቤጅንግ ግን ሁሉንም እርምጃዎች የወሰደችው አሜሪካ ጸብ አጫሪ ድርጊትን ከፈጸመች በኋላ በመሆኑ የወሰደቻቸው እርምጃዎች ሚዛዊና ትክክል መሆናቸውን ገልጻለች፡፡

      ቻይና እና ከአሜሪካ ጋር ወታደራዊ ትብብርን ጨምሮ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያም ንግግርና ውይይት የነበራት ቢሆንም በፔሎሲ ጉብኝት ምክንያት ሁሉንም ላለማድረግ ውሳኔ ማሳለፏን ማሳወቋ ይታወሳል፡፡ 

      ከዚህ ባለፈም የፕሬዝዳንት ዢ ሺን ፒንግ አስተዳደር፤ ሀገሪቱ ከአሜሪካ ጋር የነበራትን የድንበር አልባ ወንጀል መከላከል፣ ስደተኞችን የማጓጓዝ፣ አደገኛ ዕጽ ዝውውር መከላከል እና ሌሎች ስምንት የትብብር መስኮችን ማቋረጡን ገልጿል፡፡

      ቻይናና አሜሪካ በዓለም አቀፍ ደረጃ የበላይነትን ለማስፈን ከሚደረግ ሽኩቻ ባለፈ በንግድና ኢኮኖሚ ላይ ያተኮረ እሰጥ አገባ የነበራቸው ቢሆንም ታይዋን ግን የሀገራቱን ግብ ግብ የበለጠ እንዲካረር አድርጋዋለች ተብሏል፡፡ 

      News today, Politics

      ትራምፕ በተጠረጠሩበት የማጭበርበር ድርጊት ምርመራ ላይ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች “መልስ አልሰጥም” አሉ

      ትራምፕ በተጠረጠሩበት የማጭበርበር ድርጊት ምርመራ ላይ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች “መልስ አልሰጥም” አሉ
      “በዙሪያየ ያሉ ሰዎች ሁሉ ኢላማ ሲደረጉ ዝም ከማለት “ምንም አማራጭ አል

      የኒውዮርክ አቃቤ ህግ ዶናልድ ትራምፕ የሚያስተዳድሩትን ተቋም የግብር እና ብድር እፎይታ ለማግኘት በሚል ” የሚያሳስት እና ያልተገባ የንብረት ግምገማ” በማድረግ አጭበርብረዋል ሲል መክሰሱ የሚታወቅ ነው፡፡

      በዚህም መሰረት ኒውዮርክ ወደ ሚገኘው ፍርድ ቤት የቀረቡት ዶናልድ ትራምፕ በተጠረጠሩበት የማጭበርበር ድርጊት መሰረት ምርመራ ላይ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች “መልስ አልሰጥም” ማለታቸው ተሰምቷል፡፡

      ትራምፕ ጉዳዩን በማስመልከት በሰጡት መግለጫ “በአሜሪካ ህገ መንግስት ለእያንዳንዱ ዜጋ በተሰጡት መብቶች መሰረት፤ ጥያቄዎች ለመመለስ ፈቃደኛ አልሆንኩም”ብለዋል።

      ትራምፕ መልስ ላለመስጠታቸው “ቤተሰብ፣ ድርጅት እና በዙሪያየ ያሉ ሰዎች ሁሉ የፖለቲካ ፍለጎት ባላቸው ጠበቆች፣ በዐቃብያነ-ህግ የሚደገፉ የሀሰት ዜና የሚያሰራጩ ሚድያዎች ዒላማ ሲሆኑ፣ ምንም አማራጭ አልነበረኝም” የሚል ምክንያት ማቅረባቸውም ነው ፍራንስ-24 የዘገበው፡፡

      በፍሎሪዳ የሚገኘውን የአሜሪካ የፌዴራል የምርመራ ቢሮ (ኤፍ.ቢ.አይ) ከቀናት በፊት የዶናልድ ትራምፕ መኖሪያ ቤትመበርበሩ የሚታወስ ነው፡

      ፍተሻው ዶናልድ ትራምፕ ምናልባትም በደጋፊዎቻቸው ከተፈጸመው የካፒቶል ሂል ጥቃት ጋር በተያያዘ ከቤተ መንግስት ያሸሹት ሚስጥራዊ ሰነድ ይኖር ይሆን በሚል የተካሄደ ነው መሆኑን ሲ.ኤን.ኤን ዘግቧል፡፡

      ትራምፕ ኒውዮርክ በሚገኘው ህንጻቸው ላይ ሳሉ ነው መኖሪያቸው የተፈተሸው።

      “ማር-ኤ-ላጎ የሚገኘው ቅንጡ መኖሪያ ተከቦ ነው የሚገኘው፤ በብዙ የኤፍ.ቢ.አይ ፖሊሶች ተወርሮም ይገኛል” ሲሉም ነበር ዶናልድ ትራምፕ ሶሻል ትሩዝ በተሰኘ ማህበራዊ ሚዲያቸው በወቅቱ ያስታወቁት።

      ድርጊቱ በቀጣዩ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ (2024) እንዳይወዳደሩ ለማድረግ በማሰብ የተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል።

      K^አወዛጋቢው ዶናልድ ትራምፕ በፈረንጆቹ 2024 በሚካሄደው ምርጫ ለመወዳደር ፍላጎት እንዳላቸው ፍንጭ መስጠታቸው አይዘነጋም፡፡

      News today, Politics

      የቻይና ጦር በታይዋን ዙሪያ ሲያካሂድ የነበረውን ወታደራዊ ተልዕኮ ማጠናቀቁን አስታወቀ


      “ለውጊያ ሙሉ በሙሉ ዝግጁ ለመሆን” ያለመው ልምምድ እንደሚቀጥል የቻይና ጦር አስታውቋል

      ቻይና በታይዋን ዙሪያ ስታካሂዳቸው የነበሩትን የተለያዩ ወታደራዊ ተልዕኮዎችን ማጠናቀቋን አስታወቀች።

      የቻይና ጦር፤ “አሁን ያለው ሁኔታ በታይዋን የባህር ዙሪያ ያለውን ለውጥ በቅርበት መከታተል ይፈልጋል” ሲል አሳስቧል።

      ቻይና ከአሜሪካ ጋር ወታደራዊ ትብብሯን አቋረጠች
      የቻይና የጦር ልምምድ ትናንት ይጠናቀቃል ቢባልም ልምምዱ እንደቀጠለ ነው
      ጦሩ “ለውጊያ ሙሉ በሙሉ ዝግጁ ለመሆን” ወታደራዊ ልምምድ ማድረጉን እንደሚቀጥል መጠቆሙም ቻይና ደይሊ ግሎባል ታይምስ ዘግቧል።

      የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ በታይዋን ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ፤ በሩቅ ምስራቅ የነገሰው ውጥረት እንደቀጠለ ነው።

      አፈ ጉባኤዋ ባሳለፍነው ሳምንት ታይዋንን የጎበኙ ሲሆን ድርጊቱ ቻይናን እንዳስቆጣ የዓለም ብዙሀን መገናኛዎች ዘግበዋል።

      ይሄንን ተከትሎም ቻይና በታይዋን ባህር ዙሪያ ለቀናት የሚዘለቅ ወታደራዊ ልምምድ በማድረግ ላይ መሆኗን አሳውቃ ነበር።

      ቻይና ባሳለፍነው ሳምንት ልምምድ ላይ ዶንግ ፋንግ የተሰኘው የቻይና የረጅም እና አጭር ርቀት ባልስቲክ ሚሳኤሎች ወደ ታይዋን ባህር ተኩሳ እንደነበርም ሚታወስ ነው።

      በታይዋን ስድስት አቅጣጫዎች ምንም አይነት የባህር እና አየር ላይ ትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንዳይኖር ቻይና አስቀድማ ማስጠንቀቋ ይታወሳል።

      በቻይና ድርጊት ከፍተኛ ስጋት ውስጥ የገባቸው ታይዋን በበኩሏ ቻይና “ለወረራ እየተዘጋጀች” መሆኑን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በመናገር ላይ ናት፡፡

      የታይዋን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆሴፍ ዉ ቻይና “ለወረራ ለመዘጋጀት” የሚያስችላት ወታደራዊ ልምምድ እያደረገች መሆኗን መግለጻቸው ኤኤፍፒ ማክሰኞ እለት ዘግቧል፡፡

      ጆሴፍ ው የቻይናን የሶሞኑ ወታደራዊ እንቅስቀሴ በማስመልከት በታይፔ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፤ ቤጂንግ በእስያ-ፓሲፊክ አካባቢ ያለውን ሁኔታ ለመቀየር እየሰራች ነው ብለዋል።

      ቻይና፤ አሜሪካ የሚመጡትን “ከባድ መዘዞች መቻል ይኖርባታል” ስትል ዛተች
      የቤጂንግ የጦርነት ጨዋታ “የታይዋንን መብት የሚጻረር” እና በታይዋን ዙሪያ ያለውን ውሃ እና ሰፊውን የእስያ-ፓሲፊክ ቀጠናን ለመቆጣጠር የተደረገ ሙከራ ነው” ብለዋል ጆሴፍ ው።

      ቤጂንግ የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ ታይዋንን የሚጎበኙ ከሆነ ጦሯ “ዝም ብሎ እንደማይቀመጥ” ስታስጠነቅቅ መቆየቷ የሚታወስ ነው፡፡

      እናም በምስራቅ ታይዋን የባህር አከባቢ የተፈጠረው ውጥረት ወዳልተፈለገ የጦር መማዘዝ እንዳያመራ ተሰግቷል።

      News today, Politics

      ኢዜማ የመንግስት ተሿሚ አባላቱ በያዙት ኃላፊነት እንዲቀጥሉ መወሰኑን አስታወቀ

      ዶ/ር ኦንጋይ ኦዳን የደቡብ ክልል የኢዜማ የመሪ ክንፍ ተጠሪ ሆነው እንዲሰሩም ወስኗል
      የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በመንግስት የተሾሙ አመራርና አባላቱ በተረከቡት ስልጣን ይቀጥሉ ሲል ወሰነ።
       ፓርቲው በፌስቡከ ገጹ ባወጣው መግለጫ ወሳኔው በአርባ ምንጭ ከተማ ለሁለት ቀናት ተሰብስበው በነበሩት የፓርቲው መሪ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) እና የፓርቲው ሊቀመንበር ጫኔ ከበደ (ዶ/ር) እና ሌሎችም የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች የተሰጠ ነው።


      ከስብሰባቸው ጎን ለጎን ከፌደራል እስከ ወረዳ ባሉ የመንግስት መዋቅሮች ተካተው ሕዝብን በማገልገል ላይ ከሚገኙ የፓርቲው አመራሮችና አባላት ጋር በሥራ አፈጻጸም እና በአደረጃጀት ጉዳዮች ላይ የተወያዩት ከፍተኛ አመራሮቹ ጉዳዩን የተመለከተ ውሳኔ አሳልፈዋል።
      በውሳኔው መሰረትም መንግስት አብሮ ለመሥራት ያቀረበውን ጥሪ ተከትሎ በመዋቅሩ ተካተው ሥልጣን ተረክበው ሕዝብን በማገልገል ላይ የሚገኙ የኢዜማ አባላት አርአያ መሆን የሚችሉ ስለሆኑ በኃላፊነታቸው እንዲጥሉ መደረጉን መግለጫው ጠቅሷል፡፡


      በመልካም ሥነምግባር የታነጹ፣ ሌብነትን የሚጸየፉ፣ በሥራ ትጋታቸው እና በአፈጻጸም ብቃታቸው የተመሠከረላቸው እና አርአያ መሆናቸውን እንዲቀጥሉም ማሳሰብያ ተሰጥቷል እንደ ፓርቲው ገለጻ።
      የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች በስብሰባቸው በደቡብ ክልል በመንግስት መዋቅር ውስጥ ስለተካተቱ አባላት አደረጃጀት እና ተጠሪነት የመከሩም ሲሆን ኦንጋይ ኦዳ (ዶ/ር) በደቡብ ክልል የኢዜማ የመሪ ክንፍ ተጠሪ ሆነው እንዲሰሩ መወሰናቸው ተገልጿል፡፡
      ኢዜማ በመጀመርያ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤው ከመንግስት የቀረበውን የአብረን እንስራ ጥሪ ተቀብሎ መንግስት ለከፍተኛ አመራሮቹ ጭምር የሰጠውን ሹመት መቀበሉ ይታወሳል።


      በዚህም የፓርቲው መሪ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በፌዴራል መንግስት ካቢኔ ውስጥ ተካተው በትምህርት ሚኒስትርነት ሲሾሙ፤ የፓርቲው የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ካቢኔ ተካተው የአስተዳደሩ የኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ሆነው ተሾመው በማገልገል ላይ ናቸው።
      በደቡብ ክልል የመንግስት መዋቅር ውስጥ የተካተቱ የድርጅቱ አባላትም አሉ።


      ሆኖም ይህ ኢዜማ የበለጠ እንዲዳከምና “የመንግስት ተለጣፊ” ሆኖ እንዲታይ አድርጎታል የሚሉ ወቀሳዎች ከራሱ ከፓርቲው ሰዎች ጭምር እንዲሰነዘሩ ምክንያት ሆኗል።
      ጉዳዩ፤ የፓርቲው አቋምና አካሄድ ጭምር በፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ሳይቀር የልዩነት ምንጭ ሆኖ ፓርቲውን አመራር ለመቀየር እስከሚያስችል ምርጫ እስከማካሄድ አድርሶት እንደነበር ይታወሳል።


      ይህን ተከትሎ የፓርቲው አንደኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ሰኔ 26 ቀን 2014 ዓ.ም ባደረገው ምርጫ ፕ/ር ብርሀኑ ነጋን እና አርክቴክት ዮሐንስ መኮንንን መሪ እና ምክትል መሪ አድርጎ መምረጡ የሚታወስ ነው፡፡

      News today, Politics

      አሜሪካ የአልሻባብ ተዋጊዎችን ኢላማ ያደረገ የአየር ጥቃት መፈጸሟ ተነገረ

      የአልሻባብ ታጣቂዎች

      ከ 5 ሰአት በፊት

      የአሜሪካ ጦር በሶማሊያ ማዕከላዊ ሒራን ክልል በአልሻባብ ተዋጊዎች ላይ የአየር ጥቃት መፈጸሙን የሶማሊያ መንግሥት መገናኛ ብዙኃን ዘገበ።

      መገናኛ ብዙኃኑ እንዳለው ጥቃቱ የተፈፀመው የሶማሊያ መንግሥት ጥያቄ ማቅረቡን ተከትሎ ነው።

      የአየር ድብደባ ስለመፈፀሙ ግን የአሜሪካ እና አፍሪካ ወታደራዊ ዕዝ አስተያየት አልሰጠም።  

      የአሜሪካ ባለሥልጣናት በሰኔ እና በሐምሌ ወር በተፈፀሙ ሁለት የአየር ድብደባዎች ሰባት የጂሃዲስት ቡድኑ ተዋጊዎች መገደላቸውን መናገራቸው ይታወሳል።

      ከቅርብ ወራት ወዲህ አልሻባብ በመንግሥት ኢላማዎች ላይ የሚፈጽመው ጥቃት የጨመረ ሲሆን በቅርቡም ድንበር በመሻገር በኢትዮጵያ ደንገተኛ ጥቃት ፈጽሟል።

      አሜሪካ ከዚህ ቀደም በተለያዩ ጊዜያት በአል ሻባብ ቡድን ላይ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን በሰው አልባ አውሮፕላኖች ስትፈጽም ቆይታለች።

      በተለይም የቡድኑን አመራሮች ኢላማ በማድረግ በፈጸመቻቸው ጥቃቶች ከፍተኛ መሪዎቹን ጨምሮ በርካታ የቡድኑ አባላትን መግደሏ መዘገቡ ይታወሳል።

      ሐምሌ 13/2014 ዓ.ም እስላማዊ ታጣቂዎቹ ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ጋር በምትዋሰንባቸው የድንበር ከተሞች የከፈቱትን ጥቃት ተከትሎ ከባድ ውጊያ ተካሂዶ ነበር።

      ከአልቃኢዳ ጋር ግንኙነት አለው የሚባለው አልሻባብ ጥቃቱን የፈፀመው ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ጋር በምትዋሰንበት ግዛት በኩል በሚገኙት ዬድ እና አቶ ላይ ነው።

      ከኢትዮጵያ ጋር በሚዋሰኑት የሶማሊያ ድንበር አካባቢዎች ነበሩ በተባሉ የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ አባላት ጋር በተካሄደው በዚህ ከባድ ውጊያም በሁለቱም ወገን ጉዳት መድረሱን የአካባቢው ነዋሪዎች እና ባለሥልጣናት ተናግረዋል።

      የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ ዑመርም እስላማዊ ታጣቂ ቡድኑ የከፈተውን ጥቃት የኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች መክተው መመለሳቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል።

      የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫ ድንበር ተሻግረው ጥቃት ከሰነዘሩት የአልሻባብ አባላት መካከል ከ800 በላይ የሚሆኑ መገደላቸውንና በርካቶች መማረካቸውን ገልጿል።

      ቀደም ሲልም የኢትዮጵያ ሠራዊት በቡድኑ ላይ ወሰዳቸው ወታደራዊ እርምጃዎች በአሜሪካ በጥብቅ ሲፈለግ የነበረ ግለሰብን ጨምሮ ሦስት ከፍተኛ የአልሻባብ ከፍተኛ አመራሮችን መግደሉን አሳውቋል።

      በተያያዘ ዜና የአልሻባብ ታጣቂ ቡድን የቀድሞ መሪ የሆነው ሙክታር ሮቦው አዲስ በተቋቋመው ካቢኔ ውስጥ የሶማሊያ የሃይማኖት ጉዳዮች ሚኒስትር በመሆን ባለፈው ሳምንት ተሹመዋል።

      የእርሳቸው ሹመትም የአል ሸባብን ጽንፈኛ ርዕዮተ ዓለም ለመመከት የተደረገ ሙከራ እንደሆነ ተደርጎ ይወሰዳል።

      News today, Politics

      የዩክሬን ጦርነት “ክሬምያን ነጻ በማውጣት” መጠናቀቅ አለበት -ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪ


      ዘሌንስኪ ‘‘በክሬምያ የተጀመረው ጦርነት፤ ክሬምያን ነጻ በማውጣት መጠናቀቅ አለበት” ብለዋል
      የዩክሬን አካል የነበረቸው ክሬምያ እንደፈረንጆቹ 2014 በተካሄደው ህዝበ ውሳኔን ወደ ሩሲያ መቀላቀሏ የሚታውስ ነው

      የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘሌንስኪ፡የዩክሬን ጦርነት ክሬምያን ነጻ በማውጣት መጠናቀቅ አለበት አሉ፡፡

      ዘለንስኪ በሰጡት መግለጫ ‘‘ክሬምያ ዩክሬናዊት ናት፤ አንተዋትም’’ ሲሉም ተደምጠዋል፡፡

      የዩክሬን አካል የነበረቸው ክሬምያ፤ እንደፈረንጆቹ 2014 የተካሄደውና በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ተቀባይነት ያላገኘው ህዝበ ውሳኔን ተከትሎ ወደ ሩሲያ መቀላቀሏ የሚታውስ ነው፡፡

      በርካታ ዩክሬናውያን አሁን ላይ ከሩሲያ ጋር እየተደረገ ያለው ጦርነት የተጀመረው ያኔ ክሬምያ ወደ ሩሲያ ስትሄድ ነበር ብለውም ያምናሉ፡፡ይህ በእንዲህ እንዳለ በትናንትናው እለት በክሬምያ ሳኪ ተብሎ በሚታወቅ የሩሲያ ወታደራዊ ማዕከል ከባድ ፍንዳታ እንዳጋጠመ እየተነገረ ነው፡፡

      ሩሲያ፤ ባይረጋገጥም ጥቃቱን የፈጸመችው ዩክሬን ከሆነች መዘዙ ከባደ ነው ስትል ማስጠንቅቋ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

      ስለ ፍንዳታው ከመናገር የተቆጠቡት ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪ ግን፤ አሁንም ክሬምያ ተመልሳ የዩክሬን ግዛት መሆኗ የማይቀር እንደሆነ በመዛት ላይ ናቸው፡፡

      ‘‘ የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት የተጀመረው በክሬምያ ነው፤ መጠናቀቅ ያለበትም በክሬምያ ነው….ነጻ ሆና’’ም ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ፡፡

      ክሬምያን ወደ ዩክሬን የመመለስ ፍላጎት የሚያመላክተው የፕሬዝዳንቱ ንግግር፤ ከዚህ በፊት ይሉት ከነበረ የተለየ ይዘት ያለው እንደመሆኑ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡

      ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪ በወርሃ የካቲት 21 ቀን፤2022 በሰጡት መግለጫ ሩሲያ የተቆጣጠረቻቸው ግዛቶች ለቃ ከወጣች ዩክሬን ሰላም እንደምትቀበልና “ክሬምያ ቅድመ ሁኔታ እንደማትሆን” መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

      News today, Politics

      ሩሲያ ‘ካያም’ የተሰኘችውን የኢራን ሳተላይት ወደ ህዋ አመጠቀች


      ሳተላይቷ የመጠቀችው ከደቡብ ከዛኪስታን ነው

      አሜሪካ፤ ኢራን በሳተላይቷ በእስራኤል እና በሌላው አለም ወታደራዊ ኢላማ ለመለየት ያስችላታል የሚል ፍርሃት አላት

      ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና ጠቅላይ መሪ የሆኑት አያቶላ አሊ ካሜኔ በጋራ ለመስራት ቃል ከገቡ ከሶስት ሳምንታት በኋላ ሩሲያ የኢራንን ሳተላይት በትናንትናው እለት ከደቡብ ካዛኪስታን ወደ ምህዋር አምጥቃለች፡፡

      ሩሲያ ሳተላይቷን ያመጠቀችው ሁለቱ መሪዎች ምእራባውያንን በጋራ ለመመከት ከተስማሙ በኋላ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

      ኢራን የእስራኤልን የስለላ ኔትወርክ መያዟን አስታወቀች
      በ11ኛው ክፍለ ዘመን በፋርስ ገጣሚ እና ፈላስፋ ኦማር ካያም ስም የተሰየመችው የሪምት ካያም ሴንሲንግ ሳተላይት በሩሲያዋ ሶዩዝ ሮኬት ነው የተመነጨፈችው፡፡ በካዛኪስታንከሚትገኘው የሩሲያ ባይኮኑር ኮስሞድሮም የተወነጨፈችው ሳተላይቷ በተሳካ ሁኔታ ወደ ኦርቢት መግባቷን የሩሲያ ስፔስ ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡

      የኢራን ስፔስ ኤጀንሲ የመጀመሪያ የሆነው ቴሌሜታሪ ዳታ ከሳተላይት መቀበሉን የአራን ዜና አገልግሎት(ኢርና) ዘግቧል፡፡

      ቴህራን፤ ሩሲያ ሳተላይቷን ከዩክሬን ጋር ለምታደርገው ጦርነት የሚጠቅም መረጃ ለመብሰብ ትጠቀምባታለች የሚለውን ክስ ውድቅ አድርጋለች፡፡ ኢራን ሳተላይቷን ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ሙሉ በሙሉ እንደምትቆጣጠር ገልጻለች፡፡

      የአሜሪካውን የዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣን ጠቅሶ እንደዘገበው የአሜሪካ ባለስልጣናት በሩሲያ እና በኢራን መካከል ያለው የስፔስ ትብብር አሳስቧታል፤ ምክንያቱም ሳተላይቷ ሩሲያ በዩክሬን የምታደርገውን ጦርነት መርዳት ብቻ ሳይሆን በእስራኤል እና በሌላው አለም ወታደራዊ ኢላማ ለመለየት ታስችላለች የሚል ፍርሃት አላት፡፡

      Politics

      ባይደን፤ ፊንላንድ እና ስዊድን ኔቶን ለመቀላቀል ያቀረቡትን ጥያቄ በፊርማቸው አጸደቁ

      ባይደን የአሜሪካ ኮንግረስ ከወር በፊት አሳልፎት የነበረውን የውሳኔ ሃሳብ ነው ያጸደቁት

      2022/8/10 6:11 GMT

      የሀገራቱን ጥያቄ የደገፉ የኔቶ አባል ሃገራት ቁጥር 23 ደርሷል

      የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን፤ ፊንላንድ እና ስዊድን ኔቶን ለመቀላቀል ያቀረቡትን ጥያቄ በፊርማቸው አጸደቁ፡፡

      ባይደን የአሜሪካ ኮንግረስ ከወር በፊት አሳልፎት የነበረውን የውሳኔ ሃሳብ ነው ያጸደቁት፡፡

      የሁለቱ የኖርዲክ ሃገራት ኔቶን መቀላቀል ጥምረቱን የበለጠ እንደሚያጠናክረው ነው ባይደን የተናገሩት፡፡

      ፕሬዝዳንቱ ጠንካራ የዲሞክራሲ፣ ወታደራዊ ተቋማት ባለቤት ናቸው ያሏቸውን ፊንላንድን እና ስዊድንን ግልጽና ጠንካራ ምጣኔ ሃብትን ለመገንባትም ችለዋል በሚል አሞግሰዋቸዋል፡፡

      የ76 ዓመቱ አዛውንት በቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የስልጣን ዘመን ስለመላላቱ የሚነገርለትን የአሜሪካንና የአጋሮቿን ግንኙነት መልሶ ለማጠናከር እንደሚሰሩ ቃል በመግባት ነበር ወደ ስልጣን የመጡት፡፡

      የአሜሪካ ደህንነት መሰረት ነው ሲሉም ኔቶን አሞካሽተዋል፡፡ ሃገራቸው በአትላንቲክ ቀጣና ለሚኖራት ጥምረት ያላትን ቁርጠኝነትንም ገልጸዋል፡፡

      የሰሜን አትላንቲክ ቃልኪዳን ጦር (ኔቶ) አባል ለመሆን የሚጠይቁ አዳዲስ ሃገራት የጥምረቱን አባል ሃገራት ሙሉ ድጋፍ ማግኘት አለባቸው፡፡

      ሩሲያ በዩክሬን ጦርነት መጀመሯን ተከትሎ የኪቭ እጣ ፋንታ ሊገጥመን ይችላል በሚል ኔቶን ለመቀላቀል የጠየቁት ፊንላንድ እና ስዊድንም ከ30ዎቹ የጥምረቱ አባል ሃገራት የ23ቱን የተረጋገጠ ድጋፍ ማግኘታቸውን ፍራንስ 24 ዘግቧል፡፡

      የኔቶን በአትላንቲክ ቀጣና መስፋፋት አጥብቃ ስትቃወም የነበረችው ሩሲያ ፊንላንድ እና ስዊድን ኔቶን መቀላቀላቸው ያን ያህል ስጋት እንዳይደለ ብትገልጽም ከበድ ያለ የአጸፋ ምላሽን ልትሰጥ እንደምትችል ግን ማስጠንቀቋ ይታወሳል፡፡

      News today, Politics

      ተመድ በእስራኤል-ጋዛ ጉዳይ አስቸኳይ ስበሰባ አደረገ


      ድርጅቱ ተኩስ አቁሙ እምብዛም አስተማማኝ እንዳይደለ አስታውቋል
      የማይከበር ከሆነ የከፋ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችልም ነው ያስጠነቀቀው

      የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) በእስራኤል እና በእስላማዊ ጂሃድ ታጣቂዎች መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት መጣሱን ተከትሎ አስቸኳይ ስበሰባ አደረገ፡፡

      ስብሰባው በድርጅቱ የጸጥታው ምክር ቤት የተደረገ ነው፡፡

      የድርጅቱ የመካከለኛው ምስራቅ ልዩ መልዕክተኛ ተኩስ አቁም ቢደረግም እምብዛም አስተማማኝ አለመሆኑን በመጠቆም ሁለቱ አካላት ዳግም ወደ ግጭት የሚገቡ ከሆነ ጉዳቱ ሊከፋ ይችላል ሲሉ በስብሰባው ተናግረዋል፡፡

      ሁለቱም ወገኖች አጸፋዊ ምላሽ ሊሰጡ የሚችሉበት ሁኔታ መኖሩ ሁኔታዎችን የበለጠ ሊያከፋ እንደሚችልም ነው ልዩ መልዕክተኛው የተናገሩት፡፡

      መፍትሔዎችን ለመፈለግ የሚደረጉ ጥረቶችን ሊያወሳስብ ይችላልም ብለዋል፡፡

      እስራኤል ካሳለፍነው አርብ ጀምሮ በነበሩ ተከታታይ ሶስት ቀናት ዒላማ ባደረገቻቸው የታጣቂዎቹ ይዞታዎች ከባድ ድብደባዎችን ፈጽማለች፡፡ ታጣቂዎቹም በመልሱ 1100 ገደማ ሮኬቶችን አስወንጭፈዋል፡፡ በዚህም 15 ህጻናትን ጨምሮ 44 ሰዎች ሲገደሉ 360 ሰዎች መቁሰላቸው ተነግሯል፡፡

      ሆኖም ከተተኳሾቹ 20 በመቶ ያህሉ በተለያዩ የጋዛ ሰርጥ አካባቢዎች መውደቃቸውን ነው ልዩ መልዕክተኛው ቶር ውንስላንድ በድንገት ለተሰበሰው ምክር ቤት የተናገሩት፡፡

      እስራኤል ከየትኛውም አቅጣጫ የሚወነጨፉ ሮኬቶችንና ሌሎች ተተኳሾችን ለማምከን የሚያስችል አይረን ዱምን መሰል ዘመናዊ መሳሪያዎችን መታጠቋን ማስታወቋ ይታወሳል፡፡

      የእስራኤልን የደህንነት ስጋት ያነሱት ልዩ መልዕክተኛው ታጣቂዎቹ ተመጣጣኝ እርምጃዎችን ከመውሰድ ይልቅ ሮኬቶችን ማስወንጨፋቸውን ኮንነዋል፡፡

      በተመድ የእስራኤል አምባሳደር ጊላድ ኤርዳን ታጣቂዎቹ በንጹሃን መካከል በመሸሸግ ወደ ንጹህ እስራኤላውያን መተኮሳቸውን በማውገዝ ሙሉ ኃላፊነቱን ሊወስዱ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

      የአሜሪካ ተወካይ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድም ቢሆኑ እስራኤል ዜጎቿን ከአሸባሪዎች ጥቃት የመጠበቅ መብት አላት ብለዋል፡፡

      ሆኖም በድርጅቱ የፍልስጤም አምባሳደር ሪያድ መንሱር የእስራኤል ድርጊት ወረራ ነው በሚል ጥቃቱን ተቃውመዋል፡፡ ስንት ንጹሃን እስኪገደሉ ነው በሚልም ተመድ በቃ እንዲል ጠይቀዋል፡፡

      ለሶስት ተከታታይ ቀናት የዘለቀው ውጊያ በግብጽ አግባቢነት ለጊዜው እንዲቆም ስምምነት ላይ መደረሱ ይተቃወሳል፡፡

      News today, Politics

      ታይዋን፤ ቻይና “የእስያ-ፓሲፊክ ቀጠናን ለመቆጣጠር እየሰራች ነው” አለች


      ታይዋን ቻይና “ለወረራ ለመዘጋጀት” የሚያስችላት ወታደራዊ ልምምድ እያደረገች መሆኗን ገለጸች
      ጆ ባይደን አሜሪካ ታይዋንን ከቻይና ወረራ ለመጠበቅ “ኃይል ልትጠቀም እንደምትችል” መግለጻቸው ይታወሳል

      በአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት የተበሳጨችው ቤጂንግ፤ የጦር አውሮፕላኖቿንና መርከቦቿ በታይዋን ላይ ጥቃት ለመሰንዘር የሚያስችላት ወታደራዊ ልምምድ በማድረግ ላይ መሆናቸው የእየተነገረ ነው፡፡

      በዚህ ስጋት የገባቸው የታይዋን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆሴፍ ዉ ቻይና “ለወረራ ለመዘጋጀት” የሚያስችላት ወታደራዊ ልምምድ እያደረገች መግለጻቸውን ኤኤፍፒ ዘግቧል፡፡
      ጆሴፍ ዉ፡ የቻይናን የሶሞኑ ወታደራዊ እንቅስቀሴ በማስመልከት በታይፔ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ፤ቤጂንግ በእስያ-ፓሲፊክ አካባቢ ያለውን ሁኔታ ለመቀየር እየሰራች ነውም ብለዋል፡፡

      “የቻይና እውነተኛ አላማ በታይዋን የባህር ዳርቻ እና በጠቅላላው አካባቢ ያለውን ሁኔታ መለወጥ ነው”ሲሉም ተናግረዋል፡፡

      “ቻይና ልምምዱን እና ወታደራዊ መጫወቻ ደብተሩን ለታይዋን ወረራ ለማዘጋጀት ተጠቅማበታለች” በማለትም ቤጂንግን የከሰሱት ከሰዋል ጆሴፍ ዉ፤በተጨማሪም የታይዋን የህዝብን ሞራል ለማዳከም መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ልምምዶችን እና የሚሳዔል ጥቃቶችን እንዲሁም የሳይበር ጥቃትን፣ የሀሰት መረጃ ዘመቻን እና ኢኮኖሚን የማዳከም ስራ እየሰራች ነው ሲሉም አክለዋል፡፡

      የዉ ጋዜጣዊ መግለጫ የመጣው የታይዋን ጦር በደሴቲቱ ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለመከላከል የራሱን ወታደራዊ ልምምድ ማድረግ ከጀመረ በኋላ መሆኑ ነው።

      ጆሴፍ ዉ፡ የቤጂንግ የጦርነት ጨዋታ “የታይዋንን መብት የሚጻረር” እና በታይዋን ዙሪያ ያለውን ውሃ እና ሰፊውን የእስያ-ፓሲፊክ ቀጠናን ለመቆጣጠር የተደረገ ሙከራ ነው”ም ብለውታል።

      የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጆሴፍ ዉ፤ የምዕራባውያን አጋሮችን ቻይናን መቃወማቸውንም አመስግነዋል።

      “የተቀረው ዓለም አቋም ዴሞክራሲ ለአምባገነንነት ዛቻ እንደማይንበረከክ ለዓለም ግልጽ መልእክት ያስተላለፈ ነው”ም ብለዋል፡፡

      ቤጂንግ፤ የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ ታይዋንን የሚጎበኙ ከሆነ ጦሯ “ዝም ብሎ እንደማይቀመጥ” ስታስጠነቅቅ መቆየቷ የሚታወስ ነው፡፡

      እናም በምስራቅ ታይዋን አከባቢ የተፈጸረው ውጥረት ወዳልተፈለገ የጦር መማዘዝ እንዳያመራ ተሰግቷል፡፡

      ይህ በእንዲህ እንዳለ አሜሪካ፤ ታይዋንን ከቻይና ወረራ ለመጠበቅ ኃይል ልትጠቀም እንደምትችል ፕሬዝዳንት ጆ-ባይደን ከወራት በፊት በጃፓን ጉብኝታቸው መግለጻቸው አይዘነጋም፡፡

      ጆ-ባይደን “ቻይና ታይዋንን በተመለከተ ኃይል የምትጠቀም ከሆነ እኛም መጠቀማችን አይቀርም” ነበር ያሉት፡፡

      News today, Politics

      የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፤ “አፍሪካ ምን መምረጥ እንዳለባት አሜሪካ አታዝም” አሉ


      “በአፍሪካ ለታየው ዋጋ ንረት ምክንያት ምዕራባውያን በሩሲያ ላይ የጣሉት ማዕቀብ ነው” የሚለውን ክስ ብሊንከን ውድቅ አደረጉ
      የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን፤ አፍሪካ ምን መምረጥ እንዳለባት አሜሪካ “አታዝም” አሉ።

      ሩሲያን ከዓለም ለመነጠል ያለመ በተባለው የአፍሪካ ጉብኝት ላይ የሚገኙት አንቶኒ ብሊንከን፤ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው ከሰሃራ በታች ላሉ የአፍሪካ ሀገራት ይበጃል ያሉትን አዲስ የስትራቴጂ ሰነድ አቅርበዋል።

      የአሜሪካ ውጪ ጉዳይ ሚንስቴር አንቶኒ ብሊንከን የአፍሪካ ጉብኝታቸውን ጀመሩ
      ብሊንከን ባቀረቡት ጽሁፍ፡ የአፍሪካ ሀገራት ለገዛ እድገታቸው የሚታገሉ ሳይሆን የሌሎች መሳሪያ እንደሆኑ ተደረገው ሲታዩ መቆየታቸውም አንስተዋል።

      “የአፍሪካ ሀገራት ከህዝቦቻቸው ፍላጎት ውጭ በሆነ መልኩ፤ የዓለም ኃያላን ፉከክር በሚያደርጉበት ጉዳይ ላይ አቋም እንዲይዙ ሲነገራቸው ነበር” ነው ያሉት ብሊንከን።
      እንደ ሮይተርስ ዘገባ ብሊንከን፤ ሀገራቸው አሜሪካ መሰል ጫና እንደማትደገፍ የገለጹ ሲሆን፤ አሜሪካ አሁንም ቢሆን በአፍሪካ ቅድሚያ ሰጥታ የምትሰራባቸው ጉዳዮች ቢኖሩ “ዴሞክራሲ፣ ሰላም እና ጸጥታ” ናቸው ብለዋል።

      አንቶኒ ብሊንከን፤ በዛሬው እለት ምርጫ በማካሄድ ላይ ያለችውን ኬንያ አንስተው ሲናገሩም፤ “አፍሪካ ችግሮች ያሉባት፤ አሜሪካ ደግሞ መፍትሄ ሰጪናት” ብለው እንደማያስቡ ፤ ነገር ግን በጋራ በመሆን ችግሮችን ለመፍታት ለሚደረጉ ጥረቶች አሜሪካ እውቅና እንደምትሰጥ አስረድተዋል።

      የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በሊቢያ፣ ማሊ እና ማእከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ስለሚገኙና የ“ዋግነር” ቡድን በመባል ስለሚታወቁ የሩሲያ ቅጥረኛ ወታደሮች ያላቸው አስተያየትም ሰንዝረዋል።

      ብሊንከን፡ በክረምሊን የሚደገፈው የ“ዋግነር” ቡድን፤ ” በአለመረጋጋት ውስጥ ሃብትን የሚዝቅና በደል የሚፈጽም ቡድን ነው” ሲሉ ከሰውታል።
      የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በአፍሪካ ላለው የዋጋ ንረት ዋና ምክንያት ምዕራባውያን በሩሲያ ላይ የጣሉት ማዕቀብ ነው ለሚለው ክስም ምልሽ ሰጥተዋል።

      ብሊንከን በሰጡት ምልሽ “ፕሬዝዳንት ፑቲን ወረራ ከመጀመራቸው በፊትም ቢሆን ፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ 193 ሚሊዮን ሰዎች ሰብዓዊ እርዳታ ያስፈልጋቸው ነበር” የሚል መከራከሪያ አቅርበዋል።

      ያም ሆኖ የዓለም ባንክ ከነበረው 193 ሚሊዮን በተጨማሪ በጦርነቱ ምክንያት ለ40 ሚልዮን ህዝብ ሰብዓዊ እርዳታ ያሰፈልጋል ባለው መሰረት፤ አሜሪካ የምግብ እጥረት ያጋጠማቸው ሀገራት ስትደግፍ፤ ሩሲያ ግን ችግር በመፍጠር ላይ መሆኗ ተናግረዋል፡፡

      በደቡብ አፍሪካ ቆይታ ያደረጉት ብሊንከን ቀጣይ ጉዞዋቸውን ወደ ሩዋንዳን እና ዲሞክራቲክ ኮንጎ መሆኑ ተገልጿዋል።

      ብሊንከን በአፍሪካ ቆይታቸው በምግብ ደህንነት ፣ በአየር ንብረት ለውጥ፣ ንግድ እና ጤና ጉዳዮች ዙሪያ ከአፍሪካ መሪዎች ጋር እንደሚመክሩ ተናግረዋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
      አንቶኒ ብሊንከን የአሁኑ የአፍሪካ ጉብኝት ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን ባሳለፍነው ህዳር ላይ ናይጀሪያ፣ ሴኔጋል እና ኬንያን ጎብኝተው መመለሳቸው ይታወሳል።

      News today, Politics

      ዩክሬን በሩሲያ ጦር ላይ ድል እየተቀዳጀች መሆኑን ገለጸች


      የዩክሬን ጦር በሩሲያ ጦር ተይዞ የነበረ አንድ ከተማ በመልሶ ማጥቃት መረከቡን አስታውቋል
      የሩሲያ ጦር በካርኪቭ በኩል ኢዙም የሚባለውን አካባቢ ለመቆጣጠር ቢሞክርም ተምትቶ መመለሱ ተገልጿል

      ዩክሬን ወደ ግዛቷ በገባው የሩሲያ ጦር ላይ ድል እየተቀዳጀች መሆኑን ገለጸች፡፡

      ዩክሬን የሰሜን አትላንቲክ ቃልኪዳን ጦር ወይም ኔቶን እቀላቀላለሁ ማለቷን ተከትሎ ነበር ከሩሲያ ጋር ወደለየለት ጦርነት የገባችው።

      ሩሲያ ከኔቶ ለዩክሬን የተለገሱ 45 ሺህ ቶን ጥይት አወደምኩ አለች
      168ኛ ቀኑ ላይ በሚገኘው በዚህ ጦርነት ከ20 በመቶ በላይ የሚሆነው የዩክሬን ክፍል በሩሲያ ጦር ቁጥጥር ስር ውሏል።

      ዩክሬን ከምዕራባዊያን በሚደረግላት የጦር መሳሪያ እና የገንዘብ ድጋፍ ሩሲያን በመመከት ላይ እንደምትገኝ አስታውቃለች።

      የዩክሬን ጦር በሩሲያ ጦር እጅ ስር ባለችው ካርኪቭ አቅራቢያ ባደረገው የመልሶ ማጥቃት ዶቭሄንክ የተባለች ከተማን ዳግም መቆጣጠሩን ሮይተርስ ዘግቧል።

      በአካባቢው ያለችው ኢዙም እና አካባቢውን ለመቆጣጠር በማጥቃት ላይ የነበረው የሩሲያ ጦር በዩክሬን ጦር በደረሰበት ማጥቃት ማፈግፈጉም ተጠቅሷል።

      የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዶሚር ዘለንስኪ አማካሪ የሆኑት ኦለክሲ አርሴቶቪች እንዳሉት ካርኪቭ ከተማን ከሩሲያ ለመንጠቅ ከፍተኛ ውጊያ በመካሄድ ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

      የአሜሪካ መከላከያ ፖሊሲ ምክትል ጸሀፊ በበኩላቸው በዩክሬን ምድር እስከ 80 ሺህ የሩሲያ ወታደሮች እንደተገደሉባት እና እንደቆሰሉባት አክለዋል።

      የሩሲያ መከላከያ በበኩሉ በደበባዊ ዩክሬን የሚገኘው ዛፖሪዝህዚያ የኑክሌር ማዕከልን ባሳለፍነው መጋቢት ላይ የተቆጣጠረችው ቢሆንም የዩክሬን ጦር ይሄንን ማዕከል ሀላፊነት ከሩሲያ ለመረከብ ሀላፊነት በጎደለው መንገድ ተኩስ መክፈቷን አስታውቃለች።

      ዩክሬን በሩሲያ ላይ ድልን እንድትቀዳጅ ከአሜሪካ እና ምዕራባውያን ሀገራት የጦር መሳሪያ እየተደረገላት ይገኛል።

      አሜሪካ 4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ያላቸው የጦር መሳሪያ ለዩክሬን እንደምትሰጥ አስታውቃለች።

      በአጠቃላይ አሜሪካ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ 18 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ የጦር መሳሪያቆች ለዩክሬን መስጠቷን ዘገባው አክሏል።

      የሩሲያ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዲሚትሪ ኔድሜዴቭ በበኩላቸው ሩሲያ በዩክሬን ያሰበችውን እቅድ ማሳካቷ አይቀርም ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል።

      News today, Politics

      የአሜሪካ ፖሊስ የዶናልድ ትራምፕን መኖሪያ ቤትን ፈተሸ


      የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ቤት በኤፍ ቢ አይ ተፈተሸ

      የአሜሪካ ፖሊስ የቀድሞውን የሃገሪቱን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ መኖሪያ ቤትን በርብረዋል፡፡

      በፍሎሪዳ የሚገኘውን የትራምፕን መኖሪያ የፈተሸው የፌዴራል የምርመራ ቢሮ (ኤፍ.ቢ.አይ) መሆኑን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡

      ፍተሻው ዶናልድ ትራምፕ ምናልባትም በደጋፊዎቻቸው ከተፈጸመው የካፒቶል ሂል ጥቃት ጋር በተያያዘ ከቤተ መንግስት ያሸሹት ሚስጥራዊ ሰነድ ይኖር ይሆን በሚል የተካሄደ ነው መሆኑን ሲ.ኤን.ኤን ዘግቧል፡፡

      ትራምፕ ኒውዮርክ በሚገኘው ህንጻቸው ላይ ሳሉ ነው መኖሪያቸው የተፈተሸው።

      “ማር-ኤ-ላጎ የሚገኘው ቅንጡ መኖሪያ ተከቦ ነው የሚገኘው፤ በብዙ የኤፍ.ቢ.አይ ፖሊሶች ተወርሮም ይገኛል” ሲሉ ዶናልድ ትራምፕ ሶሻል ትሩዝ በተሰኘ ማህበራዊ ሚዲያቸው አስታውቀዋል።

      በቀጣዩ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ (2024) እንዳይወዳደሩ ለማድረግ በማሰብ የተደረገ መሆኑንም ነው የገለጹት።

      ዶናልድ ትራምፕ በፈረንጆቹ 2024 ለሚካሄደው ምርጫ ለመወዳደር ያላቸውን ፍላጎት በይፋ ባይገልጹም፣ ባለፉት ጥዊት ወራት ለመወዳደር ፍላጎት እንዳላቸው ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡

      ትራምፕ ከካፒቶል ሂሉ ጥቃት እንዲሁም የተሸነፉበትን የምርጫ 2020ን ውጤት በኃይል ለመቀየር ሞክረዋል፤ ሌሎች ሚስጥራዊ ሰነዶችንም አሽሽተዋል ከመባሉ ጋር በተያያዘ በምርመራ ላይ መሆናቸው ይታወቃል።

      News today, Politics

      ብሊንከን ሩሲያ በአፍሪካ ያላትን ተፅዕኖ ለመመከት ያለመ ጉብኝታቸውን ጀመሩ

      የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ሩሲያ በአፍሪካ ያላትን ተፅዕኖ ለማሳደግ የምታደርገውን የዲፕሎማሲ ጥረት ለመመከት ያለመ ጉብኝት ጀመሩ።

      ብሊንከን በዚህ ጉብኝታቸው ወደ ሦስት የአፍሪካ አገራት እንደሚጓዙ ይጠበቃል።

      የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከደቡብ አፍሪካ በኋላ ወደ ዴሞክራቲክ ኮንጎ ቀጥሎ ደግሞ ወደ ሩዋንዳ ይሄዳሉ ተብሏል።

      የብሊንከን የመጀመሪያ መዳረሻ የሆነችው ደቡብ አፍሪካ በዩክሬኑ ጦርነት ሞስኮን ለማውገዝ የምዕራባውያንን ጥሪዎች ሳትቀበል ገለልተኛ ሆና ቆይታለች።

      ከሁለት ሳምንታት በፊት የሩሲያው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ስድስት ቀናትን በፈጀ ጉብኝት አዲስ አበባን ጨምሮ ወደ ተለያዩ አገራት ተጉዘው ነበር።

      ላቭሮቭ የአፍሪካ ጉብኝታቸውን በግብጽ ጀምረው ቀጥሎም ወደ ኮንጎ ብራዛቪል፣ ዩጋንዳ እና ኢትዮጵያ ተጉዘው ከባለስልጣናት ጋር ተገናኝተዋል።

      በቆይታቸውም በተለይም በዩክሬኑ ጦርነት ምክንያት በአፍሪካ በተከሰተው የስንዴ አቅርቦት እጥረት ላይ ትኩረት ሰጥተው ንግግሮችን አካሂደው ለምግብ እጥረቱ ተጠያቂዎቹ ምዕራባዊያን አገራት ናቸው ሲሉም ተደምጠዋል።

      “ምዕራባውያን አገራት የበላይነታቸውን በሌሎች ላይ ለመጫን እየሞከሩ ነው” ሲሉም ከሰዋል። እንዲሁም ሞስኮ የዓለምን የምግብ ቀውስ አስከትላለች የሚለውን ወቀሳ አጣጥለውታል።

      News today, Politics

      ቻይና፤ አሜሪካ የሚመጡትን “ከባድ መዘዞች መቻል ይኖርባታል” ስትል ዛተችየቻይና መከላከያ ሚኒስቴር “በታይዋን የባህር ወሽመጥ ላይ ላለው ውጥረት አሜሪካ ኃላፊነቱን ትወስዳልች” ብሏል


      የፔንታጎን፣ የስቴት ዲፓርትመንት እና የዋይት ሀውስ ባለስልጣናት የቻይና እርምጃ “ኃላፊነት የጎደለው” ሲሉ በማውገዝ ላይ ናቸው

      የፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት እጅጉን ያስቆጣት ቻይና፣ አሜሪካ የሚመጡትን “ከባድ መዘዞች መቻል ይኖርባታል” ስትል ዛተች፡፡

      የቻይና መከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዉ ኪያን በኦን ላይን ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ፡ “በታይዋን የባህር ወሽመጥ ላይ ያለውን ውጥረት በትንኮሳ እንዲፈጠር ያደረገቸው አሜሪካ ናት፣ ስለዚህም አሜሪካ ለድረጊቷ ኃላፊነት በመውሰድ የሚከተሉ አስከፊ መዘዝ መሸከም ይኖርባታል” ብለዋል፡፡

      ቻይና ከአሜሪካ ጋር ወታደራዊ ትብብሯን አቋረጠች
      ይህ በእንዲህ እንዳለ የቻይና ወታደራዊ መርከቦች፣ አውሮፕላኖች እና ሰው አልባ አውሮፕላኖች በደሴቲቱ እና በባህር ሃይሏ ላይ ጥቃት መሰንዘራቸውን የታይዋን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።

      “ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት” አውሮፕላኖችን እና መርከቦችን መላካቸውንም ጭምር አስታውቋል ታይዋን መከላከያ ሚኒስቴር፡፡

      በፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት የተቆጣችው ቻይና ለአሜሪካ ምላሽ ነው በሚል አስካሁን በታይፔ ላይ የባለስቲክ ሚሳኤሎችን የመተኮስ ሙከራዎች ከማድረግ በተጨማሪ ከአሜሪካ ጋር የነበሯት የመከላከያ ፖሊሲ ማስተባበሪያን እና የባህር ኃይል-ወታደራዊ ምክክርን ያካተቱ መደበኛ ንግግሮችን መሰረዟ ባሳለፍነው አርብ ይፋ አድርጋለች፡፡

      የፔንታጎን፣ የስቴት ዲፓርትመንት እና የዋይት ሀውስ ባለስልጣናት የቻይና እርምጃ “ኃላፊነት የጎደለው” ነው ሲሉ አውግዘውታል፡፡

      የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ፤ቻይና የሁለትዮሽ ግንኙነትን ለማቆም አደንዛዥ እጾች፣ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች እና የአየር ንብረት ለውጥን ጨምሮ በስምንት ቁልፍ ጉዳዮች ላይ የወሰደችው አጸፋዊ እርምጃ፤ አሜሪካን ብቻ ሳይሆን ዓለምን የሚቀጣ ነው ሲሉ ከቀናት በፊት መናገራቸው አይዘነጋም፡፡

      ብሊንከን “የአየር ንብረት ትብብርን ማገድ አሜሪካን ብቻ ሳይሆን ዓለምን በተለይም በማደግ ላይ ያሉትን ሀገራት የሚቀጣ ነው።በሁለቱ ሀገራት መካከል ባለው ልዩነት ምክንያት ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩሩ ትብብሮችን እንደ መያዣ መጠቀም የለብንም” ሲሉ መደመጣቸውም ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

      ቻይና በታይዋን ዙሪያ እየፈጸመች ያለውን አደገኛና በቀጠናው አለመረጋጋት ሊፈጥር የሚችል ድርጊትን በተመለከተ ዋሽንግተን ከአጋሮቿ እየሰማች ነው ያሉት ብሊንከን ፤ “ ዋሽንግተን ጉዳዩን በምታስተናግድበት መንገድ እያስተናገደች ጸንታ ትቀጥላለች”ም ብለዋል ብሊንከን፡፡

      News today, Politics

      ሩሲያ፤ የዩክሬን ጦር በግዙፉ “ዛፖሪዥያ ኒውክሌር ጣቢያ” ላይ ተኩስ ከፍቷል ስትል ከሰሰች

      ሩሲያ፤ ዩክሬን የኒውክሌር ኃይል ጣቢያ ላይ የከፈተችው ተኩስ “ከባድ መዘዝ” የሚያስከትል ነው ስትል አስጠንቅቃለች

      ዩክሬን በበኩሏ ክሬምሊንን በዛፖሪዥያ አቶሚክ ሃይል ማመንጫ ላይ “የኒውክሌር ሽብር” ፈጽማለች ስትል ከሳለች

      የሩሲያ ቤተ መንግስት ክሬምሊን፤ የዩክሬን ጦር በግዙፉ የዛፖሪዥያ አቶሚክ ሃይል ማመንጫ ላይ ተኩስ ከፍቷል ስትል ከሰሰ።

      በደቡብ ምስራቅ ዩክሬን የሚገኘው ዛፖሪዥያ አቶሚክ ሃይል ማመንጫ በአውሮፓ ትልቁና በዓለም ላይ ካሉት 10 ትላልቅ የኒውክሌር ኃይል ጣቢያዎች መካከል አንዱ ነው።

      እናም ሩሲያ ፤ የዩክሬን ጦር ግዙፉን የኒውክሌር ጣቢያ ለማውደም ተኩስ ከፍተዋል በማለት ኪቭን ከሳለች።

      ሩሲያ፤ ዩክሬን ግዙፉን አቶሚክ ሃይል ማመንጫ ጣቢያ ማውደሟ “አሰቃቂ መዘዝ” ይዞ ሊመጣ እንደሚችል ልታውቅ ይገባል ስትል አስጠንቅቃለች።

      የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት “የዩክሬን ታጣቂ ሃይሎች የኒውክሌር ጣቢያን ማውደም ከዩክሬን ባለፈ ለአውሮፓ ምድር እጅግ አደገኛ ሊሆን የሚችል ተግባር ነው”ሲሉ ተደምጠዋል።

      የዩክሬን አጋሮች “እንዲህ ዓይነቱ የዩክሬን እርምጃ እንዳይቀጥል ተጽእኖ ያድርጉ” ሲሉም ጠይቀዋል ቃል አቀባዩ።

      ሩሲያ ይህን ትበል እንጅ ዩክሬን በተቃራኒው፤ የሩሲያ ኃይሎች በኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ኩባንያው ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል የሚል ክስ በማቅረብ ላይ ናት።

      ጥቃቱን ተከትሎ መግለጫ የሰጡት የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ “የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጠንካራ ምላሽ” እንዲሰጥ ጥያቄ አቅርበዋል።

      ፕሬዝዳንቱ፤ በሞስኮ ላይ ተጨማሪ ማዕቀቦች ለመጣል በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ከአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ቻርለስ ሚሼል ጋር መነጋገራቸውንም አስታውቋል ።

      ክሬምሊንን “የኒውክሌር ሽብር” ፈጽማለች ሲሉም ከሷል ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪ።

      News today, Politics

      የዩክሬኗ ዛፖሮዝሂ ክልል ከሩሲያ ጋር ለመቀላቀል ህዝበ ውሳኔ ልታደርግ መሆኑ ተገለጸ


      የዛፖሮዝሂ ክልል በደቡብ ምስራቅ ዩክሬን ትገኛለች
      እስካሁን በዛፖሮዝሂ ሕዝበ ውሳኔ እንደሚደረግ የዘገቡት የሩሲያ ሚዲያዎች ናቸው

      በደቡብ ምስራቅ ዩክሬን የምትገኘው የዛፖሮዝሂ ክልል ከሩሲያ ጋር ለመቀላቀል ሕዘበ ውሳኔ ልታደርግ መሆኑ ተገለጸ፡፡

      ግዛቲቱ ወደ ሩሲያ ለመጠቃለል ሕዝበ ውሳኔ እንደምታደርግ አስተዳዳሪው መግለጻቸውን የሩሲያ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል፡፡

      የሩሲያ ጦር የተቆጣጠራቸው የዩክሬን ግዛቶች ወደ ሩሲያ ለመቀላቀል ህዝበ ውሳኔ ሊያካሂዱ ነው
      የግዛቲቷ አስተዳዳሪ ከሩሲያ ጋር ለመቀላቀል የሚስችል ሕዝበ ውሳኔ እንደሚደረግ ያስታወቁት ዛሬ ነው፡፡

      የግዛቲቱ ደቡባዊ ክፍል አሁን ላይ በሩሲያ ጦር ቁጥጥር ስር የሚገኝ ሲሆን ሙሉ ግዛቱ ግዛቱ ሕዝበ ውሳኔ ያደርጋል ተብሏል፡፡

      ሕዝበ ውሳኔው ከዩክሬን ጋር መቀጠል ወይስ ወደ ሩሲያ ግዛት መጠቃለል የሚሉ ምርጫዎች እንዳሉትም ነው የተገለጸው፡፡

      የግዛቲቱ አስተዳዳሪ ኢቭጌኒ ባሊትስኪ ጉባዔ በተደረገበት ወቅት ሕዝበ ውሳኔ እንዲዘጋጅ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል ተብሏል፡፡

      የሩሲያ መገናኛ ብዙኃን የሆኑት ሩሲያ ቱዴይ እና ታስ እንደዘገቡት ከሆነ ከ700 በላይ የሚሆኑ ተወካዮች ሕዝበ ውሳኔ እንዲደረግ አጽድቀዋል ብለዋል፡፡

      በደቡብ ምስራቅ ዩክሬን በምትገኘው ዛፖሮዚ ግዛት ይደረጋል የተባለው ሕዝበ ውሳኔ በመስከርም ወር ሊካሄድ እንደሚችል ፍንጭ ተሰጥቷል፡፡

      በዛፖሮዚ ግዛት ሕዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ውሳኔ መተላለፉን በተመለከተ የዘገቡት የሩሲያ መገናኛ ብዙኃን ብቻ ናቸው፡፡

      ሩሲያ በምስራቅ ዩክሬን ውስጥ ላሉ ተገጣይ ግዛቶች እውቅና ሰጠች
      አሁን ላይ ሕዝበ ውሳኔ ይደረግባታል ተብላ የምትጠበቅ ግዛት ግማሽ ክፍል በሩሲያ ወታደሮች የተያዘው ገና ሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት በጀመሩ ሰሞን ነበር፡፡

      የተወሰነው የግዛቲቲ ክፍል ብቻ በዩክሬን ወታደሮች ቁጥጥር ስር እንደሆነ ተገልጿል፡፡ የሩሲያ እና የዩክሬን ጦርነት አራት ወራትን የተሻገረ ሲሆን አሁንም አልተቋጨም፡፡

      News today, Politics

      ሩሲያ፤ ፑቲንና ዘለንስኪ የሚገናኙበት ምክንያት እንደሌለ አስታወቀች

      ሁለቱ ፕሬዝዳንቶች መገናኘት ካለባቸው እንኳን ተደራዳሪዎች ስራቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ነው ተብሏል
      የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭለድሚር ፑቲን እና የዩክሬኑ አቻቸው ቮሎድሚር ዘለንስኪ ሊገናኙ የሚችሉበት ምክንያት እንደሌለ ክሬምሊን አስታወቀ፡፡

      የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፒስኮቭ ፕሬዝዳንት ፑቲን ከዩክሬኑ አቻቸው ጋር የሚገናኙበት ምንም መሰረት እንደሌለ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡

      ፒስኮቭ መሪዎቹ መገናኘት ካለባቸው እንኳን የሚገናኙት የተሰየሙት ተደራዳሪዎች ስራቸውን ከሰሩ በኋላ ብቻ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡

      ሩሲያ እና ዩክሬን ከጦርነት በኋላ ድርድር የጀመሩ ቢሆንም እስካሁን ግን ትልቅ ለውጥ ያመጣ ውሳኔ አልተወሰነም፡፡

      የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣኢብ ኤርዶሃን ጦርነት ውስጥ የገቡት የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ተነናኝተው እንዲመክሩ ሀሳብ አቅርበው ነበር፡፡

      ይሁንና ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፒስኮቭ፤ ፑቲን ከዩክሬኑ አቻቸው ጋር ሊነጋገሩ ቢችሉ እንኳን ተደራዳሪዎች የተሰጣቸውን የቤት ስራ ሰርተው ካጠናቀቁ በኋላ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡
      ሁለቱም ወገኖች የተጀመረው ድርድር ውጤት አለማምጣቱን ቢናገሩም ውጤት ላለመገኘቱ ግን እርስ በእርስ ግን እየተወነጃጀሉ ነው፡፡

      ዲሚትሪ ፒስኮቭም አሁን ላይ እየተደረገ ያለ ንግግር እንደሌለና ለዚህም ተጠያቂዎቹ ዩክሬንን የወከሉ ተደራዳሪዎች እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

      ሞስኮ እና ኪቭ ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ ይፋዊ ድርድር ጀምረው የነበረ ቢሆንም ዩክሬን፤ የሩሲያ ኃይሎች ከክሪሚያ ጭምር እንዲወጡ ጥያቄ አቅርባ ነበር፡፡

      የዩክሬን ፕሬዝዳንት አማካሪ አሌክሰይ አርስቶቪች ሀገራቸው፤ የሩሲያ ወታደሮች ከክሬሚያ እና ዶንባስ ግዛቶች እንዲወጡላት እንደምትፈልግ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

      “አሁን ፕሬዝዳንት ፑቲን ከዩክሬኑ አቻቸው ጋር መገናኘታቸው አስፈላጊ አይደለም” ያሉት የፑቲን ቃል አቀባይ፤ በዩክሬንም ሆነ በሩሲያ ወገን ያሉት ተደራዳሪዎች ስራቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ምናልባት ሁለቱ ፕሬዝዳንቶች የመገናኘት ዕድል ሊኖራቸው ይችላል ብለዋል፡፡

      News today, Politics

      የቀድሞ የሩሲያ ፕሬዝዳንት ዲሚትሪ ሜድቬድየቭ “ሩሲያ በዩክሬን ያላትን አላማ ታሳካለች” አሉ


      ሜድቬድየቭ “ምዕራባውያን ሩሲያን ለማጥፋት የረዥም ጊዜ እቅድ አላቸው” ሲሉም አስጠነቅቀዋል
      የቀድሞ የሩሲያ ፕሬዝዳንት ዲሚትሪ ሜድቬድየቭ “ሩሲያ በዩክሬን ያላትን አላማ ታሳካለች” አሉ፡፡


      የፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የቅርብ ሰው እንደሆኑ የሚነገርላቸው ዲሚትሪ ሜድቬድየቭ ፤ “ምዕራባውያን ሩሲያን ለማጥፋት የረዥም ጊዜ እቅድ አላቸው” ሲሉም ከሩሲያው ኒውስ ኤጀንሲ ታሳ ጋር በነበራቸው ቃለ መጠይቅ ተናግረዋል፡፡


      ሩሲያ ቱርክ በሩብል ለመገበያየት ተስማሙ
      በአሁኑ ወቅት የሩሲያ የጸጥታ ምክር ቤት ምክትል ሊቀመንበር ሆነው በማገልገል ላይ የሚገኙት ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ ፤ “ሩሲያ በዩክሬን ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ እያካሄደች ነው እናም በምትፈልገው መልኩ ሰላምን እያመጣች ነው” ማለታቸውም ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
      ሜድቬድየቭ፤ እንደፈረንጆቹ የ2008 የጆርጂያ ጦርነት ፣ የኔቶ ወታደራዊ ህብረት ማጠናከር እና የአሁኑ የዩክሬን ጦርነት፤ አሜሪካ ና አጋሮቿ ሩሲያን ለማጥፋት እስካሁን ያደረጓቻ ሙከራዎች አካል መሆናቸውም በአብነት አንስተዋል።


      “ዓላማው አንድ ነው፤ ሩሲያን ለማጥፋት” ሲሉም አክለዋል የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዲሚትሪ ሜድቬድየቭ፡፡
      በዩክሬን እየተካሄደ ያለው ጦርነት በእቅዳቸው መሰረት እየሄደ መሆኑን ፕሬዝዳንት ፑቲን ቀደም ሲል ገልጸው እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡
      “በዩክሬን ያለው ጦራችን በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ተልዕኮውን በሚገባ እየፈጸመ ነው፣ በዩክሬን መስራት ያለብንን ስራዎች ሁሉ እያከናወኑ ነው”ም ነበር ያሉት ፕሬዘዳንት ፑቲን፡፡


      የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቪላድሚር ፑቲን ከወራት በፊት በሰጡት አጭር መግለጫ “ሊስቆመን የሚሞክር፣ በሀገራችን እና በህዝባችን ላይ ተጨማሪ አደጋ የሚጥል ማንኛውም አካል በታሪኩ አይቶት የማያውቀው እጣፋንታ ይገጥመዋል” ሲሉ ምእራባውያን ማስጠንቀቃቸውም አይዘነጋም፡፡
      የሩሲያ ምላሽ ፈጣን እንደሚሆን የገለጹት ፕሬዝዳንት ፑቲን የወታደራዊ ዘመቻው አላማ በኪቭ አስተዳደር ለበርካታ አመታት ጥቃት እና የዘርማጥፋት ሲፈጸምባቸው የነበሩትን ዜጎች መታደግ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

      News today, Politics

      የቻይና የጦር ልምምድ ትናንት ይጠናቀቃል ቢባልም ልምምዱ እንደቀጠለ ነው


      ቻይና የአሜሪካ አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ ታዋንን መጎብኝቷን ተከትሎ ነበር የጦር ልምምዱን የጀመረችው

      የቻይና የጦር ልምምድ ትናንት ይጠናቀቃል ቢባልም ልምምዱ እንደቀጠለ ነው

      ቻይና በታይዋን አቅራቢያ የጀመረችው የጦር ልምምድ እንደቀጠለ ነው።

      የአሜሪካ ምክር ቤት አፈጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ ታይዋንን ጨምሮ አምስት የእስያ ሀገራትን መጎብኘታቸውን ተከትሎ በሩቅ ምስራቅ የነገሰው ውጥረት እንደቀጠለ ነው።

      አፈ ጉባኤዋ ባሳለፍነው ሳምንት ታይዋንን የጎበኙ ሲሆን ድርጊቱ ቻይናን እንዳስቆጣ የዓለም ብዙሀን መገናኛዎች ዘግበዋል።

      ይሄንን ተከትሎም ቻይና በታይዋን ባህር ዙሪያ እስከ ቀጣዩ ትናንት ድረስ የሚቆይ ወታደራዊ ልምምድ በማድረግ ላይ መሆኗን አሳውቃ ነበር።

      ይሁንና የቻይና ወታደራዊ የጦርነት ልምምድ ትናንት ያበቃል ተብሎ ቢጠበቅም ልምምድ ዛሬም እንደቀጠለ ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል።

      የቀጠለው ወታደራዊ ልምምድም የአየር፣የባህር እና የየብስ ጦርነት ልምምድ ሲሆን ታይዋን እና የቡድን ሰባት ሀገራት ልምምዱን ተችተዋል።እንደ ዘገባው ከሆነ ቻይና በታይዋን 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በስድስት አቅጣጫ የጦርነት ልምምዱ እንደቀጠለ ይገኛል ተብሏል።

      ቻይና ባሳለፍነው ሳምንት ልምምድ ላይ ዶንግ ፋንግ የተሰኘው የቻይና የረጅም እና አጭር ርቀት ባልስቲክ ሚሳኤሎች ወደ ታይዋን ባህር ተኩሳለች።

      በታይዋን ስድስት አቅጣጫዎች ምንም አይነት የባህር እና አየር ላይ ትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንዳይኖር ቻይና አስቀድማ ማስጠንቀቋ ይታወሳል ።ታይዋን የቻይና ድርጊት የጦርነት ትንኮሳ መሆኑን አስታውቃ እስከ እሁድ የሚቆየውን የጦር ልምምድ እንደማትታገሰው አስቀድማ ተናግራም ነበር።

      በቀጠለው የቻይና በታይዋን ባህር አቅራቢያ የጀመረችው የጦር ልምምድ ታይዋን እስካሁን በይፋ የሰጠችው መግለጫ የሌለ ሲሆን ቻይናም ልምምዱ እስከመቼ እንደሚቀጥል አላሳወቀችም።

      News today, Politics

      ተጠባቂው የኬንያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ነገ ይካሄዳል


      August 8, 2022
      በዚህ ምርጫ ላይ 22 ሚሊየን ኬንያዊያን በመራጭነት ድምጽ እንደሚሰጡ ይጠበቃል
      ተጠባቂው የኬንያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ነገ ይካሄዳል።
      ኬንያን በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ለመምራት የምረጡኝ ቅስቀሳቸው ሲያካሂዱ የነበሩ እጩ ፕሬዝዳንቶች ምርጫ ነገ እንደሚካሄድ ቢቢሲ ዘግቧል።
      ኬንያን በፕሬዝዳንትነት ለመምራት አራት እጩዎች የቀረቡ ሲሆን ባለፉት ምርጫዎች ላይ ለአራት ጊዜ ተወዳድረው ሽንፈትን ያስተናገዱት የኦሬንጅ ዲሞክራቲክ ሙቭመንቱ ራይላ ኦዲንጋ ዋነኛው ተፎካካሪ ናቸው፡፡

      ራይላ ኦዲንጋ በፈረንጆቹ 1997 ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ሀገራቸውን በፕሬዝዳንትነት ለመምራት እጩ የነበሩ ሲሆን በምርጫው ሶስተኛ ሆነው አጠናቀዋል፡፡
      በነዳጅ እና ሀይል ልማት ዘርፍ ነጋዴ የሖኑት የ77 ዓመቱ ኦዲንጋ ላለፉት አራት ተከታታይ ፕሬዝዳንታዊ የምርጫ ወቅቶች ላይ እጩ ቢሆኑም አብላጫ የህዝብ ድምጽ ሳያገኙ ቀርተዋል፡፡
      ውጤታቸውን ተከትሎም ራይላ ኦዲንጋ ከፕሬዝዳናታዊ ምርጫ ራሳቸውን ማግለላቸውን ከአምስት ዓመት በፊት ቢናገሩም ዘግይተው በሰጡት መግለጫ ለአምስተኛ ጊዜ ለፕሬዝዳንትነት መልሰው እንደሚወዳደሩ አሳውቀዋል፡፡
      ኬንያን አሁን ላይ በምክትል ፕሬዝዳንትነት እያገለገሉ ያሉት የዲሞክራቲክ ዩኒየኑ ዊሊያም ሩቶ ሌላኛው እጩ ፕሬዚዳንት ሲሆኑ የራይላ ኦዲንጋ ዋነኛ ተፎካካሪ ናቸው ተብሏል፡፡
      የ55 ዓመቱ ሩቶ ከፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር በግጭት ውስጥ ሲሆኑ የጸባቸው መንስኤ ደግሞ ፕሬዝዳንቱ ለራይላ ኦዲንጋ ድጋፍ ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው፡፡
      ከራይላ ኦዲንጋ እና ዊሊያም ሩቶ በተጨማሪ ለኬንያ ፕሬዝዳንትነት እየተፎካከሩት ያሉት ቀሪዎቹ እጩዎች ዳቪድ ዌሂጋ ጆርጅ ዋጃኮያህ ናቸው፡፡
      የሬጌ ሙዚቃ ወዳጅ እንደሆኑ የሚናገሩት እጩ ፕሬዝዳንት ጆርጅ ዋጃኮያህ የብዙዎችን ትኩረት ስበዋል።
      እጩ ፕሬዚዳንቱ በምርጡኝ ቅስቀሳቸው ላይ ማሪዋና የተሰኘው አደገኛ እጽ ማንኛውም አርሶ አደር እንዲያመርተው እና ምርቱን መጠቀም የፈለጉ ሁሉ በነጻነት እንዲጠቀሙት አደርጋለሁ፣ እንዲሁም ወደ ውጭ ሀገራት በመላክ የውጭ ምንዛሬ እንሲያስገኝ አደርጋለሁ ብለዋል።

      የእባብ መርዝ በስፋት በማምረት ለኬንያ ዋነኛ የውጭ ምንዛሬ ማግኛ መንገድ አደርጋለሁ ማለታቸው የብዙ ኬንያዊያንን ትኩረት እንዲስቡ ማድረጋቸውም ተገልጿል።
      ኬንያን በፕሬዝዳንትነት ለመምራት 55 እጩዎች ቀርበው የነበሩ ቢሆንም በመጨረሻም አራት ብቻ ቀርተዋል።
      ኬንያን ላለፉት 10 ዓመታት በፕሬዝዳንትነት የመሩት ኡሁሮ ኬንያታ የስልጣን ጊዜያቸውን ከሁለት ጊዜ በላይ ማራዘም ስለማይችሉ ለተመራጩ ፕሬዝዳንት እንዲያስረክቡ የሀገሪቱ ህገ መንግስት ያስገድዳቸዋል።

      News today, Politics

      እስራኤል በጋዛ ባደረሰችው ጥቃት ሁለት የታጣቂ አመራሮችን ጨምሮ በርካታ ፍልስጤማውያን ተገደሉ

      Ke alemi zuriya-ከዓለም ዙሪያ

      በአየር ጥቃቱ የፈረሰ ቤት

      7 ነሐሴ 2022

      እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ባደረሰችው የአየር ጥቃት የፍልስጥኤም እስላማዊ ጂሃድ ቡድን (ፒአይጄ) ሁለት አመራሮች አመራሮችን ጨምሮ በርካታ ፍልስጤማውያን ተገደሉ።

      አመራሮቹ ካሊድ መንሱር እና ጣይር ጃብሪ፣ በርካታ የቡድኑ ተዋጊዎችና ስድስት ህፃናትን ጨምሮ 32 ፍልስጥኤማውያን መገደላቸው ተዘግቧል።

      ከአርብ ጀምሮ ወደ 400 የሚጠጉ የፍልስጥኤም ሮኬቶች እና ሞርታሮች በእስራኤል ላይ መተኮሳቸውን የእስራኤል ባለስልጣን ተናግረዋል።

      እስራኤል ወታደራዊ ዘመቻ ብላ የምትጠራውን ይህንን የአየር ጥቃት የጀመረችው የፍልስጥኤም እስላማዊ ጂሃድ ቡድን በደቀነው ከፍተኛ ስጋት ነው ብላለች።

      ባለፈው አመት ግንቦት ወር ለ11 ቀናት በዘለቀው እና ከ200 በላይ ፍልስጥኤማውያን እንዲሁም በርካታ እስራኤላውያን ከተገደሉበት ግጭት ወዲህ ይህ በቅርቡ በእስራኤልና በጋዛ መካከል የተከሰተ አሳሳቢ ግጭት አድርጎታል።

      ‘ብሬኪንግ ዳውን’ ( መሰባበር) የሚል የኮድ ስም እስራኤል የሰጠችው ወታደራዊ ዘመቻ ለአንድ ሳምንት ሊቆይ እንደሚችል ባለስልጣናቷ አስጠንቅቀዋል።

      በሁለተኛው ቀን ጥቃት ትናንት ቅዳሜ በደቡባዊ ጋዛ ራፋህ በሚገኝ መኖሪያ ቤት ላይ በፈጸመችው የአየር ጥቃት ከፍተኛ የፒአይጄ መሪ ካሊድ መንሱርን መግደሏን አስታውቃለች።

      ከጋዛ ውጭ ወታደራዊ ጥቃቶችን ፈጽሟል በማለት እስራኤል የምትከሰው ካሊድ መንሱር ከዚህ ቀደም በእስራኤል ጦር ከአምስት የግድያ ሙከራዎች ተርፎ ነበር።

      ከሱ ሞት በፊት አርብ እለት ከፍተኛ የፒአይጄ አመራር የሆነው ታይሲር ጃባሪ በእስራኡል የአየር ጥቃት ተገድሏል።

      እንዲሁም በጋዛ በተፈጸመው የአየር ጥቃት ድብደባ በርካታ የቡድኑ አባላት ከመገደላቸው በተጨማሪ እስራኤል ተቆጣጥራት ባለቸው የዌስት ባንክ በተደረገ ከበባ 19 የሚሆኑ የፒአይጄ አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን እስራኤል ገልጻለች።

      የጋዛ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ለፍልስጥኤማውያን ሞት እንዲሁም ለቆሰሉት 203 ሰዎች “የእስራኤል ወራራን ተጠያቂ አድርጓል።

      News today, Politics

      የአሜሪካ ውጪ ጉዳይ ሚንስቴር አንቶኒ ብሊንከን የአፍሪካ ጉብኝታቸውን ጀመሩ

      የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ደቡብ አፍሪካ ደርሰዋል

      የአሜሪካ ውጪ ጉዳይ ሚንስቴር አንቶኒ ብሊንከን

      ብሊንከን በአፍሪካ ጉብኝታቸው ከፕሪቶሪያ በተጨማሪ ኬንሻሳ እና ኪጋሊን ይጎበኛሉ ተብሏል

      የአሜሪካ ውጪ ጉዳይ ሚንስቴር አንቶኒ ብሊንከን የአፍሪካ ጉብኝታቸውን ጀመሩ።

      ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ጦርነት መጀመራን ተከትሎ በሩሲያ ላይ ጫና ለመፍጠር ከወራት በፊት በመንግስታቱ ድርጅት በተጠራ ስብሰባ ላይ አብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገራት ድምጸ ተዓቅቦ ማድረጋቸው አሜሪካንን ጨምሮ ምዕራባዊያንን አስቆጥቷል።

      ከዚህ ጊዜ ጀምሮም በተለያዩ ጊዜያት የአሜሪካ እና አውሮፓ ሀገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት ወደ አፍሪካ በመጓዝ ጫና በማድረግ ላይ ናቸው።

      የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን ሩሲያን ከተቀረው ዓለም የመነጠል ስራውን ለማጠናከር የአፍሪካ ጉብኝታቸውን ጀምረዋል።

      ብሊንከን ከሰዓታት በፊት ደቡብ አፍሪካ መዲና ፕሪቶሪያ የደረሱ ሲሆን ከሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ስሪል ራሞፎሳ ጋር እንደሚመክሩ ይጠበቃል።

      ብሊንከን ከደቡብ አፍሪካ በተጨማሪም ሩዋንዳን እና ዲሞክራቲክ ኮንጎን እንደሚጎበኙ አስታውቀዋል።

      ብሊንከን በአፍሪካ ቆይታቸው በምግብ ደህንነት ፣ በአየር ንብረት ለውጥ፣ ንግድ እና ጤና ጉዳዮች ዙሪያ ከአፍሪካ መሪዎች ጋር እንደሚመክሩ ተናግረዋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።

      ውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ከነዚህ ጉዳዮች በተጨማሪ በግጭት ውስጥ ያሉት ዲሞክራቲክ ኮንጎ እና ሩዋንዳ ግንኙነታቸው እንዲሻሻል እንደሚሰሩም ተገልጿል።

      እንዲሁም አንቶኒ ብሊንከን በኪጋሊ ቆይታቸው ከፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ጋር በስህተት ስለታሰሩት የሆቴል ሩዋንዳ ፊልም ሰሪ ፖል ሩሴሳባጊና ጉዳይ እንደሚወያዩም ይጠበቃል ተብሏል።

      የአንቶኒ ብሊንከን የአፍሪካ ጉብኝት የሩሲያው አቻቸው ሰርጌ ላቭሮቭ ሶስት የአፍሪካ ሀገራትን ጎብኝተው ከተመለሱ በኋላ መሆኑ የጉዟቸው አላማ የሩሲያን ተጽዕኖ ከአፍሪካ ለመነጠል ያለመ እንደሆነ ሌሎች ዘገባዎች እየወጡ ይገኛል።

      አንቶኒ ብሊንከን የአሁኑ የአፍሪካ ጉብኝት ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን ባሳለፍነው ህዳር ላይ ናይጀሪያ፣ ሴኔጋል እና ኬንያን ጎብኝተው መመለሳቸው ይታወሳል።

      News today, Politics

      እስራኤል በጋዛ በሰነዘረችው ጥቃት የሟቾች ቁጥር 32 ደረሰ

      በጥቃቱ ከ265 የሚልቁ ሰዎችም ቆስለዋል ተብሏል

      እስራኤል በጋዛ በሰነዘረችው ጥቃት

      ከሟቾች መካከል ሁለት የፍልስጥኤም እስላማዊ ጂሃድ ቡድን አመራሮች ይገኙበታል

      እስራኤል በጋዛ በሰነዘረችው ጥቃት የሟቾች ቁጥር 32 ደረሰ።

      በየጊዜው ግጭት ውስጥ የሚገቡት እስራኤል እና ፍልስጥም አሁንም መልሰው ግጭት ውስጥ ገብተዋል።

      የእስራኤል ጦር ባሳለፍነው ሰኞ የእስላሚክ ጅሀድ የተሰኘው ቡድን መሪ የሆኑት ባሳም አልሳዲን በዌስት ባንክ ማሰራቸውን ተከትሎ በጋዛ አውዳሚ ግጭት ተቀስቅሷል።

      በጋዛ ሰርጥ ውስጥ እየተካሄደ ባለው በዚህ ጦርነት እስራኤል በተኮሰቻቸው የሮኬት ጥቃቶች የሞቱ ሰዎች ቁጥር 32 መድረሱን ሮይተርስ ዘግቧል።

      ከ265 የሚልቁ ሰዎች ደግሞ ቆስለው ወደ ሆስፒታል መግባታቸውን ዘገባው አክሏል።

      ከሟቾች ውስጥ ስድስቱ ህጻናት ሲሆኑ አራቱ ደግሞ ሴቶች እንደሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን የሟቾች እና የቆሰሉ ሰዎች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊያሻቅብ እንደሚችል ተጠቅሷል።

      የእስራኤል ጦር የእስላሚክ ጅሀድ የተሰኘው ቡድን ምክትል መሪ ካሊድ ማንሱርን በጋዛ ሰርጥ በሮኬት ጥቃት መግደሏን አስታውቃለች።

      የእስራኤል ጦር በፍልስጤም ጋዛ እንደሚንቀሳቀስ የተገለጸው የእስልሚክ ጅሀድ የተሰኘው ቡድን የሚለውን ለመስማት በሚል የተኩስ አቁም አውጇል።

      የፍልስጤም ጤና ሚንስቴር ባወጣው መግለጫ እስራኤል የምትተኩሳቸው የሮኬት ጥቃቶች ንጹሀንን እየገደለ መሆኑን ገልጿል።

      News today, Politics

      የአሜሪካ ውጪ ጉዳይ ሚንስቴር አንቶኒ ብሊንከን የአፍሪካ ጉብኝታቸውን ጀመሩ


      ብሊንከን በአፍሪካ ጉብኝታቸው ከፕሪቶሪያ በተጨማሪ ኬንሻሳ እና ኪጋሊን ይጎበኛሉ ተብሏል
      የአሜሪካ ውጪ ጉዳይ ሚንስቴር አንቶኒ ብሊንከን የአፍሪካ ጉብኝታቸውን ጀመሩ።
      ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ጦርነት መጀመራን ተከትሎ በሩሲያ ላይ ጫና ለመፍጠር ከወራት በፊት በመንግስታቱ ድርጅት በተጠራ ስብሰባ ላይ አብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገራት ድምጸ ተዓቅቦ ማድረጋቸው አሜሪካንን ጨምሮ ምዕራባዊያንን አስቆጥቷል።
      “ሉዓላዊነትን እና ግዛታዊ አንድነትን ማክበር ለአፍሪካ ቀንድ መረጋጋትና ልማት አስፈላጊ ነው” – ብሊንከን 
      ከዚህ ጊዜ ጀምሮም በተለያዩ ጊዜያት የአሜሪካ እና አውሮፓ ሀገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት ወደ አፍሪካ በመጓዝ ጫና በማድረግ ላይ ናቸው።
      የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን ሩሲያን ከተቀረው ዓለም የመነጠል ስራውን ለማጠናከር የአፍሪካ ጉብኝታቸውን ጀምረዋል።
      ብሊንከን ከሰዓታት በፊት ደቡብ አፍሪካ መዲና ፕሪቶሪያ የደረሱ ሲሆን ከሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ስሪል ራሞፎሳ ጋር እንደሚመክሩ ይጠበቃል።
      ብሊንከን ከደቡብ አፍሪካ በተጨማሪም ሩዋንዳን እና ዲሞክራቲክ ኮንጎን እንደሚጎበኙ አስታውቀዋል።
      ብሊንከን በአፍሪካ ቆይታቸው በምግብ ደህንነት ፣ በአየር ንብረት ለውጥ፣ ንግድ እና ጤና ጉዳዮች ዙሪያ ከአፍሪካ መሪዎች ጋር እንደሚመክሩ ተናግረዋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
      ውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ከነዚህ ጉዳዮች በተጨማሪ በግጭት ውስጥ ያሉት ዲሞክራቲክ ኮንጎ እና ሩዋንዳ ግንኙነታቸው እንዲሻሻል እንደሚሰሩም ተገልጿል።
      እንዲሁም አንቶኒ ብሊንከን በኪጋሊ ቆይታቸው ከፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ጋር በስህተት ስለታሰሩት የሆቴል ሩዋንዳ ፊልም ሰሪ ፖል ሩሴሳባጊና ጉዳይ እንደሚወያዩም ይጠበቃል ተብሏል።
      አንቶኒ ብሊንከንና ኡሁሩ ኬንያታ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ተወያዩ 
      የአንቶኒ ብሊንከን የአፍሪካ ጉብኝት የሩሲያው አቻቸው ሰርጌ ላቭሮቭ ሶስት የአፍሪካ ሀገራትን ጎብኝተው ከተመለሱ በኋላ መሆኑ የጉዟቸው አላማ የሩሲያን ተጽዕኖ ከአፍሪካ ለመነጠል ያለመ እንደሆነ ሌሎች ዘገባዎች እየወጡ ይገኛል።
      አንቶኒ ብሊንከን የአሁኑ የአፍሪካ ጉብኝት ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን ባሳለፍነው ህዳር ላይ ናይጀሪያ፣ ሴኔጋል እና ኬንያን ጎብኝተው መመለሳቸው ይታወሳል።

      News today, Politics, social life

      ሩሲያ በ62 ካናዳዊያን ላይ ማዕቀብ ጣለች

      የሞስኮ ማዕቀብ ካናዳ ከዚህ በፊት በሩሲያዊያን ላይ ለጣለችው ማዕቀብ የአጸፋ እርምጃ ነው ተብሏል

      ሩሲ እና ካናዳ

      ሩሲያ ካናዳዊያን ዲፕሎማቶች፣ የሀይማኖት መሪዎች፣ ፖለቲከኞችና ምሁራን ላይ ነው ማዕቀብ ጣለችው

      ሩሲያ በ62 ካናዳዊያን ላይ ማዕቀብ መጣሏን አስታውቃለች።

      ሩሲያ ዩክሬን የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ጦር ወይም ኔቶን እቀላቀላለሁ ማለቷን ተከትሎ ነበር ወደ ይፋዊ ጦርነት የገባችው።

       ይሄንን ጦርነት ተከትሎም በሩሲያ ላይ ከ6 ሺህ በላይ ማዕቀቦች ሲጣልባት ከ400 በላይ ዲፕሎማቶቿ ደግሞ ከተለያዩ ሀገራት ተሰናብተዋል።

      ካናዳም የሩሲያ ዲፕሎማቶችን ከማባረሯ ባለፈ በሩሲያ ጋዜጠኞች ፣ ባለሀብቶች እና ሌሎች ዲፕሎማቶች ላይ ማዕቀብ ጥላለች።

      የሩሲያ ውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ባወጣው መግለጫ ካናዳ ለወሰደችው ማዕቀብ ምላሽ በ62 ካናዳዊያን ላይ ማዕቀብ ጥላለች።

      ይህ ማዕቀብ የተጣለባቸው ካናዳዊያን ወደ ሩሲያ እንዳይገቡ እና በሩሲያ ያላቸው ሀብት እንዳይንቀሳቀስ እንደሚደረግ ሮይተርስ ዘግቧል።

      ሩሲያ ከዩክሬን ጦርነት ጋር በተያያዘ በሀገሪቱ እንዲሁም በተቋማቶቿ እና ባለሃብቶቿ ላይ ማዕቀብን ጨምሮ የተለያዩ እገዳዎችን የጣሉ እርምጃዎቹን የደገፉ ሀገራትን “ወዳጅ አይደሉም” ማለቷ ይታወሳል።

      News today, Politics

      ቻይና ከአሜሪካ ጋር ተባብራ የምትሰራባቸውን ቁልፍ ጉዳዮች ማቋረጧን አስታወቀች

      የቻይና የጦር አውሮፕላን
      የምስሉ መግለጫ,ቻይና በታይዋን ዙሪያ በባሕር እና በአየር የምታካሂደው ወታደራዊ ልምምድ እንደቀጠለ ነው

      6 ነሐሴ 2022

      የአሜሪካ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣን በታይዋን ጉብኝት ማድረጋቸውን ተከትሎ ቻይና በበርካታ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ከአሜሪካ ጋር ተባባሮ የመሥራት ስምምነቷን ማቋረጧን አሳወቀች።

      አሜሪካ እና ቻይና በዓለም የአየር ፀባይ ለውጥ፣ በወታደራዊ ጉዳዮች ላይ ሊያደርጉ የነበረው ውይይት እና የዓለም አቀፍ ወንጀሎችን በመዋጋት በኩል ተባብሮ ለመሥራት ስምምነት ነበራቸው።

      የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሴ ግዛቴ በምትላት ታይዋን ይፋዊ ጉብኝት ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው ቻይና ከአሜሪካ ጋር ተባብሮ ለመሥራት የነበራትን እቅድ ለመቋረጥ የወሰነችው።

      በተጨማሪም ቻይና ሉዓላዊ ግዛቴ ናት በምትላት ታይዋን ላይ ያላትን ይገባኝል በመቃረንም በአፈ ጉባኤ ፔሎሲ እና ቤተሰቦቻቸው ላይ ዕቀባን ጥላለች።

      ቻይና እንደተገንጣይ ግዛትዋ የምትመለከታት ታይዋን እራሷን ከቻይና የተለየች ግዛት አድርጋ ትመለከታለች።

      ቻይና ውሳኔዋን ያሳወቀችው በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ በኩል ሲሆን፣ በዚህም በአሜሪካ እና በቻይና የመከላከያ ባለሥልጣንት መካከል የሚካሄድ ውይይት ሲሰረዝ፣ ሕገ ወጥ ስደተኞችን የመመለስ ትብብር፣ የአየር ፀባይ ለውጥ፣ በዓለም አቀፍ ወንጀሎች ላይ በጋራ ምርመራ የማድረግ ሥራም እንዲቀቋረጥ ተደርጓል።

      ሁለቱ ኃያላን አገራት የዓለም የአየር ፀባይ ለውጥን ለመከላከል በቀጣይ ዓመታት መወሰድ ባለባቸው እርምጃዎች ዙሪያ ዲፕሎማሲያዊ ስምምነት ደርሰው ነበር። ባለፈው ዓመት በተደረገው ጉባኤ ላይም ቻይና የበካይ ጋዝ ልቀትን ለመቀነስ ከአሜሪካ ጋር በጋራ ለመስራት ቃል ገብታ ነበር።

      የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳለው ይህ ውሳኔ የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፔሎሲ “የቻይናን ጠንካራ ተቃውሞ ችላ በማለት ባሳዩት ከባድ ምሳሌ” ምክንያት መሆኑን ገልጿል።

      ቻይና በአሜሪካ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣን የሆኑት የፔሎሲ ጉብኝትን “የከፋ ጠብ አጫሪነት” ነው በማለት ተቃውሞዋን ያሰማች ሲሆን፣ የቻይና የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ በትዊተር ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ላይ ባለፈው ዓመት አሜሪካ ውስጥ በፖሊስ ተንቆ የተገደለውን ጥቁር አሜሪካዊን በምሳሌነት ጠቅሰዋል።

      “አሜሪካ የዓለም ፖሊስ እንድትሆንና አገራትን በማስፈራራት እንደ ጆርጅ ፍሎይድ እንድታንቅ አንፈቅድም” ሲሉ ጽፈደዋል።

      አርብ ዕለት የዋይት ሐውስ ፕሬስ ሴክሬታሪ ካሪን ጂን-ፔሪ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ናንሲ ፔሎሲ ወደ ታይዋን የመሄድ “ሙሉ መብት ነበራቸው” በማለት፣ ቻይና የወሰደችውን እርምጃ “ኃላፊነት የጎደለው” ሲሉ ተቃውመውታል።

      News today, Politics, social life

      ሩሲያ ቱርክ በሩብል ለመገበያየት ተስማሙ


      የሩሲያ እና የቱርክ ፕሬዝደንቶች በትናንትናው እለት በሩሲያ ሶቺ ከተማ ተገናኝተው መክረዋል

      ሩሲያ እና ቱርክ፤ በሩሲያው ገንዘብ ሩብልስ ለመገበያየት ተስማምተዋል፡፡

      የሩሲያ እና ቱርክ መሪዎች በትናንትናው እለት በሩሲያዋ ሶቺ ከተማ ባደረጉት ውይይት የኢኮኖሚ ትብብር ስምምነት መፈረማቸውን የሩሲያ አርቲ ሚዲያ ዘግቧል፡፡

      ሩሲያ ያለባትን የውጭ ሀገራት እዳ በራሷ ገንዘብ “ሩብል” እንደምትከፍል አስታወቀች
      ስምምነቱ መፈረሙን የገለጹት የቱርኩ ፕሬዝደንት ረሲፕ ተይፕ ኤርዶጋን ናቸው፡፡

      ሩሲያ እና ዩክሬንን የማደራደር ሚያ ያላት ቱርክ ከሩሲያ ጋር በሩብልስ ለመገበያየት መስማማቷን ፕሬዘደንት ኤርዶጋን ተናግረዋል፡፡

      ፕሬዝዳንት ጣይብ ኤርዶጋን አርብ ዕለት በቱርክ እና በሩሲያ ልዑካን መካከል የተካሄዱት ስብሰባዎች ፍሬያማ እንደነበሩ እና በሩሲያ በሚያደርጉት ጉብኝት በሶሪያ ስላለው ሁኔታ ከሩሲያ አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር እንደሚመክሩ ተናግረዋል።

      ሩሲያ በዩክሬን “ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ” ከጀመረች በኋላ ሩሲያ አሜሪካን ጨምሮ ከምእራባውያን ጋር ሁሉን አቀፍ ፍጥጫ ውስጥ ገብታለች፡፡

      አሜሪካን ጨምሮ ምእራበውያን ሀገራት ሩሲያን ያዳክማል ያሉትን ማእቀብ ሁሉ በሩሲያ ላይ አዝንበዋል፤ ሩሲያ ማእቀቡን ለመመከት ምእራባውያን ሀገራት ጋዝ በሩብል እንዲገዙ አስገድዳለች፡፡